የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በሥራ ማቆም አድማ የተሳተፉ የሕክምና ባለሙያዎችን ማሰናበቱን አሳውቋል። መመለስ የሚፈልጉ ይቅርታ ይጠይቁኝም ብሏል።
@Yenetube @Fikerassefa
@Yenetube @Fikerassefa
👎65👍14😁6❤2
ግንቦት 20
ህወሐት ‹‹ግንቦት 20ን አከብራለሁ› አለ
ፓርቲው ትናንት ባወጣው መግለጫ 34ተኛው የግንቦት 20 በአል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ገልጿል፡፡
ከዛሬ ግንቦት 16 አንስቶ ግንቦት 20 የተመለከቱ የፓናል ውይይቶች እንደሚካሄዱ የገለፀው ፓርቲው በውይይቶቹ ላይ ‹‹የትግራይ ህዝብ ያሳለፈው ትግልና ያገኘው ድል›› የሚለው እንደሚነሳና በቀጣይነት የሚያጋጥሙ ፈተናዎች እንደሚዳሰሱ አስረድቷል፡፡
የዘንድሮው ግንቦት 20 በአል የሚከበረው የህወሀትን 50ኛ አመት በማስመልከት የተዘጋጀው ፕሮግራም አንዱ አካል ሆኖ መሆኑንም አስታውቋል፡፡
የየካቲት 11ን የህወሀት 50ኛ አመት በአል አመቱን በሙሉ ለማክበር መታቀዱንም አውስቶ የዘንድሮው ግንቦት 20 አከባበር የዚሁ በአል አካል መሆኑን ገልጿል፡፡
ግንቦት 20 በመቀሌ ደማቅ ዝግጅት ለማድረግ ማቀዱንም አስረድቷል፡፡

👍45😁45🔥4❤2👎1
ታሪኩ ጋንኪሲ (ዲሽታ ጊና) የአሜሪካ ቪዛ ተከለከለ
የ"ዲሽታ ጊና" ድምጻዊ ታሪኩ ጋንኪሲ፣ በአሜሪካን የሚገኝ አንድ ድርጅት ሊሰጠው የነበረውን ሽልማት ለመቀበል ለአሜሪካ ቪዛ ጠይቆ ተከለከለ።
ታሪኩ ለአሜሪካ ኤምባሲ ቃለ መጠይቅ ሲያደርግ "አሜሪካን ሀገር በቋሚነት ለመኖር" ማሰቡን በመግለጹ፣ የቪዛ ኦፊሰሩ ወደ ሀገሩ ላይመለስ ይችላል በሚል ስጋት ቪዛውን እንደከለከለው FastMereja ዘግቧል። በዚህም ምክንያት ታሪኩ ሽልማቱን በአካል መቀበል ሳይችል ቀርቶ በወኪሉ አማካኝነት ተበርክቶለታል።
ታሪኩ ከጂንካ በላከው የቪዲዮ መልዕክት፣ ሽልማቱን ስላገኙት አመስግኖ፣ ወደ አሜሪካ የመምጣት እቅዱ ሳይሳካለት ቀርቶ አሁን ጂንካ ተመልሶ በግብርና ስራው ላይ እንደተሰማራ ገልጿል።

😁72👍24😭13❤5👀4🔥2👎1
ኢሳይያስ አፈወርቂ
የኤርትራ መንግስት በብልፅግና መንግሥት የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴን ተከትሎ በወቅቱ የኤርትራ ህዝብና መንግሥት ላደረገው ድንገተኛ ድጋፍ ምንም አይነት ፀፀት ወይም ስጋት አይሰማውም "የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቅ ዛሬ ኤርትራ 34ኛ የነፃነት ቀኗን ስታከብር ካደረጉት ንግግር የተወሰደ።

😁29👍25👀2❤1😭1
ለመምህራን ቅድሚያ ይሰጣል የተባለዉ የ120 ቢሊዮን ብር የቤት ብድር ተፈረመ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 41 ሺህ የመንግስት ሰራተኞችን የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚያደርግ የ25/75 ቤቶች ልማት ፕሮጀክት በጋራ ለማልማት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ይህ ስምምነት በተለይም ለመምህራን ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ቅድስት ወልደ ጊዮርጊስ እንደገለጹት፤ ስምምነቱ ቤት የሌላቸውን የመንግስት ሰራተኞችን ችግር ለመቅረፍ ያለመ ነው ተብሏል።
የመንግስት ሰራተኞች 25 በመቶ የቤቱን ዋጋ እንዲቆጥቡ የሚጠበቅ ሲሆን፤ ቀሪው 75 በመቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር እንደሚሸፈን ተጠቁሟል።
የብድሩ ጊዜ ለ20 ዓመታት የሚከፈል ሲሆን፣ በከተማዋ የሚገኙ 41 ሺህ የመንግስት ሰራተኞችን ተጠቃሚ ያደርጋል። ከፕሮጀክቱ የአዲስ አበባ መምህራን ቅድሚያ ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ወይዘሮ ቅድስት አክለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደተናገሩት ባንኩ ለዚህ ፕሮጀክት 120 ቢሊዮን ብር ብድር ለማቅረብ አቅዷል። የብድሩ ወለድ 14 በመቶ ሲሆን፤ ለ20 ዓመት የሚከፈል መሆኑን አስረድተዋል።
ፕሮጀክቱ ለሦስት ዓመታት የግንባታ ጊዜና አንድ ዓመት ደግሞ የብድር መክፈያ የእፎይታ ጊዜ የተሰጠው መሆኑም ተጠቁሟል ሲል ካፒታል ዘግቧል።

👍48😁20❤4🔥1
" ወደ ሃገር ውስጥ በመግባት ላይ የምተገኘውን ጣና ነሽ መርከብ ለማሳለፍ ሲባል የሃይል አቅርቦት ይቋረጣል " - አገልግሎቱ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፥ " ጣና ነሽ " መርከብን ለማሳለፍ ሲባል ነገ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ አሳውቋል።
" የመርከቧ ከፍታ ከኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስታንዳርድ በላይ በመሆኑ ዋና አስፖልት ተሻጋሪ የመካከለኛ እና ዝቅተኛ መስመሮች አደጋ እንዳያደርሱ እና መርከቧን በሰላም ለማሳለፍ ሲባል ነገ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ መርከቧን በተሸከመው ተሽከርካሪ ፍጥነት እና የትራፊክ ፍሰት ለሚወሰን ጊዜ ፦
- በሠመራ፣
- አይሳኢታ፣
- ሎግያ፣
- ሚሌ
- ኤሊውሃ አካባቢያቸው የሃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል "ብሏል።
መርከቧ አልፋ አገልግሎቱ እስኪመለስ ነዋሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ ያቀረበው አገልግሎቱ ስንት ሰዓት ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎቱ እንደሚመለስ የሰጠው ፍንጭ የለም።
EEU
@Yenetube @Yenetube

👍57😁33❤4😭1
በሞያሌ Mpox ቫይረስ የተያዘ ሰው መገኘቱን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ!
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ እስተዳደር ከሚገኙ በህመሙ መያዛቸው ከተጠረጠሩ ታማሚዎች በወሰደው ናሙና በMpox ቫይረስ የተያዘ ሰው ማግኘቱን አረጋግጧል።
ቫይረሱ እንደተገኘበት የተረጋገጠው የ21 ቀን እድሜ ያለው ህፃን ልጅ ሲሆን እናቱም በተደረገው ቀጣይ ምርመራ ለቫይረሱ እንደተጋለጠች ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ የህፃኑ አባትም ወደ ጎረቤት ሀገር ሄዶ የነበረ መሆኑ መታወቁና የሄደባቸውን አካባቢዎች እንዲሁም ከግለሰቡ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦችን የመለየትና ክትትል የማድረግ ስራ ተጀምሯል።
[ጤና ሚኒስቴር]
@YeneTube @FikerAssefa

👍36😭6❤4👎1
#ቴምር ሪልስቴት
⚠️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው ቤቶቾ እና ሱቆች
‼️ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
👉1 መኝታ 66ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
👉2መኝታ 71ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 745,500ብር
ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
👉2መኝታ 93ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 976,500ብር
ሙሉ ክፍያ 9,765,000ብር
👉3መኝታ 130ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው የሚጨርሱት
👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251939770177
+251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177

👍11❤5
Forwarded from YeneTube
🟥📣የመጨረሻ ዲያስፓራ ቁ3 ብሎክ
🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች
💸ቅድመ ክፍያ
💎ባለ 1 መኝታ በ 431 ሺ ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 619 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 751 ሺ ብር
💎ባለ 4 መኝታ በ 1,051,626 ብር
🛍️🛒ሱቆች ከ 43 ካሬ ጀምሮ
🏦60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው (እየኖሩበት ወይም አከራይተውት እስከ 20 አመት ቀስ ብለው የሚከፍሉት)
➡️በ 8% ቅድመ ክፍያ
➡️እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ ዋጋ (ለውስን ቤቶች) በመጠቀም
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ
➡️☎️ 09 72 42 75 95
➡️@Tirsit9 (telegram)
➡️Whatsapp Link-
https://whatsapp.com/dl/code=gsXOc8ttJB?mode=tac

👍4
ጃዋር መሀመድ ለኢሳያስ አፈወርቂ ንግግር መልስ ሰጠ፡፡ የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትላንት ያደረጉትን ንግግር ትርጉም ማዳመጡን በመግለፅ የጀመረው ጃዋር ‹‹በሁለት ቁልፍ ነጥቦች ላይ አስተያየት መስጠት እፈልጋለሁ›› ብሏል፡፡
ሲያስረዳም ‹‹ፕሬዝደንት ኢሳያስ የቀድሞ የጦር አጋራቸውን አብይ አህመድን የኦሮሞን ጥቅም የማይወክለውን የኦሮሙማ ርእዮተ አለም የሚያራምድ በማለት ከሰዋል›› ካለ በኋላ በዚህ ንግግር ደስተኛ አለመሆኑን አስታውቋል፡፡ ‹‹ኦሮሙማ የፖለቲካ ርእዮተ አለም አይደለም›› ያለው ጃዋር ይህ የኦሮሞ ማንነት ወይንም ባህል መግለጫ ቃል መሆኑን አስረድቷል፡፡
ልክ ኤርትራዊ ወይንም ኩኩዩ እንደማለት መሆኑንም ገልጿል፡፡ ቢሆንም ፕሬዝደንት ኢሳያስ ከ7 አመታት በኋላ አብይ የኦሮሞን እሴት እንደማይወክል በማመናቸው ደስተኛ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ለአስርት አመታት ከኤርትራ ጋር ሲሰሩ የነበሩትን የኦሮሞ ፖለቲካ መሪዎች ጨምሮ የኦሮሞ ምሁራንና የተከበሩ የአገር ሽማግሌዎች ለዲሞክራሲያዊ ሽግግር አብይን ሲደግፉ መቆየታቸውን የጠቀሰው ጃዋር ይሁንና ቤተመንግስት ከገባ በኋላ እነዚህን ገለል እንዳደረጋቸው አስረድቷል፡፡
"በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል የተፈጠረው የአጭር ጊዜ ትብብር ዘለቄታዊነት ሊኖረው እንዳልቻለ" የጠቀሰው ጃዋር እንደዚህ አይነት የአጭር ጊዜ ግብ ያላቸው ስሌቶች በሁለቱ አገራት መካከል መደገም እንደሌለበት አሳስቧል፡፡ የፕሬዝደንት ኢሳያስ የትላንቱ ንግግር በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ውጥረት መካረሩን እንዲያሳይ ጠቁሞም ‹‹በአፍሪካ ቀንድ ሌላ አውዳሚ ጦርነት ከመምጣቱ በፊት የሚመለከታቸው አካለት ይህንን አደገኛ አካሄድ ለማስቆም አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ አለባቸው›› ብሏል፡፡

👍42😁13❤6
YeneTube
Photo
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፍተኛ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ ትራምፕ ፑቲንን 'እብድ ነው' ሲሉ ተናገሩ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሞስኮ በዩክሬን ላይ ያደረሰችውን ከባድ የአየር ላይ ጥቃትን ተከትሎ በሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ደስተኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። ትራምፕ ባልተለመደ ተግሳጽ “ምን ነካው? ብዙ ሰዎችን እየገደለ ነው” ያሉ ሲሆን አክለውም ፑቲንን "ፍፁም እብድ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ቀደም ብለው ዋሽንግተን በቅርብ ጊዜ በሩሲያ ጥቃቶች ላይ የነበራት "ዝምታ" ፑቲንን የሚያበረታታ ነው ሲሉ በሞስኮ ላይ "ጠንካራ ጫና" -እንዲሁም ጥብቅ ማዕቀቦችን እንድትጥል አጥብቀው አሳስበዋል።
ሩሲያ 367 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ሚሳኤሎችን በመተኮሷ በዩክሬን በአንድ ሌሊት ቢያንስ 12 ሰዎችን ስትገድል በደርዘን የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል። ፑቲን በ 2022 ሙሉ ወረራ በዩክሬን ላይ ከጀመሩ ወዲህ በአንድ ሌሊት ውስጥ ከፍተኛው ጥቃት በትላንትናው እለት ፈፅመዋል።የአየር ሳይረን ማስጠንቀቂያ የሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሚሳኤሎች ጥቃት ሲፈፀም በበርካታ የዩክሬን ክልሎች ተሰምተዋል። በሰሜን ምስራቅ ካርኪቭ ከተማ አንድ ህፃንን ጨምሮ ቢያንስ ሶስት ሰዎች ቆስለዋል ሲሉ ከንቲባ ኢጆር ቴሬኮቭ ተናግረዋል። እሁድ እለት በኒው ጀርሲ ለጋዜጠኞች ትራምፕ ስለ ፑቲን ሲናገሩ “ለረጅም ጊዜ አውቀዋለሁ ፣ ሁል ጊዜም ከእርሱ ጋር ተስማምቼ ነበር ፣ ግን እሱ ሮኬቶችን ወደ ከተማዎች በመላክ ሰዎችን እየገደለ ነው ፣ እና በጭራሽ አልወደውም ። ” ብለዋል።
ትራምፕ አሜሪካ በሩሲያ ላይ የምትጥለውን ማዕቀብ ለመጨመር እያሰቡ እንደሆነ ተጠይቀው ሲመልሱ “በፍፁም” ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ከዚህ በፊት ደጋግመው ይዝቱ ነበር። ነገር ግን በሞስኮ ላይ ምንም አይነት ገደቦችን ተግባራዊ ለማድረግ ገና ነው ሲሉ ተናግረዋል።ብዙም ሳይቆዩ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ፑቲን "በፍፁም አብዷል" ሲሉ ጽፈዋል። "ሁልጊዜ ዩክሬን እንደሚፈልግ ተናግሬያለሁ፤ ቁርጥራጭ ግዛቶችን ብቻ አይደለም፤ እናም ምናልባት ይህ ትክክል ሊሆን ይችላል፥ ነገር ግን ይህንን ካደረገ ወደ ሩሲያ ውድቀት ይመራል!" ሲሉ ተደምጠዋል።

👍43😁22❤4😭1
ሪፖርተር ጋዜጣ ፓርላማ ገብቶ እንዳይዘግብ መከልከሉን አስታወቀ!
ላለፉት 30 ዓመታት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ተገኝቶ ዘገባዎችን ሲሠራ የቆየው ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ፓርላማ ገብቶ እንዳይዘግብ መከልከሉን አስታወቀ።ሪፖርተር ክልከለው የተጠለበት “ግልጽ ባልሆነ እና ባልታወቀ” ምክንያት መሆኑን ገልጿል። ከሚያዝያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ 'ምንም ዓይነት ምክንያት ሳይኖር ወይም በፓርላማው በይፋ ሳይገለጽ' ከበር ላይ በጥበቃ ሠራተኞች "ሪፖርተር እንዳይገባ ተብሏል” በሚል ዘጋቢዎቹ እንዳይገቡ መከልከላቸውን አስታውቋል፡፡
ሪፖርተር ለምን ፓርላማ ገብቶ እንዳይዘግብ እንደተከለከለ ጥያቄ የቀረበላቸው የፓርላማው የጥበቃ ሠራተኞች ‹‹እንዳይገባ ተብለን በቃል ተነግሮናል›› ከማለት ባለፈ፣ ለመከልከል የሚያበቃ ማስረጃ ማግኘት አለምቻሉን ገልጿል።ጋዜጣው ለፓርላማው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ምሥራቅ መኮንን (ዶ/ር) ለምን ሪፖርተር ፓርላማ እንዳይገባ እንደተከለከለ ጠይቆ፣ “እኔ አልከለከልኩም፣ በሕመም ምክንያት ቢሮ አልገባሁም፣ እንደገባሁ አሳውቃችኋለሁ” ማለታቸውንና ከገቡም በኋላ ምላሽ አለመስጠታቸውን ገልጿል፡፡
የሪፖርተር ዘጋቢዎች እንዳይገቡ የቃል ትዕዛዝ የሰጡት የፓርላማ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ንጉሤ መሸሻ (ዶ/ር) መሆናቸው በመነገሩ፣ ለእሳቸውም ሪፖርተር ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርቦ፤ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት “እኔ ያገድኩትም ሆነ የከለከልኩት ነገር የለም” በማለት ምላሽ ሰጥተዋል ብሏል፡፡ፓርላማው በይፋ ዕግድ እንደጣለ ወይም ትዕዛዝ እንደሰጠ ሳይታወቅ ክልከላ መደረጉ "ከሕግም ሆነ ከሞራል አንፃር ተገቢ አለመሆኑን" የገለጸው ሪፖርተር፣ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት (ሕግ አውጪው፣ ሕግ ተርጓሚውና አስፈጻሚው) መፍትሔ እንዲሰጡ በመጠየቅ ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡

👍26❤5👎2
የኢንሹራንስ ዘርፉ ለዉጪ ባለሃብቶች ክፍት እንዲሆን የሚያስችል አዲስ አዋጅ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተነገረ!
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሀገሪቱን የኢንሹራንስ ዘርፍ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት የሚያደርግ አዲስ አዋጅ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል።ውሳኔው የኢትዮጵያን የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ለማዘመን እየተደረገ ካለው ሰፊ ጥረት አንዱ አካል ነው ተብሏል።
ይህ የተገለጸው 51ኛው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ተቋም ዓመታዊ ኮንፈረንስ እና አጠቃላይ ስብሰባ በአዲስ አበባ በተጀመረበት ወቅት ነው።
የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምህረቱ እንደተናገሩት፣ የባንኩን ዘርፍ ለውጭ ባንኮች ክፍት ያደረገው አዲሱ አዋጅ "የፋይናንስ ዘርፋችንን ለማዘመን በተደረገው ጥረት ትልቅ ምዕራፍ" እንደሆነ ተደርጎ ይታያል። በዚህ ስኬት ላይ በመመስረት፣ ባንኩ አሁን ደግሞ ትኩረቱን የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪውን በማሻሻል ላይ አድርጓል።
Via Capital

👍23👎9❤5🔥1😭1
የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በፈጸሙት “የደፈጣ ተኩስ ጥቃት” ስድስት ሰዎች ተገደሉ
ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች፤ በጋምቤላ ክልል፣ በአኙዋሃ ዞን፣ ዲማ ወረዳ በሚገኝ ቦታ ላይ በከፈቱት “የደፈጣ ተኩስ ጥቃት” ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የወረዳው የአስተዳደር እና የፖሊስ ኃላፊዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። በትላንትናው ዕለት ጠዋት በተፈጸመው በዚህ ጥቃት፤ በዘጠኝ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን መመልከታቸውን በአካባቢው የሚገኙ የህክምና ባለሙያ ገልጸዋል።
የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ጥቃቱን የሰነዘሩት፤ ከዲማ ወረዳ 39 ሰዎች አሳፍሮ ወደ ጎግ ወረዳ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ እንደሆነ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ኡታክ ሜዶ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሱ የደፈጣ ጥቃት የተሰነዘረበት፤ ከዲማ ከተማ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ተጉዞ አቻኛ እና 45 በተባሉ ቀበሌዎች መካከል በደረሰበት ወቅት እንደሆነ የፖሊስ አዛዡ አስረድተዋል።
ታጣቂዎቹ በአውቶብሱ ላይ ተኩስ በከፈቱበት ወቅት “መሳሪያ የያዘ ተሳፋሪ” መልሶ በመተኮስ አጸፋውን መመለሱን ረዳት ኢንስፔክተር ኡታክ አመልክተዋል። በተኩስ ልውውጡ አንድ ታጣቂ መገደሉንም የፖሊስ አዛዡ ጠቁመዋል። በታጣቂዎቹ የደፈጣ ጥቃት የአውቶብሱን ሹፌር ጨምሮ የስድስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በስድስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱንም ጨምረው ገልጸዋል።
🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16005/

👍14😭5❤2
YeneTube
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከፍተኛ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ ትራምፕ ፑቲንን 'እብድ ነው' ሲሉ ተናገሩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሞስኮ በዩክሬን ላይ ያደረሰችውን ከባድ የአየር ላይ ጥቃትን ተከትሎ በሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ደስተኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። ትራምፕ ባልተለመደ ተግሳጽ “ምን ነካው? ብዙ ሰዎችን እየገደለ ነው” ያሉ ሲሆን አክለውም ፑቲንን "ፍፁም እብድ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል።…
ሩስያ በአንድ ቀን ውስጥ 110 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች መጣሏን አስታወቀች
የሩስያ ዩክሬን ጦርነት ከጀመረ 2000 ቀናት ሊሞላው በጣት የሚቆጠሩ ጊዜያት ቀርተዋል። ጦርነቱ አሁንም አውዳሚ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን ባለፉት ቅዳሜና እሁድ አስከፊው ጦርነት ተባብሶ ቀጥላል።
የዩክሬን ባለስልጣናት በተፈጸመባቸው ትልቁ የሩሲያ የአየር ላይ ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ12 ወደ 13 ከፍ ማለቱን እና ቢያንስ 60 ሰዎች መቁሰላቸውን አስታውቀዋል። ተጎጂዎቹ በሰሜን ምዕራብ ዞይቶሚር ክልል ውስጥ መገኛቸውን ያደረጉ የ8፣ የ12 እና የ17 አመት እድሜ ያላቸው ሶስት ታዳጊ ህጻናት እንደሚገኙበት ተነግሯል።
የዩክሬን አየር ሃይል ሩሲያ በአንድ ሌሊት 298 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና 69 ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን ገልጾ 266 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና 45 ሚሳኤሎችን ማውደም መቻሉንም አስታውቋል። ከዚህ በተጨማሪ የሩስያ የመከላከያ ሚኒስቴር ወታደሮቹ በዩክሬን ምስራቃዊ ዶኔትስክ ግዛት ውስጥ የምትገኘውን የሮማኒቪካ መንደር መቆጣጠራቸውንም አስታውቋል።
በተጨማሪም የሩሲያ አየር መከላከያዎች እሁድ እለት 110 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጥለፍ ያከሸፈ ሲሆን 13ቱ በሞስኮ እና በቴቨር የአየር ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መሆናቸውን አክሏል።
በሚሊዮን ሙሴ

👍23👎5❤4😁1
ህወሓትን ይተካል የተባለው ተገዳዳሪ ፓርቲ የምዝገባ ፈቃድ አገኘ
"ዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ" ጊዜያዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ ፈቃድ ተሰጠው
በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011ዓ.ም.ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ ለዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ዛሬ ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም መሰጠቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡

👍37😁15👎10❤4