Telegram Web Link
Ethiopian Building Codes Standards
Private Sector Engagement in Building Code Revision


The Ethiopian Construction Authority, in collaboration with the College of Technology and Built Environment (formerly AAiT) and The Urban Center, is organizing a series of technical sessions in June 2025 to support the ongoing revision of the Ethiopian Building Code Standards.

Designed for professionals in the construction industry, the 14 expert-led sessions of EBCS will address key themes such as structural design, fire and earthquake safety, mechanical and electrical systems, and emerging building technologies. These sessions aim to highlight the building codes and gather input from the private sector, ensuring that industry experience is reflected in the revised codes, making them both inclusive and grounded in practice.

📍Venue: The Urban Center
📅 Participation by registration only
🔗 Register here

#EthiopianBuildingCodeStandards
Open to professionals, engineers, architects, and others in the construction sector
4
83 በመቶ የሚሆነው የትራፊክ አደጋ የሚከሰተው በአሽከርካሪዎችና በተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ችግር ምክንያት መሆኑ ተገለጸ!

በከፍተኛ ደረጃ እየተከሰተ ካለው የትራፊክ አደጋ ውስጥ 69 በመቶ ገደማ የሚሆነው በአሽከርካሪዎች እና 14 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃት ምክንያት የሚከሰት መሆኑን የመንገድ ደህንነት እና መድህን ፈንድ አገልግሎት ለአሐዱ ገልጿል።

በሀገሪቱ ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ የመጣው የትራፊክ አደጋ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጹት በአገልግሎቱ የመንገድ ደህንነት ትምህርትና ግንባታ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዮሐንስ ለማ፤ ለአደጋው መጨመር ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም በዋናነት የአሽከርካሪዎች ቸልተኝነት ተጠቃሽ መሆኑን ተናግረዋል።መሪ ሥራ አስፈፃሚው አክለውም የእግረኞች የመንገድ አጠቃቀም ችግር፣ የመንገድ ሁኔታ እና በተለይ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከልክ በላይ ፍጥነት ማሽከርከር ለአደጋው ተጋላጭ የሚያደረጉ መንስኤዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

"አደጋው የሰው ሕይወት ከማጥፋቱ በተለይም አምራች የሚባለውን የሀገሪቱን ወጣት እያሳጣን ነው" ያሉት አቶ ዮሐንስ፤ በንብረት ውድመት ላይ እየደረሰ ያለው ምጣኔ ሃብታዊ ኪሳራ ቀላል የሚባል አለመሆኑን አንስተዋል።የትራፊክ አደጋው በአብዛኛው ከ5 እስከ 30 የእድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ የሚከሰት ሲሆን፤ አደጋውን የሚያደርሱት ደግሞ ከ18 እስከ 30 እድሜ ያሉ አሽከርካሪዎች እንደሆኑም አቶ ዮሐንስ ጠቁመዋል።

በ2016 ዓ.ም በንብረት ላይ በደረሰ አደጋ ብቻ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን አስታውሰዋል።የትራፊክ አደጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ አደጋው በትራፊክ ፓሊስና የሚመለከተው ባለድረሻ አካል ቁጥጥር ብቻ መቀነስ ስለማይቻል ሁሉም በጋራ ሊሰራ እንደሚገባ መሪ ሥራ አስፈፃሚው አሳስበዋል።

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
21👎1😭1
የእነ አቶ ጌታቸው ረዳ ፓርቲ በአንድ ወር ከአጋማሽ ውስጥ “በትግራይ መስራች ጉባኤዬን አካሄዳለሁ” አለ 

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ ፍቃድ ያገኘው ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ ፓርቲ (ስምረት)፤ እስከ አንድ ወር ተኩል ባለው ጊዜ ውስጥ መስራች ጉባኤውን እንደሚያካሄድ ገለጸ። ፓርቲው ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የአባላት ምልመላ እና ከክልል እስከ ቀበሌ ያሉ አደረጃጀቶችን የመፍጠር ስራዎችን እንደሚያከናውን አስታውቋል። 

ስምረት ፓርቲ ይህን የገለጸው፤ ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 23፤ 2017 በአዲስ አበባው ሸራተን ሆቴል በሰጠው የመጀመሪያው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ጋዜጣዊ መግለጫውን ከፓርቲው መስራቾች አንዱ የሆኑት የቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት በነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ ይሰጡታል ተብሎ ቢጠበቅም፤ ባጋጠማቸው “የጤና እክል” ምክንያት በመግለጫው ሳይሳተፉ ቀርተዋል።

እርሳቸውን በመተካት መግለጫውን የሰጡት የአዲሱ ፓርቲ የሚዲያ እና የኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ረዳኢ ሓለፎም፤ ፓርቲው በሚቀጥለው አንድ ወር ውስጥ ሁለት መሰረታዊ ስራዎችን እንደሚያከናውን ተናግረዋል። መቶ አባላትን በመያዝ ጊዜያዊ ፍቃዱን ከምርጫ ቦርድ ያገኘው ስምረት፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ከትግራይ እና ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች አባላትን የመልመል ስራዎች እንደሚሰራ አቶ ረዳኢ ተናግረዋል።

🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16063/

🔴 ሙሉ መግለጫውን በቪዲዮ ለመመልከት ➡️  https://youtu.be/B-oc3qLdRIg
26😁16👀1
ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ14 ሀገራት ላይ የቪዛ እገዳ ጣለች!

ሳውዲ አረቢያ በድምሩ በ14 ሀገራት ዜጎች ላይ የብሎክ ቪዛ ማውጣትን በጊዜያዊነት ማገዷን አስታውቃለች።ከነዚህ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን ጨምሮ ሰባት የአፍሪካ ሀገራት ይገኙበታል።

ይህ የቪዛ እገዳ አዲስ የጊዜያዊ የሥራ ቪዛ ማመልከቻዎችን እና በመጠባበቅ ላይ ያሉትንም የሚመለከት ነው የተባለ ሲሆን በውጭ ዜጎች የሥራ ኃይል ላይ የተመሰረቱ የሳውዲ አረቢያ ዘርፎችን እንደሚጎዳ ተገልጿል።

በእገዳው ሰለባ ሆነዋል ከተባሉት የአፍሪካ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ፣ ናይጄሪያ፣ አልጄሪያ፣ ሱዳን፣ ቱኒዚያ እና ሞሮኮ ይገኙበታል። ከዚህ በተጨማሪ ኢንዶኔዥያ፣ ኢራቅ፣ ዮርዳኖስ፣ የመን፣ ህንድ፣ ፓኪስታን እና ባንግላዲሽ ተካትተዋል።እነዚህ ሀገራት ከሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ የሰው ኃይል ፍልሰትና የገንዘብ ዝውውር ስለሚያገኙ፣ እገዳው ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያስከትል እንደሚችል ተዘግቧል።

የብሎክ ቪዛ የሳውዲ አረቢያ ቀጣሪዎች ቀድሞ በተፈቀደላቸው ኮታ የውጭ ሠራተኞችን እንዲቀጥሩ የሚያስችል ነው። የሳውዲ አረቢያ መንግስት የቪዛ እገዳውን የጣለበትን ዝርዝር ምክንያት ባይገልጽም፣ ይህ እርምጃ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ዕጣ ፈንታ አጣብቂኝ ውስጥ ሊጥል እንደሚችል ካፒታል ለመረዳት ችሏል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
49😁15👍4👎3😭2
በTelegram ላይ የተረጋገጠ ምልክት (Verified Checkmark) ለማግኘት የእርስዎን አካውንት አሁን Premium ያድርጉት
- 4GB እስከሆኑ ፋይሎችን ይጫኑ
- በፍጥነት ያውርዱ
- የእርስዎን online status ከሌሎች ይደብቁ
- እስከ 4 accounts ድረስ ይጠቀሙ
- ልዩ ስቲከሮች እና ኢሞጂዎች
🎭
- የድምፅ መልእክቶችን ጽሁፍ ያድርጉ
- ልዩ badges ያግኙ

- ማስታወቂያዎችን ያስወግዱ


አሁኑኑ ይቀላቀሉ እና የእርስዎን Telegram ተሞክሮ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግሩ! 🚀



📲 ሁሉፔይን ለመጠቀም ሁሉፔይ ሚኒ አፕን
https://www.tg-me.com/HuluPayOfficialBot/start?startapp እዚህ ሊንክ ጋር ያገኛሉ 🔗
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
14👍5
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ አሸማጋይ ድርጅት መሥራች አባል ሆነች

በቻይና የሆንግ ኮንግ ልዩ አስተዳዳር በትናንትናው ዕለት በተካሄደ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት የዓለም አቀፍ አሸማጋይ ድርጅት በይነ መንግሥታዊ ተቋም መመሥረቱ ይፋ ሆኗል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ መሥራች አባል ሆና መፈረሟ በመንግሥታት መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶችና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ በሽምግልና ለመፍታት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም፤ ተቋሙ በመንግሥታት፣ በመንግሥታትና በግሉ ዘርፍ መካከል የሚፈጠሩ ከኢንቨስትመንት ጋር የተያያዙ አለመግባባቶችን በሠላማዊ መንገድ በሽምግልና ለመፍታት ያቀደ መሆኑን መጠቆማቸውን  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል

@Yenetube @Fikerassefa
😁6828👍2😭2
የፒኤስጂ ደጋፊዎች በፓሪስ ደስታቸውን ሲገልፁ በተነሳ ግርግር 2 ሰዎች ሞተው፣ 192 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል

ፒኤስጂ ትናንት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ማሸነፉን ተከትሎ የክለቡ ደጋፊዎች በፈረንሳይ ዋና ከተማ በፓሪስ ጎዳናዎች ላይ ደስታቸውን ሲገልጹ አምሽተዋል።

በዚሁ ወቅት በተነሳ ግርግር 2 ሰዎች ሞተው 192 ደግሞ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፤ ከ500 በላይ ሰዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ይህ እንዳይመጣ ተፈርቶ ከ5 ሺህ 400 በላይ ፖሊሶች በደንብ ማስከበር ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበረ ቢሆንም፤ ደስታቸው ከቁጥጥር ውጪ የሆነባቸው ድጋፊዎች ግን በተለያዩ ቦታዎች እሳት አስነስተዋል።

በዚህም 200 ያህል መኪኖች እንደተቃጠሉ እንዲሁም የአውቶቡስ ፌርማታዎችና ሌሎች መሰረተ ልማቶች እንደተሰባበሩ ታውቋል።

ደጋፊዎቹ ከፖሊስ ጋርም ተጋጭተው የነበረ በመሆኑ፤ ፖሊስ ውሃ በመርጨት እና አስለቃሽ ጭስ በመተኮስ ለመበተን ሞክሯል።

በተነሳው ግርግር 22 ፖሊሶች እና 9 የእሳት አደጋ ሰራተኞችም ጉዳት ደርሶባቸውል።

በትናንትናው ዕለት ፓሪስ ሴንት ዠርሜን የጣሊያኑን ኢንተር ሚላን በሰፊ የጎል ልዩነት በማሸነፍ የመጀመርያውን የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያነሳ ሲሆን፤ በዚህም በፓሪስ የሚገኙ ድጋፊዎቹም ደስታቸው ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ አምሽተዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
43😭6😁4👍1
የቻናል ጥቆማ!

የonline ስራዎችን ታገኙበታላችሁ!
🚀 Upwork Profile Mastery 
Standout & land high-paying Upwork gigs!
Profile Tips 
Proposal Templates 
Niche Strategies 
📂 Free Tools + Examples 
👉 Join: https://www.tg-me.com/UpworkProfilePro 
መረጃዎችን ለመላክ @honelegn19
🎯 For Beginners:
• Profile Setup & Review 
• Proposal Writing Help 
• First Job & Rate Strategy 
• Client Communication Tips 
• Niche & Rules Guidance 
• Contract & Tool Support 
• Q&A Mentorship
🌟 Empowering freelancers with real strategies. 
መልካም እድል ለሁላችሁም!
2
🗝️  እጅግ አመቺ በሆነ አከፋፈል የቤት ባለቤት ይሁኑ

60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸውን ቤቶች በልዮ ቅናሽ

❇️  በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው DMC Real Estate የመጨረሻው መንደር ወቅቱን ባገናዘበ  ቅናሽ ዋጋ በተለያዩ ካሬ አማራጮች አቅርቦሎታል : :

⭐️ከሀያ አምስት ዓመታት በላይ ግንባታ ላይ ከቆየ አንጋፋ ድርጅት

📍አድራሻ - በመሀል ከተማ ለቡ መብራት-ሀይል

💸ቅድመ ክፍያ
   
    💎ባለ 1 መኝታ  በ 431 ሺ ብር
    💎ባለ 2 መኝታ  በ 619 ሺ ብር
    💎ባለ 3 መኝታ  በ 751 ሺ ብር
    💎ባለ 4 መኝታ  በ 1,051,626 ብር 

🛍️🛒ሱቆች ከ 43 ካሬ ጀምሮ

🏦60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው (እየኖሩበት ወይም አከራይተውት እስከ 20 አመት ቀስ ብለው የሚከፍሉት)

➡️በ 8% ቅድመ ክፍያ

➡️እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ ዋጋ (ለ20 ቤቶች) በመጠቀም የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ


➡️☎️ 09 31 14 82 42

➡️@Novi_03 (telegram)

➡️Whatsapp Link-
https://wa.me/251931148242
3
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ5 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ሬሚታንስ ወደ ሀገር ውስጥ መላኩን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ ለኢዜአ እንደተናገሩት በ2016 ዓ.ም አጠቃላይ የተላከው ሬሚታንስ 4 ነጥብ 4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ሲሆን በ2017 ዓም ዘጠኝ ወራት ብቻ 5 ነጥብ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወደ ኢትዮጵያ ተልኳል ፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
😁16👍7👎75🔥21
#ከቴምር ሪልስቴት
7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው 

🎯የክፍያ አማራጮች 40/60 ለሚከፍል

👉1መኝታ 75ካሬ 4,815,000ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 103ካሬ 6,612,600ብርሙሉክፍያ
👉3መኝታ 132ካሬ 8,474,400ብር ሙሉ ክፍያ
👉3መኝታ 146ካሬ 9,373,200ብር ሙሉ ክፍያ 9,373,000ብር 

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
1
Ethiopian Building Codes Standards
Private Sector Engagement in Building Code Revision


The Ethiopian Construction Authority, in collaboration with the College of Technology and Built Environment (formerly AAiT) and The Urban Center, is organizing a series of technical sessions in June 2025 to support the ongoing revision of the Ethiopian Building Code Standards.

Designed for professionals in the construction industry, the 14 expert-led sessions of EBCS will address key themes such as structural design, fire and earthquake safety, mechanical and electrical systems, and emerging building technologies. These sessions aim to highlight the building codes and gather input from the private sector, ensuring that industry experience is reflected in the revised codes, making them both inclusive and grounded in practice.

📍Venue: The Urban Center
📅 Participation by registration only
🔗 Register here

#EthiopianBuildingCodeStandards
Open to professionals, engineers, architects, and others in the construction sector
3
#አዲስ አበባ ከተማ ላለፉት 14ዓመታት ያህል በስራ ላይ የነበሩ የታክሲ ተራ አስከባሪዎች ማህበራት ከስራ ውጪ ከሆኑ ዛሬ ስድስተኛ ቀናቸውን እንደያዙ የደረሰኝ መረጃ ያመላክታል፡፡

ላለፉት 14 ዓመታት በአዲስ አበባ በሁሉም አከባቢዎች የታክሲ ተራ ማስከበር ስራ ላይ የነበሩ እስከ 9ሺ የሚደርሱ ተራ አስከባሪዎች ካሳለፍነው ሳምንት ረቡዕ እለት ጀምሮ ከስራ ውጪ መሆናቸውን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል፡፡
እነዚህ የታክሲ አስከባሪ ማህበራት ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በየወረዳቸው በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ተደራጅተው በዚህ ስራ ላይ ቆይተዋል፡፡

ማህበራቱ ስራ ያቆሙት በከተማዋ በሁሉም አካባቢዎች ያሉ የታክሲ ተራ አስከባሪዎች በአዲስ ሊተኩ እንደሆነ ከተነገረ ከአንድ ወር በኋላ ነው፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
11👎1
YeneTube
Photo
በአዋጅ የሚቀየር ነገር ካለመጣ 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ በተያዘለት ግዜ ይካሄዳል" ምርጫ ቦርድ

በአዋጁ ላይ በተቀመጠው ሁኔታ መሠረት 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ በተያዘለት ግዜ ይካሄዳል ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት በምርጫ ቅደመ ሁኔታዎች ዙሪያ በቦርዱ ዋና ስብሳቢ ሜላተወርቅ ሐይሉ በኩል መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም፤ በ2013 ዓ.ም ከተደረገው ምርጫ ማግሥት ጀምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የውይይት እና ጥናቶች መቅረባቸውን ዋና ስብሳቢዋ ገልጸዋል።

በጥናቱ መሠረትም ቦርዱ ማሻሻል ያለበትን ሁኔታ በመገምገም የአምስት ዓመት ስትራቴጂ በማውጣት ወደ ሥራ መገባቱን አንስተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ካለፈው ምርጫ ማግሥት የምርጫ ጉዳይ የሚመለከተው አዋጅ ቁጥር 1162 ላይ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይትት በማድርግ፤ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡን ወይዘሮ ሜላተወርቅ ሐይሉ ተናግረዋል።

አሐዱም "ለመሆኑ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጉባኤ በጊዜው የማያደርግ ከሆነ ምርጫው ጊዜው ሊቀየር ይችል እንደሆነ" ለቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ጥያቄ አቅርቧል።

ዋና ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ሐይሉ ሲመልሱም፤ "ሀገራዊ ምክክር እየተካሄደ ስለሆነ እራሳችን ቆጥበን አንቀመጥም" ሲሉ ተናግረዋል።

በአዋጅ ማሻሻያ ተደርጎ የሚመጣ አዲስ ነገር ካልመጣ በስተቀር 7ኛው ሀገራዊ  ምርጫን በተያዘለት ግዜ እንደሚያከናውንም ጨምረው ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከፀጥታ አንፃር አስቻይ ሁኔታ ባለባቸው ቦታዎች ሁሉ ምርጫው ይካሄዳል የተባለ ሲሆን፤ አስቻይ ሁኔታ በሌሉባቻው ቦታዎች ደግሞ ጊዜዉን እየጠበቀ የሚካሄድ ነው የሚሆነው ተብሏል።

በዚህ ቅድመ ዝግጅት ሥራም ከእጅ ንክኪ የሆነ የምርጫ ስርዓት ለመፍጠር እንደሚሰራ የተናገሩ ሲሆን፤ በተለይም የምርጫ ምዝገባውንና አጠቃላይ ሂደቱን በዲጂታል መንገድ እንደሚሰራም ተገልጿል።

በምርጫው ላይ የመራጮች ምዝገባ በከፊል እንዲሁም የእጩዎች ምዝገባ ሙሉ ለሙሉ በዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) እንደሚከናወንም ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ከ50 ሺሕ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን የተናገሩት ዋና ሰብሳቢዋ፤ "እነዚህን የምርጫ ጣቢያዎች እንደገና መመልከት ያስፈልጋል" ብለዋል።

በዚህም በተሰራ ሥራ እስካሁን 12 ሺሕ የምርጫ ጣቢያዎችን የመለየት ሥራ መሠራቱንም የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ አስረድተዋል።

የሀገር ወሰስጥ ተፈናቃዮች ወደ ምርጫ እንዲሳተፍ እና እንዲመረጡ ጭምር ጥናት ተደርጎ የሕግ ማዕቀፍ መሻሻያ እንደተደረገበትም ገልጸዋል።

በቀጣይ ዘርዘር ያለ የምርጫ ቅደመ ዝግጅት ሥራዎችን በመስራት ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።

@Yenetube @Fikerassefa
😁1817🔥1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የዩክሬን ድሮኖች በሩሲያ የጦር ጄቶች ላይ ከባድ የተባለ ጥቃት ፈፀሙ!

ዩክሬን በአራት የሩሲያ ወታደራዊ ካምፖች የሚገኙ 40 የጦር አውሮፕላኖች ላይ ተከታታይ ከባድ ጥቃቶችን መፈጸሟን አስታወቀች።ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ በጥቃቱ 117 ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቅም ላይ መዋላቸውን ገልፀው "34 በመቶ [የሩሲያ] ስትራቴጂክ ክሩዝ ሚሳዔል ተሸካሚዎችን" መምታታቸውን ተናግረዋል።

የዩክሬን ደኅንነት ተቋም ጥቃቱን ለመፈጸም ለአንድ ዓመት ከግማሽ ያህል ሲያቅድ መቆየቱንም ገልጸዋል።ሩሲያ በአምስት ግዛቶቿ ላይ "የሽብር ተግባር" መፈፀሟን አስታውቃለች።ጥቃቱ የተፈጸመው የሩሲያ እና የዩክሬን ተደራዳሪዎች ዛሬ ሰኞ ለሁለተኛ ዙር ድርድር ቱርክ ኢስታንቡል ከመገናኘታቸው በፊት ነው።

ሁለቱ አገራት ጦርቱን ለማጠናቀቅ ያስቀመጧቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ተከትሎ በሁለተኛ ዙር ድርድር ውጤት ይመጣል ተብሎ እንደማይገመት ታዛቢዎች ተናግረዋል።የዩክሬን ባለሥልጣናት በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ከባድ የሆነ የሚሳዔል ጥቃት እና የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ተናግረዋል።የሩሲያ ብሔራዊ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ፣ ሪያ በበኩሉ የአገሪቱ የደኅንነት መሥርያ ቤት በአገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል ታቅዶ የነበረን ጥቃት ማክሸፉን ዘግቧል።

ሁለት ግለሰቦች በፕሪሞሪ ግዛት በባቡር ሀዲድ ላይ አሻጥር ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዘግቧል።የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር የካቲት 2022 ዩክሬን ላይ ወረራ ከፍተው እስካሁን ጦርነት እየተካሄደ ነው።

@YeneTube @FikerAssefa
17👎1👀1
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር ኢስታንቡል ላይ ከመደራደሯ በፊት 160 የዩክሬን ሰው አልባ አይሮፕላን አወደመች

ሩሲያ ለዛሬ ሰኞ አጥቢያ ከ160 በላይ የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ማውደሟን አስታወቀች። እንደ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ሩሲያ ገለፃ የአየር መከላከያ ኃይሏ 162 የዩክሬን ድሮኖችን መትቶ አውድሟል። አብዛኛዎቹ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ተመተው የከሸፉት በሁለቱ ሃገራት የድንበር አካባቢዎች ነው። 57 በኩርስክ ክልል እና ሌሎች 31 በቤልጎሮድ ክልል መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቃል። ሰው አልባ ጥቃቱ የተፈፀመው ከሩሲያ እና ከዩክሬን የተውጣጡ ልዑካን ዛሬ በቱርክ ሊያደርጉት ከታቀደው ስብሰባ ሰዓታት በፊት ነው። የስብሰባው አላማ ከሦስት ዓመታት በላይ በዘለቀው የዩክሬን ግጭት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመደራደር ነው። ልኡካኗን ወደ ኢስታምቡል እንደምትልክ ያስታወቀችው ዩክሬን ትናንት የስለላ መሥሪያ ቤቷ በአራት የሩሲያ ወታደራዊ የአየር ማረፊያ ላይ በፈጸማቸው ጥቃቶች ከ40 በላይ የሩሲያ የጦር እና የስለላ አውሮፕላኖች ማውደሙን ይፋ አድርጋ ነበር። ሁለቱ ሃገራት ከድርድሩ በፊት በየፊናቸው የወሰዱት ጠንካራ ውጊያ በድርድሩ ላይ የሚኖረውት ሚና እየተጠበቀ ነው።

ፎቶ፤  በኢስታንቡል ሩሲያ እና ዩክሬን የሚደረደሩበት የቺራጋን ቤተ መንግሥት

@Yenetube @Fikerassefa
33🔥4😭1
2025/07/13 18:13:16
Back to Top
HTML Embed Code: