Telegram Web Link
እስራኤል አዲስ ጥቃት መፈፀሟ ተነገረ !

የእስራኤል አየር ሃይል አመሻሹ ላይ በኢራን መአከላዊ ክፍል በመዝለቅ ጥቃት መፈፀሙን አስታወቀ ።

የእስራኤል የስለላ ድርጅት እንደገለፀዉ ከሆነ አመሻሹ ላይ የፈፀመዉ ጥቃት የኢራንን የጸጥታ ተቋም ልብ ውስጥ ዘልቆ በመግባት ከኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ጋር ግንኙነት ያላቸውን ቦታዎች ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን የአየር መከላከያ እና የባለስቲክ ሚሳኤል ማዕከላትን ኢላማዎች መምታቱን ገልጿል ።

የእስራኤል ፕሬዘዳንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "ለኢራን ህዝብ ምንም ነገር እንደሌለን በቀጥታ እየነገርኳቸው ነው። እየተሰቃዩ መሆናቸውን እናውቃለን። የሚኖሩበትን ሁኔታ አይተናል… ትግላችን ከኢራን ህዝብ ጋር አይደለም ። ጥቃቱ የተካሄደው (ቦታው) ሰዎች በጎዳና ላይ በማይገኙበት ጊዜ ነው ፣ እናም በሲቪሎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ የተቻለንን ሁሉ አድርገናል" ብለዋል ።

ጥቃቱን በተመለከተ ከቴህራን በኩል በተገኘ መረጃ በተራራ ውስጥ በጥልቀት የተገነባው ፎርዶ የኑክሌያር ማብሊያ ጣቢያ ጨምሮ በርካታ ሰዉ የሚኖርባቸዉ አካባቢዎች በቦንብ መደብደቡን በጥቃቱ 78 ሰዎች መሞታቸውን እና ከሟቾቹ መካከል ህጻናትን ጨምሮ ሲቪሎች እንደሚገኙበት የኢራን መንግስት ቲቪ ገልጿል ።
ኢራን ዛሬ ከመሸ በኋላ በሁለት ዙር በቴልአቪቭ በ7 ቦታዎች ላይ የሚሳኤል ጥቃት ፈፅማለች።

በጥቃቱ የተነሳ የእስራኤል ዋና የጦር ማዘዣ አካባቢ እሳት መታየቱ ተዘግቧል።

Source: BBC

@Yenetube
አሜሪካ የኢራን ሚሳኤሎችን በማምከን መሳተፏ ተገለፀ

የአሜሪካ ጦር ወደ እስራኤል ያቀኑትን የኢራን ሚሳኤሎችን ለመምታት ረድቷል ሲሉ ሁለት የአሜሪካ ባለስልጣናት ለሮይተርስ ተናግረዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉት ባለስልጣናቱ፣ ተዋጊ ጄቶች ወይም የጦር መርከቦች በመጠቀም የመከላከል ሥራውን ስለመፈጸማቸው ጨምሮ ተጨማሪ መረጃ አልሰጡም።

@Yenetube @Fikerassefa
Forwarded from YeneTube
#ቴምር ሪልስቴት
⚠️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣናቸው ቤቶቾ እና ሱቆች
‼️ፒያሳ (ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት) ጀርባ
         👉1 መኝታ 66ካሬ=
         10% ቅድመ ክፍያ 693,000ብር
         ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
         👉2መኝታ 71ካሬ
        10%ቅድመ ክፍያ 745,500ብር
        ሙሉ ክፍያ 7,455,000ብር
         👉2መኝታ 93ካሬ=
       10% ቅድመ ክፍያ 976,500ብር
       ሙሉ ክፍያ 9,765,000ብር
        👉3መኝታ 130ካሬ
      10%ቅድመ ክፍያ 1,365,000ብር
      ሙሉ ክፍያ 13,650,000ብር
        👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው         የሚጨርሱት
        👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል
‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Week 2 Sessions


We’re back with five expert-led sessions in Week 2 of our 14-part workshop series, continuing the dialogue between private sector professionals and code developers:

🏢 Building Facility Management
🧯 Fire Safety & OHS
🏗 Structural Design Fundamentals
🚿 Building Plumbing Systems
📐 Spatial Design in Buildings


📅 June 10, 12 & 14, 2025
📍 The Urban Center
🖥 Also, live on TUC Facebook page & Google Meet
☕️ Free sessions with refreshments

Participants are encouraged to register only for the sessions most relevant to them.

📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7
🔗 Google Meet links will be shared 30 minutes before each session.

Many thanks to our partners for making this possible!

#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #FireSafety #StructuralDesign #Plumbing #FacilityManagement #SpatialDesign
የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ ምርጫ ቦርድ “ነጻና ገለልተኛ” ሆኖ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫው ለማስፈጸም “አንዳችም አስቻይ ሁኔታ የለም” አለ!

የስድስት ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያካተተው የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ፤ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “ነጻና ገለልተኛ ሆኖ” 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫው ለማስፈጸም “አንዳችም አስቻይ ሁኔታ የለም” ሲል ገለጸ።ኮከሱ፤ ሰኔ 02 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ የምርጫ ቦርድን “በወገኝተኝነት” እና “ለገዢው ፓርቲ በታዛዥነት” ከሷል። በዚህም "የገዢው ፓርቲ አሸናፊነት አስቀድሞ የሚታወቅ ነው" ብሏል።

መግለጫው፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከነባር አመራሮቹ “ሶሰቱን (60 በመቶ) ለመቀየር ጫፍ መድረሱን እያሳወቀን ነው” ብሏል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ፤ “ልምድ በሌላችው ኮሚሽነሮችና በወቅታዊው የፖለቲካ ያለመረጋጋት፣ የግጭትና ጦርነት ውጥረትና ሁለንተናዊ ውስብስብ ተጨባጭ ሁኔታ” ውስጥ የሚደረግ ምርጫ “ጣጣና መዘዙ” እንደሚያስከትሉ አስጠንቅቋል።በመሆኑም በዚህ ተጨባጭ እውነታ ምርጫ ቦርድ "ነጻና ገለልተኛ" ሆኖ ምርጫውን ለማስፈጸም "አንዳችም አስቻይ ሁኔታ የለም" ያለው ኮከሱ፤ “ጉዳዩ ወደከፋ አደጋና ትርምስ እንዳንገባ በእጅጉ የሚያሳስብና የሚያሰጋ ነው” ሲል በአጽንዕኦት ገልጿል።

ኮከስ ከምርጫ ቦርድ በተጨማሪ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ላይም ትችት ሰንዝሯል። በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የቀረቡ የማሻሻያ ኃሣቦችና የተነሱ ጥያቄዎች “ቦታ ሳይሰጣቸው”፣ እንዲሁም የኮሚሽነሮች ሹመት “የብልጽግናውን አዋጅ እንኳ ያልተከተለና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍላጎትና ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ነው” ብሏል።በመሆኑ የተሰጠውን ከፍተኛ ተግባርና ኃላፊነት “በህግ፣ በዕውቀትና እውነት በነጻነትና ገለልተኝነት በሚዛናዊነት ከአገራዊ ተልዕኮው አንጻር ለመፈጸም ይቸገራል” ሲል ገልጿል።

በተጨማሪም ኮሚሽኑ ከምስረታው ጀምሮ ኮሚሽኑ ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎችና ባከናወናቸው ተግባራት ኮከሱ ያነሳቸውን ችግሮች የሚያረጋግጡ አፈጻጸሞች፣ በተለይም የኮከሱን “የመፍትሄ ኃሳቦች ከመቀበል ይልቅ እንደተጻራሪና ተቃዋሚው በማየት ሲያገለኝ ቆይቷል” በማለት ከሷል፡፡አክሎም፤ “በያዘው አግላይ አካሄድ ቀጥሎ”፤ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ሥራውን “ሊያጠናቅቅ ቀርቶ አጀንዳ አሰባስቦ ባለመጨረሱ” የአንድ ዓመት ተጨማሪ ዕድሜ ተሰጥቶታል ሲል ተችቷል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
Photo
"በኢራን የኒውክሌር መሰረተ ልማቶች ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰም"፦ የኢራን አቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት ቃል አቀባይ


ከዓርብ ሌሊት ጀምሮ እስካሁን በቀጠለው የኢራንና የእስራኤል ግጭት በሁለቱም በኩል ጉዳት ደርሷል።

እስካሁን ይፋ የሆኑ አሀዞች እንደሚያመለክቱት እስራኤል በኢራን የተለያዩ ከተሞች ላይ ባደረገችው የቦንብ ድብደባ 320 ኢራናውያን ሲቆስሉ፤ ቁልፍ የሆኑ ወታደራዊ መሪዎችና አቶሚክ ሳይንቲስቶችን ጨምሮ 78 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

በእስራኤል ወገን ደግሞ 3 ሰዎች መሞታቸውንና አርባ የሚሆኑ ቆስለው በሆስፒታል እንደሚገኙ እየተዘገበ ነው።

ጥቃትና አጸፋውን ተከትሎ የኢራን አቶሚክ ኢነርጂ ቃል አቀባይ ቤህሩዝ ካማልቫንዲ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም እስራኤል በናታንዝ፣ ፎርዶ እና ኢስፋሃን አቶሚክ ጣቢያዎች ላይ በፈፀመችው ድብደባ በኒውክሊየር ጣቢያዎቹ ላይ ከደረሰው መጠነኛ ጉዳት ውጭ በኒውክሊየር መሰረተ ልማት ላይ የደረሰ ምንም ዓይነት ጉዳት የለም ሲሉ ተናግረዋል።

ካማልቫንዲ አያይዘውም፥ ኢራን ቀደም ሲል በነበራት መረጃ በኒውክሊየር መሰረተ ልማቷ ላይ ጥቃት ሊሰነዘር እንደሚችል በመገመት አብዛኛውን ወሳኝ ቁስ አስተማማኝ ወደሆነ ቦታ አዛውራለች ብለዋል።

በመሆኑም በኢራን አቶሚክ መሰረተ ልማት ላይ የደረሰ ጉዳት ምንም ዓይነት ጉዳት የለም ሲሉ መናገራቸውን የኢራን መንግስት ዜና አገልግሎት ኢርና ዘግቧል።

@Yenetube @Fikerassefa
የደብረፂዮን ላፕቶፕ ጉዳይ

የደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ላፕቶፕ ኮምፒተርን " ሰርቀዋል " ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት በዋስ እንዲፈቱ ቢወስንም አልተተገበረም።

6 የVIP የጥበቃ አባላት የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚከካኤል (ዶ/ር) ላፕቶፕ ኮምፒተርን " ሰርቀዋል " በመባል ተከሰዋል።

የመቐለ ዓዲ ሓቂ ክፍለ ከተማ ፍርድ ቤት ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሊቀመንበሩ ላፕቶፕ ኮምፒተር ስርቆት የተጠረጠሩት ግለሰቦች በዋስ እንዲፈቱ ወስኗል።

ስድስቱ ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፍርድ በሰጠው ውሳኔ መሰረት ቤተሰቦቻቸው ብር ቢያስይዙም " ከላይ የመጣ ትእዛዝ " በሚል ከእስር አልተለቀቁም ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
YeneTube
Photo
“እኔ በሕይወት እያለሁ መምህራን መኪና ኖሯቸው ከማየት በላይ የሚያስደስተኝ ነገር የለም”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)


ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የመምህራን ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ የመምህራን ጥያቄዎች ሌሎችንም አካታች በሆነ ማዕቀፍ ሊታዩ የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የመጀመሪያው ሀገር ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን እንዳለበት ጠቅሰው፤ ከዚያ ውጭ የሚቀርበው ንጽጽር ግን ኢትዮጵያ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ ጋር ስለማይሄድ ዋጋ የለውም ብለዋል።

ነጻ ሕክምና፣ ነጻ ትምህርት፣ መኖሪያ ቤት የመሳሰሉት ጥያቄዎች ሲጠየቁ የወታደሩን፣ የሐኪሙን እና የሌላውንም ደምሮ ማየት እንደሚያስፈልገ አመላክተዋል።

"እኔ በሕይወት እያለሁ መምህራን መኪና ኖሯቸው፣ መኪናቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤታቸው በር ላይ አቁመው ሲያስተምሩ ከማየት በላይ ለኔ ደስታ የለም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ውስጥ ውስጡን እየተሠሩ ያሉት ሥራዎች ሲሳኩ የመምህራን ጥያቄዎች ምላሽ ያገኛሉ ብለዋል።

የመምህራን ጥያቄ በደመወዝ ጭማሪ ብቻ የማይመለስ መሆኑን አንስተው፣ የደመወዝ ጭማሪው ላይ ብቻ ትኩረት ከተደረገ ያለችው ተበልታ ታልቃለች በማለት የሚከተለውን መዛባት ጠቁመዋል።

ያለችውን በልቶ ከመጨረስ በራስ ላይ ጨክኖ ገበታን ማስፋት፤ ለዚህ ደግሞ ምርትን ማብዛት አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።

የመምህራን ጥያቄ ከሌሎች ጥያቄዎች ጋር ታይቶ ነገን ታሳቢ ባደረገ መልኩ መመለስ እንደሚቻል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በለሚ ታደሰ
@Yenetube @Fikerassefa
2025/07/04 06:24:08
Back to Top
HTML Embed Code: