Telegram Web Link
ቦይንግ የአፍሪካ ዋና መቀመጫውን በኢትዮጵያ ሊከፍት ነው!

ግዙፉ የአውሮፕላን አማራች ኩባንያ ቦይንግ፤ የአፍሪካ ዋና መቀመጫውን በኢትዮጵያ ሊከፍት መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡የኩባንያው ውሳኔ ተቋሙ ዋና መቀመጫውን በኬኒያ አሊያም በደቡብ አፍሪካ ሊያደርግ እንደሚችል ሲሰጡ የነበሩ ግምቶችን ያስቀረ እና ኢትዮጵያ ቀዳሚ ምርጫው መሆኗን ያረጋገጠ ነው፡፡

እ.አ.አ በ2023 ኢትዮጵያ እና ቦይንግ ኩባንያ የተወሰኑ የአውሮፕላን ክፍሎችን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማምረት ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል፡፡

የአፍሪካ አየር መንገዶች በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ1 ሺህ በላይ አዳዲስ አውሮፕላኖችን እንደሚፈልጉ የኩባንያው ጥናት ያመላክታል፡፡ ከእነዚህ ወስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት አዳዲስ አውሮፕላኖች የአየር መንገዶቹን መዳረሻ ለማስፋት እንደሚያገለግሉ ዲደብሊው አፍሪካ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የእነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሆነ!

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ለማዘዋወር በመሞከር ተጠርጥረው የከባድ ሙስና ወንጀል ክስ በተመሠረተባቸው እነሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን የቀረበውን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አድርጓል፡፡

የዋስትና ጥያቄውን ያልተቀበለው ችሎቱ፣ በተከሳሾች የክስ መቃወሚያ እና በዐቃቤ ሕግ ምላሽ ላይ ለመበየን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት ቅርንጫፍ፣ ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት ሙከራ አድርገዋል በሚል ከተከሰሱ አምስት ግለሰቦች መካከል፣ አንደኛ ተከሳሽ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንንና ሁለተኛ ተከሳሽ ኢያሱ እንዳለ፣ ባለፈው ሳምንት በጠበቆቻቸው አማካይነት ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ውሳኔ ለመስጠት የተቀጠረው የዛሬ ችሎት ዋስትናውን አልተቀበለም።

የተከሳሾች ጠበቆች እና ዐቃቤያነ ሕግ በዋስትናው ጥያቄ ላይ ክርክር ያደረጉት፣ ባለፈው ሰኞ ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ነበር፡፡ጠበቆች፥ ክሱ ከሙስና ወንጀል ዐዋጅ ድንጋጌ ጋራ የማይጣጣም እንደኾነና በዐዋጁ አንቀጽ 32 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት፣ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል የሚያካትተው የመንግሥት ወይም የሕዝብ ድርጅት ሠራተኞችን ነው፤ ብለው ተከራክረዋል፡፡

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ፣ ማንኛውም ግለሰብ፣ ከባድ የማታለል ወንጀል ከፈጸመ ዋስትና የሚያስከለክል ክስ እንደሚመሠረትበት ያስረዱልኛል ያላቸውን የዐዋጁንና የወንጀል ሕጉን ድንጋጌዎች ጠቅሶ ተከራክረው ነበር፡፡

ዛሬ ሰኞ፣ ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም. የዋለው ችሎት፣ የዐቃቤ ሕግን መከራከሪያ ተቀብሎ ዋስትናውን ውድቅ አድርጓል፡፡ ችሎቱ ለውሳኔው ያቀረበውን ምክንያት ያስረዱት ከሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ ጠበቆች አንዱ አቶ ገብሩ ማኅተመ ሰይፉ፣ ውሳኔው የተሰጠው በሁለት ዳኞች መኾኑንም አስረድተዋል፡፡

ዐቃቤ ሕግ፣ ባለፈው ሳምንት በአንደኛ እና ሁለተኛ ተከሰሾች ለቀረበው የክስ መቃወሚያም የጽሑፍ ምላሽ አቅርቧል፡፡ሦስተኛው ተከሳሽ ደግሞ፣ በጠበቆቻቸው አማካይነት የክስ መቃወሚያ በዛሬው ዕለት አቅርበዋል፡፡

ችሎቱ፣ በሦስቱ ተከሳሾች የክስ መቃወሚያና በዐቃቤ ሕግ መልስ ላይ ብይን ለመስጠት፣ ለፊታችን ግንቦት 29 ቀን ቀጥሯል፡፡አራተኛ እና አምስተኛ ተከሳሽ፣ ዛሬም ችሎት አልቀረቡም፡፡ ፖሊስ አፈላልጎ እንዲያቀርባቸው፣ ካላገኛቸውም ከሚኖሩበት ወረዳ በጽሑፍ ማረጋገጫ እንዲያቀርብ ችሎቱ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
በነዳጅ ላይ ተደርጓል በተባለው የማስተካከያ እርምጃ ሀገሪቷ በዕዳ ምክንያት ነዳጅ ማስገባት ከማትችልበት ደረጃ ላይ ከመድረስ ታድጓታል ተባለ!

ባለፉት ጥቂት አመታት የነዳጅ ዋጋ አለመከለሱ በዋጋ ማረጋጊያ ፈንድ ላይ የነበረዉን ገንዘብ ተመናምኖ እንደነበር ተገለፀ።

ለነዳጅ ግዢ የሚዉለዉ ተቀማጭ ገንዘብ አልቆ እዳ እያስመዘገበ እንደነበር የገለፀዉ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አፋጣኝ የማስተካከያ እርምጃ መወሰዱ ሀገሪቷ በዕዳ ምክንያት ነዳጅ ማስገባት እንዳትችል ሊያደርግ የነበረዉን ሂደት አስቀርቷል ብሏል።

በነዳጅ ማረጋጊያ ፈንድ ላይ የነበረዉ መጠባበቂያ ገንዘብ አልቆ ዕዳ ማስመስገብ ከጀመረ ወዲህ በአንድ ወር ወስጥ ከ 10 እስከ 15 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እየተመዘገበ እንደነበር ተነግሯል።

ሀገሪቷ ለነዳጅ ግዢ የምታወጣውና በዋጋ ማረጋጊያ ፈንድ ላይ የነበረዉ መጠባበቂያ ገንዘብ አልቆ ዕዳ በማስመዝገብ በወር እስከ 15 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ሲያስመዘግብ እንደነበር ባለስልጣኑ ገልጿል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
ሠራተኛው 'በቂና ተመጣጣኝ' ክፍያ እንዲያገኝ ተጠየቀ!

የኢትዮጵያ አሠሪዎች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢአማኮ) 'የሠራተኛው ተደጋጋሚ ጥያቄ የሆነውን' የአነስተኛ ደሞዝ ወለል ይወሰን ጥያቄ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ሲል አሳሰበ፡፡

ኢአማኮ በስሩ ከሚገኙ የአሠሪ ፌዴሬሽኖች ጋር በትላንትናው ዕለት የ2015 እና የ2016 ዓ.ም ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት፤ በመንግሥት፣ በአሠሪውና በሠራተኛው የጋራ ምክከር ተደርጎ ሠራተኛው 'በቂና ተመጣጣኝ' ክፍያ እንዲያገኝ ጠይቋል።

ሠራተኛውን ወክለው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው አህመድ፤ በአብዛኛው ድርጅቶች ለሠራተኞቻቸው የሚከፍሉት የደመወዝ ክፍያ እዚህ ግባ የማይባልና በሀገራችን የተፈጠረውን የዋጋ ግሽበት መቋቋም የማይችል ነው ብለዋል።

መንግሥት፣ አሠሪና ሠራተኛ በጋራ በመነጋገር ሊያኖር የሚችል የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል በጥናት ላይ ተመርኩዞ ባልተቀመጠበት ሁኔታ ተፈላጊውን ጥራት ያለው ምርታማ ሠራተኛን ማፍራት አስቸጋሪ በመሆኑ አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ አሠሪዎች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢአማኮ) ፕሬዝዳንት አቶ ታደለ ይመር በበኩላቸው የአነስተኛ ደመወዝ ወለል ጉዳይ ተረድተን ወደ ተግባር ለመለወጥ አሠሪዎች ቁርጠኛ መሆን ይገባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ አሠሪዎች ኮንፌዴሬሽን የተለያዩ አሠሪዎች ፌዴሬሽኖችን በማሰባሰብ ለአሠሪውም ሆነ ለሠራተኛው በተደራጀ መልኩ ጥያቄዎችን የማቅረብ አላማን ሰንቆ በ2010 ዓ.ም. የተመሰረተ ተቋም ነው።

[Addis Standard]
@YeneTube @FikerAssefa
ግንቦት 20 ቀረ?

የደርግ መንግሥት ወድቆ ኢህአዴግ ሥልጣኑን የተቆጣጠረበት ግንቦት 20፤ የተለይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ወደ ሥልጣን ከመምጣቱ በፊት ለአስርት ዓመታት በድምቀት ሲከበር ቆይቷል። ቀኑ ሲከበርም ሥራ እና ትምህርት ዝግ ይሆኑ ነበር።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ግን የበዓሉ አከባበር የቀዘቀዘ ሲሆን፣ በመንግሥት ደረጃ በዓሉ በድምቀት መከበር ቢቀርም እንኳ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ግንቦት 20 ላይ ዝግ በመሆን ቀጥለዋል።

ይሁን እንጂ ከ1984 ዓ.ም. ጀምሮ ሲከበር የቆየው ግንቦት 20 አሁን በሥራ ላይ ባለው የሕዝብ በዓላት እና የእረፍት ቀናት አዋጅ ላይ በሕዝብ በዓልነት አልተደነገገም። የኢህአዴግ መንግሥት በዓሉን ማክበር ከጀመረ አራት ዓመታት በኋላ በ1988 ዓ.ም. ይህንን አዋጅ ሲያሻሽልም ግንቦት 20ን በሕዝብ በዓላት ዝርዝር ውስጥ አላካተተውም።

የሕግ ባለሙያው አቶ አንዱዓለም፤ “እኔ እስከማውቀው ድረስ ግንቦት 20 ብሔራዊ በዓል የሆነበት ሕጋዊ መሠረት አለው ብዬ አላምንም” ሲሉ በዓሉ ሲከበር የነበረው ያለ ሕጋዊ እውቅና መሆኑን ያስረዳሉ። በአዋጅ የተደነገገ ጉዳይ የሚሻሻለውም ሆነ የሚሻረው በአዋጅ መሆኑን የሚያገልጹት አቶ አንዱዓለም፤ ግንቦት 20ን ግን የሚደግፍ አዋጅ ሳይኖር “በልምድ” ሲከበር መቆየቱን ጠቅሰዋል።

በተመሳሳይ መልኩ አሁን በሥራ ላይ ባለው አዋጅ ውስጥ በየዓመቱ መስከረም ሁለት ቀን በብሔራዊ በዓልነት እንዲከበር የተደነገገው የአብዮት መታሰቢያ በዓልም አህአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ “በልምድ” መከበሩ እንዲቀር መደረጉን አንስተዋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታኅሣሥ 10/2016 ዓ.ም. ይህንን ረቂቅ አዋጅ ወደ ፓርላማ በመራበት ወቅት ቢቢሲ ያነጋገራቸው የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር የሕግ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ አቶ በላቸው ድሪባ ስለ ግንቦት 20 ለቀረበላቸው ጥያቄ “[በብሔራዊ በዓልነት] ያካተትናቸው የኢትዮጵያን ሕዝብ ታሪክ ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተው ነበር።

አቶ በላቸው፤ “[በረቂቅ አዋጁ ላይ] ይዘን የወጣነው ‘የሕዝብ ናቸው፣ ሰው ተቀብሏቸዋል’፤ እንደ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ፣ አገር፣ ዜጋ በጋራ የምንስማማባቸውን ነው” ሲሉ በሕዝብ በዓልነት ስለተቀመጡት በዓላት ገልጸዋል።

የሕግ ባለሙያው አቶ አንዱዓለም እንደሚያስረዱት ለፓርላማው በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ግንቦት 20 ሳይጠቀስ መቅረቱ በዓሉ ከዚህ በኋላ እንደማይከበር የሚያመለክት መሆኑን አስረድተዋል።

የሕግ ባለሙያው፤ “[በአዲሱ አዋጅ] ‘ኢትዮጵያ ውስጥ የሚከተሉት በዓላት ብሔራዊ በዓላት ሆነው ተደንግገዋል’ ተብሎ ከተዘረዘረ እና አንድ [ቀድሞ የነበረ] በዓል እዚህ ውስጥ ከሌለ፤ ከዚህ ቀደም በአዋጅ ውስጥ ቢኖር ራሱ በአመላካችነት (impliedly) ተሽሯል ብለን መውሰድ እንችላለን” ሲሉ ሀሳባቸውን አብራርተዋል።

አክለውም፤ “[ረቂቅ አዋጁ] ግንቦት 20 መሻሩን በግልጽ ባይጠቅስ እንኳ ዘሎታል። ስለዚህ ከአሁን ወዲህ ግንቦት 20 ብሔራዊ በዓል ነው ብለን መከራከር የምንችልበት አግባብ አለ ብዬ አላምንም” ብለዋል።

ከዚህም ባሻገር ረቂቁ፤ “ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማንኛውም አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ ወይም ልማዳዊ አሠራር በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም” በሚል ማስቀመጡ “በልምድ” ሲከበር የነበረው ግንቦት 20 እንደሚቀር አመላካች መሆኑን ገልጸዋል።

ቢቢሲ አዲስ 'የሕዝብ በዓላትን እና የእረፍት ቀንን ለመወሰን' በወጣው አዋጅ ዙሪያ ከሰራው ዘገባ የተወሰደ

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ:-

https://www.bbc.com/amharic/articles/c516kg58354o

@YeneTube @FikerAssefa
ከግንቦት 21 ጀምሮ ለ7 ቀናት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ የምክክር ምዕራፉን ይጀምራል።

ከ2 ሺህ በላይ ሰዎችም ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የስብሰባው ሥርዓቶች ምንድናቸው ?

1. ማንኛውም ተሳታፊ በነጻነት ሀሳቡን የመግለጽ መብት አለው። ሆኖም ተሳታፊዎች ከጥላቻ፣ ከአዋራጅ እና ከተንኳሽ ንግግሮችመቆጠብ፤

2. በምክክሩ ጊዜ መደማመጥን ከሚያውኩ፣ ሁከትን ከሚፈጥሩ እና መረጋጋትን ከሚነፍጉ ድርጊቶች እና ንግግሮች መቆጠብ፤

3. በጽሁፍ፣ ምልክት ወይም ድምጽ የጎንዮሽ ንግግር አለማድረግ እና ከተሳታፊዎች የሚቀርበውን ሃሳብ በአክብሮትና በጥሞና ማዳመጥ፤

4. እያንዳንዱ የምክክሩ ተሳታፊ የሚሰጠውን ሃሳብና የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ማክበር፣ በቅንነትና በታጋሽነት ማዳመጥ ፤

5. ሌላው ተሳታፊ ያቀረበውን ሃሳብ የመደገፍ ወይም የመቃወም ሁኔታ ሲኖር የሌሎች ተሳታፊዎችን መብት በሚያከብር መልኩ ማቅረብ፣

6. ተሳታፊው እድል ተሰጥቶት ሃሳቡን በመግለጽ ሂደት ላይ እያለ በማንኛውም ሁኔታ ያለማቋረጥ፤

7. የሰውን ክብር ከሚነኩ ነቀፌታዎች ፣ ዘለፋዎች ፣ ስብዕናን ከሚነኩ ንግግሮችና ድርጊቶች መቆጠብ፤

8. ሰዎች በሚያቀርቡት ሃሳብ እንዲሁም አስተሳሰብ ባይስማሙ እንኳ ሃሳባቸውን እና አስተሳሰባቸውን ማክበር፤

9. የሚሰጠውን ሀሳብ በቅን ልቦና ላይ የተመሠረተ ሆኖ ከውይይቱ  አጀንዳ ጋር አግባብነት ያለው አጭር፣ ግልጽ ያልተደጋገመ እና የተፈቀደውን ጊዜ ባከበረ መልኩ መግለጽ፤

10. በሂደቱ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ ማብራሪያ እንዲሰጥ መጠየቅ ናቸው፡፡
በሜትር ታክሲ አሽከርካሪ ከመደፈር እንደተረፈች ድምፃዊት ትዕግስት ኃይሉ (እግቱ) ገለፀች።

ትላንትና በከተማችን የሚሰራ የሜትር ታክሲ ሹፌር ሊደፍረኝ ነበረ ያለችው ድምፃዊቷ ከቤት ስወጣ ያደረሰኝን ሹፌር አመሻለሁ ሲለኝ ፕሮግራሜን ስጨርስ ቤቴን ስለሚያውቀውም መጀመሪያ በሰላም ስላደረሰኝም ወደ ቤት እንዲመልሰኝ ደወልኩለት ትንሽ ቢያረፍድም መጣ ስትል የተፈጠረውን አብራርታለች።

ቤት ልደርስ ትንሽ ሲቀረኝ መኪናውን አቁሞ ሲታገለኝ እወጋሻለሁ ብሎ ሲያስፈራራኝ፣ አምልጬ ወደ ቤት ገብቻለሁ። ሲታገለኝ ልብሴ ስለተቀደደ ኪሴ ውስጥ የነበረ ገንዘብ ሙሉበሙሉ መኪና ውስጥ ወድቆብኛል ብላለች።

ትማሩበታላችሁ፣ የእኔን ስህተት ተዘናግታችሁ አትደግሙትም ብዬ አምናለሁ ስትል እግቱ የደረሰባትን ገልፃለች።

@Yenetube @Fikerassefa
የአሜሪካ ሕክምና ቡድን ሾፊር ኢትዮጵያ ውስጥ ተገደለ!

በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት መሠረቱን ያደረገ ትርፋማ ያልሆነ የሕክምና ቡድን ሾፌር ኢትዮጵያ ውስጥ ይጓዝበት የነበረ መኪና ላይ ተኩስ መከፈቱን ተከትሉ ሕይወቱ ማለፉን ድርጅቱ አስታውቋል።

ሙስጠፋ አልኪስሚ የሕክምና ቡድኑ ዓለም አቀፍ ሾፌር ሲሆን፣ ባለፈው ዓርብ ቡድኑ በአማራ ክልል ለሥራ በሚጓዝበት ወቅት በተከፈተ ተኩስ እንደተገደለ የቡድኑ ቃል አቀባይ ኬረን ፒያት ለአሶስዬትድ ፕረስ በኢሜይል አስታውቀዋል። ሌሎች የቡድኑ አባላት ላይም ጉዳት እንደደረሰ ቃል አቀባይዋ ገልፀዋል።

በአሁኑ ወቅት ሆን ተብሎ በሠራተኞቹ ላይ ተኩስ ተከፍቶበታል ብሎ እንደማያምን ድርጅቱ አስታውቋል።በእ.አ.አ 1979 የተመሠረተው ድርጅት ቀውስ በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ይታወቃል።

በሚያዚያ 2013 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሥራውን የጀመረው ድርጅቱ፣ በአምስት ክልሎች ለሚገኙ ፍልሰተኞች፣ የሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች እንዲሁም የግጭት ሰለባ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የጤና አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
እስራኤል የጋዛ-ግብጽ ድንበር መተላለፊያን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሯን ገለጸች!

የእስራኤል ጦር በጋዛ እና ግብጽ ድንበር ላይ የሚገኘውን እና ፊላዴልፊ ኮሪደር [መተላለፊያ] ተብሎ የሚጠራውን ስትራቴጂካዊ ቀጠና መቆጣጠሯን አስታወቀች።ሐማስ ወደ ጋዛ የጦር መሳሪያ ለማስገባት የሚጠቀምባቸው 20 የሚጠጉ ዋሻዎች መገኘታቸውን የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ ተናግረዋል።

የግብጽ ቴሌቭዥን ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው እስራኤል ይህንን ያለችው በደቡባዊ ጋዛ በምትገኘው ራፋህ ከተማ የምታካሂደውን ጥቃት ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ነው ብሏል።እስራኤል ይህንን የገለጸችው ከግብጽ ጋር ከፍተኛ ውጥረት በገባችበት ወቅት ነው።

"ባለፉት ቀናት የእስራኤል ወታደሮች በግብጽ እና ራፋህ ድንበር ላይ የሚገኘውን የፊላዴልፊ ኮሪደር ተቆጣጥረዋል" ሲሉ የመከላከያ ሠራዊቱ ቃል አቀባይ ሪር አድሚራል ዳንኤል ሃጋሪ ረቡዕ ዕለት ተናግረዋል።መተላለፊያው ለሐማስ "የህይወት መስመር" ነው ሲሉ ገልጸዋል። በዚህም ቡድኑ "በጋዛ ሰርጥ የጦር መሳሪያዎችን ያስገባ ነበር" ብለዋል።

ጦሩ በአካባቢው የተገኙትን ዋሻዎች "እየመረመሩ.. እና እያጸዱ" ነው ብለዋል።ሃጋሪ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሁሉም ዋሻዎች ወደ ግብጽ ስለመሻገራቸው እርግጠኛ መሆን እንደማይቻል ተናግረዋል ሲል ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል።

የፊላዴልፊ መተላለፊያ ከግብጽ ጋር የሚያዋስንና 100 ሜትር ስፋት እና 13 ኪሎሜትር እርዝማኔ ያለው ነው።ግብጽ ከዚህ ቀደም ማንኛውንም የጦር መሣሪያ ዝውውር ለመቆጣጠር የድንበር ተሻጋሪ ዋሻዎችን ማውደሟን ተናግራለች።

“ከፍተኛ” የግብጽ ምንጭን ጠቅሶ አልቃሂራ ኒውስ እንደዘገበው ከሆነ እስራኤል "እነዚህን ክሶች የምታቀርበው በፍልስጤማውያኑ ራፋህ ከተማ ላይ የምታካሄደውን ጥቃት ለመቀጠል እና ጦርነቱን ለፖለቲካዊ ዓላማ ለማራዘም ሲሉ" ሲሉ ከሰዋል።

ሐማስ መስከረም 26 ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል ጦርነቱን ለማሸነፍ ራፋህን መቆጣጠር እንዳለባት አጥብቃ ትናገራለች።

ግጭቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት ጋዛ 36,170 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹ ህጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን በሐማስ አስተዳደር ስር ያለው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የእስራኤል ጦር በጋዛ የሚያካሂደውን የተቀናጀ ጥቃት ተከትሎ ከሦስት ሳምንታት በፊት የራፋህን መሻገሪያን ከተቆጣጠረ ወዲህ በግብጽ እና በእስራኤል መካከል ያለው ውጥረት ተባብሷል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሂደት ላይ የሙስሊሞች ውክልና አነስተኛ ነው ሲል የኢትዮጵያ እስልማና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቅሬታውን አሰማ፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ቀጥሎ አጀንዳ ያስገባ ተቋም መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር ቆይታ የነበራቸው የምክር ቤቱ የሙስሊሞች ምክክር ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት ሀጂ ኑረዲን ጀማል አጀንዳውን ለኮሚሽኑ ስናስገባ ኮሚሽኑ በደስታ እንደተቀበላቸውና ጥሩ ግንኙነት እንዳላቸው ተናግዋል፡፡

ይሁን እንጂ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ህዝበ ሙስሊም ቁጥር ያማከለ ውክልና በኮሚሽኑ ውስጥ አለመኖሩ ቅሬታ እንደተሰማቸው ገልፀዋል፡፡

"ከመጀመሪያውም ቅሬታችን ማህበረሰብ ነው የተደራጀው የሚል ሀሳብ ኮሚሽኑ ቢኖረውም በተወከሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ውስጥ ሀይማኖትን አላማከለም" የሚለው ቅሬታ እንደተሰማው የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አንስቷል፡፡

"በሀገሪቱ ውስጥ በአሁን ሰዓት ካሉት ማህበራት ሁሉ ቀድሞ ሀይማኖት ነበር ይህንን ስራ ቀድሞ ከወረዳ ጀምሮ ሳይወክል በክልል ደረጃ መደረጉ ትክክል አይደልም" ሲሉ ያስረዳሉ፡፡

"ሙስሊሞች ካልተሳተፉ የሙስሊሙን ጥያቄ ማን ሊያነሳው ይችላል?" የሚሉት ሀጂ ኑረዲን ከኮሚሽኑ ጋር ጥሩ ግንኙነት ቢኖራቸውም የተሳትፎው ጉዳይ እንዲፈታ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ከሀገራዊ ምክከር ኮሚሽኑ ጋር በዚህ ዙሪያ ምክክር ያደረገ ቢሆንም መፍትሄ አለመኑሩን ለማወቅ ችለናል፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለ 9 አጅንዳ 47 ጥያቄዎች ማስገባቱ የተገለፀ ሲሆን፣
ከአጀንዳዎቹ መካከልም በሀገሪቱ ለረጅም ግዜ የቆየው የገዢ እና ተገዢ ትርክት መቆም አለበት ኢትዮጵያን የገነቧት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው ስለዚህ የሁሉ ተሳትፎ ጎልቶ ይቅረብ፣ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ መሆኑ በግልፅ ምክክሩ ሊፈታው የሚገባ ነው የሚልም ተካቶበታል፡፡

ሌላው የሀገር ጀግኖች ላይ እና በትምህርት መማሪያዎች ላይ ያለው የሙስሊሙ ሚና መካተት አለበት የሚልና በተለይም ከህዝብ ቆጠራ ጋር ተያይዞ ሙስሊሙ ሁል ግዜ 33 በመቶ ብቻ ነው የሚለው በትክክል ተቆጥሮ ትክክለኛ ቁጥሩ ሊቀመጥ ይገባል የሚሉ አጀንዳዎች እንደተካከቱበት ተሰምቷል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የማገድ ስልጣንን ለኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ!

ማንኛውንም ሰው ከሀገር ውስጥ እንዳይወጣ የማገድ ስልጣንን፤ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ። የአዋጅ ማሻሻያው፤ በህገ ወጥ መንገድ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጪ ሀገር ዜጎች “በጥቁር መዝገብ እንዲመዘግቡ እና ከሀገር እንዲወጡ” የሚያስችል “አስተዳደራዊ ቅጣት” የመጣል ስልጣንን ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትም ሰጥቷል።

➡️ እነዚህን አዲስ ድንጋጌዎች ያካተተው የኢሚግሬሽን አዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ የተላለፈው፤ ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ቀርቦ ከጸደቀ በኋላ ነው።

➡️ ሀገራት “ሉዓላዊ ስልጣንን” ተግባራዊ ከሚያደርጉባቸው ህጎች “በዋነኛነት” የሚጠቀስ ነው የሚባልለት የኢሚግሬሽን ህግ፤ “በህግ የተከለከሉ ሰዎች በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር እንዳይወጡ እና ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ቁጥጥር የሚደረግበትን አግባብ” የሚደነግግ ነው።

➡️ በስራ ላይ ከዋለ 21 ዓመት የሞላው ነባሩ ህግ፤ “ማንኛውም ሰው ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ ሊታገድ የሚችለው በህግ መሰረት በፍርድ ቤት ሲታዘዝ ብቻ ነው” ይላል።

➡️ ዛሬ ለፓርላማ የቀረበው የአዋጅ ማሻሻያ በነባሩ ህግ የተቀመጠውን የፍርድ ቤት “ብቸኛ ስልጣን” የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ በተጨማሪነት ያጋራ ሆኗል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
ሰበር መረጃ  የአክሲዮን ሽያጭ ሊጠናቀቅ ነዉ
🛜አያት አክሲዮን ማህበር የአክሲዮን ሽያጩን ሊያጠናቅቅ መሆኑን ገለፀ

🛜ነግዶ ስለማትረፍ እርግጠኛ መሆን አይቻልም ፤ገንዘብን ካለስራ ማስቀመጥም በራሱ ኪሳራ ነው።

🛜ስለ ጥሬ እቃ፣ የቤት ኪራይ፣ የሰራተኛ አስተዳደር እና ደመወዝ ሳይጨነቁ ካለምንም ውጣውረድ ጥሪትዎን በዓመት ከግማሽ በላይ ያሳድጉ።

🛜አምና የ1,000,000 ብር አክሲዮን የገዙ የ513,800 ብር ትርፍ ተካፋይ ሆነዋል።

🛜ከ112,500 ብር ጀምሮ አዳዲስ አባላት መግዛት ይችላሉ፡፡

🛜 ቅድመ ክፍያ 40% ሆኖ ቀሪው 60% በ3 አመት የሚከፈል ይሆናል።

🛜በአንድ አክሲዮን የሪል-እስቴት፣የሆቴልና ቱሪዝም፣የትምህርት ኢንቨስትመንት፣የሲሚንቶ ፋብሪካ፣ የማርብል፣ የጠጠር እና የብሎኬት ማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን ጨምሮ የ8 ትርፉማ ድርጅቶች ባለቤት ይሁኑ፡፡

🛜ትርፋማውን የአያት አክሲዮን በመግዛት ገንዘብዎን ከግሽበት ይታደጉ !!

🛜አክሲዮኑን ለህፃናት ልጆችዎ፣ ለቤተሰብዎ እና ለወዳጅ ዘመድዎ በስጦታ ያበርክቱ፡፡
🏠በተጨማሪም በአዳዲስ ሳይቶቻችን የመኖሪያ እና የንግድ ሱቆችን በሽያጭ ላይ እንገኛለን
🕴️ የሽያጭ ባለሙያ(አማረ ፈንቴ)
   👇
☎️09 19 76 89 58 
   👇
☎️ 09 19 31 36 70
#WhatsApp 0919768958 በቀጥታ ይደዉሉ
Telegram:@Amex12192129
gmail:[email protected]
አድራሻ፡ካዛንችስ አያት ሲቲ ሴንተር 1ኛ ፎቅ
ዶናልድ ትራምፕ በታሪካዊው የክስ ሂደት በቀረቡባቸው ክሶች በጠቅላላ ጥፋተኛ ተባሉ!

የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀረቡባቸው 34 ክሶች በሁሉም ጥፋተኛ ተብለዋል።ትራምፕ ከንግድ ሰነድ ማጭበርበር ጋር ተያይዞ በቀረቡባቸው ክሶች ከ2016 ጀምሮ በስልጣን ላይ በነበሩባቸው ጊዜያት በእርሳቸው ፊርማ ተፈርመው የወጡ የገንዘብ ሰነዶች እና ቼኮች እንደማስረጃ ቀርበውባቸዋል።

ስቶርሚ ዳንኤልስ የተባለችው የወሲብ ፊልም ተዋናይት ከምርጫው በፊት ከትራምፕ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት እንደፈጸመች እና ስለዚህ ጉዳይ እንዳታወራም የ130ሺ ዶላር ክፍያ እንደተፈጸመላት በኒውዮርክ ፍርድ ቤት ቀርባ መስክራለች።

የቀድሞ የፕሬዝዳነቱ ጠበቃ ማይክል ኮሀን ይህንኑ ፍርድ ቤት ተገኝተው አረጋገረጠዋል፡፡ ጠበቃው ለዳንኤልስ በትራምፕ አዛዥነት እንዲከፈል የተጠየቀ 130 ሺ ዶላር ክፍያን አስፈጽሚያለሁ ብለዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ በኒውዮርኩ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ የተባሉት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ በስልጣን ላይ ያለም ሆነ የቀድሞ ፕቴዝዳነት በወንጀል ጥፋተኛ ሲባል የመጀመርያው ሆነዋል፡፡

ትራምፕ የፍርድ ውሳኔውን የተጭበረበረ እና አሳፋሪ ነው በሚል ሲገልጹት ጠበቆቻቸቸው በበኩላቸው ውሳኔውን እንደማይቀበሉ እና የይግባኝ ጥያቄ ለማቅረብ እየተዘጋጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ዛሬ ከሰአት ላይ ኒውዮርክ በሚገኝው ትራምፕ ታወር መግለጫ እንደሚሰጡ የሚጠበቁት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ደግሞ የምርጫ ቅስቀሳ ስራቸውን እንደሚቀጥሉ ተነግሯል፡፡ጥፋተኝነት ውሳኔው በትራምፕ ቀጣይ የፖለቲካ ጉዞ ላይ ምን ሊፈጠር እንደሚችል እስከሁን ግልጽ የሆነ ነገር ባይኖርም የሚያሳድረው ተጽዕኖ ግን ቀላል የማይባል እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ለሀምሌ 11 የመጨረሻ ፍርድ ለመስጠት ቀጠሮ የሰጠው ፍርድ ቤት ውሳኔ የትራምፕን የፖለቲካ ህይወት የሚወስን ነው፡፡ በእርግጥ ፍርድ ቤቱ ጥፈተኛ ናቸው ባላቸው ትራምፕ ላይ የሚያሳልፈው ቅጣት አልታወቀም፡፡

ሮይተርስ ያነጋገገራቸው የህግ ባለሙያዎች ግን የእስር ቅጣት ከአማራጮቹ መካከል ቀዳሚው ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡ለዚህም የንግድ ሰነዶችን ማጭበርበር ለአራት አመታት በእስር እንደሚያስቀጣ የሚደነግገውን ህግ በማሳያነት ጠቅሰውታል፡፡

[Al ain]
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
Photo
የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ “በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎችን” ጨምሮ ለስምንት አካላት የዕውቅና ሽልማት አበረከተ!

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአውሮፓ ህብረት በሀገሪቱ የተለያዩ እስር ቤቶቸ የሚገኙ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ጨምሮ ለስምንት ግለሰቦች እና ተቋም የአመቱን የህብረቱን የሹመን የሰብአዊ መብት ሽልማትን (EU Schuman Human Rights Award) አበረከተ።

በሀገሪቱ የሰብአዊ መብት እንዲከበረ እና ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በማሰማት አስተዋጽኦ አበረክተዋል በሚል ስድስት ግለሰቦች የተሸለሙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ይገኙበታል፤ ተቋማቸውን አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን አስችለዋል የሚል አድናቆት ተችሯቸዋል።

በሽልማቱ ስነስርአት ወቅት ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የህብረቱ አምባሳደር፣ ሽልማቱ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ግዜ የተሰጠ መሆኑን በመግለጽ እንደባህል በየአመቱ በኢትዮጵያ ሽልማቱ በቀጣይ አመታት ይተገበራል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፣ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ያሬድ ሃ/ማርያም፣ በሶማሌ ክልል የሚንቀሳቀሰው የሆርሙድ የሴቶች ማህበር ሊቀመንበሯ ጋሪ ኢስማኤል ዩሱፍ፣ የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብቶች ሊግ መሥራች ጌቱ ሳከታ፣ ከሰብአዊ መብት በተጨማሪ በአከባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪ መሆኑ የተገለጸው የቁም ለአካባቢ ሊቀ-መንበር መልካሙ ኦጋ፣ የኢትዮጵያ ሴት የህግ ባለሞያዎች ማህበር፣ የፈንዲቃ የባህል ማዕከል መሥራች የሆነው አርቲስት መልካሙ በላይ እና በእስር ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሽልማቱ የተበረከተላቸው ናቸው።

Via Addis Standard
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
Photo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህወሓት መልሶ ሕጋዊ እውቅና እንዲያገኝ የሚያስችል የአዋጅ ማሻሻያ ወደ ፓርላማ መራ!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት “ከሕጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ” ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ቡድኖች መልሰው እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ለመመዝገብ የሚያስችላቸውን ድንጋጌ የያዘ የአዋጅ ማሻሻያን ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ።

በሥራ ላይ ባለው “የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ” ላይ የተደረገው ይህ ማሻሻያ፤ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የተሰረዘበትን የፓርቲነት ሕጋዊ እውቅና መልሶ እንዳያገኝ ያደረገውን የሕግ ጥያቄ የሚመልስ ነው።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአዋጅ ማሻሻያውን ተቀብሎ ወደ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመራው ዛሬ አርብ ግንቦት 23/2016 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጽህፈት ቤቱ ያወጣው መረጃ እንደሚያስረዳው ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት በአራት ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ከእነዚህ ረቂቆች መካከል በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አድርጎ ስለማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበው አዋጅ ይገኝበታል።

በተጨማሪም የንብረት ማስመለስ አዋጅ እና የነዳጅ ውጤቶች የግብይት ሥርዓትን ለመደንገግ የቀረበው አዋጅም ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ውሳኔ የተሰጠባቸው ሕጎች ናቸው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፤ በዛሬው ስብሰባ ውሳኔ እንደተላለፈበት በቀዳሚነት የጠቀሰው የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ አዋጅ ነው። ማሻሻያ የቀረበበት በ2012 ዓ.ም. የወጣው የምርጫ ሕግ፤ እውቅና የተነፈጉ የፖለቲካ ፓርቲዎችን መልሶ ከመመዝገብ ጋር በተያያዘ ክፍተት ያለበት እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ጠቅሷል።

“ከሕጋዊ እና ሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማዕቀፍ ውጪ የቆዩ የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ እነዚህን አካላት ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ አድርጎ ለመመዝገብ የሚያስችል ሥርዓት በነባሩ አዋጅ ላይ አልተካተተም” ሲል በሥራ ላይ ያለው አዋጅ ላይ የታየውን ክፍተት ይገልጻል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ የመራው ማሻሻያ ላይ የፖለቲካ ቡድኖች “በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ እና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ፍላጎት በሚያሳዩበት ጊዜ” መልሰው ለመመዝገብ የሚችሉበትን ሥርዓት የሚዘረጋ እንደሆነም ተጠቅሷል።

ዛሬው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔ ላይ የተጠቀሰው የፖለቲካ ቡድኖች መልሶ የመመዝገብ ጉዳይ ከህወሓት ዳግም ሕጋዊ እውቅና የማግኘት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ውዝግብ ፈጥሮ ነበረ ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
YeneTube
ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የማገድ ስልጣንን ለኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ! ማንኛውንም ሰው ከሀገር ውስጥ እንዳይወጣ የማገድ ስልጣንን፤ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለፓርላማ ቀረበ። የአዋጅ ማሻሻያው፤ በህገ ወጥ መንገድ በኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጪ ሀገር ዜጎች “በጥቁር መዝገብ እንዲመዘግቡ…
የኢሚግሬሽን አዋጅ ማሻሻያ፤ ስለ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ኃላፊነት ምን ይላል?

በ1995 ዓ.ም. የወጣውን የኢሚግሬሽን አዋጅ የሚያሻሽል የህግ ረቂቅ በትላንትናው ዕለት ለፓርላማ ቀርቧል። አዋጁን ለማሻሻል ካስፈለገባቸው ምክንያቶች “አንዱ የተቀናጀ ድንበር ቁጥጥር አስተዳደርን” አስመልክቶ ዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ተግባራዊ ካደረገው መመሪያ ጋር የኢትዮጵያን ስርዓት ማጣጣም በማስፈለጉ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል።

የዓለም አቀፉ ድርጅቱ ተግባራዊ ያደረገው መመሪያ፤ ሀገራት የመንገደኛ ቅደመ ጉዞ መረጃ እና ምዝገባ ስርዓትን እንዲዘረጉ የሚያስገድድ ነው። ኢትዮጵያ የዚህ መመሪያ ፈራሚ ከሆኑ ሀገራት መካከል አንዷ በመሆኗ፤ ይህንኑ ስርዓት በኢሚግሬሽን ማሻሻያ አዋጅ ላይ እንዲካተት መደረጉ በአዋጅ ማብራሪያው ላይ ተመልክቷል።
በዚህ መሰረት “ማንኛውም አጓጓዥ መንገደኛን ወደ ሀገር ለማስገባት ወይም ከሀገር ለማስወጣት ከማጓጓዙ ከሶስት ሰዓት በፊት፤ የመንገደኛውን ቅድመ ጉዞ መረጃ እና ስም ዝርዝር ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት የማሳወቅ ወይም የመላክ” ግዴታ እንዲኖራቸው ተደርጓል።

“ይህ መሆኑ መረጃውን በመለዋወጥ የሚፈለጉ አደገኛ ወንጀለኞች በተለይም ሽብርተኞችን ጉዳት ሳያደርሱ በቁጥጥር ስር በማዋል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል” ሲል የአዋጁ ማብራሪያ ያስገንዝባል።

“ሀገርን የደህንነት ስጋት ላይ የሚጥሉ ሰዎች ከአየር ጉዞ ውጪ ሌሎችም የትራንስፖርት ዘዴዎች ሊጠቀሙ የሚችሉ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ”፤ ለሌሎች አጓጓዦችም የሚሆን አንቀጽ በአዋጅ ማሻሻያው ላይ እንዲካተት መደረጉ በማብራሪያው ላይ ሰፍሯል።

“ማንኛውም ከአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ውጭ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ አጓጓዥ፤ በሀገራት መካከል በሚኖር በእንካ ለእንካ መርህ ወይም በሚደረግ ስምምነት መሰረት፤ የመንገደኞችን ቅድመ ጉዞ መረጃ እና ስም ዝርዝር ወደሚሄድበት አገር ከመውሰዱ በፊት እንዲያሳውቅ” በአዋጅ ማሻሻያው ግዴታ ተጥሎበታል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa
#ከአዲስ አበባ ወደ #አዳማ ማንኛውም መልዕክት ይላኩ ይቀበሉ

22 ጎላጎል አከባቢ ኳሊቲ ህንፃ

ስልክ :- 0980526262

@addisexpressdelivery
2024/05/31 23:45:09
Back to Top
HTML Embed Code: