የኢትዮጵያ ብር በሩሲያ የባንክ ምንዛሬ ውስጥ ተካተተ!
የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ሌሊት ላይ ይፋ ባደረገው መረጃ የኢትዮጵያን ብር በምንዛሬ ዝርዝር ውስጥ አካቷል።ይህም ማለት ብርን ወደ ሩብል እንዲሁም ሩብልን ደግሞ ወደ ብር መመንዘር የሚያስችል ዕድልን ይሰጣል።
በዚህም መሰረት ባንኩ ለ100 የኢትዮጵያ ብር 57.5872 ሩብል ወይም ለ1 ብር 0.575872 ሩብል የምንዛሬ ተመን አስቀምጧል።ባንኩ ለኢትዮጵያ ብር ምንዛሬ ተመን የኮድ ቁጥር 230 የሰጠ ሲሆን በየዕለቱም የምንዛሬ ተመኑን የሚያሳውቅ ይሆናል።
የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያን ብር ጨምሮ የ12 ሀገራት ገንዘቦች ከሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ጋር ያላቸውን ይፋዊ የምንዛሪ ተመን ለማስቀመጥ ውሳኔ ላይ መድረሱን ከቀናት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል።
Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa

❤44👍15👀6😭4🔥3⚡1
"የትምህርት ቤቶች ግንባታ ምርጫ በዘርና ፖለቲካዊ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ የነበረ ቢሆንም ይህንን የሚያስቀር አሰራር ተዘርግቷል" - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
ባለፉት ዓመታት በነበረው አሰራር የትምህርት ቤቶች ግንባታ ምርጫ የሚወሰነው በገለልተኝነትና በበቂ መረጃ ሳይሆን በዘር፣ በትውወቅና ፖለቲካዊ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ ነበር ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው፣ ይህን ለማስቀረት የትምህርት ቤቶችን ሥርጭት የሚያሳይ የዲጂታል ካርታ አዘጋጅቷል ብለዋል፤ በአገሪቱ ተመጣጣኝና ፍትሃዊ የትምህርት ዘርፍ ልማትን ለማምጣት እየተሰራ ነው ሲሉም አስታወቀዋል።
በሀገሪቱ ተመጣጣኝ የሆነ የትምህርት ዘርፍ ልማትን ለማምጣት ትምህርት ቤቶች ግልጽና ትክክለኛ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ እንዲገነቡ የሚያስችል ዲጅታል የትምህርት ቤቶች ስርጭት የሚያሳይ ካርታ ተዘጋጅቷል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።አክለውም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል የትምህርት እድል ማግኘት እንዳለበት አንስተው ለሁሉም ዜጎች ትምህርትን በፍትሃዊነት ለማድረሰ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
የትምህርት ቤቶች ስርጭት ካርታ ከቀበሌ ጀምሮ በየደረጃው የትምህርት ቤቶችን ወቅታዊ ስርጭት፣ የመሰረተ ልማት፣ የህዝብ ብዛት እና ሌሎች መረጃዎችንም አካቶ የያዘ መሆኑን ተጠቁሟል።በመሆኑም ለጋሾችም ሆኑ ሌሎች የዘርፉ ባለድርሻዎች መረጃውን በመጠቀም ትምህርት ቤቶችን መገንባትና የድርሻቸውን ማበርከት እንደሚችሉ ተገልጿል።በዚህ የትምህርት ስርጭት ካርታ ትምህርት ቤቶቹ የሚገነቡት በተዘጋጀው ስታንዳርድ መሰረት ሲሆን የት ይገነባሉ የሚለውን ምላሽ የሚሰጥ መሆኑም ተገልጿል።

❤32👎8😁6👍1🔥1
YeneTube
Photo
የግብጽ እና የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ እና በቀይ ባህር ዙሪያ በስልክ መምከራቸው ተገለጸ!
የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ እና የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳለህ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ እና በቀይ ባህር ዙሪያ በስልክ መምከራቸው ተገለጸ።የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ እና የኤርትራ አቻቸው ኦስማን ሳሌህ በሀገራቱ መካከል በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በፖለቲካዊ ምክክር የተገኘውን ተጨባጭ እድገት ሲሉ የገለጹትን ለማሳደግ ተወያይተዋል ሲል አህራም ጋዜጣ በዘገባው አስታውቋል፤ በተለያዩ ዘርፎች ያለውን ትብብር ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል ብሏል።
ዘገባው በተጨማሪም ሁለቱ ሚኒስትሮች የሀገራቱን ትብብር እና ትስስረ ለማጠናከር የተወያዩት የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ ኤል ሲሲ እና የኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፍወርቂ ያስቀመጡትን መመሪያ ተከትሎ ነው ሲል ጠቁሟል።ሁለቱም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በስልክ ባደረጉት ምክክራቸው የሁለቱን ሀገራት ተጠቃሚ በሚያደረጉ በተለያዩ የቀጠናው ጉዳዮች መክረዋል ያለው ዘገባው በተለይም ደግሞ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ እና በቀይ ባህረ ዙሪያ መወያየታቸውን አስታውቋል።
ሁለቱም ሚኒስትሮች የቀጠናውን ደህንነት እና መረጋጋት ለማሳደግ በጋራ፣ በቅንጅት የሚያካሂዱትን ትብብር መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን አረጋግጠዋል ብሏል።የግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርትራ ለመልማት የምታደርገው ጥረት ሀገራቸው እንደምትደግፍ አስታውቀዋል ያለው ዘገባው በተለይም የልማት ፕሮጀክቶቿን እና መረጋጋትን ለማስጠበቅ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ግብፅ ያላትን ቁርጠኝነት አፅንዖት ሰጥተዋል ገልጸዋል ብሏል።
በተመሳሳይ የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድን በግብፅ የባህር ጠረፍ ከተማ ኤል አላሜይን ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ተቀብለው ባነጋገሩበት በድጋሚ በቀይ ባህር ደህንነት ላይ ያተኮረ መልዕክት ማስተላለፋቸውን የተመለከተ ዘገባ ማቅረባችን ይታወሳል።የቀይ ባህርን ደህንነት ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ በመግለጽ ግብጽ ለሶማሊያ የምታደርገውን ወታደራዊ ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ማለታቸውም በዘገባው ተካቷል።
Via AS

❤25😁11
ሰሬብሬኒካ፣ በአውሮጳ አስከፊ የህዝብ እልቂት የተፈፀመበት 30ኛ ዓመት
በአውሮጳ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ካበቃ በኋላ በሰሬብሬኒካ የደረሰዉ አስከፊ እልቂት 30ኛ ዓመት ዛሬ እየታወሰ ነዉ። ከ30 ዓመታት በፊት በቦስኒያ ከተማ የተፈፀመውን እልቂት ለማሰብ በስሬብሬኒካ የመታሰቢያ ሥነ ስርዓት እየተካሄደ ነው።እንደ ጎርጎረሳዉያኑ አቆጣጠር በ 1995 የተፈፀመው የስሬብሬኒካ እልቂት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በአውሮጳ ውስጥ ከታዩት ሁሉ የከፋው የጦር ወንጀል ነው ተብሎም ይታሰባል።
የቦስኒያ ጦርነት ከማብቃቱ ጥቂት ቀደም ብሎ በቦስኒያ ሰርብ ጦር አዛዥ ራትኮ ምላዲች የሚመራ ጦር ሰሪብሬኒካ ውስጥ በተባበሩት መንግስታት ጥበቃ የሚደረግለትን ክልል እንደ ጎርጎረሳዉያኑ ሐምሌ 11 ቀን 1995 ዓ.ም በወረረበት ወቅት ከ8,000 የሚበልጡ ሙስሊም ወንድና ሴት ልጆችን አፍኖ ገድሏል እንዲሁም ቀብሯል። ሰሜን ምስራቅ ቦሲኒያ በምትገኘዉ ሰሬብሬኒካ ጭፍጨፋን ለመዘከር ከመላዉ ሃገሪቱ ብሎም ከመላዉ ዓለም በከተማዋ ይሰበሰባሉ።
Via DW

❤25😭23👎2😁1👀1
ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ግብይት ጀመረⵑ
የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በይፋ ግብይት የጀመረ ሲሆን የወጋገን እና የገዳ ባንኮች ሰነዶቻቸውን በማስመዝገብና መስፈርቶችን በማሟላት ግብይታቸውን በይፋ አስጀምረዋል።
የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያው መጀመር ኢንቨስተሮች ለረጅም ጊዜ ሲጠይቁት የነበረ በመሆኑ አዳዲስ የኢንቨስትመንት እድሎችን የሚከፍት እንደሆነ የዘገበው ኢዜአ ነው ።

❤22👀5👍1
ፒያሳ የመጨረሻው ሱቅ እና ቤት ሽያጭ ❗️
ፒያሳ ሀገር ፍቅር ቲያትር እና ሚኒሊክ አደባባይ መሀል የንግድ ሱቆች
* የግል የሚያደርጉት የንግድ ሱቆች ፒያሳ ላይ ብቸኛው እየሸጠ ያለው ቴምር ሪልስቴት ነው
* ሚኒሊክ አደባባይ ጋር በመንግስት የሚሰራው የ አውቶብስ እና የታክሲ ተርሚናል አጠገብ
* በከተማው ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ቦታ ከተማው ላይ ሱቅ የፈረሰባቸው ነጋዴዎች የከተሙበት
* 4700 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ እስኬሌተር የሚገጠምለት G+5 የሆነ የገበያ ማዕከል
* በ 1 ዓመት ከ 6 ወር የሚያልቅ ከፍለው እስኪጨርሱ በዶላርም ሆነ በግንባታ እቃዎች ግሽበት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አይደረግም
* በወር ከ80,000 ብር በላይ የኪራይ ገቢ የሚኖራቸው
* ከ 900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
ቴምር ሪልስቴት.......
ከሀገር ውጪ ለምትኖሩ ወገኖቻችን በሙሉ ካላችሁበት ሀገር ሆናችሁ ፕሮሰስ ማድረግ የምትችሉበትን እና መግዛት መዋዋል የምትችሉበትን መንገዶች አመቻችተናል!
ለበለጠ መረጃ በቀጥታ ወይም በዋትሳፕ ዋናው ቢሮ ይደውሉ
☎️ +251976195835
በዋትሳፕ ያገኙናል -
https://wa.me/251976195835
Telegram username
@Ruthtemersales
🙏🙏🙏
🌴🌴🌴
https://www.facebook.com/share/1ABkH3oH9x/

❤8😭1
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
❤2
የትራምፕ አስተዳደር ከ1,000 በላይ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞችን ከስራ አሰናበተ
የትራምፕ አስተዳደር የፌደራል የመንግስት ሰራተኞችን ቁጥር ለመቀነስ በሚያደርገው ጥረት፣ ከ1,000 በላይ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞችን ከስራ እንዳሰናበተ የሲቢኤስ ኒውስ ዘገባ አመልክቷል።
ዘገባው እንደሚያመለክተው፣ ባለፈው አርብ ለውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞች በተላከ እና በቢቢሲ የአሜሪካ ዜና አጋር በተገኘ ማስታወቂያ መሰረት፣ በግዳጅ ከስራ ከተሰናበቱት ውስጥ 1,107 የሲቪል ሰርቪስ እና 246 የውጭ አገልግሎት ሰራተኞች ይገኙበታል ተብሏል።
ከዚህ ቀደምም፣ የፌደራል መንግስትን በስፋት የማደራጀት ጥረት አካል በመሆን፣ ከ1,500 በላይ የሚሆኑ ሌሎች የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞች በፈቃደኝነት ስራቸውን ለቀው እንደነበር ተገልጿል።
ይህን የጅምላ ሰራተኛ ቅነሳ የሚተቹ ወገኖች፣ ቅነሳው የመስሪያ ቤቱን ስራ በእጅጉ እንደሚጎዳ ሲከራከሩ ቆይተዋል።
@Yenetube @Fikerassefa

❤17😭5
ግብጽ የከረሙት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ወደ ቱርክ በማቅናት በአንካራ ከኤርዶጋን ጋር መምከራቸው ተገለጸ!
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ መሃሙድ ትላንት ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ አንካራ በማቅናት ከፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶሃን ጋር መምከራቸው ተገለጸ፤ በግብጽ ካይሮ የከረሙት የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሸክ ከቱርኩ አቻቸው ጋር በዝግ መምከራቸውን የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በአንካራው ስብሰባ የሁለቱ መሪዎች በቀጠናው ስላሉ ውጥረቶች መወያየታቸውን የጠቆሙት የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ኤርዶጋን በቀጠናው እየተስተዋሉ ያሉ ውጥረቶች የአፍሪካ ቀንድን መረጋጋት የበለጠ ሊያናጉ የሚችሉ መሆናቸውን በመግለጽ ሰጋታቸውን መግለጻቸውን አስታውቀዋል።
ባሳለፍነው ሳምንት የወጡ የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈረመው የአንካራው ስምምነት እክል እንዳጋጠመው እና መቆሙን አመላክተዋል፤ ከሚያዚያ ወር ወዲህ ምንም አይነት የውይይት መርሃግብረ አልተያዘም ብለዋል።

❤24😁10
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት 350.13 ቢሊዮን ብር ሆኖ ጸደቀ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት 350.13 ቢሊዮን ብር ሆኖ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ ፀደቀ።ይህ በጀት ካለፈው የበጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ108 ቢሊዮን ብር ወይም የ45 በመቶ ዕድገት ያሳየ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አብዱል ቃድር ሬድዋን አስታውቀዋል።
አቶ አብዱል ቃድር ሬድዋን የበጀት ረቂቅ አዋጁን ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት፣ በጀቱ የሚሸፈንባቸውን ዋና ዋና የፋይናንስ ምንጮች ዘርዝረዋል።
በዚህም መሰረት፡-
- ከታክስ ከ238 ቢሊዮን ብር በላይ ወይም 68 በመቶ
- ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ከ56 ቢሊዮን ብር በላይ
- ታክስ ካልሆነ ገቢ ከ46 ቢሊዮን ብር በላይ
- ከመንገድ ፈንድ 1.8 ቢሊዮን ብር
- ከውጭ ብድርና እርዳታ ደግሞ 6.98 ቢሊዮን ብር እንደሚገኝ ተገልጿል።
ከፀደቀው አጠቃላይ በጀት ውስጥ፣ 70.35 በመቶ ለካፒታል በጀት፣ 26.22 በመቶ ለመደበኛ በጀት እንዲሁም 3.43 በመቶ ለመጠባበቂያነት መያዙ ታውቋል።

❤20👎6
Forwarded from HuluGames Community
100 አሸናፊዎች የሚያገኙ 100 ብር!
በዚህ ሻሞ ለመሳተፍ:
1. @hulujackpot
2. @HuluPayGiveaways
የማሸነፍ እድልዎን ያሳድጉ:🚀
▫️ የግል ሊንክዎን ያጋሩ = እድልዎ ይጨምራል
▫️ የበለጠ ያጋሩ = የበለጠ የማሸነፍ እድል
▫️ ለእያንዳንዱ ሰው በሊንክዎ የተሳተፈ = ተጨማሪ ነጥብ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤8👍1
YeneTube
Photo
የቤት ሰራተኛዋን ገድለው ሁለት ህፃናትን አግተው አስር ሚሊዮን ብር የጠየቁ አጋቾችን በቁጥጥር ስር አውሎ ህፃናቱን ለቤተሰቦቻቸው ማስረከቡን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ!
ደርጊቱ የተፈጸመዉ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ/ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አለም ባንክ ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ ከቀኑ 11፡45 ላይ ነዉ፡፡
የቤት ሰራተኛ የሆነችው ሀብታሟ ወርቁ በመኖሪያ ቤት ውስጥ በስለት ተወግታ መሞቷን እና እህትማማች የሆኑ የአስርና የሰባት ዓመት ዕድሜ ያላቸው ህፃን እምነት አሽናፊ እና ጄሪ አሽናፊ መጥፋታቸው ለአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ሪፖርት ይደሰርሰዋል፡፡
ጠቅላይ መምሪያው የፎረንሲክ ፣ የምርመራ እና የክትትል ቡድን አባላትን በማደራጀት ወንጀል ወደተፈፀመበት ስፍራ ከሄዱ በኃላ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ሥራው መጀመሩን የጠቅላይ መምሪያው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ገልፀዋል፡፡
የሟች ማንነት እንጂ የገዳይ ማንነት አለመታወቁ ፣ ሀብታሟን ማን ገደላት ? ህፃናቱስ የት ተሰውሩ ? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እና ወንጀል ፈፃሚውን በቁጥጥር ስር ለማዋል እንዲሁም የጠፉትን ህፃናት ለማግኘት ክትትሉ በቀጠለበት ሒደት መንግስቱ ደላሳ የተባለ ግለሰብ ለህፃናቱን ወላጅ እናት ለወ/ሮ ሃዊ ዮሴፍ ስልክ በመደወል ህፃናቱን ማገቱን 10 ሚሊዮን ብር ካልተሰጠው ልጆቹን እንደሚገድላቸው እንዲሁም ጉዳዩን ለፖሊስ ካሳወቀች በህፃናቱ ላይ የከፋ እርምጃ እንደሚወስድ የሚገልፅ መልእክት ያስተላልፋል፡፡
ህፃናቱ ከዚህ ቀደም አጋቹን ስለሚያውቁትና የደገሰላቸውን የሞት ድግስ ባለማወቃቸው ያለጭንቀት ሲጫወቱ እና ልጆቹ እርሱ ጋር መሆናቸውን የሚያሳይ ቪዲዮ ለወ/ሮ ሃዊ ይልካል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር ባደረጉት የክትትል ሥራ የፖሊስ አባላት ቀንና ሌሊት ባደረጉት ያላሰለሰ ክትትል አጋቹን እና ሌሎች ተባባሪዎቹን ሐምሌ 5 ቀን 2017 ዓ/ም በቁጥጥር ስር በማዋል ሁለቱንም ህፃናት በአዳማ ከተማ ልዩ ቦታው ቦሌ ሰፈር እየተባለ ከሚጠራ አካባቢ ታግተው ከተቀመጡበት ቤት በሰላም ማስለቀቁን ኮማንደር ማርቆስ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ ከወንጀሉ ጋር በተያያዘ አራት ተጠርጣዎችን ይዞ ምርመራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡
የህፃናቱ ወላጅ እናት ወ/ሮ ሃዊ ዮሴፍ እና አባታቸው አቶ አሸናፊ ጫኔ እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ በተፈፀመው የወንጀል ድርጊት በእጅጉ ተጨንቀው እንደነበር ተናግረው አዲስ አበባ ፖሊስ እና ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረጉት ጥረት ልጆቻቸውን በሰላም በማግኘታቸው በፀጥታ አካላት ተግባር ኩራት እንደተሰማቸው ገልፀዋል፡፡
ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው እንቅስቃሴ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም የኦሮሚያ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ከፍተኛ ድርሻ ማበርከታቸውን ለዚህም በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ስም ኮማንደር ማርቆስ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
መሰል ችግር ሲያጋጥም ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ ተገቢ እንደሆነ ፖሊስ አስታውቆ ነገር ግን ልዩ ልዩ ማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ስለ ወንጀሉ መረጃ ማሰራጨት ለወንጀል ፈፃሚዎቹ ምቹ ሆኔታን እንደሚፈጥር ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ተገቢው ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡
Via AMN

❤70😭19👍3
መንግሥት ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ላይ በመሳተፍ የ173 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉደለቱን እንደሚሸፍን አስታወቀ!
መንግሥት ለ2018 ካፀደቀው በጀት ውስጥ 173 ቢሊዮን ብር የሚሆነውን የተጣራ የበጀት ጉደለት፣ በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ አማካይነት የዕዳ ሰነዶችን በመሸጥ ጉደለቱን እንደሚሸፍን አስታወቀ።
መንግሥት ይህንን ያስታወቀው የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ የመንግሥት የግምጃ ቤት ሰነዶች ምዝገባና የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ግብይትን ባለፈው ዓርብ ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. በይፋ በተጀመረበት ዕለት ነው።
የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ የሚሰጠውን የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ግብይት ባለፈው ዓርብ ሐምሌ 4 ቀን 2017 ዓ.ም. በይፋ ባስጀመረበት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው የመክፍቻ ንግግር ያደረጉት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ግበያ ሥራ መጀመር የበርካታ ዓመታት የሪፎርም ሥራዎች፣ የፖሊሲ ቅንጅትና የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ ቁርጠኝነት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ: https://ethiopianreporter.com/143326/

❤13😁2👎1🔥1