Telegram Web Link
ቅዱስ ሲኖዶሱ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል፤
ሲኖዶሱ በምክክር ኮሚሽኑ ቅር መሰኘቱንም አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በርካታ አጀንዳዎችን በመቅረጽ ውይይት ሲያካሄድ መሰንበቱን ገልጧል፡፡ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያኗ አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት፣ ለመንፈሳዊ ዕድገትና ለምእመናን ደኅንነት ትኩረት በመስጠት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፊያለሁ ብሏል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

• በቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በሀገራችን መንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው መልካም የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፤

• በመላው ሀገራችን በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት እንደቀጠለ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት ተቆጥበው የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት በውይይትና በምክክር እንዲፈቱ እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንኦት ጥሪውን አቅርቧል፤

• የሀገራዊ ምክክር ሀገረ መንግሥትን ከመመሥረት ጀምሮ በአስታራቂነትና በሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን እስከአሁን ድረስ በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ ሳይኖር ኮሚሽኑ የተሳታፊ ልየታንና አጀንዳ መረጣ አጠናቆ ወደ ምክክር ትግበራ እየገባ መሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስን ቅር አሰኝቷል፡፡ በመሆኑም የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡

Via Ethio FM
@YeneTube @FikerAssefa
ሶማሊያ የተመድ የፀጥታ ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና ተመረጠች!

ሶማሊያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና ተመረጠች።በጦርነት ስትታመስ ለኖረችው ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር የምክር ቤቱ አባል ሆና መመረጧ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል ተደርጎ ተወስዶላታል።ሶማሊያ ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ከመግባቷ በፊት እአአ በ1970ዎቹ የምክር ቤቱ ተለዋጭ አባል ነበረች።

ሶማሊያ የምክር ቤቱ አባል መሆኗ ከጽንፈኛው እስላማዊ ቡድን አል-ሸባብ ጋር የምታደርገውን ውጊያ በተመለከተ ለተመድ ውሳኔ ግብዓት ትሆናለች።የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት በመላው ዓለም ለሚፈጠሩ ግጭቶች ዓለም ምን አይነት ምላሽ መስጠት እንዳለበት ይወስናል።የጸጥታው ምክር ቤት ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸው አምስት ቋሚ አባላት ያሉት ሲሆን በየሁለት ዓመቱ የሚለዋወጡ 10 ተለዋጭ አባል አገራት አሉት።

አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ፣ ቻይና እና ሩሲያ ቋሚ አባላት ናቸው። ሶማሊያ ለቀጣይ ሁለት ዓመታት ተለዋጭ አባል ሆና እንድታገለግል ከዴንማርክ፣ ግሪክ፣ ፓኪስታን እና ፓናማ ጋር ተመርጣለች።አንድ አገር ተለዋጭ አባል ሆኖ ለመመረጥ ቢያንስ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሁለት ሦስተኛ አባል አገራት ድጋፍን ማግኘት ይኖርበታል።

ሶማሊያ ይህን መቀመጫ ያገኘችው ለምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የተቀመጠውን ወንበር ያለተቀናቃኝ ከወሰደች በኋላ ሲሆን፤ ከ193 አባል አገራት የ179 ድምጽ ማግኘት ችላለች።ሶማሊያ ያገኘችውን ድል ተከትሎ የልዑካን ቡድንን መርተው ወደ ኒው ዮርክ ያቀኑት የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ ፊቅ አገራቸው “በዓለም አቀፉ መድረክ የተሰጣትን ቦታ ትረከባለች” ብለዋል።“በዓለማችን ሰላም እና ደኅንነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሶማሊያ የተሰጣትን ሚና ለመውጣት ዝግጁ ነች” ሲሉም አክለዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
ኢሰመኮ በሽብር ተከሳሾች የመብት ጥሰት አቤቱታ የመጨረሻ ምርመራውን እንዲያቀርብ ፍርድ ቤት አዘዘ!

በእነአቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ የተካተቱ የሽብር ተከሳሾች ባቀረቡት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ላይ ለሚያደርገው ምርመራ፣ ኢሰመኮ ተጨማሪ ጊዜ ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡ተከሳሾቹ፣ በቤተሰብ የምግብ አቅርቦት እና ጥየቃ ላይ “በማረሚያ ቤት ተጥሎብናል” ያሉት ገደብ፣ ከፍርድ ቤቱ ዳግመኛ ትዕዛዝ በኋላ መነሣቱን ለችሎቱ ገልጸዋል። ኾኖም፣ ገደቡ ሊቀጥል ይችላል፤ ብለው እንደሚሰጉ አመልክተው፣ ተጠያቂነት እንዲኖር አመልክተዋል፡፡

በእነአቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ የሽብር ክስ ከተመሠረተባቸው 52 ተከሳሾች መካከል፣ አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ 16ቱ፣ ዛሬ ኀሙስ፣ ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ጉዳያቸው እየታየ ባለበት፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ችሎት ቀርበዋል፡፡የዛሬው ችሎት ከተቀጠረባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ፣ ተከሳሾቹ፥ በአዋሽ አርባ እና በዐዲስ አበባ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ “ተፈጽመውብናል” ባሏቸው የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ላይ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አጣርቶ እንዲያቀርብ በፍርድ ቤት የታዘዘውን የምርመራ ውጤት ለመጠባበቅ ነበር፡፡

በችሎቱ የተገኙት፣ የኮሚሽኑ የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ሥራ ክፍል የሪጅን ዲሬክተር ሰላማዊት ግርማይን ጨምሮ ሦስት የኢሰመኮ ባልደረቦች፣ ምርመራው መጀመሩን አስረድተዋል፡፡ ነገር ግን ምርመራ የሚካሔድባቸውን ቦታዎች ለመጎብኘትና ለተያያዥ የምርመራ ሒደቶች፣ ከሚመለከታቸው አካላት ፈቃድ ማግኘትን ጨምሮ ጊዜ የሚጠይቁ ጉዳዮች መኖራቸውን ጠቅሰው፣ ለኮሚሽኑ የአንድ ወር ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታው በዝርዝር መቅረቡን የገለጹት ከተከሳሽ ጠበቆች አንዱ አቶ ሰሎሞን ገዛኸኝ፣ የኮሚሽኑን ባልደረቦች ማብራሪያ ያደመጠው ችሎቱ ተጨማሪ ጊዜ መፍቀዱን ጠበቃው ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ የምርመራ ሪፖርቱን እንዲያቀርበ በፍርድ ቤቱ የታዘዘው፣ ተከሳሾቹ በእስር ላይ እያሉ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንደተፈጸመባቸው በማመልከታቸውና ፖሊስ በማስተባበሉ ምክንያት ነው፡፡በተመሳሳይ፣ ተከሳሾቹ፥ “የቤተሰብ ጥየቃ እና የምግብ አቅርቦትን ጨምሮ በማረሚያ ቤት እየተፈጸመብን ነው፤” ያሉትን የመብቶች ጥሰት አቤቱታ ተከትሎ፣ ችሎቱ የሰጠው ትእዛዝ አፈጻጸም ምን እንደሚመስል የተከሳሾቹን ቃል አድምጧል፡፡

ችሎቱ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ከመደበኛው የጊዜ ቀጠሮ በተለየ የማረሚያ ቤት ኃላፊዎችን ምላሽ ማዳመጡን፣ ተከሳሾቹ በዛሬው የችሎት ውሎ አስታውሰዋል። በዕለቱ፣ በድጋሚ የመብቶች ጥሰት እንዳይፈጸም ፍርድ ቤቱ ካዘዘ በኋላ፣ አድሏዊ በኾነ መንገድ፣ በቤተሰብ ጥየቃ እና የምግብ አቅርቦት ላይ ተጥሎ ነበረ፤ ያሉት ገደብ መነሣቱን አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ ተከሰሾቹን ወክለው ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡

ኾኖም፣ ችግሩ ሊቀጥል ይችላል፤ የሚል ስጋት እንዳላቸውም ከጠበቆቻቸው መካከል የኾኑት አቶ ሰሎሞን አመልክተዋል፡፡ በዛሬው ችሎት ላይ፣ የተከሳሽ ጠበቆች የክስ መቃወሚያ ያቀረቡ ሲኾን፣ የዋስትና ክርክርም ተደርጓል።የተከሳሽ ጠበቆች፣ በደንበኞቻቸው ላይ የቀረበው ክስ ዋስትና እንደማያስከለክል ያስረዱልናል ያሏቸውን የሕግ ድንጋጌዎች ጠቅሰው ሲከራከሩ፣ ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ፣ የሽብር ክሱ ከ15 ዓመት በላይ ሊያስቀጣ የሚችል መኾኑን፣ እንዲሁም ተከሰሾቹ በዋስትና ከተለቀቁ “ወደ ጫካ በመሔድ አብረዋቸው የተከሰሱ ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን ሊቀላቀሉና ሊያመልጡ ይችላሉ፤” በሚል ተከራክሯል።

ችሎቱ፣ በክስ መቃወሚያውና በዋስትናው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት፣ ለፊታችን ሰኔ 12 ቀን ቀጥሯል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በሦስት መዝገብ ተከፍለው፣ ትላንት ለመጀመሪያ ጊዜ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍረድ ቤት ልደታ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀረቡት 112 የሽብር ወንጀል ተጠርጣሪዎች፣ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡የዛሬው ችሎት የተቀጠረው፣ በሁለቱ መዝገቦች ዐቃቤ ሕግ፣ ክስ ለመመሥረት በጠየቀው የተጨማሪ የ15 ቀን ጊዜ እና ፖሊስ፣ በአንድ መዝገብ ሥር ባሉ 88 ተጠርጣሪዎች ላይ ለጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ፣ ብይን ለመስጠት ነበር፡፡

ችሎቱም፣ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ለዐቃቤ ሕግ የተጠየቀውን የክስ መመሥረቻ ጊዜ በመፍቀድ፣ ለሰኔ 12 ቀን ሲቀጥር፤ በ88ቱ ተጠርጣሪዎች ፖሊስ ለጠየቀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ላይ ደግሞ ብይን ለመስጠት ለነገ መቅጠሩን አቶ ሰሎሞን ገዛኸኝ ተናግረዋል፡፡ኹሉም ተጠርጣሪዎች፣ ትላንት በተጠናቀቀው የአስቸኳይ ዐዋጅ ዐውድ ውስጥ፣ በቁጥጥር ሥር ውለው በአዋሽ አርባ እና በዐዲስ አበባ በሚገኙ ማቆያዎች የነበሩ ናቸው፡፡

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
የ2017 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት በጀት ወደ አንድ ትሪሊየን ብር የሚጠጋ እንዲሆን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወሰነ፡፡

የ2017 ዓ.ም የፌደራል መንግስት በጀት የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነውን የ2016 - 2018 የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችን እና የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊስካል ማዕቀፍን ማስፈጸም እንዲቻል በሚያደርግ መልኩ መዘጋጀቱን ምክር ቤቱ ተነግሯል፡፡

የ2016 የፌደራል መንግስትን የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም፣ የመንግስት የፋይናንስ አቅም እና ተጠባቂ ገቢዎች፣ እንዲሁም አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የተሰጣቸውን ተልዕኮና ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስፈልጋቸውን ወጪ በመገምገም በጀቱ እንዲዘጋጅ ተደርጓል ተብሏል፡፡

በዚሁ መሰረት ለፌዴራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ወጪዎች፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ እና ተጠባባቂ ወጪን ጨምሮ ወደ አንድ ትሪሊየን የሚጠጋ በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡በጀቱ ለአንድ ትሪሊዮን ብር የተጠጋ ተብሎ ቢጠቀስም ስንት እንደሆነ ግን በዝርዝር አልተገለፀም።

ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2017 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን የጠቅላ ሚንትርጽ /ቤት ተናግሯል፡፡ ሰኔ 30 የሚጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት የፌደራል መንግሥት በጀት 801.6 ቢሊዮን ብር አንደነበር ይታወሳል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
ሰኔ 9 ሊሰጥ የነበረው የሬሚዲያል ፈተና ወደ ሰኔ 11 ቀን ተዛወረ!

ሰኔ 9 ሊሰጥ የነበረው የሬሚዲያል ፈተና ወደ ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም መዛወሩን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የሬሚዲያል (የማካካሻ) ትምህርት የማጠቃለያ ፈተናን ከሰኔ 3 እስከ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለመስጠት የፈተና ፕሮግራም ተዘጋጅቶ እንደነበር አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጂ ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በመሆኑ በዕለቱ ይሰጥ የነበረው ፈተና ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ባካሄደው የመልካም አስተዳደር ምዘና፤ የማዕድን ሚኒስቴር “ዝቅተኛ አፈጻጸም” ማስመዝገቡ ተገለጸ!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በፌደራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ያለውን “መልካም አስተዳደር አፈጻጸም” በተመለከተ ላለፉት 10 ወራት ባደረገው ምዝና፤ የማዕድን ሚኒስቴር “ዝቅተኛ አፈጻጸም” ማስመዝገቡን አስታወቀ። የማዕድን ሚኒስቴር አፈጻጸሙ ዝቅ ያለው፤ የተቋቋመበት አዋጅ “የተሟላ ስልጣን እና ኃላፊነት ለሚኒስቴሩ የማይሰጥ በመሆኑ” ምክንያት እንደሆነ ተነግሯል። 

▶️ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፤ የመንግስት አስፈጻሚ አካላት በአዋጅ የተሰጣቸንው ተግባራት “ጥራት፣ ቅልጥፍ እና ግልጽነት ባለው መንገድ” እየሰሩ መሆናቸውን የመከታተል እና የመቆጣጠር ስልጣን አለው።

▶️ ተቋሙ የማዕድን ሚኒስቴርን ጨምሮ በ15 የፌደራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ላይ ከየካቲት 3፤ 2015 ጀምሮ ለ10 ወራት የቆየ “የመልካም አስተዳደር አፈጻጸም” ምዝና ማከናወኑ ተገልጿል። 

▶️ ተቋሙ ምዝነናውን ለማከናወን የተጠቀማቸው፤ “ተጠያቂነት፣ ግልጽነት፣ ፍትሃዊነት፣ ለህግ ተገዢነት እና ውጤታማነት” የሚሉትን የመልካም አስተዳደር መለኪያዎች ነው። 

▶️ በእነዚህ መለኪያዎች የተሻሻለ አፈጻጸም በማምጣት ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ የያዙት የገንዘብ፣ የትምህርት እና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ናቸው። የግብርና፣ የጤና እና የፍትህ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ተከታዮቹን ደረጃዎች አግኝተዋል።

▶️ “መሻሻል የሚገባው” በሚለው ምድብ በብቸኝነት የተቀመጠው የማዕድን ሚኒስቴር ነው።

ዝርዝሩን ለማንበብ፦ https://ethiopiainsider.com/2024/13258/

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
ከመጠለያ የወጡ የሱዳን ስደተኞችን ወደ ሌላ ቦታ እንደሚያዛውር አገልግሎቱ አስታወቀ!

በምዕራብ ጎንደር ዞን ሁለት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የመጠለያ ጣቢያዎች ያሉ ሱዳናውያን ስደተኞችን፣ ወደ ሌላ ቦታ ለማዛወር እየሠራ መኾኑን፣ የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በተቋሙ፥ የኩመር፣ የአውላላ እና የዓለምዋጭ መጠለያ ጣቢያዎች አስተባባሪ አቶ ታምራት ደምሴ፣ የሱዳን ስደተኞችን “አፍጥጥ” ወደሚባል ቦታ ለማዛወር እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

ከመጠለያ ጣቢያቸው ለቀው መንደር ዳር መኖር ከጀመሩ አንድ ወር እንደሞላቸው የሚናገሩት የሱዳን ስደተኞ ደግሞ፣ ደግሞ፣ የአካባቢው የጸጥታ ችግር እና የአገልግሎት እጥረት እንደሚያሳስባቸው ገልጸው፣ ፍላጎታቸው ከኢትዮጵያ ውጪ ወደ ሦስተኛ ሀገር መሔድ እንደኾነ አመልክተዋል፡፡

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ራያ አላማጣ አንድ ወጣት በህወሓት ታጣቂዎች መገደሉ ተሰማ ተከትሎ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ተቃውሞውን አሰምቷል::

@Yenetube @Fikeassefa
አየር መንገዱ ወደ አክሱም ዳግም በረራ ጀመረ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አክሱም ከተማ አቋርጦት የነበረውን በረራ ዛሬ ዳግም ጀምሯል፡፡

ላለፉት ስድስት ወራት ሲካወኑ የነበሩ የጥገና ሥራዎች መጠናቀቃቸውን ተከትሎ ነው አውሮፕላን ማረፊያ በዛሬው ዕለት ዳግም ለአገልግሎት ክፍት የሆነው፡፡

በዳግም በረራ ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይም÷የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው እና የትግራይ ክልል ጊዜያው አስተዳደር ርዕሰ መሥተዳድር ጌታቸው ረዳ ተገኝተዋል፡፡

[FBC]
@YeneTube @FikerAssefa
Notcoin 🤑   Dollar 💵
💎 ከ 500 NOTCOIN ጀምሮ ያላቹ እና P2P ላይ መሸጥ ወይም ትክክለኛ ገዢ ማግኘት ያልቻላቹ እኔጋር መሸጥ ትችላላቹ


ለመሸጥ ➡️ Dm  @abi_millionaire

🤑🤑🤑🤑🤑🤑🤑🤑🤑🤑
በምዕራብ ጎጃምና ሰሜን ጎጃም ዞኖች 6ኛና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተና አይወስዱም ተባለ

ዘንድሮ በሚሰጠው የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የክልልን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ በምዕራብና ሰሜን ጎጃም ዞኖች እንደማይሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

ከ354 ሺህ በላይ የ6ኛና 8ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ደግሞ በሌሎች አንፃራዊ ሰላም ባለባቸው ዞኖች እንደሚሰጥ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊና የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል፡፡

ከክልሉ ወቅታዊ የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ በዚህ ዓመት መመዝገብ ከነበረባቸው 6. 2 ሚሊዮን ተማሪዎች መካከል የተመዘገቡት 4 ሚሊዮኑ ብቻ መሆናቸውን ትምህርት ቢሮ ከዚህ በፊት ገልፆ ነበር፡፡

Via ዶቼ ዌሌ
@Yenetube @Fikerassefa
የሽግግር ፍትሕ ማስተግበሪያ ፍኖተ ካርታ ዝግጅት መጠናቀቁን የፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲውን መተግበር የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ተጠናቅቆ ለውይይት ዝግጁ መሆኑን የፍትሕ ሚኒስቴር አስታውቋል።ለውይይት ዝግጁ የሆነው ፍኖተ-ካርታ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአባልነት የሚሳተፉበት ጊዜያዊ እና ዘላቂ ተቋማዊ የቅንጅት አመራር ሥርዓት ስለሚቋቋምበት ሁኔታ፤ ስለ ሽግግር ፍትሕ ስልቶች አተገባበር ቅደም-ተከተል መካተቱን የፍትሕ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

ከትግበራ ምዕራፍ ረቂቅ ፍኖተ ካርታው በተጨማሪ የሽግግር ፍትሕ ጊዜያዊ የተቋማት የቅንጅት አመራር ሥርዓት ማቋቋሚያ ረቂቅ መመሪያ፣ የሽግግር ፍትሕ ስልቶች አተገባበር ቅደም-ተከተል ማብራሪያ ሰነድ መዘጋጀታቸውን ገልጿል።

በዚህም መሰረት የፍኖተ ካርታውን ረቂቅ ሰነድ ጨምሮ በተዘጋጁት የማስተግበሪያ ሰነዶች ላይ የሚደረጉ ውይይቶች ሲጠናቀቁ የፖሊሲው ትግበራ ምዕራፍ ዋና ዋና ተግባራት መከናወን እንደሚጀምሩ ሚኒስቴሩ አታውቋል።

ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ፤ በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት የተከሰቱ መጠነ-ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ውስብስብ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በወንጀል ተጠያቂነት፣ እውነትን ማፈላለግ፣ ይፋ ማውጣት እና ዕርቅ ማውረድ፣ በቅድመ-ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ምሕረት፣ በተቋማዊ ማሻሻያ እንዲሁም በማካካሻ ስልቶች ላይ የተዋቀረ መሆኑን መግለጫ አስታውሷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ እና ለታንዛኒያ በማዕድን ሀብታቸው እንዲሁም እያደገ ለመጣው የኤክስፖርት ገበያቸው በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ብድር ለመስጠት ተስማምታለች።

ደቡብ ኮሪያ ለኢትዮጵያ በአራት ዓመታት ውስጥ ለመሠረተ ልማት፣ ለሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ ለጤና እና ለከተማ ልማት የሚዉል 1 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ለማድረግ ስምምነት ማድረጓ ተዘግቧል።

ከዚህ በተጨማሪ በዚህ ስምምነት ታንዛኒያ በአምስት አመታት ውስጥ 2.5 ቢሊዮን ዶላር በቅናሽ ብድር ታገኛለች ተብሏል። በምላሹ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ለምስራቅ እስያ ሀገር የውቅያኖስ ሀብቶቿን እና ለንፁህ ኢነርጂ ወሳኝ የሆኑ ማዕድናትን እንደ ኒኬል፣ ሊቲየም እና ግራፋይት እንዲያገኙ የሚያስችል ሁለት ስምምነቶችን መፈራረሟን ነዉ ለማወቅ የተቻለው።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ?

ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential
Customers) እንዲደርስስ?

-ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤
-በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤
-በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን።

ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ።

ቴሌግራም፡ @adsommar
ስልክ፡ 0954260423
አብዛኞቹ ኢትዮጵያውን ስደተኞችን የያዘች ጀልባ ተገልብጣ ቢያንስ 38 ሞቱ!

አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን የሆኑ ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ከየመን የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ ተገልብጣ ቢያንስ 38 ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ።ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ለነፍስ አድን ሠራተኞች እንደተናገሩት ጀልባዋ 250 የሚጠጉ ሰዎችን አሳፍራ የነበረ ሲሆን፣ ለመገልበጥ የበቃችውም በካበድ ነፋስ ምክንያት ነው ተብሏል።መሞታቸው ከታወቀው 38 ሰዎች ውጪ ሌሎች 100 ሰዎች የደረሱበት ያልታወቀ ሲሆን፣ እነሱን ለማግኘት ፍለጋ እየተደረገ ነው።

ከየመን ዋና ከተማ አደን በስተምሥራቅ የምትገኘው የሩደም አካባቢ ባለሥልጣናት እንዳሉት አደጋው በደረሰባት ጀልባ ላይ ተሳፈረው ከነበሩት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሲሆኑ፣ የመንን ወደ ወደ ባሕረ ሰላጤው አገራት ለመሸጋገሪያነት ይጠቀሙባታል።የሩደም አካባቢ አስተዳዳሪ የሆኑት ሃዲ አል-ኹርማ ለሮይተርስ ዜና ወኪል እንደተናገሩት በጀልባዋ ላይ የመስመጥ አደጋው የደረሰው ወደ ባሕር ዳርቻው ከመቃረቧ በፊት ነው።በስፍራው የነበሩ ሰዎች 250 የሚሆኑ ስደተኞችን አሳፍራ አደጋው የደረሰባት ጀልባ ላይ የነበሩ በርካታ ሰዎችን ሕይወት ማትረፋቸው ተነግሯል።

“ዓሳ አስጋሪዎች እና ነዋሪዎች አብረዋቸው በጀልባዋ ላይ የነበሩ 100 የሚሆኑት ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁን የተናገሩ 78 ሰዎችን በሕይወት አድነዋል” ሲሉ ባለሥልጣኑ ተናግረዋል።ጨምረውም በአደጋው ምክንያት የጠፉትን ሰዎች ለማግኘት የሚደረገው ጥረት የቀጠለ ሲሆን፣ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ድርጅትም ስለደረሰው አደጋ እንዲያውቅ መደረጉ ተገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሪፖርት እንደሚያመለክተው ባለፈው የአውሮፓውያን ዓመት ብቻ 97,000 ስደተኞች በጦርነት ውስጥ ወደ ምትገኘው የመን ገብተዋል።በየመን ያለው ጦርነት እና በቅርቡ የየመን ሁቲ ታጣቂዎች በቀይ ባሕር ላይ ጥቃት እየሰነዘሩ ቢሆንም ስደተኞች ወደ አገሪቱ በአደጋኛ የባሕር ጉዞ መግባታቸውን ቀጥለዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerA
የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ጸደቀ!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባ የሕዝብ በዓላትን እና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ አጸደቀ፡፡የሕዝብ በዓላት በሥነ-ምግባር የታነጻ ሀገር ወዳድ ማሕበረሰብ ለመገንባት ብሎም ለሀገርና ሕዝብ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ሕጋዊ ዕውቅና መስጠት አስፈላጊ መሆኑ በስብሰባው ላይ ተገልጿል፡፡

በዚህም የሕዝብ በዓላት የሚከበሩት በሀገር አቀፍ ደረጃ በመሆኑ እነዚህን ጉዳዮች የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን ተፈጻሚነት ባለው ሕግ በአዋጅ እንዲወሰን ማድረግ ተገቢነት ያለው ስለሆነ አዋጁ መዘጋጀቱ ተብራርቷል፡፡ነባሩ የሕዝብ በዓላት እና የዕረፍት ቀን መወሰኛ አዋጅ የሕዝብ በዓላት ሲከበሩ ጥቅም ሊያስገኙ በሚችሉ መልኩ በድምቀት የሚከበሩበትን ዝርዝር የአከባበር ሥነ-ሥርዓት አለማስቀመጡም ተመላክቷል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa
የመንግስት የልማት ድርጅቶች በፌደራል መንግስት ግዢ እና የንብረት አስተዳደር አዋጅ እንዲተዳደሩ ተወሰነ!

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌዴራል መንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አዋጅን በሙሉ ድምጽ አጸደቀ።

አዋጅ ቁት 1333/2016 ሆኖ የጸደቀው የግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ከዚህ ቀደም በግዥና ንብረት አስተዳደር ሂደት ላይ የሚያጋጥሙ የመልካም አስተዳደር ችግርን የሚያርም፣ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ እንዲሁም ወጥነት እንዲኖር የሚያደርግ እንደሆነ ተገልጿል።

የጸደቀው አዋጅ በመንግስት የልማት ድርጅቶች ላይ ተፈጻሚ ቢሆን ተወዳዳሪነታቸውን ይጎዳዋል የሚል ጥያቄ ቢነሳም የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተቋማቱ በጥንቃቄ የግዥ መመሪያ አዘጋጅተው በዚያ መስራት እንዳለባቸው አስረድቷል።

@YeneTube @FikerAssefa
ዋን ራይድ በዘርፉ አዳዲስ አማራጮችን ይዞ መጣላችሁ! የናንተ የሆነውን ዋን ራይድን ምርጫዎ እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል።🎉🎉🎉

ከኮሚሺን በተጨማሪ ያልተገደበ የማይል ጥቅል በመሙላት ትርፋማ ይሁኑ ለእለታዊ ጥቅል 50ብር ለሳምንታዊ ጥቅል 200ብር ወርሃዊ ጥቅል 500ብር

የማኅበራዊ ትስስር ድኅረ ገጾቻችንን ይቀላቀሉ Facebook: https://www.facebook.com/rideinoneInstagram: https://www.instagram.com/rideinoneTelegram Group: http://www.tg-me.com/rideinoneTikTok: https://www.tiktok.com/@rideinon

መተግበሪያውን ያውርዱ | ይመዝገቡ| ቤተሰብ ይሁኑ!

𝐃𝐫𝐢𝐯𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩 https://shorturl.at/bdyFO
𝐏𝐚𝐬𝐬𝐞𝐧𝐠𝐞𝐫 𝐀𝐩𝐩 https://shorturl.at/lJLZ6
ዋን ራይድ በአንድ ይጓዙ!!
የፍትህ ሚኒስቴር የሽግግር ፍትህ ማስተግበሪያ ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ መጠናቀቁን ይፋ አደረገ።

የፍትህ ፖሊሲው በተለያዩ ጊዜያት በሀገሪቱ የተከሰቱ መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እና ውስብስብ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለመ እንደሆነ የፍትህ ሚኒስቴር በመግለጫው አመልክቷል። በወንጀል ተጠያቂነት፤ እውነትን ማፈላለግ፤ ይፋ ማውጣት እና እርቅ ማውረድ ጋር ተያይዞ ለሚከናወነው ሂደትም አስፈላጊ የሆኑ ተግባራትን ለማከናወን የሚረዳ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ አዘጋጅቶ ባለፈው ሚያዝያ ወር ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቅርቦ ማጸደቁንም አስታውሷል።

ፍኖተ ካርታው የሽግግር ፍትህን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ነጻና ገለልተኛ ተቋማት ተቋቁመው የሽግግር ፍትህ ሂደት ተግባራዊ እስኪያደርጉ በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት የሽግግር ፍትህ ማስተግበሪያ ፍኖተ ካርታውን ተዘጋጅቶ ለውይይት ለባለድርሻ አካላት ማቅረቡን አስታውቋል።

በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የሚከታተሉ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ለተፈጸሙና እየተፈጸሙ የሚታዩት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂነት እንዲሰፍን በተደጋጋሚ ይጠይቃሉ።

@Yenetube @Fikerassefa
የ2017 በጀት የውጭ ምንዛሬ ግብይት ላይ የሚደረግ ማሻሻያን ታሳቢ አድርጎ እንዳልተዘጋጀ የገንዘብ ሚኒስትሩ ተናገሩ!

የ2017 በጀት ሲዘጋጅ ብር ከዶላር አኳያ ያለውን የምንዛሬ ተመን የሚያዳክም ውሳኔ ተግባራዊ ይደረጋል በሚል ታሳቢ እንዳልሆነ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ተናገሩ። በኢ-መደበኛው እና በባንኮች በሚደረገው ይፋዊ ምንዛሬ መካከል ያለውን ልዩነት የሚያጠብ እርምጃን አስመልክቶ “የቀረበ ነገር የለም” ያሉት አቶ አህመድ፤ የፌደራል መንግስት በጀት የተዘጋጀው “የነበረው አካሄድ እንደሚቀጥል ታሳቢ ተደርጎ” መሆኑን አስታውቀዋል። 

የገንዘብ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት፤ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 4፤ 2016 በተካሄደው የተወካዮች መደበኛ ስብሰባ ላይ ከፓርላማ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው። አቶ አህመድ ዛሬ ፓርላማ የተገኙት፤ ለፌደራል መንግስት የተመደበውን የ2017 በጀት አስመልክቶ ዝርዝር መግለጫ ለማቅረብ ነበር።

ሚኒስትሩ 40 ደቂቃ ገደማ ከፈጀው የዛሬው የበጀት መግለጫ ንግግራቸው ግማሹን ያዋሉት፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለፉት ዓመታት አስመዝግቧል ያሉትን “ስኬቶች” እና ያጋጠሙትን “ተግዳሮቶች” ለማስረዳት ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ላለፉት 3 ዓመታት ሲተገብረው የቆየው የመጀመሪያው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራም በዚህኛው የሚኒስትሩ የንግግር ክፍል በስፋት ተዳስሷል።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ የጀመረው ሁለተኛው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ፤ ይቀርፋቸዋል ተብለው ከሚጠበቁ  ተግዳሮቶች መካከል አንዱ “የውጭ ምንዛሬ እጥረት” መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። የፌደራል መንግስት “የውጭ ምንዛሬ አጠቃቀምን ለማሻሻል አስፈላጊ የሆኑ የማሻሻያ እርምጃዎች” እንደሚወስድም ጠቁመዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
2024/06/12 00:11:20
Back to Top
HTML Embed Code: