ህወኃት ጠ/ሚኒስትሩ በፓርላማ ለሰጡት ሃሳብ ምን አለ?
ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተገኝተው ትግራይን በተለይም የተከፋፈሉትን የህወሓት አመራሮች አስመልክቶ ለሰጡት ሃሳብ ህወኃት ባለ 3 ነጥብ መግለጫ አውጥቷል፡፡ በመግለጫው ምን አለ?
@YeneTube @FikerAssefa

በአሜሪካ ቴክሳስ የጎርፍ አደጋ 15 ሕፃናትን ጨምሮ የ51 ሰዎች ሕይወት አለፈ!
በማዕከላዊ ቴክሳስ በደራሽ ጎርፍ አደጋ 15 ሕፃናትን ጨምሮ 51 ሰዎች ከሞቱ በኋላ በመቶዎች የሚቆጠሩ የነፍስ አድን ሠራተኞች የጠፉ ሰዎችን ፍለጋ ተሰማሩ።በጣም የተጎዳው ኪር የተባለው አካባቢ ሲሆን 43 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ፤ በጓዳሉፔ ወንዝ አጠገብ በሚገኘው የክርስቲያን ወጣቶች ካምፕ የነበሩ 27 ሕፃናት ደግሞ ጠፍተዋል።
የአካባቢው የፖሊስ አዛዥ ላሪ ሊታ "ፍለጋው ይቀጥላል። ሁሉም ሰው እስኪገኝ ድረስ ሥራው ይቀጥላል" ሲል ቃል ገብቷል።ትራቨስ እና ቶም ግሪን የተባሉ አካባቢዎችን ጨምሮ በሌሎች የግዛቱ ክፍሎች ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል።
በማዕከላዊ ቴክሳስ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በርካታ የደራሽ ጎርፍ ማስጠንቀቂያዎች ወጥተዋል።እስካሁን 850 የሚሆኑ ሰዎች በሕይወት መትረፍ ችለዋል።የቴክሳስ ገዥ ግሬግ አቦት ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የፍለጋ ጥረቶችን ለማስፋፋት የአደጋ ጊዜ አዋጅ መፈራረማቸውን ተናግረዋል።የአካባቢው ባለስልጣናት "በዚህ ክስተት ሰለባ የሆኑትን እያንዳንዱን ሰው ፈልገው እንዲያገኙ ለማድረግ ሌት ከቀን እንሰራለን" ብለዋል።
የፍለጋ እና በሕይወት የማዳን ተልዕኮው እንደሚቀጥል የተናገሩት ባለስልጣናቱ፤ ይሁን እንጂ ጥረቱ በሕይወት የማዳን ጥረት አይደለም ብለዋል።በጎርፉ ተጠርገው የተወሰዱ ሰዎችን ለማግኘት የነፍስ አድን ሠራተኞች ወደ ጓዳሉፔ ወንዝ እየወረዱ መሆኑንም ተናግረዋል።

ከባህር ኃይል ትልቅነት መለኪያዎች አንዱ የሆነው የተዋጊ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ (Aircraft Carrier) ነው።
እነዚህ ተንሳፋፊ የአየር ማረፊያዎች ጄቶችንና ሄሊኮፕተሮችን በምድር ላይ ወዳለ ማንኛውም ቦታ ያስነሳሉ።የተዋጊ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ በአየር ላይ የተመሰረቱ አውሮፕላኖችን ለመደገፍ እና ለማሰማራት የተነደፈ፣ በባህር ላይ የሚንቀሳቀስ የአየር ማረፊያ ሆኖ የሚያገለግል የጦር መርከብ ነው።
እነዚህ ግዙፍ መርከቦች ያሏቸው ሃገራትን እና አሜሪካ ከተቀረው አለም ያላትን የባህር እና አየር ሃይል ልዩነት የዳሰስንበትን ዝግጅት በዩትዩብ ገጻችን ላይ ይከታተሉ። ዝግጅታችን ከተመችዎ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ።
https://youtu.be/CeI0EpJQeGw

YouTube
የተዋጊ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦች ያሏቸው ሃገራት እና የአሜሪካ የባህር ኃይል ታላቅነት
ዛሬ የባህር ኃይል ትልቅነት መለኪያዎች አንዱ የሆነውን የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከቦችን (aircraft carriers) እንቃኛለን። እነዚህ ተንሳፋፊ የአየር ማረፊያዎች ጄቶችንና ሄሊኮፕተሮችን በምድር ላይ ወዳለ ማንኛውም ቦታ ያስነሳሉ።የአውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ በአየር ላይ የተመሰረቱ አውሮፕላኖችን ለመደገፍ እና ለማሰማራት የተነደፈ፣ በባህር ላይ የሚንቀሳቀስ የአየር ማረፊያ ሆኖ የሚያገለግል የጦር መርከብ…
የእስራኤል እና የሃማስ ድርድር ዛሬ በዶሃ ለጋዛ ስምምነት እና ታጋቾችን ለመልቀቅ እንደገና ሊጀመር ነው
ይህ የሚሆነው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ዋይት ሀውስ ከመጎብኘታቸው በፊት ነው።
ኔታንያሁ ቀደም ሲል የጦርነቱ ቁልፍ አስታራቂ ወደሆነችው ኳታር ቡድን እየላኩ መሆኑን አስታውቀው ነበር፤ ምንም እንኳን የሃማስ ምላሽ ለአሜሪካ ደጀንነት የተደረገው የተኩስ አቁም ረቂቅ ስምምነት “ተቀባይነት የሌላቸው” ፍላጎቶችን እንደያዘ ገልጸው ነበር።
አሁን ወደ 22ኛው ወር እየተቃረበ ያለውን ጦርነት ለማስቆም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ግፊት ተከትሎ ኔታንያሁ ሰኞ ዕለት ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘዋል። ዶናልድ ትራምፕ ውጊያውን ለማቆም አዲስ ጥረት እያደረጉ ነው።
ከድርድሩ ጋር በቅርበት የሚያውቁ እና ከሃማስ ጋር ቅርበት ያላቸው የፍልስጤም ባለስልጣን ለአኤፍፒ እንደተናገሩት አለም አቀፍ አስታራቂዎች ለቡድኑ “አዲስ ዙር ተዘዋዋሪ ድርድር...ዛሬ በዶሃ ይጀምራል” ሲሉ አሳውቀዋል።
በዋናው ተደራዳሪው ካሊል አል-ሃያ የሚመራው የቡድኑ ልዑክ በኳታር ዋና ከተማ ደርሷል ሲሉ ባለስልጣኑ አክለዋል።
አርብ ዕለት ሃማስ በድርድሩ “ወዲያውኑ እና በቁም ነገር ለመሳተፍ” ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
የእስራኤል ተደራዳሪዎችም በመንገድ ላይ መሆናቸውን ያረጋገጡት ኔታንያሁ፣ “ሃማስ በኳታር የቀረበው ሃሳብ ላይ ሊያደርጋቸው የሚፈልጋቸው ለውጦች... ለእስራኤል ተቀባይነት የላቸውም” ብለዋል።
@Yenetube @Fikerassefa

ኢሎን መስክ የፖለቲካ ፓርቲ አቋቋመ
ኢሎን መስክ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ያለው የቅርብ ወዳጅነት በአለመግባባት ከተጠናቀቀ ከሳምንታት በኋላ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ አቋቁሜያለሁ አለ።
ቢሊየነሩ የፖለቲካ ፓርቲን ማቋቋሙን ለሪፐብሊካን እና ዲሞክራቲክ የሁለት ፓርቲ ስርዓት ፈተና እንደሆነ በመግለጽ በማህበራዊ ሚዲያው ኤክስ ገጹ ላይ አስታውቋል።
ሆኖም ፓርቲው በይፋ በአሜሪካ የምርጫ ባለሥልጣን መመዝገቡ ግልፅ አይደለም
ከአሜሪካ ውጭ በመወለዱ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ብቁ ያልሆነው መስክ ፓርቲውን ማን እንደሚመራው አልተናገረም።
መጀመሪያ ከትራምፕ ጋር በነበረው አለመግባባት ወቅት ፓርቲ የመመስረት ሃሳብን አንስቶ የነበረው መስክ፣ አለመግባባቱ እየተካረረ መጥቶ በአስተዳደሩ ውስጥ የነበረውን ኃላፊነት ለቅቆ ከቀድሞ የቅርብ ወዳጁ ጋር የተካረረ አለመግባባት ውስጥ መግባቱ የአደባባይ ሚስጥር ነበር።
መስክ ከፕሬዚደንት ትራምፕ ጋር የተካረረ አለመግባባት ውስጥ በነበረበት ወቅት የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን በአሜሪካ ውስጥ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ መኖር ይኖርበት እንደሆን የሚጠይቅ አስተያየት ለጥፏል።
መስክ በቅዳሜው ልጥፍ ላይ ያንን የሕዝብ አስተያየት በመጥቀስ "2 ለ 1 በሆነ ውጤት፣ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ እንዲኖር ፍላጎታችሁን አሳይታችኋል! አገራችንን በቆሻሻና በሌብነት ወደ ኪሳራ ስለመውሰድ ስንነጋገር የምንኖረው በአንድ ፓርቲ ስርዓት እንጂ በዲሞክራሲ አይደለም።" ሲል ጽፏል።
አክሎም "ዛሬ የአሜሪካ ፓርቲ የተመሰረተው ነፃነታችሁን ሊመልስላችሁ ነው" ብሏል።
ከቅዳሜ ጀምሮ የፌዴራል ምርጫ ኮሚሽን ፓርቲው በይፋ መመዝገቡን የሚጠቁሙ ሠነዶችን ይፋ አላደረገም።
በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ከተለምዷዊው የሁለት ፓርቲ ስርዓት ውጪ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችም ቢኖሩም፣ እውነተኛ ጫና ለመፍጠር በአገር አቀፍ ደረጃ ጠንካራ ተቀባይነት ማግኘት አዳጋች ነው።
ባለፈው ዓመት በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደ ሊብሪተያን ፓርቲ፣ ግሪን ፓርቲ እና ፒፕልስ ፓርቲ ያሉ እጩዎች ትራምፕን ወይም የዴሞክራቲክ ተቀናቃኛቸውን ካማላ ሃሪስን እንዳያሸንፉ ለማድረግ ያልተሳካ ሙከራ አድርገዋል ።
መስክ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የትራምፕ ዋና ደጋፊ ነበር።
ባለፈው ዓመት በተደረጉ የምርጫ ቅስቀሳዎች ወቅት ከፕሬዚደንቱ ጎን በአጋፋሪነት የነበረው መስክ ሥልጣን ከያዙ በኋላም የአራት ዓመት ልጁ ትራምፕን እንዲያገኝ ኦቫል ኦፊስ ድረስ ይዞት መጥቷል።
መስክ የትራምፕን የምርጫ ቅስቀሳ በገንዘብ ከደገፉ ባለሀብቶች መካከል ዋነኛው ነው። ፕሬዚደንቱ ዳግም ሥልጣናቸውን እንዲይዙ 250 ሚሊዮን ዶላር አውጥቷል።
ከምርጫው በኋላም በፌዴራል በጀት ውስጥ የሚታዩ ወጪዎች ላይ ቅነሳዎችን የመለየት ኃላፊነት የተሰጠውን የመንግስት ቅልጥፍና (ዶጅ) ተብሎ የሚጠራውን ተቋም እንዲመራ ተሾመ።
ከትራምፕ ጋር የነበራቸው ውዝግብ የጀመረው በግንቦት ወር አስተዳደሩን ለቅቆ በወጣበት ጊዜ እና የትራምፕን ግብር እና የወጪ ዕቅዶችን በይፋ መተቸት ሲጀምር ነው።
የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ትልቅ ቆንጆ" ሲሉ በይፋ የሰየሙት ረቂቅ በጀታቸው በአገሪቱ በምክር ቤት ጸድቋል።
ሕጉ ከፍተኛ ወጪን እና የግብር ቅነሳን ያካተተ ሲሆን በአሜሪካ በጀት ላይ በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ውስጥ ከሦስት ትሪሊየን ዶላር በላይ ጉድለት እንደሚያስከትል ተገምቷል።
በኤሌክትሪክ የሚንቀሳቀሱ መኪኖችን የሚያመርተው ግዙፉ ቴስላ ባለቤት የሆነው መስክ የትራምፕ ሕግ በአረንጓዴ ሽግግር ላይ ወይም እንደ ቴስላ ላሉ ምርቶች ድጎማ ማድረግ ላይ አያተኩርም ሲል ይተቻል።
ትራምፕ በዚህ ሳምንት በማኅበራዊ ድረ ገጻቸው ትሩዝ ሶሻል ላይ "ኤሎን በታሪክ ውስጥ ከየትኛውም የሰው ልጅ የበለጠ ድጎማ ሊያገኝ ይችላል" ሲሉ ጽፈዋል። "ያለ ድጎማ ኤለን ምናልባት ሱቁን ዘግቶ ወደ አገሩ ደቡብ አፍሪካ መመለስ ይኖርበታል።"
ትራምፕ የቢሊየነሩን ሌሎች ንግዶችን በመጥቀስ ለመስክ ኩባንያዎች የሚደረጉ ድጎማዎችን እንዲመለከት የቅልጥፍና ቢሮውን እንደሚያዙ ዝተዋል።
በተጨማሪም መስክ ለአሜሪካ መንግሥት ሮኬቶችን የሚያመጥቀውን ስፔስ ኤክስ እና ለአሜሪካ እና አውሮፓ የመከላከያ ኃይሎች የሳተላይት አገልግሎት የሚሰጠውን ስታርሊንክ ባለቤት ነው።
Via:- BBC

የሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ በሚቀጥለው ሳምንት ይፋዊ ግብይት ሊጀምር ነው
ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ( ስቶክ ገበያ) በሚቀጥለው ሳምንት ሥራ ሊጀምር መሆኑ ተሰምቷል። ይህ እርምጃ ለአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ትልቅ ምዕራፍ እንደሆነ ታውቋል።
ገበያዉ በኖቬምበር 2023 በተደረገ የካፒታል ማሰባሰቢያ ዘመቻ 1.5 ቢሊዮን ብር በማሰባሰብ ከታሰበው ግብ በ631% በልጧል። ይህ ገንዘብ ከ48 የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተቋማት የተገኘ መሆኑ ይታወቃል።
በሕዝብና በግል ሽርክና የሚሰራው አዲሱ የበይነመረብ ንግድ ልዉዉጥ መድረክን መንግሥት 25%፣ የግል ዘርፍ ደግሞ 75% ድርሻ አላቸዉ። አሁን ላይ ገዳ ባንክ አ.ማ. እና ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ. በገበያው ላይ ከተመዘገቡት ኩባንያዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
የሰነደ መዋዕለ ንዋይ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ እስከ 50 ኩባንያዎችን፣ በአሥር ዓመታት ውስጥ ደግሞ ከ90 በላይ ንግዶችን ለማካተት አቅዷል። ይህ ልውውጥ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማዘመን፣ ግልጽነትን ለማሳደግ እና ለንግዶች ካፒታል ማሰባሰቢያ አዳዲስ አማራጮችን ለመስጠት ያለመ ሲሆን፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን እንደሚያነቃቃም ይጠበቃል።
ዝርዝሩን ያንብቡ

አል-ፋሽጋ ዳግም በኢትዮጵያውያን እጅ ገባ
ለዘመናት የኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች የእርሻና የኑሮ መሰረት የነበረው ለም መሬት፣ አል-ፋሽጋ፣ ዳግም ወደ ህጋዊ ባለቤቶቹ ተመልሷል።
የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን የውስጥ ችግር እንደ መልካም አጋጣሚ በመቁጠር፣ በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎንደር ዞን የሚገኙትን የመተማና የቋራ ወረዳ ለም መሬቶችን በኃይል ተቆጣጥሮ ነበር።
በወቅቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በቅርብ ርቀት ላይ ሆኖ ሁኔታውን በትዕግስት ሲከታተል የነበረ ሲሆን፣ መንግሥትም ችግሩን በዲፕሎማሲና በውይይት ለመፍታት ያለውን ፍላጎት በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወሳል፡፡
በዚህ የሱዳን ወረራ ወቅት ኢትዮጵያውያን ገበሬዎች ከእርሻቸው ከመፈናቀላቸውም በላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብልና የንብረት ውድመት እንደደረሰባቸው አይዘነጋም፡፡
የሱዳን ባለሥልጣናት ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ታጣቂዎች በአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት በመታገዝ የአማራ ክልል አዋሳኝ ወደኾኑ የሱዳን ለም መሬቶች በመስፋፋት ላይ ናቸው ሲሉ መክሰሳቸው ተዘግቦ ነበር፡፡

ቶምቦላ እጣ ወጥቷል
ቶምቦላ ሎተሪ 2017 ዕጣ ዛሬ ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በዕድል አዳራሽ የወጣ ሲሆን የወጡት የዕጣ ቁጥሮች ከላይ ተያይዟል።

Forwarded from YeneTube
#TemerProperties
ከዚህ በፊት 7 ሳይቶችን ጥንቅቅ አርጎ ያስረከበዉ ቴምር ፕሮፐርቲስ አሁን
📌 በሳርቤት
📌 በፒያሳ መኖሪያ እና የንግድ ሱቆች
✅ 10% ቅድመ ክፍያ
✅ ሰፊ የጋራ መገልገያ
✅ ቢያከራዩት,ቢሸጡት ወይም ቢኖሩበት አዋጭ
✅ ተመጣጣኝ ዋጋ
🏡 ሊሴ ገ/ማርያም አጠገብ
👉1 መኝታ 63ካሬ=
10% ቅድመ ክፍያ 693,000 ብር
ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር
👉2 መኝታ 86 ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 946,000 ብር
ሙሉ ክፍያ 9,460,000 ብር
👉3 መኝታ 114 ካሬ
10%ቅድመ ክፍያ 1,219,800 ብር
ሙሉ ክፍያ 12,198,000 ብር
👉ቀሪውን 90% በ16ዙር ብር ያለምንም
ጭማሪ በብር ከፍለው የሚጨርሱት
👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ
⚠️በተጨማሪም ሱቅ በ900ሺ ብር ቅድመ ክፍያ እዛው ፒያሳ ሚኒሊክ አደባባይእየሸጥን እንገኛለን::
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251976195835
WhatsApp
Message Temer properties on WhatsApp. https://wa.me/251976195835
Telegram user
@Ruthtemersales
TEMER PROPERTIES
Create | Construct | Deliver
#TemerProperties #Temerrealestate

አቅመ ደካማወችን ሀረጋውያኖችን በነፃ
https://vm.tiktok.com/ZMSayMdXa
በተለያየ የጤና ችግር የሚሰቃዩትን እየ ፈወሰ
ደስታቸውን እየመለሰ የሚገኘውን የህክምና ተቋም https://vm.tiktok.com/ZMSay8eV2/
ሰወች እንዴት እንደተፈወሱ ሲመሰክሩ እንስማ እንይ ቻናሉን እንቀላቀል
https://vm.tiktok.com/ZMSaDEhoN
በስጋውይም ሆነ በመንፈስ ደውየ ከተቸገሩ መተው በመመርመር ይታከሙ ይፈወሱ
44ት አይነት በሽታወችን እየፈወስን እንገኛለን
አድራሻ አዲስ አበባ አየርጤና ወደካራ ናትራን ኩፓንያ ፊት ለፊት
ቁጥር ሁለት ባህርዳር ዲያስፖራ በአሮጌው አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት
☎️ 0917040506
☎️0912718883
ይደውሉ ይምጡ ይታከሙ ይፈወሱ ይመስክሩ

ቻይና ከኢትዮጵያ ለሚመጣ የአኩሪ አተር ተረፈምርት መግባት እንዲችል ይሁንታ ሰጠች፡፡
የቻይና ጉምሩክ ይፋ ባደረገው መረጃ የቻይናን የጥራት ደረጃ ከጠበቀ ከኢትዮጵያ የሚመጣ የአኩሪ አተር/soymeal እንዲገባ ይሁንታ ሰጥቷል፡፡የአኩሪ አተር ተረፈምርቱ በዋናነት ለእንስሳት መኖ የሚያገለግል ነው፡፡
ከአሜሪካ ጋር የንግድ ጦርነት ውስጥ የገባችው ቻይና የአኩሪ አተር ገቢ ምርት ላኪ አገራትን የማስፋት ስራ እየሰራች ትገኛለች፡፡ነገር ግን አሁንም ምርቱን በዋናነት የምታስገባው በአለም ላይ በምርት ቀዳሚ ከሆነችው ከአሜሪካ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በኢትዮጵያ በተለይ የኢንደስትሪ ግብአት እንደሆነ የሚነገርለት የአኩሪ አተር ምርት በተለይ ግብይቱ ወደ ኢሲኤክስ ከገባ ወዲህ ከጊዜ ወደ ጊዜ ምርቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑ ይጠቀሳል፡፡ሆኖም በዋጋም ከፍተኛ ጭማሪ እያሳየ መሆኑን በግብአትነት የሚጠቀሙ እንደ ዘይት ፋብሪካ ያሉ ድርጅቶች በቅሬታ ይገልፃሉ፡፡
Via KGEthiopia

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት የአል ሲሲን ግብዣ ተከትሎ የሁለትዮሽ ውይይት ለማድረግ ግብፅ ገቡ!
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲን ግብዣ ተከትሎ የሁለትዮሽ ውይይት ለማድረግ ግብጽ ገብተዋል። ፕሬዝዳንቱ ትናንት እሁድ ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም በግብፅ የባህር ዳርቻ ከተማ በሆነችው ኤል አላሜይን ሲደርሱ፣ በግብፅ ባለስልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
መሪዎቹ በሁለቱ ወንድማማች አገራት መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ ትብብር እና ታሪካዊ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የሁለትዮሽ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ቪላ ሶማሊያ አስታውቋል።በተጨማሪም የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ከግብጹ አቻቸው ጋር በፀጥታ፣ በንግድ፣ በትምህርት እና ቀጠናዊ መረጋጋትን ጨምሮ ቁልፍ በሆኑ ዘርፎች ትብብርን ለማጠናከር ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
እንዲሁም ሁለቱ ሀገራት በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና፣ በቀይ ባህር መስመር ልማት እንዲሁም ሽብርተኝነትንና ጽንፈኝነትን ለመዋጋት በሚደረጉ የጋራ ጥረቶች ላይ እንደሚመክሩ የሶማሊያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።ከዚህ በፊት በጎርጎሮሳውያኑ ነሐሴ 2024፣ ግብፅና ሶማሊያ የመከላከያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል። ከስምምነቱ ከአንድ ወር በኋላ ደግሞ የሶማሊያ ባለሥልጣናት "የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በታህሳስ 2023 አሥርት ዓመታትን ያስቆጠረውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ካነሳ ወዲህ ትልቁ የጦር መሳሪያ ጭነት" ሲሉ የገለጹት የግብፅ ግዙፍ ወታደራዊ የጭነት መርከብ ሶማሊያ ሞቃዲሾ ወደብ መድረሱ አይዘነጋም።
በሶማሊያ የግብፅ ወታደራዊ ተሳትፎ መጨመሩ ከኢትዮጵያ በኩል ትችት የገጠመው ሲሆን ኢትዮጵያ ድርጊቱን ካይሮ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ካላት ተቃውሞ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ትመለከተዋለች።
@YeneTube

YeneTube
Photo
ምክር ቤቱ በሰፊው ሲተች የቆየውን ድንጋጌ አረመ!
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ካፀደቀው ማሻሻያ አዋጅ ውስጥ በስፋት ሲተች የቆየውን ድንጋጌ አርሞ አጸደቀ።የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ 10/ 2017 ዓ/ም ባካሄደው 31ኛ መደበኛ ጉባዔ በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ማሻሻያ አጽድቋል።
በተሻሻለው አዋጅ 1387/2017 አንቀጽ 26 ንዑስ አንቀጽ 4 መሰረት በልዩ የወንጀል ምርመራ ሂደት ወቅት መርማሪው ከአቅሙ በላይ የሆነ ጉዳይ ሲገጥመው ነፍስ ከማጥፋት በስተቀር ራሱን የመከላከል ማንኛውንም እርምጃ መውሰድ እንደሚችል ተደንግጓል።ድንጋጌው መጀመሪያ በሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ "ውጤታማ" የሽፋን ምርመራዎችን ለማረጋገጥ እና ለሕዝብ ጥቅም የሚሠሩ ሰዎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው በሚል ቀርቧል።
ይሁን እንጂ ይህ ድንጋጌ እንዲታረም የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውሳኔ ሀሳብ አዘጋጅቶ አቅርቧል። የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ኢሳ ቦሩ ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ ያቀረቡ ሲሆን፤ ከአሁን በፊት የነበረው የረቂቅ አዋጅ ድንጋጌ እንዲታረም መደረጉ አተገባበሩ ላይ “አሉታዊ ተፅእኖ” ሊያስከትል እንደሚችል ተናግረዋል።
አዋጁም ለሕትመት ሳይበቃ ቀድሞ እንዲታረምና እንዲስተካከል መደረጉ የሚበረታታ ተግባር መሆኑንም ተገልጿል።ያለመከሰሰ መብት የሚሰጠው አከራካሪው ድንጋጌ በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና በፖለቲካ ሰዎች በተለይም በ አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካዩ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል።
ሰኔ በተካሄደው የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ ደሳለኝ፤ ድንጋጌው በስውር ምርመራ የሚያደርጉ ሰዎች "ማሰቃየት ወይም ኢ-ሰብአዊ አያያዝ" ቢፈጽሙ እንኳ ተጠያቂ እንዳይሆኑ ሊያደርግ እንደሚችል በማስጠንቀቅ ተቃውመውታል።
ማሻሻያው ትኩረቱ በህገወጥ የገንዘብ እንቅስቃሴ ላይ እንጂ በፖለቲካ ተዋንያን ወይም በሲቪል ማህበረሰብ ላይ አይደለም በሚል ከመንግስት ባለስልጣናት ማረጋገጫ ቢሰጥም በአዋጁ ላይ የአዲስ ስታንዳርድ ርዕሰ አንቀጽን ጨምሮ በርካታ ትችቶች መቅረባቸው ይታወቃል።
Via AS

በጉርሱም ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ!
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጉርሱም ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ።አደጋው ከጉርሱም ወረዳ ወደ ጅግጅጋ ከተማ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከባጃጅ ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡
በአደጋውም ባጃጁ ውስጥ የነበሩ የ6 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ማለፉን በወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል መከላከል መምሪያ ም/ሃላፊ ኢንስፔክተር ቱሪ ድሪባ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።የተከሰተው አደጋ መንስኤ በፍጥነት ማሽከርከር መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
Via FBC

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው እርዳታ በአዲስ መዋቅር ስር ሆኖ እንደሚቀጥል አስታወቀች!
የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (USAID) ቢዘጋም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተፈጸሙ “የሁለትዮሽ የእርዳታ ስምምነቶች” በሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ስር በተዘረጋው አዲስ መዋር እንደሚቀጥሉ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ። ኤምባሲው ዋነኛ ናቸው ያላቸው የሰብአዊ እርዳታ፣ ዓለም አቀፍ ጤና እና የምግብ ዋስትና መርሃ ግብሮች በአዲሱ መዋቅር እንደሚቀጥሉ ዛሬው ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል።
አሜሪካ በእነዚህ ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምትሰጠው እርዳታ እንደሚቀጥል ኤምባሲው ማረጋገጫ የሰጠው፤ የሀገሪቱ ተራድኦ ደርጅት የሆነው USAID ባለፈው ምንት በይፋ መዘጋቱን ተከትሎ ነው። ላለፉት 64 ዓመታት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሰብአዊ እና የልማት እርዳታ ሲያቀርብ የቆየው ይህ ተቋም የተዘጋው፤ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ድርጅቱን ቀስ በቀስ ሲያዳክመው ከቆየ በኋላ ነው።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፤ ድርጅቱ የነበሩትን ኃላፊነቶች ካለፈው ሰኞ ሰኔ 24፤ 2017 ጀምሮ በይፋ ተረክቧል። ሽግግሩ “ድግግሞሽን ለመቀነስ”፣ “ተጠያቂነትን ለማጠናከር” እና የእርዳታ መርሃ ግብሮችን ከዩናይትድ ስቴትስ “የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እና የብሔራዊ ደህንነት ዓላማዎች ጋር ለማጣጣም የሚያስችል” ሆኖ እንደተቀረጸ የአሜሪካ ኤምባሲ በዛሬው መግለጫ ጠቁሟል።
Via Ethiopia Insider