Telegram Web Link
#በብርሃን_ፀዳል

በብርሃን ፀዳል ተከባ እመቤቴ
በደመና ዙፋን ተቀምጣ ከፊቴ
የጽጌውን ዜማ ስንዘምር በደስታ
በምስጋናሽ መጠጥ/ሲሰማኝ እርካታ/(፪)

እንባዬ ሲቀዳ ናፍቆትሽ መስጦኝ
ከደስታ በላይ አንቺን ስላየሁኝ
ምኞቴ ተሳክቶ ፊትሽን አይቼው
የሌሊቱ ህልሜ /የቀን ምኞቴ ነው/(፪)
#አዝ
ሩኅሩኅ ነሽና ይህ ህልሜ ተሳክቶ
አመስግኜሽ ድንግል ህልናዬ ረክቶ
ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን/ህሊናዬ ይትጋ/(፪)
#አዝ
ልጅሽ ልሁን ድንግል ከስርሽ አልጥፋ
አንቺን በማመስገን ህሊናዬ ይርካ
የምስጋናሽ ብዕር ብራናሽ ልሁን
ስምሽ ይፃፍብኝ /በልዩ ህብር/(፪)


💚  @yeorthodoxmezmur  💚
💛  @yeorthodoxmezmur  💛
❤️  @yeorthodoxmezmur  ❤️
✞  ድል አለ በስምህ

ድል አለ በሰምህ
ድል አለ በቃልህ /2/
ተራራው ይናዳል አማኑኤል ስልህ
ባህር ይከፈላል መድኃኔአለም ስልህ

ቃዴስን ታላቁን በረሃ
አለፍነው  ሳንጠማ ውኃ
ፈርኦንን ከባህር የጣለው
ጌታዬ የፀና ሰምህ ነው
አምላኬ የፀና ስምህ ነው

አዝ____

በእልልታ ቢፈርሰ ኢያረኮ
ጠላትም ቢወድቅ ተማርኮ
ቢሰጠን ለእኛ ከተማው
የሆነው ሁሉ ባንተ ነው/2/

አዝ___
  
ከክፋት ሁሉ ብናመልጥ
የማራ ውኃ ቢጣፍጥ
ብንበላ መና ከሰማይ
ሰለ ሆንክ ነው አዶናይ
ሰለ ሆንክ ነው ሁሉን ቻይ

አዝ____

የቆምነው ዛሬ በሕይወት
ስምህን አድርገን ነው ጉልበት
ከሜዳ ተጠርተን ብንነግስ
ሆነህ ነው ክብርና ሞገስ

             ዘማሪ
  ገብረ-ዮሐንስ ገብረ-ጻድቅ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

💚  @yeorthodoxmezmur  💚
💛  @yeorthodoxmezmur  💛
❤️  @yeorthodoxmezmur  ❤️

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ
እመ አምላክ | @Z_TEWODROS TELEGRAM CHANNEL |
✞እመ አምላክ✞

እመ አምላክ (፪)
አስቢኝ በሰርክ

ሃዘኔ ጭንቀቴ በጣም በዛብኝ
ከልጅሽ አማልጅኝ አንቺው አስታርቂኝ
ከመንበሩ ቆመሽ ንገሪው ለልጅሽ
እናቱ ነሽና እሱ አያሳፍርሽ
አዝ =
እኔ ኃጥአተኛው በደሌን አውቃለው
ምርኩዜ ነሽና እከተልሻለው
መንገዱ ጠፍቶብኝ የጽድቁ ጎዳና
መብራቱን አብሪልኝ እመጣለሁና
አዝ =
መመገብ ይቅርብኝ አልራብምና
ስምሽን ስጠራ እጠግባለውና
አበው ሊቃውንቱ በአንቺ ይመካሉ
እመ አምላክ እያሉ ስምሽን ይጠራሉ
አዝ =
ከገሃነም አውጭኝ ከዚያ ነበልባል
ከሲዖል ወድቄ እንዳልቃጠል
ያ የስቃይ ሃገር ባህሩ ያሰጥመኛል
አንቺ ከለመንሽው ልጅሽ ያዝንልኛል
አዝ =
ወገን አታድርጊኝ ከሲዖል ከተማ
መድረሻ ያሳጣኝ የእሳቱ ጨልማ
አወድሳሸለው በኤፍሬም ውዳሴ
ሁኝልኝ ጠበቃ አደራ ለነፍሴ
አዝ =
እኔስ እፈራለው ምግባሬን ሳየው
ደካማው እምነቴ እየለየኝ ነው
አልረሳሽም ድንግል እማጸንሻለው
አማላጅነትሸ መድኅን ነው አውቃለው

ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ


    ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

💚  @yeorthodoxmezmur  💚
💛  @yeorthodoxmezmur  💛
❤️  @yeorthodoxmezmur  ❤️

    ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Audio
የልደት መዝሙር ስብስብ ||Yeldet mezmure sebeseb
Audio
የገና መዝሙራት | የጌታ ልደት እና ጥምቀት መዝሙር - Ethiopian Orthodox Genna Mezmurs
Audio
የገና /ልደት በዓል መዝሙሮች ስብስብ - Gena / Lidet Ethiopian Orthodox Mezmur New recommended
https://youtu.be/a7rdN5OQloY?si=UrMjtxdUuWP5tGlv

ለመንግሥትከ ሰፋኒት/አዲስ የልደት መዝሙር/

ለመንግሥትከ ሰፋኒት እንዘ ይትመሐለሉ ዓውዳ /2/
ኧኸ ሰብአ ሰገል /2/ አወፈዩ ጋዳ /2/

ድንቅ ዜና ሰምተው እረኞች ዘመሩ
ፍቅር ስለሳበው ወልድን ከመንበሩ
ጽድቅ ከሰላም  በአንድ ተባበሩ።

አዝማች  ኧኸ ሰብአ ሰገል /2/ አወፈዩ ጋዳ /2/

የሰማይ መልአክ ሲናገር ልደቱን
ወርቅ ገበሩለት ከርቤና ዕጣኑን
አልፋ እና ኦሜጋ ለጸናው መንግስቱ

አዝማች      ኧኸ ሰብአ ሰገል /2/ አወፈዩ ጋዳ /2/

በጨርቅ ተጠቅልሎ የሠራዊት ጌታ
ሲወለድ በበረት በታላቅ ደስታ
እንደ ሰብአ ሰገል በመያዝ ስጦታ
እኛን ለወደደን እንዘምር በእልልታ

አዝማች  ኧኸ ሰብአ ሰገል /2/ አወፈዩ ጋዳ /2/

ለመንግሥትከ ሰፋኒት እንዘ ይትመሐለሉ ዐውዳ /2/
      ኧኸ ሰብአ ሰገል /2/ አወፈዩ ጋዳ /2/
2024/05/29 04:40:22
Back to Top
HTML Embed Code: