Telegram Web Link
ተወደዳቹ የዚህ ቻናል ተከታታዮች ለብዙ ጊዜ በአንዳንድ ችግር ምክኒያት ፖሰት ማድረግ አልቻልንም ነበር ለዛም ትልቅ ይቅርታን እንጠይቃለን አሁን በአዲስ መልክ ለእናንተ ይጠቅማል የምንለውን ሁሉ ልናቀርብላቹ ዝግጅታችንን ጨርሰናል የተለያዩ መጽሀፍት audio & pd f አስተማሪ ታሪኮች ተከታታይ ልብ ወለድ ግጥም በቀን 1 ፖስት ይኖረናል ስለምትከታተሉን እናመሰግናለን ፖስቱ ከዛሬ 2፡30 ጀምሮ ይጀምራል ለጓደኞቻቹ ሼር በማረግ ይተባበሩን
ለእናቴ



ሚስጥር ነው ሴትነት
እምቅ ሐያልነት ጥልቅ ረቂቅነት
በኅልዮ መዳፍ ወይ በገቢር ጥፍር
ደርሰው የማይነኩት ችሎ ማይቧጨር
የብርሐን ወስፌ የማለዳ ጨረር
ረቂቅ ምንጭነት የህይወት ዳና በር
ሴትነት ሐይል ነው ወሰንየለሽ ድንበር

አይኔን ያነቃሁ ለት
የተነፈስኩ እለት
ተማም ገጿን ያየሁ ክንፍ አልባ መልአክ
ያቺ ሴት በኔ አለም ሁለተኛ አምላክ

ጫንቃ ትከሻዋ በሸክም የማይጎዝል
ጫማ አልቦ እግሯ በህማም የማይዝል
ሴት ማለት ፣
የአፍታ ሽረት ናት ለዘለዓለም ቁስል ።

ህይወት አሸክማኝ ፥መከራና ደስታን፥እኩል እንደ አክርማ፤
ደስታውን ለኔ አርገሽ፥ እንባ መከራዬ፥ ባንቺ እየተቀማ።
አንቺ የምህረት ርስት ፥አንቺ የበረከት ጠል
አንቺ የስጦታ ምድር ፥ አንቺ የእምነት ጠለል
አንቺ የወይራ በትር ፥ አንቺ የወገን ኩራት
አንቺ ለጨለመ ዓለም፥ አንቺ የፋኖስ መብራት።


ለቡከን እግሬ መራመድ፥ እንዳይጠለፍ በእክል
እጄን ይዞ ያስቆጠረኝ ፥ጀግና ልብሽ ነው ትክክል።

ዝሁል አካልሽን ፥ለግፍ ባይለውም
ሰው ዝንጉ ፍጡር ነው፤
የፍጥረቱ ጌታ በቃሉ ያዘዘውን፥ በጀኝ አይለውም።

በሾተል አንደበት ፣በተርቡት ሰው ምላስ
አይተረተርም የልብሽ ጣቃነት፣
አለት ያንቺ መንፈስ።

ሴት እመ ብልሃት የዘዴ እናት አባቱ
ጥንትም መላ ካንቺ ነው ምንጩ ስር መሰረቱ

ብልሐትን እንደ ጠገራ፣ አገር ካንቺ ተውሶ
ለጠላት ሾህ የሆንበት ፣መሪር ልክ እንደ ኮሶ

በሽሮ በቆሎ ብቻ ፥ፋሲካ የምትደግሺ
በእፍኝሽ በያዝሽው ጥሬ፥ አገር የምትመልሺ።
በመናኛ በእራፊ ፥ገመና የምትሸፍኚ፥አገር የምታለብሺ
ሴት ማለት አንቺ ነሽ በቃ ሎሌ የምታነግሺ።



✍️©እስራኤል


📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
"...እውነት ለመናገር አጓጉል ትምክህቴ ሲሟሽሽ ሀሳቤም ሲቀየር ይታወቀኝ ነበር። ለዚህ ደግሞ ያጋለጠኝ የመጣሁበት ሽምደዳ ላይ ያተኮረ ተግባር የሌለው የትምህርት ሥርዓት እንደሆነ ይሠማኛል፡፡

ግብርና ተምረን ገጠርና ጭቃ የምንጠየፍ፣ እንስሳት ሳይንስ ተምረን ዶሮ የምንጠላ፣ አዛባ የምንጠየፍ፣ መካኒካል ኢንጅነሪንግ ተምረን ግሪስ የምንጠየፍ ሆነናል።

እንደውነቱ ግን ሕግ ተምረን ጭቅጭቅ ከጠላን፣ ሕክምና ተምረን በሽተኛን ከተሰቀቅን ሙያው ስሙ እንጅ ተግባሩ ውስጥ የሌለን መሆኑን ያመለክታል።"

ከመፅሐፉ የተወሰደ

#ችቦ
Dr. Alemayehu Wassie

ይህ በዶክተር አለማየሁ ዋሴ የተፃፈው መፅሐፍ በቅርፅ ከዚህ በፊት ከታተመው ሰበዝ ከተሰኘ መፅሐፉ ጋር ተመሳሳይ ነው።
ደራሲው ሰበዝ 2 ብዬ ያላወጣሁት ከሰበዝ የቀጠሉ ታሪኮች ስለሌሉ ነው ብሎናል።
መልካም ንባብ!

@yetebeb
For job seeker's
Contact us on
👉👉👉@ti_63
@ti_63
@ti_63
እንደንቦቹ!

"ንቦች ከቆሻሻ ይልቅ ማር ይሻላል ብለው ለዝንቦች በማብራራት ጊዜያቸውን አያጠፉም" (ካልታወቀ ምንጭ)

እንደ ንቦቹ ዝም ብላችሁ ዓላማችሁ ላይ አተኩሩ!

@yetbeb
" በሺህ የሚቆጠሩ ሻማዎች
በአንድ ሻማ ሊለኮሱ ይችላሉ ያ በመሆኑም የሻማው እድሜ አያጥርም...
የኛን ደስታ ለሰው
በማካፈላችንም የኛ ደስታ አይቀንስም "

ጉታማ ቡድሃ

@yetbeb
Forwarded from Dr. Eyob Mamo
ለምን የሰው ባሪያ እንደሆነክ!


በውስጥህ ያለው ጥማት ነው የሰው ባሪያ የሚያደርግህ፡፡

• ተቀባይነት የማግኘት ጥማት ሁሉን ሰው አስደሳች የመሆን ባሪያ ያደርግሃል፡፡
• የፍቅር ጥማት በፍቅር ሽፋን የግል መጠቀሚያ የሚያደርግህ ሰው ባሪያ ያደርግሃል፡፡
• የስኬት ጥማት የማይሞላ ተስፋ ሰጪ ሰዎች ባሪያ ያደርግሃል፡፡
• ትኩረት የማግኘት ጥማት የተለማመጡኝ ባይ ሰዎች ባሪያ ያደርግሃል፡፡

ከእነዚህና እነዚህን ከሚመስሉ ፈጽመው ሊያረኩ ከማይችሉ ነገሮች ውጪ መኖር እንደምትችል ራስህን አሳምነህና አስለምደህ ቀና ብል መኖር እስካልለመድክ ድረስ ከሰዎች ባርነት ነጻ ልትሆን አትችልም፡፡ ከሰዎች ባርነት ነጻ እስካልወጣህ ድረስ ደግሞ እንደዞረብህና እንደተዘባረቀብህ ትኖራለህ፡፡


ዛሬ የውሳኔ ቀን ይሁንልህ!


መልካም እንቅልፍ!
😓 #ንነጽር_፺፫

እኔ የከፋኹ ነኝ እኮ!

38 ዓመታት በበሽታ እየማቀቀ በበዛው ምሕረትህ፣ በሰፋው ፍቅርህ፣ በበረታው ክንድህ ያለ ድካምና ያለ ስስት አዳንኸው። ያዳንኸው እሱ አንተን ማመስገንና ዘለዓለም ለአንተና በአንተ መኖር ሲገባው ስለ አዳኝነትህ ጥፊን ሸለመህ።

ጌታ ሆይ አንድ ጊዜ ብቻ ነበር አይደል እጁን የዘረጋብህ? ምን አልባት ይሄ ሰው አንድ ቀን ተጸጸቶ ቢያለቅስ ይበቃው ይሆናል። ነገር ግን አምላኬ እኔ ስንት ቀናቶችን ባለቅስ ነው ለበደሌ ደመወዝ የሚሆነኝ? ስንት ቀናትን ላንባ? ስንት ሌሊታትን እንቅልፍ ልጣ? ስንት ስንት? እኮ ስንት ዓመታትን ልጸጸት?

በአካል አግኝቼ በጥፊ ባልመታህም፤ የጸሎቴን ምላሽ ስታዘገይብኝ እኮ በምናብ ስዬ ደጋግሜ መትቼሃለው።
በአካል አግኝቼ ባልዘባበትብህም፤ ያው ትሰማለህ ብዬ እኮ ስድብን ሸልሜሃለው።
ክርስቶስ ሆይ! ደግሜ ደጋግሜ እኮ እጅ በሌለው ምላሴ መትቼሃለው።

ታድያ ስንት ዘመናት ብጸጸት ይበቃኛል? መሐሪ ነህ አውቃለው ዕድሜ ልክህን እየተጸጸትኽ ኑር አትለኝም። ወደ አንተ የመምጫ ጊዜዬ ሊደርስ ሲል ድጋሚ እንዳልመታህ እባክህን የመመለሻ ጊዜ ስጠኝ?😓

ምንም እንኳ ስሜ
#መጻጕዕ ባይሆንም #ከመጻጕዕ የከፋሁ #የመጻጕዕ ቀዳሚ #መጻጕዕ መሆኔን አልዘነጋም!

         🌘Dn Mekuriya Murashe


📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
@yetbeb
ከመቀመጥ መሞከር ...

አንዳንዴ ብዙ ነገር እንሞክርና ይሰለቸናል ያን ሞከርኩ አልተሳካም ይሄን ሞከርኩ አልተሳካም ብለን መሞከር ያስጠላናል።

እኛ እንዲ ባንል እንኳን ቤተሰብና ጓደኛ አንተ ምንድነው ያንን ሞከርክ አልሆነም  ይሄን ሞከርክ አልሆነም እንደገና ደግሞ ይሄን ልትጀምር ?? ብለው ደግመን እንዳንሞክር ያሸማቅቁናል።

በል ተነሱ! አሁን ጀምሩ ከመቀመጥ ምንም የምናገኘው ነገር የለም እንኳን ተስፋ ቆርጠን ተቀምጠን ሰርተንም መለወጥ ከባድ ነው። ከመቀመጥ ደግሞ መሞከር እጅግ ይሻላል!

ደግመህ ሞክር ፣ ደግመሽ ሞክሪ!
የኢትዮጵያ ስልጣኔ - ከበላይ ግደይ.pdf
9.1 MB
የተወደደው የኢትዮጵያ ስልጣኔ የተሰኘው መጽሀፍን ይዘንላቹ መጥተናል @yetbeb
2024/05/16 20:27:19
Back to Top
HTML Embed Code: