Telegram Web Link
የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ .pdf
16.8 MB
📚ርዕስ:- የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ
📝ደራሲ:- ዶ/ር እዮብ ማሞ
📜ዘውግ:- ሳይኮሎጆ
📅ዓ.ም:- 2012
📖የገፅ ብዛት:- 152
@yetbeb
አልኬሚስቱ..pdf
27.8 MB
ልቦለድ በሚመስል ታሪክ ውስጥ የሰውን ንጹህ ፍላጎት እጣ ፋንታና ለስኬትና ለህልሙ የሚያደርገውን ጉዞ ቁልጭ አርጎ የሚያሳይ ብዙዎች ይሄንን አንብበው እንደተተቀየሩ የመሰከሩለት ጥሩ መጽሀፍ ነው ይነበብ
💥ፅናት💥

💫በስንፍና ወይም በፍርሃት ፣በተፈጥሯዊ ተግዳሮት ወይም በሰው ሰራሽ ፈተና ሳንበገር በእውቀታችን መሠረት ተግባራችንን የመምራት ፅናት ማዳበር ይገባል።

💫ለእውነታ ታማኝ የመሆን አስተዋይነት ያስፈልገናል።

💫እውነታ ላይ ተመስርተህ እውቀት መገንባት ፣ በእውቀት ላይ ተመስርተህ መምረጥና መወሰን፣ በውሳኔህ ላይ ተመስርተህ መፈፀም ከተጨባጭ ተግባር አንፃር ለእውነታ ታማኝ መሆን ነው ።

💫ድርጊትና ተግባር የእውነታ ውጤት ነው።


ሰላም ዋሉ

"መልካምነት ከሁሉም በላይ ነው።"
@yetbeb
#ታንኮራፊያለሽ!

አንድ ሰው  የሚስቱ ማንኮራፋት ይረብሻቸዋል። እና ሁሌ "በጣም ስለምታንኮራፊ ልተኛ አልቻልኩም " ይላታል። እሷም አታምነውም ነበር ። ከዛም አንድ ቀን ስታንኮራፋ  ሪከርድ አረጋት ። በማግስቱ ግን ድጋሜ  ከእንቅልፏ አልተነሳችም።

እና ከዛን ቀን ጀምሮ እንቅልፍ እንቢ ሲለው ያንን ሪከርድ ደጋግሞ ይሰማዋል ። አንዳንዴ የሚያስጠሉን ወይም የሰለቹን ነገሮች ሊናፍቁን ይችላሉ።

እናንተ የምትሰሩበት ቢሮ ዛሬ ብትሞቱ ከሶስት ቀን በኋላ የስራ ማስታወቂያ ይለጠፋል። የሚወዷችሁ ሰዎች ግን በህይወት እስካሉ እናተን ያስታውሳሉ ።

እስኪ ዛሬ ከሚወዷችሁ ሰዎች ጋር  ግዜያችሁን አሳልፉ ። ደውሉላቸው ፍቅር ስጧቸው 
@yetbeb
አትሸፋፍኑት! ይገለጥ !!

Do not resist pain! Allow it to be there !
Ekhart Tolle


ህመምና ጉዳትህን አትቃወም ፤ ይኖር ዘንድ ፍቀድለት እንጂ!

ኤካርት ቶሌ

      ሕይወታችን እኛ ባሰብነውና በተመኘነው ልክ ሁሌም አትሄድም ። ደስ ይል  ነበር እኮ ምኞታችን ሁሉ ቢሰምር ፤ ያቀድነው ሁሉ ቢሳካ ፤ ውጥናችን ቢተገበር ፤ የወደድነውን ብናገባ ፤ በመረጥንበት ብንኖር ፤ የተማርነውን ብንተገብር ፤ ትምህርታችንን በማዕረግ ብንደመድም ፤ የፈለግነውን ሁሌም ብንከውን።

      በሕይወት ሁሌ መስከረም የለም ሐምሌና ነሐሴም ጭምር እንጂ ካሰብነው በተቃራኒው ልንኖር ፤ የከፈትነው ሊከስር ፤ የወደድነውን ልንድር ፤ የተመኘነውን ላንኖር ፤ የተማመንበት ላይኖር ፤ የተመረኮዝነው ሊሰበር ፤ ፈጽሞ ያልጠበቅነው ሊከሰት  ውጥናችን ላይሰምር ፤ ሀሳባችን ላይከወን ፤ አካላችን ሊጎድል ፤ ጤናችን ሊታወክ.... ይችላል። ይሄን ሁሉ ታዲያ እንደኮሶ ባይጥመንም ለመሻር የግዳችንን መቀበል እና መጎንጨት አለብን!!

     መታመም ደስ ባይልም ፤ መጎዳት ቢያስከፋም ፤ መክሰር ቅስም ቢሰብርም ፤ መውረድ አንገት ቢያስደፋም ፤ መከዳት አቅል ቢያስትም ፤ ማጣት ቢያስጠላም ፤ መናቅ ቢያምምምምምም ..... ያለን ብቸኛ አማራጭ መታገል ሳይሆን እንዲሆን መፍቀድ ነው። በቃ የሆነው ሁሉ ሊሆን ግድ ነው! ያለን አማራጭ መቀበልና አብሮ ከክስተቱ ጋር መኖር ብቻ ነው!


   ራሳችሁን ታዘቡ እስቲ ምን ያህል ከእውነታው እንደምንጣላ ፤ የቱን ያህል ስሜታችንን እንደምናፍነው ። ሌላው ቢቀር በቅጡ ለማልቀስ እንኳ እኮ ያልታደልን ነን 'እንዴት እኔ? ሰው ምን ይለኛል? ለማን ደስ ይበለው? ወንድ ልጅ አያለቅስም '.... እያልን በጊዜው ሊወገድ የሚገባው ሀዘን ፤ ቁጣና ብስጭት በራሳችን ላይ ግዙፍ አለት ሆኖ እስኪደድርና  ማንነታችን እስኪሆን እናደርሰዋለን። ይሄ ግን አይጠቅምም!

ሁሉም ነገር በጊዜና ወቅቱን ጠብቆ ሲሆን ደስ ይላል ። ለምን ሆነ ብለን የሆነውን ነገር ከምንቃወም መቀበልና የሚሰማን ስሜት እንዲወጣ ማድረጉ ፍቱን ነው!

🎀 በቸር ያቆየን!!🎀
@yetbeb
እባካችሁ!

• የምታወሩት መልካም ነገር ከሌላችሁ፣ እባካችሁ ቢያንስ ክፉ ነገር ከማውራት ዝም በሉ!

• የመለገስ ፍላጎቱ ከሌላችሁ፣ እባካችሁ ቢያንስ የሰውን አትውሰዱ!

• የምትገነቡት ነገር ከሌላችሁ፣ እባካችሁ ቢያንስ ሰዎች የገነቡትን አታፍርሱ!

• የምትጀምሩት አዲስ ነገር ከሌላችሁ፣ እባካችሁ ቢያንስ ሰዎች የጀመሩትን ነገር አታደናቅፉ!

• የምታደንቁት ሰው ከሌላችሁ፣ እባካችሁ ቢያንስ ሰዎችን አታንቋሹ!

• ከሰዎች ጋር ለአንድ ዓላማ የመተባበር ፍላጎቱ ከሌላችሁ፣ እባካችሁ ቢያንስ የሰዎችን አንድነት አታውኩ!

ፈጣሪ የሰላም ሰው ያድርገን!

@yetbeb
የእግዚአብሔር ጥበቃ !

ትላንትና ማታ ቤተክርስትያን ቁጭ ብለን አባትና ልጅ አጠገባችን መጥተዉ ገና ቁጭ እንዳሉ ልጅ አባቷ እቅፍ ዉስጥ ሆና “አባዬ ወክ እንዉጣ” እያለች ታስቸግራለች

አባት ማስቸገሯን መቀጠሏ ስለረበሸዉ እዛዉ አካባቢ እንድትንቀሳቀስ ይለቃታል ልጅ ገና ከመለቀቋ ፊት ለፊቷ ወዳገኘችው መንገድ ሩጫዋን ቀጠለች

ይሄንን ያየ አባት ልጁ ሳታየዉ ከኃላዋ ይከተላት ጀመረ እንዳትወድቅበት ሊይዛት ፣ እንዳትጠፋ ሊጠብቃት ፣ ፍላጐቷን ሳይነፍጋት እንድትራመድ ፈቅዶ እያደረግኩልሽ ነዉ ሳይል በሚችለዉ ሁሉ አለላት

በጣም ርቃ ባይደርስባት እንኳን ፊት ለፊቷ ያሉትን ሰዎች ያዙልኝ ይላል እንጂ ተስፋ ቆርጦ አይተዋትም

ታድያ የፈጠረን ለእኛ ሲል ራሱን መስዋዕት ያደረገልን የሰማዩ አባታችን እማ እንዴት እየጠበቀን ይሆን ?

እንኳን አደረሳችሁ !

ስላልተዉከን ተመስገን 🙏
@yetbeb
2024/05/16 05:13:45
Back to Top
HTML Embed Code: