Warning: mkdir(): Permission denied in /var/www/bootg/function.php on line 101

Warning: file_put_contents(aCache/detail/y/e/t/e/yetenantun_lenege.txt): Failed to open stream: Permission denied in /var/www/bootg/function.php on line 103
ማዕዶት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ - Telegram Web
ሥራ ላይ ነኝ !!
*~★~*

• ይህችንም በየፌስቡካችሁ #SHARE በማድረግ ለእነ እንቶኔ ንገሩልኝማ። ኣ?

#ETHIOPIA | ~ እኔማ እኔ ዘመዴ እንደ ንሥር ታድሼ፣ እንደ ነብር ተምዘግዝጌ፣ እንደ ዝሆን ገዝፌ፣ እንደ አንበሳ እያገሳሁ እንደ ዘንዶ ያረጀ ቆዳዬን በአዲስ አብረቅራቂ ጠንካራ ስድብ በማይበሳው ቆዳ ቀይሬ ከች ልል ነኝ። ለወዳጆቼ፣ ለጓደኞቼ፣ ለተዋሕዶ ልጆችማ የመሸነፍ፣ የእጅ መስጠት ምሳሌና ምልክትማ አልሆናትም።

•••
ይኸውላችሁ የአየር ሰዓቱን በነፃ እጠቀምበት ከሰጠኝ አንድ የቴሌቭዥን ጣቢያ ጋር የውል ስምምነት እንፈጽም ዘንድ ድርጅቱ ሕጋዊ የውል ስምምነት መፈረሚያ ቅጽ ልኮልኝ እሱን እያየሁት እያሳየሁትም ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው። በእውነት የቴሌቭዥን ጣቢያው ዋና ሥራ አስኪያጅና በመሃል እንደ ድልድይ ያገለገለኝ ወዳጄ ላሳዩኝ ከመጠን በላይና ለበዛው ደግነታቸው ምስጋናዬ እጅግ የበዛ ነው። ቃላቶችም ያጥሩኛል።

•••
የተዘጉት የፌስቡክና የዩቲዩብ ቻናሎቼ እስኪከፈቱ፣ የራሴንም የሳታላይት ቴሌቭዥን ጣቢያ እስካቋቁም ድረስ በሚልየን የሚቆጠሩ አድማጭ ተመልካቾች ባሉት በራሱ በቴሌቭዥን ጣቢያው የፌስቡክና የዩቱዩብ ቻናሎችም እጠቀም ዘንድ የቴሌቪዥን ጣቢያውን የዩቲዩብ ቻናል ፓስወርዱን ሰጥተውኝ እንጎራደደብት ዘንድም ቃላቸውንም ፈቃዳቸውንም ሰጥተውኛል በግል ህይወቴም ቢሆን መራብ መጠማትም እንደሌለብኝ ነገረው በሥራዬ መጠን በወዜ ላቤን ጠፍ አድርጌ ከሚገኘውና ሲስተሙ ከሚከፍለው የድርሻዬን ይሰጡኝ ዘንድ እንደሚገባም በውል ወረቀቱ ላይ አስፍረዋል። ወደ ጀርመኖች የእርዳታ ሲስተም አልመለስም ማለት ነው። አሁን የሚቀረው እኔ ውሉን ከመፈረሜ በፊት “ ዘመዴ አስሬ ለካ አንዴ ቁረጥ ” በሚለው መርሄ መሰረት የሕግ ባለሙያ ጓደኞቼ የስምምነት ውሉን በሕግ ዓይን እንዲያዩት በማድርግ አረንጓዴ የይለፍ መብራት እንዲያበሩልኝ ማድረጉ ብቻ ነው የሚቀረኝ። ጌዲ ደውል። አያሌው ወዴት ነህ? ሰምታችኋል።

•••
ከዚያማ ምኑ ይጠየቃል። እኔ ዘመዴ በየቤታችሁ፣ በየቴሌብጅናችሁ መስኮት ብቅ ብዬ መንበጫበጭ ብቻ ነው። በዩቱዩብና በፌስቡክ፣ በእጅ ስልኮቻችሁም፣ በላፕቶፕ፣ በአይፓድና በየኮምፒዩተሮቻችሁ ከተፍ እያልኩ አንደ አማኝ ስለ ሃይማኖቴ፣ እንደ ዜጋም ስለ ሃገሬ የጀመርነውን ነጭ ነጯን የመነጋገር ጉዳይ አጠንክረን እንገፋበታለን ማለት ነው። እየሆነ ያለው እንግዲህ እንዲህ ነው። አከተመ።

•••
የአየር ሰዓቴም እንደተለመደው በተለመደው ሰዓት እንዲሆን ከተለቢጅን ጣቢያው ጋር እደራደራለሁ። ሊያሳድገኝ የመጣውን የቴሌቭዥን ጣቢያ፣ በዚህ በመከራ፣ በጭንቅ ሰዓት ከጎኔ የቆመውን የቴሌቭዥን ጣቢያም እኔም ጓደኞቼን አስተባብሬ በጎደለው ሁሉ በመሙላት አብሬው እቆማለሁ ማለት ነው። አከተመ።

•••
አጅሬ ሰይጣን 2 በሮችን ገርበብ አድርጎ ቢዘጋብኝም የእኛ አምላክ የሰይጣንም ፈጣሪ ልዑል እግዚአብሔር ደግሞ 9999 ያልተዘጉ በሮችን ብርግድ፣ ወለል አድርጎ ከፍቶ ይኸው ተጠቀምበት ብሎ አሳየኛ። አሁን ዋይፋይ ፍለጋ መንከራተት የለም። ሰዓት ጠብቀን በየቤታችሁ በተለብጅን መስኮት እንገናኛለን። ምን ይሳነዋል የእኛ ጌታ? ምንም።

•••
"እኔ ግን እላለሁ! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት፣ ቅድስት፣ ርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜ ትርሳኝ። ትክዳኝም። ባላስብሽና ባልሟገትልሽ ባልሞትልሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ። ሳለጎበድድና ሳለከዳሽ እንድኖርም አምላክሽ ይርዳኝ። ይህን ባላደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ።

•••
" ጌታ ሆይ ! ከዚህ በፊት በሆነው፤ አሁንም እየሆነ ባለው እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ።" አሜን።

"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ"

¶ ድልና ትንሣኤ ለኢትዮጵያ ሀገሬና ለተዋሕዶ ሃይማኖታችን ! ውድቀትና ጥፋት፤ ለሁለቱም ጠላቶች። አራት ነጥብ።

• ይህንንም ራሴው በእጄ ጻፍኩት። +49 1521 5070996 ደግሞ የቴሌግራም፣ የቫይበር፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው።

•••

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ጥቅምት 9/2013 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
ፍጻሜው እንዲያምር
ጸ ል ዩ ኝ
*~★★~*

• ሸሩን እንተውና #SHARE እናድርገው።

#ETHIOPIA | ~ እየመጣን ነው።

•••
ዛሬ ማታ በእኔና በቴሌቭዥን ጣቢያው መካከል የመጨረሻው ድርድር ይካሄድና ፊርማዬን ዕድሉን ላመቻቸልኝ የቴሌቭዥን ጣቢያ አኖራለሁ። ጣቢያው የሰጠኝን ነፃነት እኔ ራሴ ለራሴ የሰጠሁት አይመስለኝም። በዩቱይብ አደርግ እንደነበረው በዚያው መንገድ በራስህ እይታ ህልምህን ኑረው ነው ያለኝ የቴሌቭዥን ጣቢያው። ከዚያ ጥቂት የቴክኒክ ስልጠና ይሰጠኝና በቀጥታ ወደ አየር ላይ እወጣለሁ። የቴሌቭዥን ጣቢያውንም ስምና የሚገኝበትን ፍሪኴንሲ ጭምር እነግራችሁና የሳታላይት መቀበያ ዲሻችሁን ታስተካክላላችሁ። የፌስቡክ ገጹም፣ የዩቱዩብ ቻናሉም መርሃ ግብሬን ያሰራጫሉ። ለማንኛውም በሁሉም ጉዳይ እግዚአብሔር ይጨመርበት። አሜን።

•••
በሌላ በኩል ምስጋና ለተዋሕዶ ልጆች፣ ምስጋና ለወንድም ጓደኞቼ ይግባቸውና በፈረንጆቹ የዩቱዩብ ቻናል እንዳልጠቀም ብከለከልም የእኛዎቹ የአይቲ ባለሙያዎች #ዘመዴTUBE የሚል ራሱ ያን ዩቱዩብን የሚተካ የዩቲዩብ ቻናል ገንብተው ሊያስረክቡኝም ከጫፍ ደርሰዋል። ዛሬ በቪድዮ ኮንፍረንስ አጠቃላይ ሥራውን አይቼውም ወድጄዋለሁ። ቻናሉ በዚህ ሳምንት ለሙከራ አየር ላይ ይውላል። አይደለም ለእኔ ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ በባለቤትነት የሚጠቀሙት፣ እያሻሻልን የምናሳድገው ቻናልም ይሆናል። አይደለም ቻናል አክሱም ላሊበላን የገነቡ የአባቶቻችን ልጆች እኮ ነን። ስለዚህም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን። ፍጻሜውም ይመር። አሜን።

•••
ሌላም ያልተሰሙ ገና በመንገድ ላይ ያሉ ብዙ የምሥራቾችም አሉ። የራሴ የቴሌቭዥን ጣቢያ ምሥረታም መንገድ ላይ ነው። 11 ኮሚቴዎች ያሉት የቦርድ አባላት መረጣም አልቋል። ቦርዱም የመጀመሪያውን ስብሰባውን ባለፈው ሰኞ ዕለት አካሂዷል። ቀጣይ ሥራም በፍጥነት ተሠርቶ ወደ ተግባር ይኬድ ዘንድ አቅጣጫ ተቀምጦ፣ ወደ ሥራ ለመግባት ኮሚቴ ተመርጦ ለቀጣይ ቀጠሮ ቀጠሮ ተይዞ በደስታ ተለያይተናል።

•••
እናም ምን ለማለት ፈልጌነው መሰላችሁ። ባለ ማዕተቦች የሆነ ችግር በገጠማችሁ ጊዜ እጅ እንዳትሰጡ፣ አትቆዝሙ፣ ተንቀሳቀሱ። ሰይጣን አንድ በር ቢዘጋባችሁ ሰይጣን በዘጋባችሁ በራፍ ላይ ቆማችሁ ስታለቅሱ፣ ስታላዝኑ አትዋሉ። ዞር ዞር ስትሉ እግዚአብሔር 99 ያልተዘጉ በራፎች ከፍቶ ይጠብቃችኋል። ሁሌ ስለ ከፍታ አስቡ። በራብ በጥማት ውስጥ ጥጋብ ደስታ ሊመጣ እንደሚችል አስባችሁ ተንቀሳቀሱ። በህመማ ችሁ ወቅት ድህነት ጤና እንደሚመጣ አስባችሁ በተስፋ ተሞልታችሁ ተንቀሳቀሱ፣ በፍፁም ጨለማውም ይሄዳል፣ ኃዘኑም ያልፋል፣ ማጣት በማግኘት ይተካል። ተንቀሳቀሱ። ተስፋ አትቁረጡ። ከፍ ብላችሁም ብረሩ። ምክሬ ነው።

•••
"እኔ ግን እላለሁ! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ እናትዓለም፤ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ የቅድስት ክርስቶስ ሠምራና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት፣ ቅድስት፣ ርትዕት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜ ትርሳኝ። ትክዳኝም። ባላስብሽና ባልሟገትልሽ ባልሞትልሽም ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ። ሳለጎበድድና ሳለከዳሽ እንድኖርም አምላክሽ ይርዳኝ። ይህን ባላደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ።

"ጌታ ሆይ! ከዚህ በፊት በሆነው፤ አሁንም እየሆነ ባለው እና ወደፊትም በሚሆነው ነገር ፤ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ።" አሜን።

"ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ"

¶ ድልና ትንሣኤ ለኢትዮጵያ ሀገሬና ለተዋሕዶ ሃይማኖታችን ! ውድቀትና ጥፋት፤ ለሁለቱም ጠላቶች። አራት ነጥብ።

•••

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ጥቅምት 11/2013 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
አይቻልም ብሎ ነገር የለም። በእግዚአብሔር የማይቻል ነገር የለም። ያውም ባለ ማዕተብ ሆነህማ በፍፁም እጅ መስጠትን እንዳታስበው።
ሰበር መረጃ
.......................
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በምሥጢር እየተካሄደ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ በትናንትናው ዕለት ጉባኤውን ጨርሶ መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር የተፈጠረውን ቅራኔ ለመፍታት ዛሬ ጠዋት ምልአተ ጉባኤውን አስቀጥሏል። ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጋር በተያያዘ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በጋዜጣዊ መግለጫው ሳይገኙ መቅረታቸው ይታወቃል።

እንደደረሰን ሙሉውን መረጃ የምናቀርብ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን
የኢየሱሰ ክርስቶስ ስሞች ክፍል አንድ

1. ሁሉን ቻይ - “ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፡— አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል። ራዕ1:8

2. አልፋ እና ኦሜጋ - “እኔ አልፋና ኦሜጋ ፣ ፊተኛውና መጨረሻው ፣ መጀመሪያ እና መጨረሻው እኔ ነኝ” ራእይ 22:13

3. ኢየሱስ “ እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። ሉቃ 1:31

4. የእምነታችን ፈጻሚ - " የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ ዕብ. 12 2

5. ክንድ - “ “የያዕቆብንና የዮሴፍን ልጆች፥ ሕዝብህን በክንድህ አዳንሃቸው።” መዝሙር 76፥1

6. የሕይወት እንጀራ - “ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።”የሐ 6:35

7. የእግዚአብሔር ልጅ - “እነሆም ፣ ከሰማይ የመጣ ድምፅ“ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው ”አለ። ማቴ. 3:17

8. ሙሽራው - “ኢየሱስም አላቸው- “ ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እስከሆነ ድረስ የሰርጉ ተጋቢዎች ሊያዝኑ ይችላሉን? ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ቀናት ይመጣሉ በዚያን ጊዜም ይጦማሉ ፡፡ ማቴ. 9 15

9. የማዕዘን ራስ - “ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ድንጋይ ሆነ”። መዝ. 118 22

10. አዳኝ - “ ከሙታን ያስነሣውን ልጁን ከሰማይ እስኪመጣ መጠበቅ ፣ ከሚመጣው ቁጣ የሚያድነን ኢየሱስን” 1 ተሰ 1 10

11. ታማኝ እና እውነተኛ - “ሰማይ ሲከፈት አየሁ ከእኔም በፊት ነጭ ፈረስ ነበረ ፣ በላዩም ታማኝ እና እውነተኛ ይባላል። በፍትህ ይፈርዳል እንዲሁም ይከፍላል ፡፡ ” ራእይ 19 11

12. መልካም እረኛ - “እኔ ጥሩ እረኛ ነኝ። መልካሙ እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል ፡፡ ” ዮሐ 10 11

13. ታላቁ ሊቀ ካህናት - “ስለዚህ ፣ እኛ ሰማያትን የሚያልፍ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን ፣ ኑዛዛችንን አጥብቀን እንያዝ ፡፡ ዕብ. 4 14

14. የቤተክርስቲያኗ ራስ - “እናም ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገብቶ በሁሉ ላይ የበላይ አድርጎ ለቤተክርስቲያን ሰጠው።” ኤፌ. 1:22

15. ቅዱስ አገልጋይ - “… እናም ለመፈወስ እጅህን ስትዘረጋ ባሮችህ ባሪያዎችህ በሙሉ ቃልህ እንዲናገሩ ፍቀድላቸው በቅዱስ አገልጋይህም በኢየሱስ ስም ምልክቶች እና ድንቆች ይከናወናሉ ፡፡ ” ሐዋ 4 -30

16. እኔ ነኝ - “ኢየሱስም አላቸው። እውነት እውነት እላችኋለሁ ፣ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ ነበርኩ። ዮሐ 8 58

17. አማኑኤል - “… ወንድ ልጅ ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ፣ ትርጉሙም‹ ከእኛ ጋር እግዚአብሔር ›ማለት ነው ፡ 7 14

18. በቃላት ሊገለጽ የማይችል ስጦታ - “ ለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን ፡፡ 2 ቆሮ. 9 15

19. ፈራጅ - “እርሱ በሕያዋንና በሙታን ላይ ፈራጅ ሆኖ የሾመው እርሱ ነው።” የሐዋርያት ሥራ 10:42

20. የነገሥታት ንጉስ - “እነዚህ በጉን ይወጋሉ ፤ በጉም የጌቶች ጌታ እና የነገሥታት ንጉስ ስለሆነ ድል ይነሣል ፣ ከእነርሱም ጋር ያሉት የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ድል ይነሣሉ። ራእይ 17:14

21. የእግዚአብሔር በግ - “በማግስቱ ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ“ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ”አለ ፡ ዮሐ 1 29

22. የዓለም ብርሃን - “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ፤ የሚከተለኝ ሁሉ በጨለማ አይመላለስም የሕይወት ብርሃን ግን ይኖረዋል” ዮሐ 8 12

23. የይሁዳ አንበሳ - “ከእንግዲህ ወዲህ አታልቅስ; እነሆ ፣ ከይሁዳ ነገድ አንበሳ ፣ የዳዊት ሥር ፣ ጥቅልሉንና ሰባቱን ማኅተሞቹን ይከፍት ዘንድ ድል ነሥቷል ፡፡ ራእይ 5 5

24. የሁሉም ጌታ - “በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አደረገው ፣ ከስምም ሁሉ በላይ የሆነውን ስም ሰጠው ፣ ስለዚህም በሰማይና በምድር ካሉ ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ። ለእግዚአብሔር አብ ክብርም ከምድርም በታች ምላስም ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው። ፊል. 2 9-11

25. ክርስቶስ ቀ- “አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል አንድ መካከለኛ ደግሞ አለ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው ፡፡ 1 ጢሞ. 2 5

26. መሲህ - “መሲሑን አገኘነው” (ማለትም ክርስቶስ) ፡ ዮሃንስ 1:41

27. ኃያል - “በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር አዳኛችሁ ፣ ቤዛህ ፣ የያዕቆብ ኃያል እንደሆንሁ በዚያን ጊዜ ያውቃሉ።” ነው 60 16

28. ነፃ የሚያወጣው - “ስለዚህ ልጁ ነፃ ካወጣችሁ በእውነት ነፃ ትሆናላችሁ” 8:36

29. ተስፋችን - “ ተስፋችን ክርስቶስ ኢየሱስ።” 1 ጢሞ. 1: 1

30. ሰላም - “ሁለቱን ቡድኖች አንድ ያደረገው እርሱም የጠላትን መለያየትን ግንብ ያፈረሰ እርሱ ራሱ ሰላማችን ነውና” ኤፌ. 2 14

31. የነቢይ ነቢይ “ኢየሱስም አላቸው። ነቢይ በትውልድ አገሩ ፣ ከዘመዶቹም ከቤተሰቡም በቀር ክብር አይሰጥም አላቸው። ማርቆስ 6 4

32. ቤዛ - “ እኔን ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም፥
ኢዮብ 19:25

33. ትንሳኤ- “ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት ስለ ኃጢአታችን እንደ ሞተ ፣ እንደ ተቀበረ ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት በሦስተኛው ቀን እንደተነሣ ፡፡ 1 ቆሮ. 15 3-4

34. አለት - “ከተከተላቸው ከመንፈሳዊው ዓለት ጠጥተዋልና ፣ ዓለትም ክርስቶስ ነበር” 1 ቆሮ. 10 4

35. መስዋእትነት - “ይህ ፍቅር ነው ፤ እግዚአብሔርን እንደወደድን አይደለም ፤ እርሱ ግን እኛን እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ አድርጎ ልጁን እንደ ላከ ነው እንጂ። 1 ዮሐንስ 4 10

36. አዳኝ - “ዛሬ በዳዊት ከተማ አዳኝ ተወልዶላችኋልና እርሱም ክርስቶስ ጌታ ነው።” ሉቃስ 2 11

37. የሰው ልጅ - “የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና።” ሉቃስ 19 10

38. የልዑል ልጅ - “እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል። ጌታ እግዚአብሔር የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል። ” ሉቃስ 1 32

39. ከሁሉ በላይ ፈጣሪ - “በሰማያትም በምድርም ሁሉ ፣ የሚታዩ እና የማይታዩ ፣ ዙፋኖች ወይም ገዥዎች ወይም ገዥዎች ወይም ባለሥልጣናት ሁሉም በእርሱ ተፈጥረዋል በእርሱ እና ለእርሱ ሁሉም ነገሮች ተፈጥረዋል ፡ እርሱ ከሁሉ በፊት ነው በእርሱም ነገሮች ሁሉ ተጣመሩ… ” ቆላ 1 16-17

40. ሕይወት - “ኢየሱስም“ እኔ ትንሳኤ እና ህይወት እኔ ነኝ ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞቱም እንኳ በሕይወት ይኖራል ”አላት ፡ ዮሐንስ 11:25

41. በር - “እኔ በሩ ነኝ ፡ ማንም በእኔ በኩል ቢገባ ይድናል ወደ ውስጥም ይወጣል ወደ ውጭም ግጦሽ ያገኛል ፡፡ ዮሐንስ 10: 9

42. መንገድ - “ኢየሱስ መለሰ ፣“ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም ” ዮሐ 14 6

43. ቃል- “በመጀመሪያ ቃል ነበረ ፣ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ፣ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።” ዮሐንስ 1: 1

44. እውነተኛ የወይን ግንድ - “እኔ እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ ፣ የወይኑም ገበሬ አባቴ ነው” ዮሐንስ 15: 1

45.
እውነት - “እናም እውነቱን ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል።” ዮሐ 8

46. ድል ​​አድራጊ - “ድል አድራጊ ለሆንኩ ፣ እኔ ድል እንደሆንኩ እና ከአባቴ ጋር በዙፋኑ ላይ እንደተቀመጥኩ ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ የመቀመጥ መብትን እሰጣለሁ” ራእይ 3:21

47. - ድንቅ መካር፣
48- ኃያል አምላክ ፣
49--_ የዘላለም አባት ፣
50- የሰላም ልዑል - “ለእኛ አንድ ሕፃን ተወልዶልናልና ለእኛ ወንድ ልጅ ተሰጥቶናልና መንግሥቱም በጫንቃው ላይ ይሆናል። እርሱም ድንቅ መካር ፣ ኃያል አምላክ ፣ የዘላለም አባት ፣ የሰላም ልዑል ይባላል። ” ነው ኢሳ 9 6
ለዛሬ ይብቃኝ እቀጥላለሁ

አማኑኤል አምላክ ችርነቱ ምህረቱ አይለየን ፍቅርና ሰላሙን ያድለን አሜን
ጥቅምት 2013 ,
መጋቤ ምስጢር ቡሩክ አሳመረ
ቤተክርስቲያን የሚለዉ ቃል በሶስት ዓይነት ፍች አጠቃቀም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እናገኛለን።


[ #ክፍል_፩ ]

የመጀመሪያዉ ፍች የተወሰነ ቦታን ያመለክታል ሕንጻ ቤተክርስቲያን እንለዋለን። ህነጻ ቤተክርስቲያኑ የእግዚአብሔር መመለኪያ ቤትስለሆነ ክርስቲያኖች ተሰብስበዉ፦

የሚጽልዩበት፣የሚባረኩበት
ሥርዐተ እግዚአብሔርን የሚፈጽሙበት
ሕገ እግዚአብሔርን የሚፈጽሙበት
ሕገ እግዚአብሔር የሚማሩበት
ንስሐ የሚገቡበት ስለሆነ ቤተክርስቲያን ብለን እንጠራዋለን።


እኛ እግዚአብሔር በሕንጻዉ ብቻ ይወስናል አላልንም ነገር ግን የአምልኮቱ ቤት ነዉ አልን እንጂ። ለዚህም እንዲሰራ ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ ተሰጠ እንጂ አንዳችም በራሱ ፍቃድ የሠራ የለም።

«……#የመጻፍ_ቅዱስ_ማስረጃ…… »

፩• በእዉነት እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ነዉ እኔ አላወቅሁትም ነበር አለ።ፈራ፥እንዲህም አለ፦ ይህ ስፍራ እንዴት ያስፈራ ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነዉ እንጂ ሌላ አይደለም ይህም የሰማይ ደጂ ነዉ። [ዘፍ 28፥16]

፪•በመካከላቸዉም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ።እኔ እንደማሳይህ ሁሉ እንደማደሪያዉ ምሳሌ እንደ ዕቃዉም ሁሉ ምሳሌ፥እንዲሁ ሥሩት። [ዘጸ 25፥8 ]

፫•የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማንያ ዓመት በሆነ ጊዜ ፥ሰሎሞን በእስራኤል በነገሠ በአራተኛዉ ዓመት፥ዚፍ በሚባለዉ በሁለተኛዉ ወር የእግዚአብሔርን ቤት መስራት ጀመረ። [ 1ኛ ነገ 6፥1 ]

፬•ዳዊትም፦ይህ የእግዚአብሔር ቤት ነዉ፥አለ [1ኛ ዜና 22፥1 ]

፭•ስለዚህ የእግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ወደ ኢየሩስሌም በምሕረት ተመልሻለሁ ቤቴ ይሠራባታል ላይ በኢየሩሳሌም ላይ ገመድ ይዘረጋባታል፥ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦
[ ዘካ 1፥16 ]

፭•ኢየሱስም ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ የተጻፈ አይደለምን? እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኃት አላቸዉ።
[ ማር 11፥17 ]

፮•በመቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠዉ አገኘ፤የገመድም ጅራፍ አበጀ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸዉ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎችንም ገለበጠ፥ርግብ ሻጮችንም ይህ ከዚህ ዉሰዱ፤የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድረጉት አላቸዉ።ደቀ መዛሙርቱም የቤትህ ቅናት ይበላኛል ተብሎ እንደ ተጻፈ አሰቡ። [ ዮሐ 2፥13 ]

፯•በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ ታዉቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፤ቤቱም የእዉነት ዓምድና መሠረት፥የሕያዉ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ነዉ።[1ኛ ጢሞ 3፥15]

፰•በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁዓት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ዻዻሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋዉ ሁሉና ለራሳቹሁ ተጠንቀቁ።[ሐዋ 20፥28]

[ #ክፍል_፪ ]

ሁለተኛዉ የክርስቲያኖች ሕብረት ወይም አንድነት ቤተክርስቲያን ይባላል።

፩•ወንድምህም ቢበድልህ፥……ለቤተክርስቲያን ንገራት ደግሞም ቤተክርስቲያንን ባይሰማት፥እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ። [ ማቴ 18፥7 ]

፪•በዚያን ቀንም በኢየሩሳሌም ባለች ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፣ሁሉም ከሐዋሪያት በቀር ወደ ይሁዳና ሰማሪያ አገሮች ተበተኑ። [ ሐዋ 8፥1 ]

[ #ክፍል_፫ ]

ሶስተኛዉ እያንዳንዱ ግለሰብ ቤተ ክርስቲያን ይባላል።የክርስቲያኖች ሰዉነት በመንፈስ ቅዱስ የተቀደሰ በሥጋዉ ደሙ ተታተመ የክርስቶስ ቤት ነዉ።
« ……#ሐዋሪያዉ_ቅዱስ_ጳዉሎስ ……»
፩•ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖር የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታዉቁምን በዋጋ ተገዝታችኃልና ለራሳችሁ አይደላችሁም በማለት አስተምሯል። [1ኛ ቆሮ 619 ]

፪•ማንም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ የእግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነዉና፥ያዉም እናንተ ናችሁ። [1ኛ ቆሮ 6፥19 ]

፫•ሳወል ግን ቤተ ክርስቲያንን ያፈረሰ ነበር፤ወደ ሁሉም ቤት እየገባ ወንዶችም ሴቶችንም እየጕተተ ወደ ወኂኒ አሳልፎ ይስጥ ነበር። [ሐዋ 8፥3 ]

፬•በቤታቸዉም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።ከእስያ ለክርስቶስ በኰራት ለሆነዉ ለምወደዉ ለአጤኔጦን ሰላምታ አቅርቡልኝ። [ሮሜ 16፥5 ]
🙏🙏🙏⛪️ ዕለተ ዓርብ ⛪️🙏🙏🙏

የስቅለት ቀን፣ መስቀል፣ መሰቀል፣ አሰቃቀል ማለት ነው፡፡ መስቀል በቁሙ መስቀያ፣ መመዘኛ፣ መሰቀያ፣ መንጠልጠያ፣ ለሞት የሚያበቃ መከራ 📙በማር 8፤34 ወጸውዖሙ ለሕዝብ ምስለ አርዳኢሁ ወይቤሎሙ ዘይፈቅድ ይፀመደኒ ይጽልአ ለነፍሱ ወያጥብዕ ወይፁር መስቀል ሞቱ ወይትልወኒ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ሕዝቡን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፡፡ ሊከተለኝ የሚወድ ሰው ራሱን ይካድ፤ ጨክኖም የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ ይላል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በ1ኛ ቆሮ. 1፤17 ላይ ወኢኮነ በጥበበ ነገር ከመ ኢንስዐር መስቀሎ ለክርስቶስ የክርስቶስን መስቀሉን ከንቱ እንዳናደርግ ነገርን በማራቀቅ አይደለም ይላል፡፡
ጌታችን በተሰቀለ ዕለት ከሰድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ፡፡ /ፀሐይ ጨለመ/
እነሆም የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ከሁለት ተቀደደ፤
ምድርም ተናወጠች፤
ዓለቶችም ተሰነጠቁ፤
መቃብሮችም ተከፈቱ፤
ተኝተውም ከነበሩት ቅዱሳን ብዙዎች ተነሱ፤
ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ለብዙዎች ታዩ፡፡
📙ማቴ. 27፤51/

🙏ጌታችን ለዓለሙ ያሰበውን ቤዛነት ሊፈጽም በመስቀል ላይ መሰቀሉ የሚታሰብበት ነውና ለስቀለቱ መታሰቢያ የሚሆን አጎበር ተዘጋጅቶ ከርቤ እየታጠነ ስቅለቱ የሚመለከቱ ምንባባት ሲነበብና ሲሰገድ ይዋላል፡፡
⛪️የሰው ልጅ በሙሉ በእግረ አጋንንት ረግጦ ከፈጣሪው ተጣልቶ ለ5500 ዘመን በጨለማ መኖሩን ለማስታወስም 👉መንበሩ ታቦቱ በዚህ ቀን በጥቁር ልብስ ይሸፈናሉ፡፡ ዲያቆኑም በቤተ ክርስቲያን በመዞር የሚያሰማው የቃጭል ድምፅ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለቅሶ 👉አንድም ዋይ ዋይ እያሉ የተከተሉት የኢየሩሳሌም ሴቶችን ሙሾም ምሳሌ ነው፡፡
📙ሉቃ. 23፤31

🔔📣በዕለተ ዓርብ ነፍሳት ከሲኦል ወጡ፡፡📣
አንቀጸ ገነት ተከፈተልን፣
ርስተ መንግስተ ሰማያት ተመለሰችልን፤
አባታችን አዳምም ከፈጣሪው ጋር ታረቀልን በማለት 👉ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃዶ እያልን የተድላ፣ የደስታ ምልክት ወይም መገለጫ የሆነ ልምላሜ ያለውን ቆጽለ ሆሣዕና ወይም ቄጤማ ግጫ ይዘን የምሥራች እንባባላለን፡፡
📙ኤፌ. 2፤14-15
🔔 ወዘእንበለ ምሳሌሰ ኢተናግሮሙ፣ ያለ ምሳሌ አልተናገረምና እንዳለ
📙ማቴ 13፤34-35
🔔በኖኅ ጊዜም ርግብ ሐጸ ማየ አይኅ፣ ነትገ ማየ አይኅ፣ የጥፋት ውኃ ጎደለ፣ አለቀ እያለች ቈጽለ ዕፀ ዘይት ይዛ ለኖኅ አብስራዋለች፡፡
📙ዘፍ. 8፤8-11
🔔ርግብ የካህናት፣ ኖኅ የምእመናን፣ ኖኅ እጁን ዘርግቶ ርግብን እንደተቀበላት ካህናትም በየመንደሩ እየዞሩ 👉ክርስቶስ ተመረመረ ዲያብሎስ ታሰረ በማለት ቄጤማ ሲያድሉ ምእመናንም እጃቸውን ዘርግተው መቀበላቸው የዚህ ምሳሌ ነው፡፡ ስለዚህ አሁንም ቢገኝ የወይራ ልምላሜ ቢታጣ ግጫን እየታደልን 👉የምሥራች መባባላችን ነፍሳት ከሲኦል ለመውጣቸው መታሰቢያ ነው፡፡ ይህን ቈጽለ ልምላሜ ይዞ ተድላ፣ ደስታ መግለጽ ከጥንት ጀምሮ ሲያያዝ የመጣ ነው እንጂ እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ለዚህ በመጀመሪያዪቱ ቀን ከበጎ እንጨት ፍሬን የሰሌንና የተምር ዛፍ ልምላሜ ይዛችሁ በየዓመቱ ሰባት ቀን ተድላ፣ ደስታ ታደርጋላችሁ ብሏል፡፡
📙ዘሌ. 23፤40-44/

🙏🙏🙏 ዕለተ ዓርብ ነግህ 🙏🙏🙏

⛪️ ዕለተ ዓርብ የአዳምን ነጻነት ለመመለስ 👉የአዳምን ዕዳ በደል አምላካችን የተሸከመበት ዕለት የኀዘን ዕለት የድኅነት ዕለትም ነው፡፡ በዚሁ ዕለት ሁሉም ነገር እንደተለመደው ይከናወናል:: መሪው እዝል ይመራል ሕዝቡ ይከተላል አራቱ ወንጌላት ይነበባሉ፡፡ በየመሀሉ ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት፤ ሲነጋም ሊቃነ ከህናት ተማከሩ የሚለው ዜማ በመሪ በተመሪ በሕዝብ ተሰጥዎ ይከናወናል፡፡ ምንባቡም ስግደቱም ድጓውም እንደ አለፈው ይቀጥላል፡፡

🙏🙏🙏 በሦስት ሰዓት 🙏🙏🙏

⛪️ ሥዕለ ስቅለቱ መስቀሉ ወንጌሉ መብራቱ ጽንሐሑ በመቅደሱ በር ላይ ይዘጋጃል ዲያቆኑ በቃለ ማኅዘኒ በሚያሳዝን ቃል ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ ይላል፡፡ ካህናቱም ምእመናኑም በዜማ እየተቀበሉ ይሰግዳሉ፡፡ ምስባክ ተሰብኮ አራቱ ወንጌላት ይነበባሉ፡፡ በየመሀሉ የሰዓቱ ድጓ ይቃኛል፡፡

🙏🙏🙏 ስድስት ሰዓት 🙏🙏🙏

⛪️ የዕለቱ መሪ እዝል ይመራል፡፡ ሦስቱ ካህናት ጽንሐሑን ይዘው ከርቤ እያጠኑ ዲያቆናት መብራት እያበሩ ለመስቀልከ ንስግድ እያሉ ያዜማሉ ምእመናን ዜማውን እየተቀበሉ ይሰግዳሉ፡ ከዚያም ዲያቆኑ ቀነውኒ እደውየ ወእገርየ የሚለውን ምስባክ ሰብኮ አራቱ ወንጌላት ይነበባሉ በየመሀሉ ድጓው ይዜማል፡፡
ከዚህ ቀጥሎ ምእመናን ይቀመጣሉ ሦስቱ ካህናት 👉ጥቁር ልብስ ለብሰው በሚያሳዝን ዜማ አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ ፤ጌታዬ ሆይ ስለ እኔ ሞትህ ወዮ እኔ ልሙትልህ እያሉ ሦስት ጊዜ ያዜማሉ፡፡ ሕዝቡ ይቀበላል በዚያው አያይዘው ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ እያሉ በዜማ ይጸልያሉ ሕዝቡ ይቆማል ሥርዓተ ስግደቱም ይከናወናል፡፡

🙏🙏🙏 በዘጠኝ ሰዓት 🙏🙏🙏

⛪️ሌላው እንደተለመደው ሆኖ👉 ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ ሦስት ጊዜ ካህናቱ በዜማ ይሉታል ምእመናንም ይቀበላሉ፡፡ ምስባክ ተሰብኮ አራቱ ወንጌላት ይነበባሉ ስግደት እንደተለመደው ነው፡፡ በሦስት ሰዓት፣ በስድስት ሰዓት፣ በዘጠኝ ሰዓት፣ ወንጌላቱ ተነበው እንዳለቁ ለምእመናን ትምህርተ ወንጌል ይሰጣል፡፡ ይህ ግን እንደ ቋሚ ሥርዓት ሳይሆን እንደ ሁኔታው አመቺነት ነው፡፡

🙏🙏🙏 አሥራ አንድ ሰዓት 🙏🙏🙏

⛪️ካህናት በአራቱ መዕዘን ቁመው አራት መቶ እግዚኦታ ያደርሳሉ፤ ዕለቱን የሚመለከቱ መዝሙራት ተመርጠው ይነበባሉ፡፡
🔔 ንሴብሖ እየተባለ ቤተ መቅደሱን በመዞር በከበሮ በጽናጽል በሕማሙ ያዳነን እግዚአብሔር ይመሰገናል፡፡ ዑደት የሚደረገው ሥነ ስቅለቱን በመያዝ ነው፡፡
🔔ምእመናን በሰሙነ ሕማማት የሠሩትን ኃጢአት እየተናዘዙ በካህናት አባቶች ንስሐ ይቀበላሉ፤ 👉በወይራ ቅጠልም ቸብ ቸብ ይደረጋሉ የመከራው ተሳታፊዎች መሆናቸውን ለመግለጥ ነው፡፡
🔔ወይራ ጽኑዕ ነው የተቀበልከው መከራም ጽኑዕ ነው እኛም ይህን መከራ ለመቀበል ዝግጁ ነን ለማለት ነው፡፡ 👉በታዘዙት መሠረትም ሰግደታቸውን ያጠናቅቃሉ፡፡
⛪️ከዚያ በኋላ በካህኑ ኑዛዜ ምእመናን ወደ የቤታቸው ይሰናበታሉ፡፡
🔔መስቀል መሳለም አሁንም የለም ።
🙏የቻለ ከሐሙስ ጀምሮ አሊያም ከዓርብ ማታ ጀምሮ እስከ ዕለተ ትንሣኤው ድረስ ያከፍላል /ይጾማል/ የተጀመረውም በዕለተ ስቅለቱ በሐዋርያትና በእመቤታችን እንደሆነ አበው ያሰተምራሉ፡፡

🙏🙏🙏 አክፍሎት 🙏🙏🙏

⛪️አክፍሎት ማለት፦
🔔 ማካፈል፣ ማጠፍ፣ መደረብ፣ ሁለቱን ቀን አንድ አድርጎ መጾም፣ 👉ጌታ ከተያዘበት እስከተነሣበት ድረስ ይህ ሥርዓት የመጣው በቤተ ክርስቲያናችን ልማድ እመቤታችን፣ ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታን ትንሣኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሣኤ በመቆየታቸው ምክንያት ነው፡፡

https://www.tg-me.com/yetenantun_lenege
“እንደ ጲላጦስ ግራ የገባው ዳኛ አትሁኑ!” (ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ)

የሰሜን ወሎ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ


“እግዚአብሔር አዳም በመበደሉ ምክንያት ከአዳም እስከ ልጆቹ ስንጎሳቆል፣ ችግር ላይ ስንወድቅ ነዉ የፈለገን፤ እኛም እሱን መፈለግ አለብን! ድሃው፣ ስደተኛው፣ የከፋው፣ ርሃብተኛው፣ የታዘረው በዝቷል፡፡ አይዞህ ባይ ይሻል! ፈጣሪን ፈልገን የምናገኘውም በእንደዚህ ዓይነቱ ትሩፋት ነው፡፡ በዓለ ፋሲካውን ከተሰደዱት፣ ከአጡት፣ ጋር አብራችሁ አክብሩ!” በማለት ምክር ሰጥተዋል፡

ብፁዕነታቸው “በንግዱ መስመርም ያላችሁ ወቅቱን በመዋጀት ሳማያዊ ቤታችሁን አስቡ፡፡ በእርግጥ ሁሉ ነገር ተወዷል ይገባኛል አቅሜ ቢደክምም ልቦናዬ ያውቃል፡ከ100 ብር እቃ ላይ አምስት ብርም ትርፍ ነው፡ 10 ብርም ትርፍ ነው፡፡ በሰበባሰበብ ግን ክፉዎን ጊዜ አንተባበረው ከ100 ብር ላይ እጥፍና ከዚያ በላይ ለማግኘነት ምክንያት መፈለግ በእግዚአብሔር ዘንድ ትርፍ ሳይሆን ኪሳራ ነው፡አንዳንዴ አስቸጋሪ ወቅትን አትገዙት ተከስሮም ቢሆን መጥፎ ጊዜን ከወገን ጋር በማለፍ ለንሰሃ ጊዜ ማግኘት ትርፉ ታላቅ ነው” በማለት መክረዋል፡፡

“በመሪነት ደረጃም ያላችሁ እንደ ጲላጦስ ግራ የገባው ዳኛ አትሁኑ! ጲላጦስ ጌታን ምንም ዓይነት ለግርፋት ለስቅላት ቀርቶ ለወቀሳ የሚሆን ወንጀል አላገኘሁበትም ካለ በኋላ “ስቀለው፡ ስቀለው” እያሉ የሚጮሁት ስለበዙ ብቻ በትክክለኛ አቋሙ እንዳይፀና በጊዜያዊ ጥቅሙን ግራ ተጋብቶ ተገቢ ያልሆነ ፍርድ ሰጥቷል፡፡ ዛሬ ወቅቱ ተገቢ የሆኑና ያልሆኑ ድምፆች የተበራከቱበት መጥፎ ጊዜ ነው መሪዎች እንደ ጲላጦስ ጥቅም ይቀርብኛል በሚል ሥጋት ግራ ሳትጋቡ እውነተኛ ድምጽን ሰምታችሁ ፍትህ ስጡ” በማለት አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ አሳስበዋል፡፡ @yetenantun_lenege
በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ እንግዳ ቃላት እና ትርጉማቸው ፡-

በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

#ኪርያላይሶን
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን»ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ «አቤቱ ማረን»ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ«ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡

#ናይናን
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡

#እብኖዲ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው

#ታኦስ
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡

#ማስያስ
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው

#ትስቡጣ
«ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው

#አምነስቲቲ_ሙኪርያቱ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡

#አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ -ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

#አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው፡፡

©ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@yetenantun_lenege
እንኳን ለብርሃነ ትንሳዔው በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል!
@yetenantun_lenege
ከትንሳኤ በኀላ ያሉ ዕለታት
#ሰኞ
#ሰኑይ_ማእዶት ይባላል እንደ ቤተክርስቲያን ይትባሕል ከትንሣኤ እስከ ዳግማዊ ትንሣኤ ያለውን ሳምንት እንደ አንድ እሁድ እናከብራለን። ለዚህም ነው ዕለታቱን እንደ ሰንበት እናከብራቸው ዘንድ በፍትሐ ነገሥት ላይ አባቶቻችን ትእዛዝ የቀረጹልን።

ማእዶት ማለት መሻገር ማለት ነው። አደወ ማለት ተሻገረ ማለት ሲሆን ማእዶት መሸጋገሪያ ማለት ሊሆን ነው። ማእዶት የትንሣኤ እሑድ ማግስት ጌታ ክርስቶስ በትንሣኤው ምዕመናንን ከሞት
ወደ ሕይወት ያሻገረበት ቀን የትንሣኤው ማሳሰቢያ ነው። (ከሣቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ገጽ ፻፶) መሻገር በዕብራይስጥ ፓሳሕ ከሚባለው ቃል ይመሳሰላል ትርጉሙም ፋሲካ መሻገር ማለፍ የሚል ትርጉም ይሰጣል።

ሁላችን እንደምናውቀው እስራኤላውያን ከሚያክብሯቸው አበይት በዓላት አንዱም ፋሲካ ነው። ምክንያታቸው ደግሞ እግዚአብሔር ከሞተ በኩር ያሳለፋቸውን ዕለት ያስቡበታል። ቤተክርስቲያናችንም ይህንን በዓለ ትንሣኤን የፋሲካ በዓል የማክበሯ ምሥጢር ወይም የትንሣኤው ምሥጢር ነፍሳት በአምላካችን ትንሣኤ ከሞት ወደ ሕይወት ፣ ከአሳር ወደ ክብር ፣ ከሲዖል ወደ ገነት መሻገራቸውን በማሰብ አማናዊው ፋሲካ ወይም አሸጋጋሪው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብላ ታምናለች። እናምናለን።

ቅዱስ ጳውሎስ በብሉይ ኪዳን በታረደው የፋሲካ በግ (ዘዳ፲፮:፮) ምትክ አማናዊው ክርስቶስ እንደታረደልን እና ሞት ላያገኘን በሕይወት ለሕይወት እንዳሸጋገረን ሲገልጥ እንዲህ ብሏል:-"" እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤" (፩ ቆሮ ፭:፯) ቅዱስ ጳውሎስ ስለ እርሾም ሆነ ስለ አዲሱ ሊጥ በምሳሌ የሚነግረን እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ፋሲካ ሲያከብሩ ያደርጉት የነበረ ስርዓትን ነው።

ይኸውም ፋሲካን ያከበሩት ገና ከነጻነት በፊት ነው። ምክንያቱ ደግሞ ከላይ እንዳየነው ከሞተ በኩር መቅሰፍት ለመዳን እና ከእግዚአብሔር ፍርድ ለመዳን ነበር። በአዲስ ኪዳንም ያለን ክርስቲያኖች በተለይ ይህንን ዕለት ወይም ማእዶትን ስናስብ አምላካችን ከሞት ወደ ሕይወት እንዳሻገረን ፣ ከአሳር ወደ ክብር እንዳሳለፈን ፣ ከድካም ወደ ኃይል እንዳሻገረን ፣ ሁላችን ወደ መንግሥተ ሰማያት ፋሲካችን በሆነው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሸጋገርን በማመን ሊሆን ይገባል።

የፋሲካው ጌታ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞት ላይ እንድንዘባበትበት ሞትን ፣ ፍርሃትን ፣ ጭንቀትን ፣ ተስፋ መቁረጥን ፣ ሐዘንን ፣ ለቅሶን ፣ ትካዜን ፣ ድካምን ፣ ሥጋትን እና መቃብርን ሁሉ አጥፍቶ አሻግሮናል። ክብር ማዕዶታችን
ለሆነ ለእርሱ ይሁን። አሜን ክብር ይግባውና አምላካችን የሰው ልጅ ሞትን እንዲሻገር ሁለት ነገሮች(እምነት እና ምግባር ) እንደሚያስፈልጉት በመዋለ ስብከቱ እንዲህ ሲል አስተምሮናል:-
"እውነት እውነት እላችኋለሁ ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።

እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።" (ዮሐ፭:፳፬-፳፭) ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ዕለቷ ፋሲካ እንደሆነችና እንደሰትባት ዘንድ የተገባች እንደሆነች እንዲህ ሲል በመዝሙሩ አዚሞታል:- " ፋሲካ ዛቲ ዕለት ቅድስት
ይእቲ (ይህቺ የፋሲካ ዕለት ልዩ ናት) ፣ ዛቲ ዕለት ንትፈሳሕ በቲ (በዚህ ዕለት
ሐሴት እናድርግባት)..."

@yetenantun_lenege
ከትንሳኤ በሁአላ ያሉ ዕለታት
#ማክሰኞ #ቶማስ_ይባላል

እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሲፈጥረው የሚያንቀላፋና የሚነቃ አድርጎ ፈጥሮታል፡፡
ማንቀላፋቱ የሞት ፤ መንቃቱ ደግሞ የትንሣኤ ምሳሌ መሆኑን ስናስብ ሁሌም ይደንቃል፡፡

አባቶቻችን የትንሣኤውን ምሥጢር በአበው እና በስነፍጥረትም ይመስሉታል፤ አቤል ከሞተ በኋላ በደሙ መናገሩ እና የሔኖክ ሳይሞት በእግዚአብሔር መሰወሩ የትንሣኤ ምሣሌ ናቸው፡፡ በተፈጥሮ ፀሐይ መውጣቷ የመወለዱ ፤ መጥለቋ የሞቱ እና ዳግመኛ መውጣቷ የትንሣኤው ምሣሌ ነው፡፡ አምላካችን ክብር ይግባውና በእርሱ ያመንን ሁላችን እንደምንነሳ የእርሱ ከሙታን መካከል በሥልጣኑ መነሳት ለሁላችን መነሳት በኩር መሆንና ማረጋገጫም እንደሆነ በቃሉም በተግባሩም ያስተማረን የትንሣኤ ጌታ ነው፡፡

በቃሉ "በመቃብር ያሉት ሁሉ ድምጹን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል ፤ መልካም ያደረጉ ለሕይወት ትንሣኤ ፤ ክፉም ያደረጉ ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉና በዚህ አታድንቁ " (ዮሐ፭፡፳፱) እንዲሁም በተግባር የአራት ቀን ሬሳ አልዓዛርን አስነስቷል፡፡ (ዮሐ፲፩፡፵፫) የትንሣኤው ምሥጢር ሁላችን አምላክ የሆንበት ፤ በሁሉ ላይ ሥልጣን ያገኘንበት ፤ነጻ ወጥተን ነጻ አውጪ የሆንበት ፤ ከማይጠፋ ዘር እንደተወለድን ያረጋገጥንበት ፤ ሞትን የተዘባበትንበት ፤ ጨለማን የረታንበት ከዓለም እና ከዲያብሎስ እስራት ነጻ የወጣንበት ልዩ ክብር ኃይል እና ጸጋን ያገኘንበት ምሥጢር ነው፡፡

ይህቺ ዕለትም ይህንኑ ምሥጢር ነው የምትገልጥልን ሐዋርያው #ቶማስ ተብሎ ለምን ተሰየመ የሚለውን ከማየታችን በፊት ማነው የሚለውን ማየት ነገርን ከስሩ እንድንረዳው ይረዳናልና እውነት ሐዋርያው ቶማስ ማነው?

ሐዋርያው ቶማስ

ሐዋርያው ቶማስ የስሙ ትርጓሜ ፀሐይ ማለት ሲሆን የቀድሞ ስሙ ዲዲሞስ ይባላል ትርጉሙም ጨለማ ማለት ነው፡፡ ቁጥሩ ከ፲፪ ሐዋርያት ነው፡፡ (ማቴ፲፡፫) (መዝገበ ታሪክ ክፍል ሁለት ገጽ፹፱) ፤ ሐዋርያ ማለት ደጅ አዝማች ፤ ቀላጤ ፤ ምጥው ፤ ፍንው ፤ ሂያጅ ማለት ነው፡፡(ወንጌል ቅዱስ ገጽ፻፶፱) ሐዋርያው ቶማስ አልዓዛር በሞተ ጊዜ ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም አቅራቢያ ወደነበረው መቃብሩ ለመሄድ በተነሳ ጊዜ አይሁድ ሊገሉት ስለሚፈልጉ ሌሎቹ ሐዋርያት ክርስቶስ እንዳይሄድ ቢፈልጉም ቶማሰ ሌሎቹን ሐዋርያት በድፍረት እኛም ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ አብረን እንሂድ ያለ የእምነት ሐዋርያ ነው፡፡ (ዮሐ፲፩፲፮) ሐዋርያው ቶማስ ጌታችንን በእውነት እስከ ሞት ድረስ ያመነው ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ በ8ኛው ቀን እሁድ ሲሆን ሐዋርያት የነገሩትን ካላየው አላምንም ብሎ የተወጋ ጎኑን ከዳሰሰ በኋላ ነው፡፡ የእምነት ምስክርነቱም ጌታዬ አምላኬም ብሎ የገለጠው፡፡

(ዮሐ፳፡፳፬) ሐዋርያው ቶማስ መንፈስ ቅዱስን ከሐዋርያት ጋር ከተቀበለ በኋላ በ፵፮ ዓ.ም ገደማ በፋርስና በሕንድ እንዳስተማረ የተለያዩ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይገልጣሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ ፤ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ፤ ቅዱስ አምብሮስ ተጠቃሾች ናቸው፡፡በመጨረሻም ብዙ ተአምራት እና ድንቅን አድርጓል፡፡ የሐዋርያው ቶማስ ተአምር እና አገልግሎት ብዙ ተአምራትን ቢያደርግም ለአሁኑ አንዱን ብቻ እናያለን፡፡ የኸውም የሉክዮስ አገልጋይ ሆኖ በሕንጻ ማነጽ እና በሐውልት መስራት ተቀጥሮ በሚሰራበት ወቅት
የሉክዮስን ሚስት ከእነ ልጆቿ እና አገልጋዮቿ አሳምኖ ያጠመቀ ሐዋርያ ነው፡፡

ሐዋርያው ቶማስ ለሕንጻ እና ለሐውልት ማሰሪያ ከሉክዮስ የተቀበለውን ገንዘብና ወርቅ ሁሉ ለነዳያን በመመጽወቱ ንጉሡ እጅና እግሩን አሥሮ ቆዳውን አስገፍፎ ስልቻ አሰፍቶ በአሸዋ ሞልቶ አሸክሞት ገበያ ለገበያ ሲያዞረው የሉክዮስ ሚስቱ
አርሶንዋ ተመልክታ በድንጋጤ ሞታለች፡፡ ንጉሡም ለሚስቴ መሞት ምክንያት አንተ ነህ ካዳንካት እኔም በአምላክህ አምናለው ሲለው ጌታችን ቁስሉን እንደ ውኃ አቀዝቅዞለት ካለችበት ሄዶ ስልቻውን ቢያስነካት ተነስታለች በዚህም
ሉክያኖስ አምኖ ተጠምቋል፡፡

ሐዋርያው ቶማስ በራሱ ቆዳ በተሰራ ስልቻ እየተዘዋወረ ሙት አስነስቷል ፤ ድውያንን ፈውሷል አሕዛብን አሳምኖ አጥምቋል ፤ በቀንጦፍያ አንድ ሽማግሌ ሰባት ልጆቹን ገድለውበት ሰባቱንም ከሞት አስነስቷል ፤ በኢናስም በቃሉ ትምህርት እና በእጁ ተአምራቱ ብዙዎችን አሳምኖ አጥምቋል፡፡

የሐዋርያው ቶማስ ሰማእትነት


በሕንድ የነበሩት የብራሕማን እምነት ተከታዮች የቶማስ ትምህርት የእነርሱን እምነት የሚጻረር እና የሚያጠፋ መሆኑን ተገንዝበው ተነሱበትና በብዙ ስቃይ አሠቃይተው በ፸፪ዓ.ም በሰማዕትነት አርፏል፡፡ በሶርያ ትውፊት መሠረት የሐዋርያው የቶማስ አጽም በአንድ የሶርያ ነጋዴ ተወስዶ በኤዴሳ በክብርአርፏል፡፡ (የእግዚአብሔር መንግሥት ታሪክ በምድር ላይ አንደኛ መጽሐፍ ገጽ ፺፪)

ሐዋርያው ቶማስ ለምን ሰምቶ አላመነም?


እንደ ወንጌል ትርጓሜ ሐዋርያው ቶማስ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዝግ ቤት ገብቶ ሰላም ለእናንተ ይሁን ባለ ጊዜ አልነበረም ፤ በነገሩት ጊዜም አላመነም ያለማመኑ ምክንያት ሰዱቃዊ ስለነበር እና ሐዋርያቱ አይተው እርሱ ሰማው ብሎ ከሚያስተምር ማየት ወዶ ነው፡፡

"ጌታዬ አምላኬ" (ዮሐ፳:፳፰)

@yetenantun_lenege
✥ ፹፩ (81) መፅሐፍ ቅዱስ እዚህ

አራቱ ወንጌላት(ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ ዮሐንስ)

ወንጌል የሚለው ቃል ትርጉም፦

በግእዝና በአማርኛ <ወንጌል> የምንለው ቃል ትርጉም፦ ብስራት፣ ስብከት፣ የምሥራች ማለት ነው። ይህ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ተገልጦ ከመታየቱ በፊት በግሪክ ቋንቋ ለሚወዱት ሰው የምሥራች ተብሎ የሚሰጥ የደስታ መግለጫ የሆነ መልካም ስጦታን ያመለክት ነበር።

ከክርስቶስ ልደት በኋላ ግን ወንጌል የሚለው ቃል በክርስትና እምነት በተለይም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሲነገር የሚከተሉትን ሁኔታዎች ያመለክታል።

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ወይም ያስተማረው መልካም የምስራች ነው። ስለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚነገረው መልካም የምሥራች ዜና ሠናይ ነው። ትምህርቱንም <ወንጌል> ብሎ ለመጀመሪያ ጌዜ የጠራው ራሱ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ወንጌል ማለት የምስራች ወይም መልካም ዜና ለመሆኑ ተከታዩን የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባብ አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳስተማረን መመልከት ያስፈልጋል፦

ኢየሱስ ክርስቶስ በትምህርቱ፦

􀂾 ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል። ማቴ. ፳፬፡፲፬

􀂾 እውነት እላችኋለሁ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል። ማቴ. ፳፮፡፲፫

􀂾 ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ማር. ፲፮፡፲፭ ያለ ሲሆን ከጌታችን ቀጥሎም ሐዋርያትና የጌታ ደቀመዛሙርት ሁሉ ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰብኩትንና የሚጽፉትን <ወንጌል> ብለው ጠርተውታል።

📗 ወንጌላዊው ማቴዎስ፦

􀂾 ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር። ማቴ. ፬፡፳፫
􀂾 ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር። ማቴ.፱፡፴፭

📒 ወንጌላዊው ማርቆስ፦

􀂾 ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከ ወደገሊላ መጣ። ማቴ. ፩፡፲፭

📕 ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፦

ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለተወለደ እንደቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለተገለጠ ስለ ልጁ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሮሜ.፩፡፬ ስለዚህ <ወንጌል> ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሚነገረው መልካም የምሥራች ነው።

ብንናገርም ወንጌል ስንል አንድ ወንጌል እንጂ ያለን ብዙ ወንጌላት አሉን ማለት አይደለም። ወንጌላት ስንል ጸሐፊዎቹ ፬ እንደመሆናቸው መጠን እያንዳንዳቸው የጻፉት ወንጌል በጸሐፊዎቹ ስም ስለተጠራ ነው።

ስለ ወንጌል የተነገሩ ትንቢቶች፦
በብሉይ ኪዳን ስለክርስቶስ የተነገሩ ትንቢትዎች ሁሉ ስለ ቅዱስ ወንጌል የተነገሩ መኾናቸውን መረዳት ያስፈልጋል። ኢየሱስ ክርስቶስ ስለመወለዱም ሆነ በምድር ላይ ተመላልሶ ስለማስተማሩ እንዲሁም ለሰው ልጆች ሲል የመስቀል ሞት ስለመሞቱ አስቀድመው ነቢያት እያንዳንዱን ተናግረውት ነበር።

ይህም በነቢዩ አሞጽ የተጻፈው ቃል ፍጻሜነትን ያገኝ ዘንድ ነው። በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም። አሞጽ ፫፡፯ ከዚህ በታችም ፍጻሜአቸው በግልጽ የተነገረውን ሁለት ትንቢቶች ብቻ እንመለከታለን።

✓ የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ። ዘፍጥ. ፲፪፡፫ ተብሎ በብሉይ ኪዳን የተጻፈው ቃል ፍጻሜነቱን ሐዋርያው ቅዱስ

📘 ጳውሎስ እንዲህ ሲል ጽፎታል፦

መጽሐፍም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ። በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ። ገላ. ፫፡፰

✓ የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።

የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፤ ኢሳ. ፷፩ ፡ ፩-፪ ተብሎ በብሉይ ኪዳን የተጻፈው ቃል ፍጻሜነቱን ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ እንዲህ ሲል ጽፎታል፦ (ለጌታም)የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ። የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ። ሉቃ. ፬ ፡ ፲፯-፲፱


#ይቀጥላል

@yetenantun_lenege
የአራቱ ወንጌላት መልእክትና ይዘት፦

አራቱ ወንጌላት በየክፍላቸው መዝግበው የያዙት ስለአምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክና ሥራ ነው። ሁሉም ይህንኑ ታሪክና ሥራ ቢናገሩም እያንዳንዳቸው ከሌሎቹ የሚለዩበት የአመዘጋገብና ያገላለጽ ሁኔታ አለ። ለምሳሌው ያህል ለመጥቀስ በአንዱ የወንጌል ክፍል ተመዝግበው በሦስቱ ወንጌላት ላይ ያልተመዘገቡና የማይገኙ፣ በሁለቱ ወንጌላት ተመዝግበው በተቀሩት በሁለቱ ላይ የማይገኙ፣ እንዲሁም በሦስቱ ወንጌላት ተመዝግበው በቀሪው አንድ ላይ ያልተመዘገቡና የማይገኙ አንዳንድ የጌታ ታሪኮችና ሥራዎች ስለሚገኙ ነው። ይህንን ጠንቅቆ ለመረዳት በእያንዳንዱ መጽሐፍት ግርጌ ባለው የኅዳግ ማመሳከሪያ በመጠቀም ፬ቱንም ወንጌላት ማነጻጸር ይቻላል።
የማቴዎስ፣ የማርቆስና የሉቃስ ወንጌላት <ሲኖፕቲክ> ተብለው ይጠራሉ።

<ሲኖፕቲክ> ማለት ተመሳሳይ ማለት ሲሆን ቃሉ የግሪክ ቃል ነው። ሦስቱ ወንጌላት በይዞታቸው በብዙ ክፍል ስለሚመሳሰሉ ይህንን መመሳሰላቸውን ለማስረዳት የተሰጣቸው ስያሜ ነው። ምክንያቱም ሦስቱም ወንጌላት አንድ ዓይነት መልእክታትን ጽፈው ይገኛሉና። ምንም እንኳን የጌታ ተመሳሳይ ታሪክና ሥራ በ፫ቱ ወንጌላት ጠቀስም የአንዱ ወንጌላዊ አገላለጽ ከሌሎቹ የተለየ ስለሚሆን ሁሉንም የወንጌል ክፍል ማንበቡ አስፈላጊ ነው።

የዮሐንስ ወንጌል ነው። ይህም ወንጌል የመዘገበው እንደ ሦስቱ ወንጌላት ስለጌታ ታሪክና ሥራ ቢሆንም በብዛት እነርሱ ያልመዘገቡትን አንዳንድ ታሪክና ሥራዎች መዝግቦ ይገኛል። ስለዚህ በይዞታው ከሦስቱ ወንጌላት ይለያል። ሦስቱ ወንጌላትና አራተኛው ወንጌል በሚከተሉት ሦስት ነገሮች ይለያያሉ።

እነርሱም፦
ሦስቱ ወንጌላት የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ምድራዊውን ታሪክ (የትስብእቱን ማለት የሰውነቱን ነገር) አጉልተው ይጽፋሉ።

📗 ወንጌላዊው ማቴዎስ፦

አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፡ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፡…ማታንም ያዕቆብን ወለደ፡ ያዕቆብም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን የወለደች የማርያምን እጮኛ ዮሴፍን ወለደ። ማቴ. ፩ ፡፩-፲፯ በማለት የጌታን የትውልድ ዝርዝር ጽፏል።

📒 ወንጌላዊው ማርቆስ፦

ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም በፊልጶስ ቂሣርያ ወዳሉ መንደሮች ወጡ በመንገድም። ሰዎች እኔ ማን እንደ ሆንሁ ይላሉ? ብሎ ደቀ መዛሙርቱን ጠየቃቸው። እነርሱም። መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ከነቢያት አንዱ ብለው ነገሩት። እናንተስ እኔ ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? ብሎ ጠየቃቸው። ጴጥሮስም አንተ ክርስቶስ ነህ ብሎ መለሰለት። ማር.፰፡፳፯-፳፱ በማለት የጌታን የሰውነቱን ነገር ጽፏል።

📕 ወንጌላዊው ሉቃስ፦

ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ሆኖት ነበር፤ እንደመሰላቸው የዮሴፍ ልጅ ሆኖ የኤሊ ልጅ፡ የማቲ ልጅ፡…የሄኖስ ልጅ፡ የሴት ልጅ፡የአዳም ልጅ፡ የእግዚአብሔር ልጅ። ሉቃ.፫፡፳፫-፴፰። በማለት የጌታን የትውልድ ዝርዝር ጽፏል።

􀀩 አራተኛው ወንጌል ግን ጌታ ከሰማይ መውረዱንና የመለኮቱን ነገር አጉልቶ ይጽፋል።

ይኸውም፦ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። ዮሐ. ፩፡፩-፫ ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።

ዮሐ. ፫ ፡፲፫፤ እንግዲህ አይሁድ ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ ስላለ ስለ እርሱ አንጐራጐሩና አባቱንና እናቱን የምናውቃቸው ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለምን? እንግዲህ። ከሰማይ ወርጃለሁ እንዴት ይላል? አሉ። ኢየሱስ መለሰ አላቸውም። እርስ በርሳችሁ አታንጐራጕሩ። የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ ተብሎ በነቢያት ተጽፎአል፤ እንግዲህ ከአብ የሰማ የተማረም ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል።
አብን ያየ ማንም የለም፤ ከእግዚአብሔር ከሆነ በቀር፥ እርሱ አብን አይቶአል። እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው።

የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ። አባቶቻችሁ በምድረ በዳ መና በሉ ሞቱም፤ ሰው ከእርሱ በልቶ እንዳይሞት ከሰማይ አሁን የወረደ እንጀራ ይህ ነው። ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው። ዮሐ. ፮፡፵፩-፶፩፤
እናንተ ከታች ናችሁ፥ እኔ ከላይ ነኝ፤ እናንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፥ እኔ ከዚህ ዓለም አይደለሁም። ዮሐ.፰፡፳፫ እንግዲህ ከላይ በተገለጹት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ምክንያት ሦስቱ ወንጌላት ምድራውያን ወንጌላት ሲባሉ አራተኛው ወንጌል ደግሞ ሰማያዊ ወንጌል ይባላል።
.
.
.
#ይቀጥላል

@yetenantun_lenege
ሦስቱ ወንጌላት ኢየሱስ ክርስቶስ በማስተማር ዘመኑ ከገሊላ ወደ ኢየሩሳሌም ከወጣባቸው ጊዜያት አንዱን ብቻ ማለትም ሊሞት አንድ ሳምንት ሲቀረው ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ተብሎ እየተዘመረለት ስለመግባቱ ብቻ መዝግበዋል። ወደ ኢየሩሳሌምም ቀርበው ወደ ደብረ ዘይት ወደ ቤተ ፋጌ ሲደርሱ ያንጊዜ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከ እንዲህም አላቸው።

በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁ አምጡልኝ። ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ፤ ወዲያውም ይሰዳቸዋል። ለጽዮን ልጅ እነሆ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሏት ተብሎ በነቢይ የተነገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ።

ደቀ መዛሙርቱም ሄደው ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ፥ አህያይቱንና ውርንጫዋንም አመጡለት፥ ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ፥ ተቀመጠባቸውም። ከሕዝቡም እጅግ ብዙዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፥ ሌሎችም ከዛፍ ጫፍ ጫፉን እየቈረጡ በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር። የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም።

ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር። ወደ ኢየሩሳሌምም በገባ ጊዜ መላው ከተማ። ይህ ማን ነው? ብሎ ተናወጠ። ማቴ.፳፩ ፡፩-፲ ከማር.፲፩ ፡፩-፲፩ እና ከሉቃስ ፲፱፡፳፰-፵፭ ጋር በማነፃፀር ያንብቡ።

አራተኛው ወንጌል ከገሊላ ኢየሩሳሌም የወጣበትን ፬ ጊዜያት መዝግቧል። ይኸውም፦

📗 የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። ዮሐ. ፪፡፲፫

📗 ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።ዮሐ.፭:፩

📗 ወንድሞቹ ግን ወደ በዓሉ (ወደ ኢየሩሳሌም)ከወጡ በኋላ በዚያን ጊዜ እርሱ ደግሞ በግልጥ ሳይሆን ተሰውሮ ወጣ። ዮሐ. ፯፡፲

📗 ከፋሲካም በፊት በስድስተኛው ቀን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ። በዚያም እራት አደረጉለት፤ ማርታም ታገለግል ነበር፤ አልዓዛር ግን ከእርሱ ጋር ከተቀመጡት አንዱ ነበረ። ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቱ ንጥር ወስዳ የኢየሱስን እግር ቀባች፤ በጠጕርዋም እግሩን አበሰች፤ ቤቱም ከናርዶስ ሽቱ ሞላ። ነገር ግን ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ አሳልፎ ሊሰጠው ያለው የስምዖን ልጅ የአስቆሮቱ ይሁዳ።

ይህ ሽቱ ለሦስት መቶ ዲናር ተሽጦ ለድሆች ያልተሰጠ ስለ ምን ነው? አለ። ይህንም የተናገረ ሌባ ስለ ነበረ ነው እንጂ ለድሆች ተገድዶላቸው አይደለም፤ ከረጢትም ይዞ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ስለ ነበረ ነው። ኢየሱስም። ለምቀበርበት ቀን እንድትጠብቀው ተውአት፤ ድሆችስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፥ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም አለ።

ከአይሁድም ብዙ ሕዝብ በዚያ እንደ ነበረ አውቀው መጡ፥ ከሙታንም ያስነሣውን አልዓዛርን ደግሞ እንዲያዩ ነበረ እንጂ ስለ ኢየሱስ ብቻ አይደለም። የካህናት አለቆችም አልዓዛርን ደግሞ ሊገድሉት ተማከሩ፥ ከአይሁድ ብዙዎች ከእርሱ የተነሣ ሄደው በኢየሱስ ያምኑ ነበርና።

በማግሥቱ ወደ በዓሉ መጥተው የነበሩ ብዙ ሕዝብ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲመጣ በሰሙ ጊዜ፥ ዮሐ. ፲፪፡ ፩- ፲፪
ሦስቱ ወንጌላት ኢየሱስ ክርስቶስ በገሊላ እና በአካባቢዋ እንዲሁም በመጨረሻ ወደ ኢየሩሳሌም በመጓዝ ላይ እና ከገባ በኃላ ያስተማረውንና የሠራውን ነገር በስፋት መዝግበዋል። ይኸውም፦

📒 ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር። ማቴ.፬፡፳፫፤

📒 በምኵራባቸውም እየሰበከ አጋንንትንም እያወጣ ወደ ገሊላ ሁሉ መጣ። ማር.፩፡፴፱፤

📒 ኢየሱስም በመንፈስ ኃይል ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ ስለ እርሱም በዙሪያው ባለችው አገር ሁሉ ዝና ወጣ። ሉቃ.፬፡፲፬፤

📒 አራተኛው ወንጌል ግን በገሊላ፣ በሰማርያና በይሁዳ እየተመላለሰ የሠራቸውን ሥራዎችና -ያስተማራቸውን ትምህርቶች በሰፊው መዝግቦ ይዟል።

📒 እንግዲህ ኢየሱስ ከዮሐንስ ይልቅ ደቀ መዛሙርት ያደርጋል ያጠምቅማል ማለትን ፈሪሳውያን እንደ ሰሙ ጌታ ባወቀ ጊዜ፥ ይሁዳን ትቶ ወደ ገሊላ ደግሞ ሄደ፤ ዳሩ ግን ደቀ መዛሙርቱ እንጂ ኢየሱስ ራሱ አላጠመቀም። በሰማርያም ሊያልፍ ግድ ሆነበት።

📒 ስለዚህ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ስፍራ አጠገብ ወደምትሆን ሲካር ወደምትባል የሰማርያ ከተማ መጣ፤ ዮሐ. ፬፡፩-፭

📒 ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። ዮሐ. ፭፡፩ ከላይ እንደተገለጸው የ፬ኛው ወንጌል (የዮሐንስ ወንጌል) ከሦስቱ ወንጌላት ጋር ብዙ ልዩነት እንዳለው ተመልክተናል። ሆኖም ግን ከ፬ኛው ወንጌል ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ምንባባት በ፫ቱ ወንጌላት ውስጥ ይገኛሉ። ለምሳሌ፦

🎚 የመጥምቁ ዮሐንስ ምስክርነት፣
🎚 የጌታ ጥምቀት፣
🎚 ፭ እንጀራና ፪ ዓሣ ማበርከቱ
🎚 ሕማማቱ፣
🎚 ስቅለቱና ትንሣኤው በአራቱም ወንጌላት የተመዘገቡ ናቸው።

ታዲያ እነዚህም ቢሆኑ በ፬ኛው ወንጌል ከተገለጡት ከ፫ቱ ወንጌላት አገላለጥ በተለየ መንገድ ነው። ፬ቱንም ወንጌላት የሚያገናኛቸው ግን ሁሉም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መናገራቸው ነው።

ከዚህ በታች ደግሞ የኢየሱስን ማንነት እና ታሪክ እንማራለን። ኢየሱስ ማን ነው?

ጌታችን ሰው ከሆነ በኋላ የተጠራበት ስሙ <ኢየሱስ> የተባለው ስም ነው። <ኢየሱስ> የሚለው አጠራር የግሪክ ቋንቋ አጠራር ሲሆን ትርጉሙ <አዳኝ> ማለት ነው። ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ>። ማቴ.፩፡፳፩
.
.
.
#ይቀጥላል

@yetenantun_lenege
2024/04/29 11:36:32
Back to Top
HTML Embed Code: