⚡️⚡️⚡️⚡️ አሁን

አሁንን የሌለዉ ትናንትም ነገም የለዉም። አሁን የሌለበት ቦታ ትናንትም ነገም የለም... ጊዜና ቦታ በዘመን ዉስጥ ከታሰሩበት አንዷ ከሆነችዉ የምድር ገጽ ላይ የሆንን እኛ፣ አሁንና ዛሬ ያለን ትናንተን የምናከማቸዉ ነገን የምንሞላዉ በአሁን ጊዜ( ቅጽበት) ጥርቅም ነዉና አሁኖችን መጠቀም ነገንም ትናንትንም መቅረጽ አለብን😊 ነገና በኃላ ፤ ትናንትና ቅድም ልዩነት የላቸዉም፤ ባለፈና በሚመጣ ጊዜ ዉስጥ ናቸዉ፡፡


ዛሬ ዉስጥ ትናትም ነገም አለ ከአሁን በፊትና ከአሁን በኋላ ያለዉ ጊዜ ቅድም ትናንት(ትዝታ) ፤በኋላ ነገ(ተስፋ) ጋር ተመሳሳይ ስለሆኑ🤔 ነገንና ተስፋን በቅርብ ለማወቅና ለመለማመድ ይረዳሉ፡፡


ነገንና ትናንትን ለማወቅ የምድር🌎 ዙረትን መጠበቅ አያስፈልግም፡፡ የምድርን በራስዋ ዛቢያ ላይ የመዞር ፍጥነት ብንጨምር ዛሬን አሳጥረን አሁን ዉስጥ ልንከተዉ እንችላለንና ከ24 ሰዓት ወደ 1 ሰከንድ...


መኖር የታሰረዉ አሁን ዉስጥ ነዉ ፤አሁንን ያላወቀ ባዶ ትናንት(ታሪክ፣ትዝታ)😔 ባዶ ነገ(ተስፋ) ይኖረዋል😔... ነበርኩ ብሎ የሚያኖረዉ፣ የሚያወራዉ ፤አገኛለሁ ብሎ የሚጠብቀዉ የሌለዉ ባዶነት ዉስጥ ያለ ባዶ ነዉ... አሁንን እንኑራት😊

For more join us

@yetikurtmender

@yetikurtmender

@yetikurtmender

📩@Tikuret_bot
ራስን ማወቅ


💥እነዚህ ነጥቦች እራሳችንን እንድናውቅ ይረዱናል።

1. ውስጣችንን መስማት

እግዚአብሄር ሲፈጥረን ህሊናችን ከሱ ሃሳብ ጋር እንዲስማማ አድርጎ ነው... የተሳሳተ ነገር ስናደርግ ብዙ ጊዜ ህሊናችን ይወቅስናል፥ ውስጣችን ደስ አይለውም። አንድ ነገር ስናደርግ ውስጣችንን መጠየቅ ፥ ውስጤ ምንድን ነው ሚስማኝ? ምንድን ነው እግዚአብሔር ለውስጤ ሚናገረው ብለን መጠየቅ እናም ከዛ ከሚሰማን ነገር ወይ የውስጥ ድምጽ ጋር መስማማት።
ያልሆነውን ስናስመስል ውስጣችን ምቾት አይሰማውም...ምክንያቱም ውስጣችን ያለው ድምፅ እግዚአብሔር የእርሱን ባህሪ እንድንወርስ ከማንነታችን ጋር ያያዘው ስለሆነ ነው። ስለዚህ ለራስ ታማኝ መሆን፥ አባቴ ወይ ጎረቤቴ ምን ያላል ወይ ከኔ ይጠብቃል ከማለታችን ይልቅ እግዚአብሔር የሰጠኝ ህሊናዬ የውስጥ ድምጼ ምን ይላል ብለን መጠየቅ።
አንድ አንዴ ውስጣችን የሚለንን ስምቶ ለዛ መታዘዝ ይከብደናል ምክንያቱም እድሜ ልካችንን የኖርነው የውጭ ድምጽ እየስማን ስለኖርን። ከራሳችን ጋር እንስማማ

2. የራስን ዋጋ ማወቅ

ስንፈጠር እኛን የመስለ ሌላ አልተፈጠረም... በእግዚአብሔር እያንዳንዳችን ልዩ ሆነን ነው የተፈጠርነው። የአንድ ስው ዋጋ በምንም በማንም አይለካም። ይኛ ዋጋ የፈለግነው ነገር ሲሳካ አይጨምርም ወይ ስንደክም ወይ ስንወድቅ አይቀንስም። ሃብት፥ውበት፥ትምህርት ደረጃ፥የትውልድ ስፍራ እና ዘር ዋጋችንን አይጨምረውም ወይ አይቅንሰውም።
የሰው ሁሉ ዋጋ እኩል ነው ግን ያንዱ ሌላውን አይተካውም... ስለዚህ እኔ ይሄ ስለሌለኝ ወይ ስላለኝ መደሰት፥ መከበር ወይ በሰላም መኖር አይገባኝም አንበል። ሰው ለኛ ሚሰጠን ዋጋ ሳይሆን እኛ ለራሳችን የምንሰጠው ዋጋ ነው ወሳኝ ነገር። አብዛኛው ጊዜ ሌላው ሰው የሚሰጠን ዋጋ እኛ ለራሳችን ከሰጠነው ዋጋ ጋር አንድ ነው።

3. አይምሮን ማደስ

ከልጅነታችን ጀምሮ ስለኛ ብዙ ተነግሮናል...ያንን እንደ እውነታ ወስደን ሳናስብው ማንንታችን እድርገናቸዋል። አሁን ግን ቆም ብለን ስለኛ የምናስባችው ነገሮች ከየት እንደመጡ እንመርምር እና ለኛ የማይጥቅሙን ነግሮች ሁሉ እናስወግድ። አንተ እኮ ፈሪ ነህ፥ ትምህርት አይገባህም፥ ጸባይህ ለሰው አይገባም፥አትረባም፥መልክህ አያምርም፥ መናገር አትችልም ዝም በል፥ ካንተ ያ ወይ ይሄ ይሻላል፥
አይሳካላልህም፥ የተለያዩ መጥፎ እና ማንነታችንን በመጥፎ ሊቅይሩ የመጡ ንግግሮችን ሁሉ ከአይምሮአችን አጥቦ ማውጣት... ቆም ብለን እንዚህን ሃሳቦች በመልካም ሃሳቦች እንተካቸው።

4. ነገሮችን እና እራስን መለየት

በአካባቢያችን የሚሆኑ ነግሮች የራሳቸው ማንነት አላቸው የነሱን ማንነት ከእኛ ጋር አለማያያዝ። ለምሳሌ ትምህርት ቤት ጥሩ ውጤት ሳናመጣ ስንቀር ያንን ወስደን እኔ ማለት ሰነፍ ነኝ ወይ እንዲህ ነኝ ከማለት በፊት ትምህርቱን ጥሩ ውጤት ላመጣ የሔድኩበት መንገድ ጥሩ አልነበርም ስለዚህ በሚቅጥለው በየትኛው መንገድ ልሂድ ብሎ ማሰብ...
ባጠቃላይ እኔ እንዲህ ነኝ ብሎ ከመደምደም በፊት እንዴት ያንን ነገር ልስራው ወይ ላሻሽለው ብሎ ማሰብ። ሌላ ምሳሌ ከሰው ጋር ያለን ግንኙነት መልካም ካልሆነ አይ እኔ ጥሩ ጓደኛ አልሆንም ከማለት በፊት ነገሩን ከራስ ማንነት ወጣ አድርጎ በምን መንገድ መግባባት እንችላለን፥ ምን ብናደርግ ይሄ ይስትካከላል ማለት አለብን...

5.እራስን ከሌላው ጋር አለማወዳደር....

ከላይ እንዳልነው ሁላችን ስንፈጠር ልዩ ልዩ ሆነን ነው። የሌላው ሕይወት ለመማሪያ ምሳሌ ሊሆነን ይገባል እንጂ ማወዳደሪያ ምስፈርት መሆን የለብትም። ሰው ሁሉ በየራሱ የሚሄድበት መንገድ አለው ፥ ያንተ መንገድ ከሌላው ይለያል፥ የሰው መንገድ ላይ መግባት አንተ መድረስ የሚገባህ ቦታ
አያደርስህም። አንተ ማድርግ በምትችለው እና እግዚአብሔር በሰጠህ ነገር መዝነው ...የሌላውን ሰው ስጦታ ትተን ይኛ የተሰጠን ላይ ማተኮር።

6. መልካምን ማሰብ ጥሩ ጥሩ ንገሮችን ማሰብን አይምሮአችንን ማስለመድ...

ብዙ ጊዜ ለሰው ምንለውን እንጠነቀቃለን በቃላችን እንዳንጎዳቸው ቃላት እንመርጣለን ስለራሳችን ግን ያን ያህል አንጠነቀቅም። ስለ ራሳችን የምናስበው እና ምንናገረው ነገር መልካም ንገር እንዲሆን መጠንቀቅ አለብን።
ስለራሳችን እንዲሁ በውስጣችን እንናገራለን እናስባለን ያ ሃሳብ መልካም መሆን አለበት። እራሳችንን መሆን ይከብደናል ስለራሳችን ያለን ሃሳብ መጥፎ ከሆነ። እራሳችንን ማበረታታት፥ መልካም ይሆንልሃል ፥በእግዚአብሔር የተወደድክ ነህ እያልን ብዙ ብዙ መልካም ነገሮችን መናገር አለብን።

7. እራሳችንን በስዎች አይምሮ ውስጥ አለማየት.

ብዙ ጊዜ እራሳችንን እንዳንሆን ሚያረግን እራሳችንን በሰው ውስጥ ሆነን ነው ምናየው ነው.. ማለትም ስናወራ ያ የሚስማን ሰው ስለኛ ምን እንደሚያስብ በሱ ውስጥ ሆነን እራሳችንን ማየት እንጀምራልን ከዛን መናገር የምንፈልገውን ሳይሆን መስማት የሚፍልገውን ማውራት እንጀምራለን። ይህ እንዳይሆን ስናወራ ወይ ስንኖር ውስጣችን እንደሚለው መሆን አልበት። ብዙ ጊዜ ውስጣችን የሚለውን መስማት ስንል መጀመሪያ ውስጣችን እግዚአብሔር ከሚለው ጋር መስማማቱን ማረጋገጥ አለብን።

💥💥💥ሰላም ለሀገራችን 🙏🙏🙏💥💥💥

@yetikurtmender

@yetikurtmender

@yetikurtmender

📩 @Tikuret_bot
ጭንቀት

አንዳንድ ሰዎች በየምክንያቱ ይጨናነቃሉ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን አብዛኛዎቹ የምንጨነቅባቸው ነገሮች ቀድሞውኑ መሰረት የሌላቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌነት የሚከተለውን የአንድ ጥናት ውጤት እንመልከት፡፡ የምንጨነቅባቸው ነገሮች . . .

>> 40% በፍጹም ለማይደርስብን ነገር ...
>> 30% ምንም ልንለውጠው ስለማንችለው ስላለፈው ነገር ...
>> 12% ሰዎች ስለእኛ ስለሚናገሩብን ፍርድ፣ ወሬና ሃሜት ...
>> 10% ስለጤንነታችን (ስለተጨነቅን የሚብስ) ...
>> 8% ስለእውነተኛ ልናስብበት ስለሚገባ ሁኔታ ...

በፍጹም ለማይደርስብን ነገር …
ያለን አማራጭ ምክንያታዊነትን ማዳበር ነው፡፡ ሁኔታው ሊደርስብንና ላይደርስብን የሚችልበትን የእድል መጠን አመዛዝነን ያለመድረሱ ሁኔታ ካመዘነ፣ መጨናነቅን የማቆምን ሂደት መጀመርና እየተዉ መሄድ የግድ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ግን እንዲሁ ምክንያት ፈልገው የመጨነቅ “ሱስ” አለባቸው፡፡ ይህ ዝንባሌ የሚመጣው ለረጅም ጊዜ በአጣብቂኝ ሁኔታ ከማሳለፍና ስሜታችን የጭንቀት ሰለባ ሆኖ ከመክረሙም የተነሳ ሊሆን ይችላል፡፡ ያም ሆነ ይህ ፍጹም የማይደርስ ነገር ተለይቶ ሊታወቅና ከስሜታችን የደም ዝውውር ውስጥ ሊወገድ ይገባዋል፡፡

ምንም ልንለውጠው ስለማንችለው ስላለፈው ነገር …
ያለን አማራጭ ፈጽሞ አንዴ የሆነ ነገር መሆኑንና ምንም ብናደርግ ልንለውጠው እንደማንችል በመቀበል አእምሮን በአዳዲ ነገሮች መሙላት ነው፡፡ ይህን ማድረግ ካልፈለግን ግን እስቲ አንዴ የሆነውንና ያለፈውን ነገር ለመለወጥ የአንድ ወር ጊዜ እንስጠውና የምንችለውን ያህል እንሞክርና ካልቻልን ነገሩን ለመተው ለራሳችን እድል እንስጠው፡፡

ሰዎች ስለእኛ ስለሚናገሩብን ፍርድ፣ ወሬና ሃሜት …
ያለን አማራጭ መቆጣጠር የማንችለውን የሰውን ባህሪይ ለመቆጣጠር ከመጦዝ ይልቅ መቆጣጠር የምንችለውን የራሳችንን በሆነ ባልሆነው የመጨነቅ ዝንባሌ ለመቆጣጠር መስራቱ ይመረጣል፡፡ ሰዎች ስለአንተና በአንተ ላይ የሚሉት ነገር አንተ ካልፈቀድክለት በስተቀር ምንም ሊያደርግህም እንደማይችል አትዘንጋ፡፡ ብትችል ወሬው አንተ ጋር የማይደርስበትን መንገድ ፍጠር፡፡ ካልቻልክ ደግሞ ወሬው ወደ ስሜትህ የማይደርስበትን ጥንካሬ አዳብር፡፡

ስለጤንነታችን (ስለተጨነቅን የሚብስ) …
ያለን አማራጭ ስለጤነታችን የሚያሳስበን ሁኔታ ካለ ያንን ለማስቀረት ወይም ለመቀልበስ የምንችለውን ያህል መሞከር ነው፡፡ ጭንቀታችን ግን “ምናልባት እታመም ይሆን” የሚል ከሆነ፣ ይህ የራስ በራስ ትንበያ እንደሚፈጸም አትጠራጠር፡፡ ጭንቀት በሽታን የመሳብ ባህሪይ አለውና፡፡

ስለእውነተኛ ልናስብበት ስለሚገባ ሁኔታ …
ያለን አማራጭ በቅድሚያ፣ ሁኔታው በትክክልም የሚያሳስብና በቅጡ ካልያዝነውም የሚስጨንቅ ጉዳይ ስለሆነ ማሰባችንና በመጠኑም ቢሆን መጨነቃችን ትክክለኛው መሆኑን አምኖ መቀበል አስፈላጊ ነው፡፡ ሲቀጥል ያሳሰበንን ሁኔታ በምን መልኩ ብንጋፈጠው ልናሸንፈው እንደምንችል በሚገባ ማሰብን ይጠይቃል፡፡ አእምሮን በጭንቀት ከመሙላት ይልቅ ትክክለኛውን ምላሽ በማሰብ መሙላት በብዙ እጥፍ ይመረጣል፡፡ በጉዳዩም ላይ ሰውን ማማከሩም አንዱ መንገድ ነው፡፡
ለራሳችን መንገር የሌለብን 4 ነገሮች...

የተለያዩ ችግሮች ውስጥ የምታልፉበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለችግሮቹም ራሣችሁን ተጠያቂ ታደርጉ ይሆናል...በየትኛውም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑም ግን ደካማነታችሁን የሚያጎሉና ከሠዎች በታች ሆናችሁ እንድትታዩ የሚያደርጉ ቃላትን መጠቀም የለባችሁም በማለት የሥነ-ልቦና ምሁራን ይመክራሉ፡፡ እነኚህ ቃላት አስተሳሰባችን ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የመፍጠር አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡ ፡ ለራሳችን የምንናገራቸው አሉታዊ ቃላት ከፍተኛ ጉዳት እንዳላቸው ከሕይወት ልምዴ ተገንዝቤያለሁ የሚሉት የሥነ-ልቦና ባለሙያው ማይክ ቡንድራንት በተለይ የሚከተሉትን ቃላት ለራሳችሁ ፈፅሞ መንገር የለባችሁም ይላሉ፡፡

❄️ የማልረባ ነኝ
ይህ በራስ መተማመናችሁን በቀጥታ የሚገድል አነጋገር ነው፡፡ የማትረቡ ወይም አንዳች ዋጋ የሌላችሁ መሆኑን ለራሳችሁ መንገር አሉታዊ አስተሳሰብ በአእምሯችሁ እንዲሰርፅ የማድረግ ኃይል ስላለው ቃሉን መጠቀም ተገቢ አይደለም፡፡

❄️አልችልም

አንዳንድ ነገሮችን በምትፈልጉት ደረጃ መስራት የማትችሉባቸው ሁኔታዎች በሚፈጠሩበት ጊዜ አቅማችሁን ልትጠራጠሩ ትችላላችሁ፡ ፡ የምታደርጉት ነገር ጥቅም እንደ ሌለው ለራሳችሁ መንገር ለሥራ ያላችሁን የተነሳሽነት ስሜት ይቀንሠዋል፤ አቅማችሁን ያሣጣችኋል፡፡ ይህ አነጋገር እውነታውን ከመግለፅ በላይ ራሳችሁን መልሶ የማጥቃት አቅም አለው፡፡ አንድ ነገር ከመሥራታችሁ በፊት እወድቃለሁ/ አይሣካልኝም ከማለት ይልቅ ደጋግሞ በመሞከር ለውጤት መብቃት እንደምትችሉ ማመን አለባችሁ፡፡

ሠዎች አይወዱኝም

ሠዎች አይወዱኝም የሚለውን ስሜት በአእምሯችን ማስረፅ ሌሎች ከእኛ የተሻሉ እንደሆኑ እንድናስብና ለራሳችን ጥረት ተገቢ ውጤት እንዳንሠጥ ያደርገናል፡፡ በሌሎች ያለመወደድ ስሜት ከተሠማን ደግሞ ለራሳችን የምንሠጠው ክብርም ይቀንሳል::

ለውጥ ማምጣት አልችልም

አንድን ነገር ለመለወጥ አቅማችሁ ካልፈቀደ ራሣችሁን አታስገድዱት፡፡ ፍፁም መሆንንም ከራሣችሁ አትጠብቁ፡፡ በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ የምትሠጧቸው ሀሳቦች የራሳቸው አዎንታዊ ተፅእኖ አላቸው፡፡ ስለዚህ ‹ለውጥ ማምጣት አልችልም›› የሚለው ቃል ለራሳችሁ መንገር ከሌለባችሁ አሉታዊ ቃላት መካከል አንዱ ነው፡፡
በአጠቃላይ ስሜታችሁን የሚጎዱ እንዲህ ዓይነት ቃላትንና አነጋገሮችን መጠቀም ትታችሁ አንደበታችሁን በመጠበቅ በየዕለቱ ለምታከናውኗቸው ተግባራት ትኩረት በመስጠት ውጤታማ መሆን ትችላላችሁ፡፡

ምንጭ፡- Psychcentral.com

@yetikurtmender

@yetikurtmender

@yetikurtmender

📨@Tikuret_bot
10 መሳጭ ቁምነገሮች ከብራዚላዊው ደራሲ
ፓውሎ ኮ'ሊሆ… The Alkemist☺️
=========================
1. አንድን ነገር የምር ከፈለግከው፣ አጠቃላዩ
ሁለንተና ያን ነገር
እንድታገኘው በአንዳች ተዓምራዊ መንገድ
ይተባበርሃል፡፡
2. አንድ ቀን ከእንቅልፍህ ስትነቃ ጊዜህ
አልቆ ልታገኘው
ትችላለህ፡፡ ስለዚህ ልታደርገው
የምትፈልገውን ነገር አሁኑኑ
አድርገው፡፡
3. ስኬታማ ለመሆን ከፈለግክ አንድ ሕግ
አክብር - ፈጽሞ
ራስህን አትዋሽ፡፡
4. የሕይወት ሚስጥሩ ሰባት ጊዜ ወድቆ
ስምንት ጊዜ መነሳት
ነው፡፡
5. ሰዎች እንዲ'ረዱህ ከመጠን በላይ
አትድከም - ሰዎች
እንደሆኑ የሚሰሙት መስማት የሚፈልጉትን
ነውና፡፡
6. ሕልምህ እንዳይሳካ የሚያደርግ አንድ
መጥፎ ነገር አለ -
አይሳካልኝም የሚል ፍርሃት፡፡
7. በዓለም ላይ ያለ ማንኛውም ሰው ሊገባው
የሚችው አንድ
ቋንቋ አለ - ፍቅር !
8. ስትሸነፍ አይደለም የተሸነፍከው፤ በቃኝ
ብለህ ስታቆም
እንጂ !
9. ምንም ምክንያት ከማያሻቸው ነገሮች
አንዱ ማፍቀር ነው፡፡
10. አንድ ነገር አስታውስ - ልብህ ያለበት
ቦታ ሀብትህም
ተቀምጧል፡


🙂🙂🙂🙂🙂🙂🙂

@yetikurtmender

@yetikurtmender


@yetikurtmender
ወጣትነት መስራት የምንችለውን ሁሉ ስህተት ሰርተን ከሁኔታው ተምሮና በስሎ የማለፊያ መስክ ነው።
Dr.Eyob


Join&share
👇
@yetikurtmender
@yetikurtmender
@yetikurtmender
.....
በህይወትህ ውስጥ😖 ጨካኝ ቀናትና ፈታኝ ጊዜያት ይኖራሉ። አንተን የሚሰሩህም እነርሱ ናቸው። በየትኛውም ከባድ የህይወት አጋጣሚ ውስጥ ስታልፍ ትልቅ 🤔ትምህርት ትማራለህ...ትምህርቱ ደግሞ አንተን😇 ይቀይርሃል። ቢያንስ ቢያንስ "ሁሉም ነገር ያልፋል" የሚል የህይወት እውነትን ትረዳለህ....
ፍቅር ስትሰጥ አትሰስት ምላሽ አትጠብቅ ምላሽ ከጠበክ ውለታ ውያለው ውለታዬን መልሱ እንደማለት ነው ፍቅር መስጠት እንጅ መቀበል አያውቅም...
በመኖርህ ውስጥ ስለኖሩልህ ሰዎች ውለታ ታስባለህ። በአንፃሩ ስለምትኖርላቸው ሰዎች እጣ ፈንታም ትጨነቃለህ። ህይወት ፍቅርን ታስተምርሃለች... በልምድ ጉዞህ ውስጥ ሰውን በማንነቱ መምረጥ ትችላለህ። ማንን መውደድ እንዳለብህም ትገነዘባለህ። በተለያዩ ክስተቶች መሀል የእውነት አንተን የሚወድህ ማን እንደነበረም ታውቃለህ። ክስተቶች ሰዎችን ያበጥራሉ
💥💥💥💥💥💥
በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ ...ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል ። ሰምቶ ማመን ፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም ። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል ።

መልካም ዕለተ ሰንበት🙏

👇
@yetikurtmender

@yetikurtmender

@yetikurtmender
Forwarded from ማረፊያ ጥበብ
ሀገሬ ዶሮ ናት

ባለጊዜው ሁሉ ከማንም የገዛት
የገዛት በሙሉ ዘቅዝቆ የያዛት
አዋቂ ነኝ ባዩ ልገንጥልሽ ያላት
ሀገሬ ዶሮ ናት!

ወንድማገኝ_ለማ
🧤የዱባና የቲማቲም ተክሎች በሳምንት እና ቀናት ውስጥ ያድጋሉ፤ ለረጅም ቀናትና ሳምንታት ፍሬያማ ሆነው ብዙ ያመርታሉ የበረዶው ጊዜ ሲያልፍ ግን ፍሬያቸው ረግፎ ይሞታሉ።

በተቃራኒው ዛፎች ለማደግ ብዙ ወራትን አመታትን ይወስዳሉ፤ ካደጉ በኋላ ግን የበረዶውንና ከባዱን ጊዜ በኩራት ያልፉታል። አየህ በፍጥነት ወደላይ ሽቅብ ከወጣህ በፍጥነት ቁልቁል ትወርዳለህ!

ዛፎቹን እንዲቆዩ ያደረጋቸው በአመታት መሬት ለመሬት የዘረጉት ስር ነው፤ አንተም ለገንዘብና ስኬት ሳትጓጓ ራስህ ላይ በደምብ ስራ! አለበለዚያ ስኬት የመሰለህ ነገር ጊዜያዊ ስለሆነ እንደ ንፋስ ሽው ብሎ ያመልጥሀል።

የተባረከ ሰንበት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
ውሳኔዋችን ስትወስን በሌላ ሰው ሀሳቦች ከተገደብክ :
በማንኛውም ተግባር ስኬታማ አትሆንም :
የራስክን ፍላጎት ወደ ገንዘብ መቀየር አትችልም

👍👍🙏🙏🙏🤚
ከመጀመሪያ ውሳኔዋች አንዱ ዝም ብለክ ማድመጥና ማየት ይሁን ።
ምን እንደምታደርግ ለዓለም ተናገር :
መጀመሪያ ግን አድርገክ አሳየው ።
ካንተ የተሻለ ሰው ጋር ስትሆን የተሻለ ትሆናለክ የተሻለ ታስባለክ ስለዚህም ምርጫክን መርምር
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏አንዳንዴ ያንተ(ቺ) አላማ ለማሰናከል ወደ ህይወታችን ውስጥ ይገቡና ለኛ የሚበጀንን ለመወሰን ይጥራሉ ይሄኔ ነው እንግዲህ የአላም ቁርጠኝነት የሚያስፈልገው ።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ታላቅነት የሚፀነሰው መፃህፍትን በማንበብ፣ ሰዎችን በማማከርና ልምድ በመውሰድ ሲሆን ታላቅነት የሚወለደው ግን ራስን በማድመጥ ነው።

የቱ ጋር እንዳለህና ወዴት መሄድ እንደምትፈልግ፤ እስካሁን ምን እንዳሳካህና ወደፊት ምን መጨበጥ እንደምትፈልግ ልታውቅ የምትችለው ጊዜ ወስደህ ራስህን ካደመጥክ ብቻ ነው። ለራስህ ጊዜ ስጥ ወዳጄ!

ሰናይ ሰንበት ተመኘንላችሁ🙏
@Inspire_Ethiopia
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
The owner of this channel has been inactive for the last 5 months. If they remain inactive for the next 27 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.
ሰላም ሰላም የ ትኩረት መንደር ቤተሰቦች... እንዴት ናቹ? አንድ ሀሳብ  ይዤላቹ መጥቻለው እንደምትወዱት አልጠራጠርም. ብዙዎቻቹ መፅሀፍ ማንበብ ፈልጋቹ አልመቻች ብሏቹ ወይም ስንፍና አሸነፏቹ ከሆነ መፍትሄ አለኝ! የማነባቸውን መፅሃፍት highlight ወይም ይዘታቸውን ከመፅሃፎቹ ያገኘውትን ቁም ነገር በፅሁፍ ከፈለጋችሁም በድምፅ አጋራቹዋለው። 1 መፅሃፍ ለ 1 ሳምንት!!  ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል

@yetikurtmender

  @yetikurtmender

🎤
2025/06/28 21:55:53
Back to Top
HTML Embed Code: