Telegram Web Link
Audio
🛑ተከታታ ስለኾነ ይደመጥ!!!

"" ሥርዓተ ጸሎት ""

"ዘሰብዐቱ ጊዜያት" (ክፍል ፩)

(መጋቢት 6 - 2016)

ዲ/ዮርዳኖስ አበበ

ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
መታዘዝ

"አቤቱ ጌታ ሆይ:- አንተ ወደዚህ ዓለም መጥተሃል::ለእናትህ ለቅድስት ድንግል ማርያምና ለቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ትታዘዝላቸው ነበር:: አንተ ራስህ ፈጣሪ ሆነህ ሳለህ ለፈጠርሃቸው ሰዎች በፍቅር ትታዘዝላቸው ነበር:: አንተ እኮ ሰማይና ምድር የሚታዘዙልህ አምላክ ነህ! መታዘዝህ ሥልጣንህን አያጠፋውም:: መታዘዝን በእኔ ውስጥ ቀድስ  ከመታዘዝ ሩጬ እንዳላመልጥ ከአንተ ጋር እሰረኝ:: እኔ በአንተ መታዘዝ ውስጥ ተካፋይ መሆኔ ይታወቀኝ ዘንድ ትእዛዝህን እቀበላለሁ:: በእኔ ዐይኖች ፊት እንደመገረፍ ስለሚቆጠር መታዘዝ ለእኔ መራራ ነው:: ከአንተ ጋር ከሆንኩኝ ግን እጅግ ጣፋጭ ነው:: የአንተን የመታዘዝ ልምድ ለእኔ አስተምረኝ፣አለማምደኝ አድለኝም:: ይህን ካደረግህልኝ እውነተኛ ትዛዥ የሆንኸው አንተን በእኔ ውስጥ ስትሰራ እመለከታለሁ::ጽድቅን ለመፈፀም ታዛዥ የሆንኸው አንተ ለእኛ ምሳሌ ነህ::" /ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ

@dmse_tewado
​​​​ቅድስት (የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት)

«ቅድስት» ማለት የዘይቤ ፍችው « የተቀደሰች የተለየች » ማለት ነው። ምስጢራዊ መልእክቱ ግን የምስጢረ አድኅኖት ታላላቅ ሥራውን ለመጀመር መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ በገዳመ ቆሮንቶስ ገብቶ ከቆመ ሳያርፍ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ የጾማት የአርብዓው ቀንና ሌሊት ልዩ የሆነችና ክብርት ጾም የምትጀመርበትን ሁለተኛ ሳምንት ከልብ ያሳስበናል፡፡ ማቴ. 4-2

ቅድስት የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ስያሜውም ከኢትዮያዊው የዜማ ሊቅ ከቅዱስ ያሬድ የተገኘ ነው። ከዚህ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ይዘመራል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ሰንበቱን ስለ ቅድስና ልጆቿን ታስተምርበታለች ፡፡

በቅዳሴ ጊዜ የሚሰበከው ምስባክ ፤ የሚነበቡ መልዕክታት ፤የሐዋርያት ሥራ ና ወንጌል ስለ ቅድስት የሚያስተምሩ ናቸው፡፡

‹‹ቅዱስ›› ማለት ልዩ፤ ክቡር ማለት ነው፡፡እግዚአብሔር አምላካችን በባሕርዩ ቅዱስ ነው፡፡ ይህም ቅድስና ከማንም ያላገኘው የባሕርይ ገንዘቡ ነው። መጻሕፍትም የባሕርይ ቅድስናውን ተባብረው መስክረዋል፡፡ ባባሕርዩ ቅዱስ ስለሆነ ‹‹ቅዱስ፡ቅዱስ፡ቅዱስ›› እየተባለ ይመሰገናል፡፡ ( ኢሳ 6፡1-3፤40፡25 ራዕ 15፡4 ፤ 1ሳሙ2፡2-3፡፡) እኛም ቅዱስ ልጁ በሥጋ ተገልጦ እንዳስተማረን በየዕለት ጸሎታችን ‹‹ስምህ ይቀደስ›› እንለዋለን፡፡

የቅድስና ምንጭ ፡ ቅድስናን የሚሰጥ እርሱ ብቻ ነው፡፡ ‹‹ ቅዱስ ›› የሚለው ቃል ለሰዎች ፡ለመላእክት ፡ ለቦታ ፡ለዕቃ: ለዕለታት … ቢቀጸልም ቅድስናቸው በባሕርይው ቅዱስ ከሆነው ከእግዚአብሔር የተገኘ ነው፡፡ ይህም የጸጋ ቅድስና ይባላል፡፡

እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ በመልኩና በምሳሌው አክብሮ የፈጠረንን እኛም ቅዱሳን እንድንሆን ይፈለጋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁን›› ተብሎ ስለተጻፈ የጠራቸው ቅዱስ እንደሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ›› ያለንም
ይህንን ሲያስተምረን ነው። ከመፈጠራችን አስቀድሞ መጠን በሌለው ፍቅር የወደደን እግዚአብሔር ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣን ፤ ለውርደት ሳይሆን ለክብር፤ ለርኩሰት ሳይሆን ለቅድስና፤ ለሞት ሳይሆን ለሕይወት ነው፡፡ የመፈጠራችንም ዓላማ በፊቱ በፍጹም ምግባርና ሃይማኖት በመመላለስ ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነው፡፡ ብርሃን ከጨለማ፡ ጽድቅ ከኃጢአት፡ ጋር ኅብረት የለውምና ከእርሱ ጋር ለዘላለም ነግሰን ለመኖር በቅድስና መኖር ይጠበቅብናል፡፡

ቅድስናችን በኑሮአችን ሁሉ እንዲሆን ታዘናል (1ጴጥ1፡15)፡፡ ስለዚህ በተሰማራንበት የሥራ መስክ ፣ በማኅበራዊ ኑራአችን ፣በምንበላው ምግብ ፣በምንለብሰው ልብስ ፣ በንግግራችንና በመሳሰለው ሁሉ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘውን በማድረግ እግዚአብሔርን በሚሞት ሥጋችን እናክብረው፡፡ ‹‹እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ የኃጢአትንም ጭንቀት ከእኛ አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግስት እንሩጥ፡፡

የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ ፣ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል ›› ተብሎ እንደተጻፈ ደምን እስከ ማፍሰስ ድረስ ተጋድሎ አድርገን ከኃጢአት ርቀት በቅድስና እንድንኖር ይገባናል (ዕብ 12፡1)።

ሥጋዊ ምኞታችንንና መሻታችንን ሰቅለን አሮጌው ሰዋችንን አስወግደን ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለን በቅድስና እንድናኖር ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን፡፡
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ቅዱሳን አንተን ባወቁበት መጠን አውቅህ ዘንድ እሻለሁ የቅዱሳኑ ንፅህና ግን በእኔ ዘንድ የለም። እጠጋለው ኀጢአቴም ዳግመኛ ታርቀኛለች እጠጋለው ኀጢአቴም ዳግመኛ ታርቀኛለች።አቤቱ ጌታዬ ሆይ አደከመቺኝ አንተን በፍፁም ንፅህና አፈልግህ ዘንድ ከለከለቺኝ።ደክሞኝም ፈፅሜ እንዳልተውህ ያቀመስከኝ የፍቅርህ ጣዕም ትዝ ይለኛል። አቤቱ ተጨነኩ አንተስ እስከመቼ ዝም ትላለህ? እስከመቼስ ለፈቃዴ ትተወኛለህ?...

አቤቱ አንተን እንደወደዱህ እንደ ቅዱሳንህ ከፈቃዴ እንድሰዋልህ ቅድስት የምትሆን በጎ ጭካኔንን አስጨክነኝ።

“ከፈቃዴ እሠዋልሃለሁ”
  — መዝሙር 54፥6


https://www.tg-me.com/dmse_tewado
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤

ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/

https://www.tg-me.com/dmse_tewado
Audio
🔴ስንክሳር የመጋቢት13

ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
Audio
"" ይህንንስ እውነት አልሽ! "" (ዮሐ. ፬:፲፰)

"ዜናሃ ለብእሲት ሳምራዊት (ቅድስት ፎጢና)"

(መጋቢት 11 - 2016)

ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
#ምኩራብ
(የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት)

ምኩራብ ማለት ለአምልኮትና ለትምህርት ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጥ የአይሁድ ቤተ ጸሎት ነው። ጌታ በመዋዕለ ስብከቱ በእስራኤል ሀገር ብዙ ምኩራቦች ስለነበሩ እየገባ ወንጌልን አስተምሮባቸዋል። በዚህም “ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሀረ ቃለ ሃይማኖት” እንዲል ቅዱስ ያሬድ ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገብቶ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ። ከሚለው የቅዱስ ያሬድ ዜማ ሥያሜውን አግኝቷል።

በምኩራብ ጸሎትና ትምህርት ይፈጸምበታል። መሥዋዕት ግን አይከናወንም። መሥዋዕት ግን በታላቁ ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ብቻ ይፈጸም ነበር። በዚህ ሳምንት የሚነገረው ታሪክ ጌታ ቤተ መቅደሱን የገበያ ማዕከል አድርገው ሸቀጥ ዘርግተው በጉን ላሙን ርግቡን እየሸጡ አገኛቸው። በዚህ ተቆጥቶ በጉን ላሙን ርግቡን ከምኩራብ አስወጥቶ ሸቀጣቸውንና መደርደሪያቸውን እንዲሁም ወርቅና ብራቸውን በነፋስ በተነባቸው ይላል።

በዚህ ሁኔታ ከቤተ መቅደስ አስወጥቶ "ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች እናንተ ግን የሽፍቶችና የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት" በማለት ወቅሷቸዋል። “አሰስሉ ወአውፅኡ ዘንተ እምዝየ ወኢትረስዩ ቤተ አቡየ ቤተ ምሥያጥ” እንዲል ዮሐ. 2፥16፤ ማቴ. 21፥13። ይህን ተአምር በማሳየት ቤተ ጸሎት የተቀደሰ ከገበያ የተለየ መሆኑን አስተምሮበታል።

በሰንበተ ምኩራብ ጌታ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለዋጮችን ማስወጣቱ ወርቅና ብሩን በነፋስ መበተኑ ላሞችን በጎችን በጅራፍ መግረፉ ቤተ መቅደሱን ማንጻቱ ወዘተ ይነገራል።

(የዚህም በዓል ታሪክ ዝርዝር ሁኔታው ማቴዎስ 21፥12-13 ላይ ተጠቅሷል፡፡)

#የቅዳሴ_ምንባባት

ቆላስ. 2፥16-23
«እንግዲህ በመብል ወይ በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፣ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው፡፡ .......፡፡»

ያዕ. 2፥14-26
«ወንድሞቼ ሆይ፣ እምነት አለኝ የሚል፣ ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን ......፡፡»

ሐዋ. 1ዐ፥1-9
«በቂሣርያም ኢጣሊቄ ለሚሉት ጭፍራ የመቶ አለቃ የሆነው ቆርኔሌዎስ የሚሉት አንድ ሰው ነበር፡፡ እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክና የሚፈራ ለሕዝብም እጅግ ምጽዋት የሚያደርግ ወደ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ የሚጸልይ ነበረ፡፡ ....፡፡"

#ምስባክ- መዝ 68፥9
እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ
ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ
ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡

(የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና
የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና
ነፍሴን በጾም አስመረርኋት፡፡)

#ወንጌል፡- ዮሐ 2፥12-25
«ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፣ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ፡፡ የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡ ወደ መቅደስም በሬዎችንና በጎችን ርግቦችንም የሚሸጡትን ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፤ የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፣ .....፡፡»

(ከመድብለ ታሪክ እና ግጻዌ የተወሰደ)
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
#ለሰይጣን_ጊዜ_የለኝም

መምህሩ ተማሪዎችን ሊፈትን በአንድ ሰዓት ውስጥ የሚመለሱ ሁለት ጥያቄዎችን አዘጋጀ። ተማሪዎች ራሳቸውን አዘጋጅተው ወደ ፈተና ክፍል ገበተው ወንበር ወንበራቸውን ይዘው ይጠብቃሉ። መምህሩ የፈተና ወረቀቱን ይዞ ገባ። የፈተናውን መመሪያ ተናግሮ የፈተና ወረቀቱን አደለና ሰዓት ይዞ "መጀመር ትችላላችሁ" አላቸው።

የመጀመሪያው ጥያቄ ስለ እግዚአብሔር የምታውቀውን ጻፍ የሚል ነው። ሁለተኛው ጥያቄ ደግሞ ስለ ሰይጣን የምታውቀውን ጻፍ ይላል፡፡ "ለአንዱ ጥያቄ 30 ደቂቃ ነው የተሰጠው ማለት ነው" ብለው ሰዓት ሳያልቅባቸው ሁለቱንም ጥያቄዎች ለመጨረስ ተሎ ተሎ ይጽፋሉ። ፈተና ከተጀመረ 30 ደቂቃ መሙላቱ ሰዓት ያዩ ተማሪዎች ከአንደኛው ጥያቄ ወደ ሁለተኛው አልፈው መስራት ጀምረዋል፡፡ በአእምሮአቸው የመጣላቸውን ሐሳብ በቻሉት ፍጥነት ይጽፋሉ፡፡ መምህሩም ሁሉም ተማሪ የየራሱ መስራቱን እየዞረ ይከታተላል።

"ለማጠናቀቅ አስር ደቂቃ ይቀራችኋል" አለ መምህሩ። መልሰን ጨርሰናል ብለው ያሰቡ ተማሪዎች ግማሾቹ ፈተና ወረቀቱን ለመምህሩ ሰጥተው ሲወጡ፥ ሌሎቹም የመለሱትን ደግመው ያነባሉ፡፡ ያልጨረሱም የቀረችውን ደቂቃ ለመጠቀም ይጣደፋሉ። ከአስር ደቂቃ በኋላ "ሰዓት አልቋል ሁላችሁም መስራት አቁሙ" አለ መምህሩ፡፡ እየዞረም ፈተና ወረቀቱን መሰብሰብ ጀመረ፡፡ አንድ ተማሪ ጋር ሲደርስ ግን አሁንም መልስ እየጻፈ ያገኘውና "ሰዓት አልቋል ሲባል አትሰማም እንዴ?" ብሎ ወረቁትን ተቀበለው፡፡

ሁሉም ተማሪዎች ለሁለቱም ጥያቄ የሚያውቁትን የመለሱ ሲሆን አንዱ ተማሪ ግን ለጥያቄ ቍጥር አንድ (ስለ እግዚአብሔር የምታውቁትን ጻፉ ለሚለው) ብቻ ነው መልስ የሰጠው። መምህሩ በዚህ ተማሪ መልስ ተገርሞ "ለምንድ ነው ለሁለቱንም ጥያቄዎች መልስ ያልጻፍከው?" ብሎ ጠየቀው። እርሱም "#ለሰይጣን_ጊዜ_የለኝም" ስለ እግዚአብሔር ራሱ የማያልቅ ቢሆን እኮ ነው የተሰጠን ሰዓት አልቆ ገና እየጻፍኩ ያስቆምከኝ" አለው ይባላል፡፡

እውነት ነው ነገረ እግዚአብሔር ቢጽፉት፣ ቢናገሩት፣ ቢሰሙትና ቢያዜሙት የማያልቅና የማይሰለች ጥልቅ ምሥጢር ነው። የፈለግነው ያህል ጊዜ ብንሰጠው እንኳን በጅምር እያለን ጊዜው ያልቃል። በቃሉ ፍቅር፥ በምሥጢሩ ተመስጦ ውስጥ ሆነን ወደማያልፈው ዓለም እንሻገራለን፡፡

ይህንን ገንዘብ ለማድረግ ግን ለሰይጣንና ለጉዳዮቹ የሚሆን ጊዜ የለኝም ማለት ይገባል፡፡ ከጊዜ ውጭ የሚሰራ ነገር የለምና ለሰይጣን የሚሆን ጊዜ ከሌለን ከኃጢአት ሁሉ መራቃችን አይደል? ለሰይጣን ጊዜ ላለመስጠት ደግሞ ከእርሱ ጋር መጣላት ነው። መቼም ሰው ለጠላው ነገር የሚሆን ጊዜ አይኖረውም። ምንም ስራ ባይኖረውም እንኳ ከጠላው ጋር ላለመገናኘት ምክንያት ፈጥሮ ይርቅ የለ? ስለዚህ ለሰይጣን ጊዜ እንዳይኖርህ ከእርሱ ጋር ተጣላ። የሚገርመው ከሰይጣን ጋር ስትጣላ ደግሞ ከሰው እና ከእግዚአብሔር ጋር በፍቅር መኖር ትችላለህ፡፡ ከ24ቱ ሰዓት ለሰይጣን የሚሆን ጊዜ ከሌለን መቼም ቢሆን ኃጢአት ሊያሰራን የሚችልበት ዕድል ወይም አጋጣሚ አይኖርም። የተሰጠን ጊዜ ለሰጪው አምላክ መልሰን እንሰጠው ዘንድ ማስተዋሉን ያድለን።
Audio
"" ሥርዓተ ጸሎት "" (ክፍል ፪/2)

"ጸሎት ዘሰብዓቱ ጊዜያት" (ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

(መጋቢት 13 - 2016)

ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ትውልድ_ሁሉ
ትውልድ ሁሉ ንጽናሽን ክብርሽን ሁልግዜ ያደንቃሉ /፪/
መመኪያችን መጠጊያችን ተስፋችን አንቺ ነሽ እያላሉ /፪/
ያገኑሻል ያከብሩሻል ፍጥረታት በሙሉ /፬/
2024/06/01 05:57:51
Back to Top
HTML Embed Code: