Telegram Web Link
ሀገር አጣብቅኝ ውስጥ ባለችበት ሙፍቲ ዛሬም ህዝበ ሙስሊሙን ወደ አመፅ ሚያሰገባ ተግባር እየፈፀሙ ነው

ሰበር ዜና
***
ከለዉጡ በኋላ የተባረሩት በአዲስ አበባ 10ሩም ክፍለ ከተሞች የነበሩት የቀድሞ የአዲስ አበባ መጅሊስ አመራሮች ዳግም ወደቦታቸው እንዲመለሱ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር በደብዳቤ ጠየቁ!
-------
RN05
.
ሙፍቲ ሃጂ ዑመር የቀድሞ ህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት ጋሻ-ጃግሬዎች የነበሩ እና በሙስሊሙ ላይ ተጭነው ለዛ ሁሉ ግፍ እና መከራ ተባባሪ የነበሩ ለዉጡ ሲመጣ ምንም ሳይጠየቁ ከስልጣናቸው ብቻ እንዲወርዱ ከተደረጉት መሃል ከነበሩት ዉስጥ የአዲስ አበባ መጅሊስ የአስሩም ክፍለከተሞች የቀድሞ ባለስልጣናት ወደ ቀድሞ ስልጣናቸው እንዲመለሱ ለሚመለከተው አካል ደብዳቤ መጻፋቸውን የሚገልጽ መረጃ ደርሶናል ።
.
በአንድ በኩል "ህዝባዊ መጅሊስ ለማቁቋም ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር አብሬ እየሰራሁ ነው" የሚሉት ሙፍቲ ሃጂ ዑመር የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዘዳንት የሸህ ሱልጣን አማንን ደብዳቤ በመሻር የቀድሞው አህባሽ መራሽና ህዝበ ሙስሊሙን ለበርካታ ስቃዮችና እንግልቶች ያበቃው መጅሊስ ወደ ስልጣን እንዲመለስ መወሰናቸውን እና ለዚሁም እየሰሩ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
የሳውዲ መንግስት ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍ በሚስኪን ስደተኛ ኢትዮጲኖች ላይ ለምን ይፍፅማል ? ረሱል እንኳን ዱአ ያረገላት ሀገር እኮ ናት ሀበሻ
https://youtu.be/0prvHWw9ZFA
በደሴ ከተማ የሰዓት እላፊ ታወጀ
================

የደሴ ከተማ አስተዳደር ለከተማዋ ሕዝብ “ሁለንተናዊ ደህንነት ሲባለ” የሰዓት እላፊ አዋጅ መጣሉን አስታወቀ።

የከተማ አስተዳደሩ ፍቃድ ከተሰጣቸው የጸጥታ አካላት ውጪ የትኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ማድረግ ተከልክሏል ብሏል።

የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ደግሞ እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ብቻ እንዲሆን መወሰኑን የከተማዋ አስተዳደርን በመጥቀስ የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በፌስቡክ ገጹ ላይ አስታውቋል።

ከሰሞኑ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣውን ግጭት በመሸሽ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ከሰሜን ወሎ አካባቢዎች ወደ ደሴ ተፈናቅሎ እየገባ እንደሆነ ሲነገር ቆይቷል።

የከተማ አስተዳደሩም በደሴ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተፈናቃይ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የሐይማኖት ተቋማትን ጨምሮ ከልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሠራት ላይ እገኛለሁ ብሏል።
ሰበር ዜና መጅሊስ

የመጅሊሱን ህንፃና መሬቶች የነጃሺ የመስጂድና የምርምር ተቋም እነረዲሁም አዲስ የተሰራውን የመጅሊስ ህንፃ ከታለመለት አላማ ውጪ ሸንሽኖ በሕገ ወጥ መልኩ ለማከራየት እየተሰራ መሆኑ ታወቀ

ለመጅሊሱ ለውጥ ክሽፈት ሲታትሩ የነበሩት ግለሰቦች እውነተኛ አላማ መጋለጥ ጀምሯል!

የመጅሊሱ ፀረ ለውጥ ሀይሎች አላማ አልፋና ኦሜጋ የሙስሊሙን ተቋም መዝረፍ እና ትኩረታቸው ሁሉ የጥቂት ግልሰቦችን ጥቅም ማስጠበቅ እንደነበረ የሥራ አመራር ቦርዱ በተደጋጋሚ ሲገልፅ መቆየቱ ይታወሳል። በተለይም በአሁኑ ጊዜ ህዝቡ ለወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ሙሉ ትኩረቱን ሰጥቶ ባለበት ወቅት ለህገወጥ ሥራዎቻቸው ህዝቡ ስለሚዘናጋ ያመቸናል በሚል የመጅሊሱን ህንፃና መሬቶች ከታለመለት አላማ ውጭ ለመጠቀም በይፋ ማስታወቂያ አውጥተው ተከራዮችን በማፈላለግ ላይ እንደሚገኙ የሥራ አመራር ቦርዱ ደርሶበታል።
እነዚህ ህገ ወጥ ግለሰቦች የዋና ግቢ አዲሱን ህንፃ ከታለመለት የመጅሊሱ ህዝባዊ አገልግሎት በተቃራኒ በረጅም ጊዜ ኪራይ ገንዘብ ለተለያዩ የግል ጥቅማጥቅሞች ክፍያ ለማዋል በእንቅሰቃሴ ላይ ይገኛሉ።

ይባስ ብሎም የነጃሺ አለም አቀፍ የመስጊድና የምርምር ተቋም ቦታ ለታለመው ግንባታ የቀረበውን የ60 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ አንቀበልም በማለት ከመለሱ በኋላ አሁን ግቢውን በጥቃቅን ሱቆች ሸንሽኖ ለረጅም አመታት ለማከራየት እየተሞከረ ይገኛል። በዚህ ቦታ ላይ የይገባኛል ክርክር ካስነሱት ኃይሎች ግፊት በተጨማሪ ቦታው በመንግስት የተሰጠው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገቢው ግንባታ እንዲገነባበት ካልሆነ መልሶ ለመቀማት ከማስጠንቀቂያ ጭምር ጋር እንደነበር ይታወሳል። በመሆኑም አሁን የተያዘው የኪራይ ሰብሳቢነት ሂደት ከተሳካ ከቦታው ቅንጥብጣቢ ለመሰብሰብ በረጅም ጊዜ ውል የግንባታውን ሂደት እንዳይሳካ በማድረግ የሙስሊሙን ህልም ማጨለም ይሆናል።
በዚህ ሂደት እንደ ከዚህ ቀደሙ የመጅሊስ አመራር የመጅሊሱን ንብረቶች በመሸጥ እና በማከራየት የግል ጥቅሞችን በማጋበስ ህዝቡ ገፍቶ "ተቋሜን" ብሎ ሲጠይቅ ያለምንም ተጠያቂነት ዞር ለማለት እንደታሰበ ያሳያል።
ስለሆነም ከላይ የተገለፀው የህንፃ እና ቦታ ኪራይ ውሳኔ በህገ ወጥ አካላት የተላለፈ የህዝቡን ጥቅም በእጅጉ የሚጎዳ ተግባር መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል። በተጨማሪም ይህን የቀረበውን ህገወጥ የኪራይ ማስታወቂያ ተከትሎ ነገ በህግ ሊያስጠይቅ ስለሚችል ማንም ወገን የገዛ ገንዘቡን እንዳያባክን እና የህዝበ ሙስሊሙ ሀብት ምዝበራ ላይ እንዳይሳተፍ የሥራ አመራር ቦርዱ በጥብቅ ያሳስባል።

ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ ተጨማሪ መረጃዎችን በተከታታይ የምናጋራ ይሆናል።
አስደሳች ዜና ታሊባን እነ አሜሪካን በጦርነት በማሸነፍ አፍጋኒስታንን ኢስላማዊ መንግስት ስር ተቆጣጠረች አላሁ አክበር
https://youtu.be/JHcqttMTgkE
ኢና ሊላሂ ወ ኢነ ኢለይሂ ራጅዑን

ተወዳጁ መሀመድ አወል ሳላህ ወደ አኼራ ሄደ

አላህ ለሱ ጀነተል ፍርዶስን ለቤተሰቡ መፅናናትን እንመኛለን
ሁላችንም ዱአ እናድርግለት

ዙህር ላይ በኮልፌ መካነ መቃብር ሁላችንም እንገኝ
አላህ ይዘንለት ያረቢቢ
አምስት ልጆቹን ጥሎ ወደማይቀረው ህይዎት አልፏል።

Share በማድረግ ያሰራጩ
የወንድማችን ሙሐመድ ሳልህ ልጆች ልጆቻችን ናቸው።
ቤተሰቦቹ ቤተሰቦቻችን ናቸው። እርሱን ማጣት ሃዘኑ ከባድ ነው። ከወንድማችን ቤተሰቦች ጎን በመቆም የአላህን ውዴታ እንፈልግ።

በቤተሰቦቹ ፈቃድ የቤተሰብ እድር አባላት በሆኑ ሶስት ሰዎች የባንክ ሂሳብ ተከፍቷል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000427892232
ይማም አህመድ
ኢስማዒል ይስማው
ሙሐመድ ተስፋዬ
የኡስታዝ መሀመድ አወል ሳላህ የቀብር ስነስርአት ተፈፀመ አላህ የጀነት ያድረገው

ሁላችንም በዱአ አንርሳው
አምስት ልጆቹን ጥሎ ወደማይቀረው ህይዎት አልፏል።

የወንድማችን ሙሐመድ ሳልህ አምስት ልጆቹን ጥሎ ወደማይቀረው ህይዎት አልፏል። ከወንድማችን ቤተሰቦች ጎን በመቆም የአላህን ውዴታ እንፈልግ።

በቤተሰቦቹ ፈቃድ የቤተሰብ እድር አባላት በሆኑ ሶስት ሰዎች የባንክ ሂሳብ ተከፍቷል።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000427892232
ይማም አህመድ
ኢስማዒል ይስማው
ሙሐመድ ተስፋዬ
«ኢንና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!»

የእስር ባልደረባዬ ወንድም ሙሐመድ አባተ ጠያቂያችን የነበሩት እናቱ አርፈዋል። አላህ በምህረቱ ይመልከታቸው። በትዕግስታችሁ አላህ ላንተና ለመላው ቤተሰባችሁ ታላቅ ምንዳን ይመንዳችሁ። ለሞቱት እናታችንም አላህ ጀነተል ፊርደውስን ይለግሳቸው። መከራችሁንም አላህ በመልካም ሁኔታ ይለውጥላችሁ።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1028367904668415&id=100024856459321
በአማርኛ ተፅፎ ወደ ዐረብኛ የተተረጎመ የመጀመሪያው ኢስላማዊ የታሪክ መፅሃፍ።

«ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከ615-1700 የጭቆናና የትግል ታሪክ» የተሰኘውና የዛሬ አስር ዓመት ለሕትመት የበቃው የኡስታዝ አህመዲን ጀበል የታሪክ መጽሐፍ ወሂብ አብዱልዋሲ እና ሙክታር ከዋጃ በተሰኙ ግለሰቦች አማካኝነት ከአማርኛ ወደ አረብኛ ተተርጉሞ ለዐረብኛ አንባቢያን በኳታር ሀገር ዶሃ ለህትመት በቅቷል።

መጽሐፉ ለጊዜው በኳታር ሀገር በሚገኘው በግዙፉ «ጀሪር የመጽሐፍት መደብር» ሦስቱ ቅርንጫፎች ዉስጥ በመሸጥ ላይ ይገኛል።
2024/06/16 02:41:48
Back to Top
HTML Embed Code: