Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ውድ የቻናላችን አባላት እንኳን ለአዲሱ አመት 2013 በሰላም አደረሳችሁ በአሉ የሰላም የፍቅር የመተሳሰብ ይሁንልን መልካም በአል
Channel photo updated
እንኳን ለ2013 ዓ.ም አደረሰን!
መልካም ይሁንልን!
💚💛❤️

Bara Haaraa Gaarii
Hambaliyo sanad cusuub
ርሑስ ሓድሽ ዓመት
Qusba liggidii Sinnil Yamqay
Happy New Year

@youthkiper
ኢትዮጵያ አዲስ የገንዘብ ኖቶቿን ይፋ አደረገች!

ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት መጠቀም እንደምትጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አምመድ (ዶ/ር) ይፋ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ይህ አዲሱ የገንዘብ ኖት የ200 ብር ገንዘብ ይጨምራል ብለዋል። እነዚህ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶች ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ ይረዳሉ ሲሉም ነው የጠቀሱት።

@
[ ከ200 በላይ አስገራሚ የታክሲ ላይ ጥቅሶች ]
1. እንኑር ብለን ነው እንጂ መሞት አያቅተንም!
2. የያዝናት እድሜ አይደለም ለጠብ ለፍቅር እንኩአን
አትበቃም!
3. ብቸኝነት ደስ የሚለው ሽንት ቤት ብቻ ነዉ
4. ማች ከመሞቱ በፊት ፍቅረኛውን ዜብራላይ ይስም ነበር
5. ጭቅጭቁን ትተን ብንፋቀር ምነው ሁሉም ቅርብ ወራጅ ነው
ከፈጣሪ በቀር
6. ታክሲ ዉስጥ መጨቃጨቅ ኣሸባሪነት ነው
7. ሰዉ ብቻ ነዉ የምንጭነዉ በስህትት የተሰቀለ ካለ ይዉረድ
8. የሰራ የእጁን የተቀመጠ የቂጡን ያገኛል
9. አንገትክ ብቆረጥም ዋናዉ ጤና ነዉ
10. መብትዎን ታክሲ ላይ ትዝ ኣይበልዎ
11. ጤፍና በርበሬ ሲወደድ ችላቹ ታክሲ ላይ ታማርራላቹ
12. መንግስትና ተሳፋሪ ሊወርዱ ሲሉ ነገር ነገር ይላቸዋል
13. ስልጣን የህዝብ ማስተዳደሪያ እንጂ ማስፈራሪያ አይደለም
14. የምተኛዉ የማይተኛ ጌታ ስላለኝ ነዉ
15. አምላኬ 100000000 ዶላር እና ጤንነቴን ስጠኝ
16. ጡትና መንግስት ጊዜውን ጠብቆ መውደቁ አይቀርም
17. ምከረው ምከረው አንቢ ካለ በሴት አስመክረው
18. ጎንበሥ ቀና ብዬ ባገለግላቸው ከወንዝ የተገኘ ድንጋይ
መሠልኳቸው
19. ፍቅረኛዬን አጣው ብለህ አትጨነቅ ታክሲም ማጣት አለና
20. ጠጋ ጠጋ በሉ! ! በኛ ታክሲ ተዋውቀው ብዙ ሰው ተጋብቷል
21. ነገረኛ ተሳፋሪ አደባባይ ላይ " ወራጅ አለ " ይላል
22. ሰውን ስትወድ ከመልካም ስብዕናው ውጪ ምኑንም ሳታይ
ይሁን
23. አንድ ማፍቀር ግድ ነው ሁለት ማፍቀር ግን ንግድ ነው
ሶስት ማፍቀር ግን ኮንትሮባንድ ነው
24. መዶሻ ጭንቅላት ያለው ሰው ሁሉም ስው ሚስማር
ይመስለዋል
25. ከሰራህ ትበላለህ ካልሰራ ሲበሉ ታያለህ
26. እግዝአብሄር ድሃን ማስደሰት ሲፈልግ አህያውን አጥፍቶ
እንዲያገኘው ያደርጋል
27. የበታችነት ከተሰማ ዛፍ ላይ ዉጣ
28. ጨበሶ ከመቃጠል በልቶ መመዘን ይሻላል
29. ቅናት ያገረጣዉ ፊት ቅባት አያወዛዉም
30. አስተዉሎ የሚራመድ ጫት ተራ ይደርሳል
31. እንኳን ተሳፋሪ ሙታንም ይሸጋሸጋል
32. ተሳፍሪ ጠጋጠጋ በሉ የአባይ አደራ አለብን
33. ባለጌ ሰው ዜብራ ላይ ወራጅ ይላል
34. ከጫት ሙቀት እንጂ አይገኝም እውቀት
35. ዜብራውን አንስተን አህያ እናስተኛልህ ወይ(ለሹፌሮች)
36. ለወሬኛ እና ለአምስት ሳንቲም መልስ የለንም
37. ፍቅር ፍቅር እያልሽ አትጨማለቂ ልቤ ዉስጥ ለመግባት
ጫማሽን አዉልቂ
38. አባይን ያላየ ሄዶ ማየት ይችላል
39. ሴት ልጅ ታርሳ የምትገኝ ቢሆን ኖሮ ወንድ ሁላ ገበሬ
ይሆን ነበር
40. ሰዉን አትናቁ ሰው እንዴት ይናቃል ቅማል እንኳን በአቅሙ
ሱሪ ያስወልቃል
41. እስቲ ይሁን ብለን የተከለዉ ቃጋ ጎበስ ጎበስ አለ እኛኑ
ሊወጋ
42. ባላገር ሲሰለጥን በዜና ይደንሳል
43. መሀይም ሀብታም ደሃን የፈጠረ ይመስለዋል
44. ምን ጊዜው ቢረዝምም ቋንጣ እና ባለ ስልጣን መውረዱ
አይቀርም
45. ዝናብ ጥሎ ጥሎ መሬቱ ጭቃ ሲሆን ያን እያነሱ
ግርግዳዉ ላይ ልጥፍ
46. በፍየል ዘመን በግ አትሁን
47. ሹፌሩን በፍቅር ማሣቅ እንጅ በነገር ማሣቀቅ ክልክል ነው
48. ትሞህርት በዱላ ቢሆን ኖሮ አህያ ፕሮፌሰር ትሆን ነበር
49. ሴት ልጅ ሒሣብ ሥትማር እንጂ ስትከፍል አይተን አናቅም
50. ደሀ ነዉ ችስታ ነዉ ብለሽ ትይኛለሽ ጭንና ዳሌ እንጂ
አንችስ ምን አለሽ
51. መልስ ለረሳ ማትሪክ ላይ እንመልሳለን
52. ሴትና ሎተሪ ለማይፈልጋቸዉ እንጂ ለሚፈልጋቸዉ
አይወጡም
53. ሹፌር ለጠበሰ ባለ 100ብር ረዳት ለጠበሰ ባለ 50
ብርካርድ እንሞላለን
54. የቅድብ ፀጉርና ምቀኛ አያድጉም
55. ንፁህ ህሊና ምቹ ትራስ ነዉ
56. ላታመልጪኝ አታሩጪኝ
57. ስራ ያጣ ተሳፋሪ ጋቢና ይቀመጣል
58. የማያልፍለት ደሃ ሀብታምን ይጋብዛል
59. በባጃጅ ስትጋዝ ንፋስ መታኝ አትበል ባጃጅ የመኪናዎች
የልጅ ልጅ ናትና
60. ደንበኛ ካልቀበጠ ንጉስ ነዉ
61. ጧት ስትሄድ በእንቅፋት የመታህ ድንጋይ ማታ ከደገመህ
ድንጋዩ አንተ እንጂ እሱ አይደለም
62. ጋይስ እንጀራ የለም እንጂ ወጥ ቢኖር ኖሮ በልታቹ ትሄዱ
ነበር
63. ድብርትንና ጥይትን ተኝቶ ማሳለፍ ነው
64. ጠጋ ጠጋ በሉ ሁሉም ቅርብ ወራጅ ነው ከፈጣሪ በቀር
65. ከድሃ ቤት ጥቅስ ከሀብታም ቤት ጥብስ አይጠፋም
66. የቤትክን አመል እዛው
67. በፍርፍር ያዘነ በጥብስ ይደሰታል በፍቅር ያዘነ.....?
68. የመኖር ወርቃማ ዘዴ መቻቻል ብቻ ነው
69. ሁለት ክንድ አንድ ሜትር ነው ከዛ ያሳለፈ ውሸታም ነው
70. የሰው ልጅ አረም የበዛበት የመከራ ተክል ነው
71. የሚፈልገውን ያላገኘ ልብ ዘውትረ መንገደኛ ነው
72. የአለም ሙቀት መጨመር መንስኤ ጭቅጭቅ ነው
73. ፈገግታዬ ብዙ ነው ልቤ ግን ለአንድ ሠው ነው
74. ባለጌና ዋንጫ ወደ አፉ ሰፊ ነው
75. መስታወት በቆጣሪ ቢሆን ኖሮ ሴቶች ምን ይዉጣቸዉ ነበር
76. ድሀ በህልሙ ቂቤ ባይጠጣ ኖሮ ምን ይዉጠዉ ነበር ?
77. ማንበብ ከቻልክበት ሁሉም ሰው መፅሀፍ ነው
78. ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ቃል አትናግር
79. ባጃጅን አወቅሽ አወቅሽ ሲሏት ታፔላ አወጡላት
80. ይሄ አናት ለቴስታ እንጂ ለትምህርት አይሆንም
81. ለኛ ከራሳችን የበለጠ የሚያስብልን የለም
82. ዝቅ ብለህ ስትሰራ ሁሉም ነገር ዝቅ ብሎ ይታይሃል
83. ማንም ሠው የጣለውን ሲያነሱበት አይወድም
84. ከሹፌሩ ጋር የምትጨቃጨቁ በኢቦላ እለቁ
85. ፍቅር ካለ ታክሲ ባሥ ይሆናል
86. የኪስ ሌቦች ቆዩ ሒሳቡን ሳንቀበል ስራ እንዳትጀምሩ
87. ሲጠሉህ ሳይሆን ሲወዱህም ለምን በል
88. ለሰዉ ሳይሆን ለራስህም ታመን
89. አለመዘጋጀት ለውድቀት መዘጋጀት ነው
90. ሂሳብ ሳይከፍሉ ሀሳብ አይጀምሩ
91. ሰርቶ የማይዝናና አህያ ብቻ ነዉ
92. ሹፌሩን በፍቅር እንጂ በነገር መጥበስ ክልክል ነው
93. እንደምን አደራቹ ውሸት መሮኛል ስራ ፈልጉልኝ
94. ኑሮና ታክሲ ካልታገሱት አይሞላም
95. እስክናውቅ እንጂ እስክናብድ አንማርም
96. የትም ፍጪው ምግቡን ብቻ ስጪኝ
97. አንድን ሳትይዝ ሁለትን አታገኝም
98. ያለዉን የሰጠ ባዶዉን ይቀራል
99. ሱሪህን ሳይሆን ራስህን ዝቅ አድርገህ ኑር
100. ህይወት በደረጃ ፈተና በኩረጃ
101. ለመኖር ብላ እንጂ ለመብላት አትኑር
102. ሾርባ ያቃጠለው በርጎ ይናደዳል
103. ያልተነገረ እንጂ ያልተባለ የለም
104. ሠርቶ የማይዝናና አህያ ብቻ ነዉ
105. የጊዜ ጀግና እንጂ የሰው ጀግና የለውም
106. ሰው እና ድፎ በትዛዝ እንደፋለን
107. እንደ ባሪያ ከሰራ እንደ ንጉስ ትኖራለህ
108. አንድ ጎል እና አንድ ሚስት አትመን
109. ወይ ጉድ ሀይሩፍ በዶልፊን ይስቃል አሉ
110. ሰዉን ማመን ቀብሮ ሳይሆን ቀብድ ተቀብሎ ነዉ
111. በፍቅር ለወደቀ የመሬት ስበት ተጠያቂ አይደለም
112. የማያልፍለት ደሀ ሀብታም ይጋብዛል
113. በሰዉ ላይ ከምትስቅ መጀመሪያ ራስህን እወቅ
114. አበሻ አንድ እግሩን ካልቆጹለት የሁለተኛው እግር ጥቅም
አይገባውም
115. ከምታማ ወንጌል ሰማ
116. ዝቅ ብሎ የሠራ ከፍ ብሎ ይኖራ
117. የሰነፍ አእምሮ የሰይጣን ቤተ_ሙከራ ነዉ
118. ለስራ ያልታደለ አእምሮ ለተንኮል ማንም አይወዳደረዉም
119. የሴት ልጅ ውበቷ ታማኝኀቷ
120. ከማይረባ ጉልበት ይሸለል ልብ አርጉልኝ ማለት
121. መኖር ደጉ ብር ባያስቆጥረን ቀን ያስቆጥረናል
122. የእናት ሞትና የድንጋይ መቀመጫ እያደር ይቆሮቁራል
123. "ቀስ ብሎ ማደግን ሳይሆን ቁሞመቅረትን ፍራ"አለች
ባጃጅ!!!
124. አራዳ እናቱን ሚ
ረዳ
የዘመኑ ወጣት አእምሮ በር የለውም ። ቢኖረውም የሚያስወጣ እንጂ የሚያስገባ አይደለም ። ከራሱ ዓለም ሃሳብ አውጥቶ እኔ ያልኩት ካልሆነ ይላል እንጂ የሌላውን ሐሳብ አይመዝንም ።

ሲወለድ ጀምሮ ሁሉን አውቆ የተፈጠረ ይመስለዋል ። ያለብዙ ችግር ያገኘውን ዕውቀቱን ተፎካካሪ የሌለው ሀይል ያደርጋል ። በትንሽ ዕውቀት ብዙ ነገር ፈታቶ የሚገጣጥም ይመስለዋል ።

#_ይወሰዳል መንገድ ያመጣል መንገድ
#_አዳም_ረታ
ወንዶች ሆይ ልብ በሉ!

አምላክ ልቧ ቆንጆ የሆነችውን ሴት እንዲስጣችሁ አምላክን ለምኑ ። ያንተ የሆነችውን ሴት አምላክ እስኪሰጥህ ትእግስት ይኖርህ ልብህ ያርፈባትን ውደድ አፍቅር አይንህ እዛም እዚህም አይቀላውጥ በቁንጅና ፣ በተክለሰውነትና ባለባበስ አትማርክ ሴት ልጅ ባለባበሷ እና በመልኳ አይትህ አትናቅ ቆንጆ ስታማርጥ ያንተ የሆነችውን እና ህይወትህን የምታጣፍጥህልህን ሴት እንዳታጣ ። ለማፈቀር ወይም ለመፈቀር ሰው መሆን በቂ ስለሆነ ።

የሰው አስቀያሚ የለውም የአስተሳስብ እንጂ ቆንጆ አይደለችም ፣ አለባበሷ ይደብራል ፣ አቋሟ አያምርም አትበል ቀርበህ የውስጧን ውበት ሳታይ በላይ ውበቷ አታጣጥላት ለተረዳው ሰውና በሳል ለሆነ ሰው ከላይ ውበት ይልቅ የውስጥ ውበት ሚዛን ይደፍልና ፥ ስለዚህ ላንተ ከተመቸችህ ምንም ትሁን የአንተን ህይውት አንተ እንጂ ሌላስው አይኖርልህም ለራስህ ብለህ ኑር ለራስህ ብለህ አስተውል ለስው ብለህ ምንም ነገር አታድርግ ለህሊናህ እንጂ ።

ቆንጆ አግብቼ የእከሌ ሚስት ቆንጆ ናት ወዘተ እንዲባልልህ ሳይሆን ለህይወትህ የምትመችህን የምትስማማህን ሀሳብህን የምትርዳህ እና ከልብ የምታፈቅርህን ከፈለክ አይንህ ሳይሆን ልብህ ያአያትን አግባ ።
@youthkiper
"ሚስት ጫማ ናት!"


በድሮ ጊዜ ነው.... በደጉ ዘመን አንድ ሠው ከመሬት ተነስቶ ብዙ ሰዎች በተሰበሰቡበት "ሴት ማለት እንደ ጫማ ናት ስንፈልግ እንቀይራታለን" እያለ የተለያዩ ለጆሮ ፀያፍ የሆኑ የሴትን ልጅ ክብር የሚነኩ ንግግሮችን መለፈፍ ያዘ።

በአካባቢው የነበረው ሠው በሙሉ ደንግጦ ወደ አንድ ደግ ጥበበኛ ሰው ከማየት ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረውም።የዚህን ጊዜ እኚያ ጥበብ የተለገሳቸው ሰውዬ በጥሞና ከሰሙት በኋላ"ልክ ብለሃል ልጄ ሴት ጫማ ናት ራሱን እንደ እግር ለሚያይ ሰው.... እንዲሁም ዘውድ ናት ራሱን እንደ ንጉስ ለሚያይ ሰው" ብለው አሳፈሩት።

ሚስት ለባሏ ዘውድ ናት
ይህን ያውቁ ይሆን ? የፊዚክስ ሊቁ አይዛክ ኒውተን እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ድንግል ነበር። 🤭 *የአለማችን ታላቁ ና ቁጥር አንድ ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን መኪና መንዳት በፍፁም አይችልም ነበር።ይኸውም ሳይንቲስት በዕድሜ ዘመኑ ካልሲ አድርጎ አያውቅም
በወጣትነትህ ያሽኮረመምካት ህይወት በጉልማስናህ ለመዳራት ፣ በወጣትነትህ ያስፈገግካትን ህይወት በጉልምስናህ ለማስገልፈጥ ተአምር አትሻም ፡፡ የህይወት ፅጌዋ የሚፈነዳው ፣ ምንጯ የሚንፎለፎለው በወጣትነትህ ላይ ነው ፡፡ወጣት ከሆንክ የቀጠፍከው የጽጌረዳ እንቡጥ እጅህ ላይ ሊፈካ ይችላል ፡፡

ወጣት ከሆንክ ልትተክለው ያዘጋጀኸውን የብርቱካን ችግኝ የበሰለ ፍሬ ልትበላ ትችላለህ ፡፡ በቃ !! ወጣት ከሆንክ አለም አይገዛህም ፤ ትገዛዋለህ ፡፡ ህይወት አይበይንብህም ፤ ትበይነዋለህ ፤ ዘመን አይቃኝህም ፤ ትቃኘዋለህ ፡፡ ታድያ ይህ ሁሉ የሚሆነው የወጣት ልብ ከታደልክ ነው ፡፡

ወጣትነት ግጥምና ዜማ የለውም !

በግ ያጨባበጠን ዛሬያችን ፤
በማይገናኝ ትናንትና ፣
የኀሊት እየተሳበ ፣
ጎህ የቀደደው ነጋችን ፣
ምን ሊያመጣብኝ እንዳሰበ አላውቅም ፡፡

የወጣት ልብ ድርና ማጉ ጉጉትና ፍቅር ነው ፡፡ ጉጉትና ፍቅር ተዋህደው የሚፈጥሩት ብርሃን ነው ወጣትነት ፡፡ ወጣትነት በምትጠልቅ ጀምበር ተቅላሎት እንደተዋበ አድማስ ሟች ውበት ሳይሆን ፣ ገና ከአድማስ ማህጸን መውጣት የጀመረች የንጋት ጀምበር የምትነድፈው ብርሃን ነው ፡፡

በንጋት ብርሃን አለም ሁልጊዜ አዲስ ናት ፣ ህይወትም እንዲሁ ናት ፡፡ በወጣት ከሆንክ ያገጠጠብህ መከራ መሮ ጥርሱ ሳይሆን ፣ ለስላሳው ከንፈሩ ቀድሞ ይታይሀል ፡፡ ሊግጥህ ባሰፈሰፈው የመከራ ጥርስ በፍርሃት ለመራመድ ጊዜ የለህም ፤ በከንፈሮቹ ልስላሴ ውበት ተመደህ ፣ ተመስጠህ ትፈላሰፋለህ ፡፡አባትህ ሙሾ ለሚደረድርለት መከራ አንተ ለአዝማሪ ግጥምም ታቀብላለህ ፡፡

የልጅነት ጥሪትህን አሟጠህ ፣ የነፍስህን መሻት ናኝተህ የህይትህን ዘፈን ዜማና ግጥም የምትደርሰው አንተው ነህ ፡፡ አለም ታጅብሃለች ፡፡ በወጣትነትህ የሙሾ ግጥም ከተቀኘህ አለም የእድር ጡሩንባ አይገዳትም ፡፡ ለ<<አባ አየሽ ወይ ለምለም >> እርግጫ መንቀል ፤ <<ለሆያሆዬህ>> ምድርን በዱላ ነርታ አዋራ ማጨስ አይከብዳትም ፡፡ ለዚህ ደግሞ ከዚህ ከታጨቅንበት ድንኳን የተሻለ መሟገቻ አይገኝም ፡፡
((( ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ )))
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥነትን ሳይጠብቁ ቀድመው ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 25 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ለተመራቂ ተማሪዎች ጥሪ በማድረግ ወደ መማር ማስተማር ሥራው እንዲገቡ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው የውይይት መድረክ ውሳኔ ተላልፏል።

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ጥሪ ከተደረገ በኋላ ከመጓጓዣ ሂደት ጀምሮ በየዩንቨርሲቲዎቹ በሚኖራቸው ቆይታ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዳይዛመት ከፍተኛ ዝግጅት መደረግ እንዳለበትም ተገልጿል።

በቀጣይነትም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሁኔታ ጋር በሚስማማ መልኩ ተለዋዋጭ እቅዶችን በመያዝ ቀሪዎቹ ተማሪዎች ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ እንደሚሠራ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደቻሳ ጉሩሙ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል።via FanaNewsFBC
UPDATE| ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ሲጠሩ ተማሪዎች የሚጠሩበት ምድብ

የጥሪ ምደባ ቅደም ተከተል:-

1.GC --> First phase
[ ተመራቂ ተማሪዎች --> የመጀመሪያ ምድብ ተጠሪ ]

2.3rd and 4th --> second phase
[ 3ኛ እና 4ኛ ዓመት --> ተማሪዎች ሁለተኛ ምድብ ተጠሪ ]

3.1st and 2d year --> 3rd phase to be returned
[ 1ኛ እና 2ኛ ዓመት ተማሪዎች --> 3ኛ ምድብ ተጠሪዎች ]



©Abrhaley የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ኅብረት ተጠሪ

#FORWARD
በ1930 አካባቢ በአሜሪካን ሃገር በልብስ ሱቅ ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ሲድ እና ሃሪ የሚባሉ ሰዎች ወንድማማቾች ነበሩ፡፡ ሲድ የሽያጭ ሰራተኛ ሲሆን ሃሪ ደግሞ የስፌት ክፍሉን ይመራል፡፡ ሲድ ልብስ ሲገዛ መጥቶ ልብሱን በመስታወት ውስጥ አይቶት የወደደውን ደንበኛ ባየ ቁጥር ሁሉ ውስጥ ወዳለው ወንድሙ ይጠራና ‹ሃሪ ይሄ ሱፍ ስንት ነው?› ይለዋል፡፡ ሃሪም ‹‹ያ ቆንጆው ሱፍ አይደል? 42 ዶላር›› ብሎ ይመልሳል፤ (42 ዶላር በጊዜው በጣም ከፍተኛ ዋጋ ነው፡፡) ሲድም ደንበኛው በሚገባ እንዲሰማ ለማመቻቸት ሲል ‹‹ምን ያህል አልከኝ?›› ብሎ ጥያቄውን ይደግምለታል፡፡ ሃሪም ‹‹አርባ ሁለት ዶላር›› ብሎ ጮክ ብሎ ይናገራል፡፡

በዚህ ጊዜ ሲድ ወደ ገዢው ይዞርና ‹‹22 ዶላር ነው አለ›› ብሎ አሳስቶ ለደንበኛው ይነግረዋል፡፡ የሲድን መሳሳት የሰማው ደንበኛም ‹የሱፍ እውነተኛ ዋጋ (42 ዶላር) መሆኑን ሻጩ ሳያውቅ› በሚል ጥድፊያ ቶሎ ከፍሎ ይወጣል፡፡

አንድን ነገር ውድ፣ ቆንጆ ወይም ሰፊ ነው የምንለው ሌላ ርካሽ፣ መልከ ጥፉ ወይም ጠባብ ነገር ሲኖረን ነው፡፡ ከዚያ ውጪ ባሉ ሁኔታዎች የፍፁም ውሳኔ ሰጪነት ችግር አለብን፡፡

አንዲት ደስ የምትል ሴት አንድ መካከለኛ ወንድ ልታገባ ትችላለች፡፡ ከዚያም የልጅቷ ቤተሰቦች ብዙም ጥሩ ካልሆኑ መደበኛ የሆነው ሰው (ባልዬው) ንጉስ ይሆናል፡፡

በቆነጃጂቶች የሚሰሩ ማስታወቂያዎችን እንመልከት፡፡ አሁን እኛ ሳቢ የሚመስሉን ቆንጆዎች ብቻ እንደሆኑ የምናምንበት ደረጃ ላይ ነን፡፡ ጓደኛ የምትፈልግ ከሆነ ከቆንጆ ጓደኛህ ጋር አትሂድ፡፡ ሰዎች ከእውነተኛው ማንነትህ ማራኪነትም በታች  የሆነ ቦታ ይሰጡሃል፡፡
እንኳን አደረሳችሁ
መልካም በአል
Have a colorful Demera & Meskel Holiday!

Wishing you abundant health, peace & joy on this holiday and always!



@youthkiper
ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ ደመራ በዓል በሠላም አደረሳችሁ።

🚩በዓሉ የሠላም ፣ የጤና ፣ የፍቅር ፣ የአንድነት ፣ የብልፅግና እንዲሆን ፈጣሪ አምላክ ፍቃዱ ይሁን!"

@youthkiper
2024/05/29 04:41:48
Back to Top
HTML Embed Code: