♥️ ያደረ ፍቅር 🌷
🦋 ክፍል _አንድ
ከእለታት በአንዱ ቀን እናቴ እና አባቴ ተጋቡ ፣ ከእለታት በአንዱ ቀን ሳይፈልጉኝ ተረገዝኩ ፣ እናቴ ልጁ በድህነታችን ላይ እከክ ሊሆንብን ነው በጊዜ ይሰናከል ብትልም አባቴ አፈር ግጬም ቢሆን ይወለዳል ብሎ ተሟግቶ ነው አሉ እኔን ለውልደት ይሁን ውግደት ያበቃኝ ፣ ደግሞ ክፋቱ... መምጣቴን አልፈለኩትም ይሁን እናቴ ሳትፈልገኝ በመረገዜ ልበቀላት ምጡ ከብዶባት በቀዶ ጥገና እንድወለድ እሱንም እናቲቱን ለማትረፍ ብቻ በተሞከረ ሙከራ አትሙት ያላት ነፍስ ይዤ ይህቺን ምድር ተቀላቀልኩ መወለዴ ከፋ እናቲቱን ለማትረፍ በተሞከረ ሙከራ እኔ ተርፌ እናቴ ሞተች። አባቴ ገና ካገባት አመት እንኳን ያለሞላት ሚሽቱን በእኔ ምክንያት ቢያጣትም አብዝቶ ይወደኛል፣ በአምላኩ ላይ ታላቅ እምነት የነበረው አባቴ ሁሉም ለበጎ ለአንዳች ተአምር ነው ሲልም ተቀበለኝ። ተአምር ተባለ እንግዲህ ስሜንም ያገኘሁት ከዚሁ ይመስለኛል ይኼ ሁሉ የሆነበት የሆነ ታአምር አለው ያለው አባቴ "ታአምር ነው የእሱ ስራ "አለኝ ስሜ ነው ይኼ ሁሉ ያሻው ሰው "ተአምሩ" ሲለኝ ያሻው " የእሱ ስራ" ቢለኝም ምስኪኑ አባቴ ብቻ "ታአምር ነው የእሱ ስራ "እያለ ነው የሚጠራኝ....እንግዲህ የምጠራበት ስሜ ታአምር ሆኖ ጸደቀ።።።።።
ታዲያላቹ እናቴ ትክክል ነበረች ለቤተሰቡ በረሀብ ውሎ ማደር ምክንያት ሆንኩ አባቴ ግን ቃሉን አክባሪ ነው ለዛም ነው አፈር ግጦ ያሳደገኝ ፣ የተወለድኩት በ ምዕራብ ሸዋ ዞን በኦሮሚያ ክልል በምትገኝ አምቦ የምትባል ከተማ ውስጥ ቢሆንም ራሴን ያወቅኩት አዲስ አበባ መጥቼ ነው። ትንሽ እድሜዬ እየጨመረና እራሴን እያወኩ በመጣው ቁጥር እናቴን እየጠላው ለአባቴ ልዩ ፍቅር እያሳደርኩ መጣው፣ ህይወት ናታ ሰወች ክፉ እንዳደረጉብን ፣ክፉ እንዳሰቡብን እንኳን ተነግሮን ደመ ነፍሳችን እንኳን ሹክ ካለን ጥላቻ፣ ብቻ ከአምቦ ከተማ የለቀቅነው ጎረቤቱ ሁሉ ይሄ ገፊ እያለ ሲቦጫጭቀኝ አባቴ በመስማቱ ትንሽ እያደኩ ስመጣ ለኔ እዛ መኖር ከባድ መሆኑን በማመኑ ነበር ፣እድሜ ለአባቴ ይሄንን ቃል በልጅነቴ ባልሰማውም እያደኩ ስመጣ ለእናቴ መሞት ምክንያት አድርጌ ራሴን መውቀስን አልተውኩም ቢሆንም ሳትፈልገኝ ልትወልደኝ እንደነበር ሳስታውስ ደግሞ እጠላታለው ፣ ይኼንንም ለአባቴ በተደጋጋሚ ነግሬዋለው ተው ልጄ እንደዛ አትበል እያለ ሲመክረኝ ባስ ሲልም ሲመታኝ ቢሰነብትም ለእናቴ ያለኝ ጥላቻ እንኳንም አላወቅኳት ያስብለኛል ፣ በትምህርቴ በጣም ጎበዝ ስለነበርኩ አባቴ አብዝቶ ይወደኛል፣ የልጅነቴን ጊዜ በጣም እወደዋለው ብዙው የህይወቴ ክፍል ልጅነቴ ላይ ያለ ይመስለኛል ፣ የሚኮላተፍ ምላስ ስለነበረኝ ብዙ ሰዎች ይወዱኛል ለዛም ይመስለኛል ከእጄ ማስቲካ እና ከረሜላ የማይጠፋው ፣ ሁሌም ከረሜላውን ለኔ ማስቲከውን ለሷ ነበር የምሰጠው፣ ማክዳ ትባላለች በተኮላተፈ አንደበቴ ስጠራት ማልዳ አልኳት ስያሜውን ስለወደደችው ከፍ ስልም በህይወቴ ማልዳ የወጣች ብርሀን እንደሆነች ስረዳ እንኳንም ማልዳ አልኳት እላለው። የጎረቤታችን ልጅ ናት ታዲያ የምንማረው አንድ ትምህርት ቤት አንድ ክፍል ውስጥ ያውም አብረን ስለሆነ የምንቀመጠው ፍቅራችን ሀገር ያስቀና ነበር። አባቴ ስራ ውሎ አምሽቶ ስለሚመጣ ከትምህርት ቤት መልስ አባቴ እስኪመጣ እነማልዳ ቤት እጠብቀዋለው ። እኔና ማልዳ ትምህርት ቤት ለሚያየን ጓደኛሞች ከሰፈርራችን ትንሽ ራቅ ብሎ ለሚያየን እህትና ወንድም ለሰፈር ጓደኞቻችን የእቃቃ ማድመቂያ ባል እና ሚስት ነን። የእቃቃ ሚስቴን አድገን እንኳን ሚስቴ፣ ባሌ ነበር የምንባባለው እኔ ብዙም ለትምህርት ፍላጎት ስላልነበረኝ ከአስረኛ ክፍል ነው ያቋረጥኩት ከዛ ከአባቴ ቅርብ ወዳጅ ከነበረው አቶ ገበየው ጋር መርካቶ ካለው ትልቁ ሱቅ ውስጥ በተላላኪነት እንዳገለግል ተቀጠርኩ፣ ትምህርቱን ብጠላውም ሂሳብ ላይ ጎበዝ ስለነበርኩ በሂሳብ ስራ አቶ ገበየውን ስለማግዛቸው ጥሩ የሚባል ክፍያ ይከፍሉኛል፣መርካቶ እንግዲህ ከገቡባት አትለቅም አንድ አመት ያክል በአንድ ሱቅ ብቻ ተወስኜ ብሰራም ከዛ በኋላ ስራዬ የጠራቸውና ገንዘብ የጠራኝ ቦታ ሁሉ ስገኝ በሁለት አመት ውስጥ የራሴን ሱቅ ለመክፈት በቃው፣በዚህ ጊዜ አባቴ እርጅና እየተጫነው ከቤት መዋል ጀመረ ። አሁን ተራዬ ነው ብዬ ስራ ልክ እንደጀመርኩ እቤት እንዲቀመጥና እኔ እንድሰራ አጥብቄ የለመንኩት ቢሆንም አሻፈረኝ ብሎ የሰነበተ ቢሆንም አሁን ግን ሳይወድ በግድ እርጅና እጅ አሰጠው ፣ ማልዳ አሁን የባህርዳር ዩንቨርሲቲ የህግ የሁለተኛ አመት ተማሪ ነች። በባለፈው አመት እሷን ለማየት በሴሚስተሩ ሶስት ጊዜ እሄዳለው በጣም ከናፈቀችኝ ደግሞ በሳምንትም እሄድ ነበር። አሁን ከሄድኩ ሁለት ሳምንት ሆኖኛል ግን ማልዳዬ በጣም ናፍቃኛለች ሰዐቴን አየሁት የጠዋቷ ፀሀይ ወደማቃጠል ተለውጣለች 5:10 ክላስ ትሁን አትሁን ስል ደወልኩላት ብዙም አላስጠበቀችኝም ስልኩ ተነሳ
"ባሌ"
"ማልዳዬ የኔ ሚስት ክላስ ትሆኛለሽ ብዬ ነበር"
"ጠዋት ነበረኝ አራት ተኩል ወጣው"
"ናፍቀሽኝ"
"እኔም"
"ነገ ልምጣ "
"ነገኮ ሀሙስ ነው ቀኑን ሙሉ ነው ክላስ አለኝ"
"እሺ በቃ ቅዳሜ እመጣለው "
"እሺ"
"ማል የሚቸግርሽ ነገር አለ እንዴ?ብር ካስገባሁላት ሶስት ቀን መሆኑን አላጣሁትም ግን በቃ እንድትጨናነቅ አልፈልግም።
"እንዴ ትላንት አይደል እንዴ የላክልኝ አትጨነቅ እኔኮ ሲቸግረኝ እጠይቅሀለው" አለችኝ ከላኩላት ሶስት ቀን ቢሆነውም ለማቅረብ ትላንት ምትለውን ቃል ተጠቅማ።
"እሺ በቃ ቡሀላ ደውልልሻለው ደግሞ ራስሽን ጠብቂ"
"እሺ ውዱ ባሌ እወድሀለው"
ይኼን ቃል ከሷ ስሰማ ነፍሴ ቀጥ ልትል ይቃጣታል "እኔም ውድድድድ እሺ ሚስቴ" ስልኩን ዘጋሁት ማልዳዬን ሚስቴ ስላት የእውነት የሰማንያ ሚስቴ የሆነች ያህል ይሰማኛል ቅዳሜ ራቀኝ በዛ ላይ ማልዳዬ ደውላ ስትመጣ ምነግርህ ነገር አለ ስላለችኝ ቅዳሜን ይበልጥ ገፋችው።...
#ይቀጥላል ክፍል ሁለት
💕🍃🌹🍃......
😘 JOIN & SHARE 😘
@zahkyu
@zahkyu
Any comments
@nahom20
👒👒......🍃🌹🍃........👒👒

♥️ ያደረ ፍቅር 🌹
🔥 ክፍል ሁለት
.
.
አባቴ ጀንበር ስትጠልቅ መመልከት ያስደስተዋል ግን በዚህ ውሽንፍሩ ባየለበት ብርድ እደጅ አየዋለው ብዬ አላሰብኩም ገና የግቢያችንን በር ከፍቼ ወደ ውስጥ ስዘልቅ ሳየው ደነገጥኩ እሱም እኔን ሲያየኝ ከጀንበሯ ጋር የጀመረውን ንትርክ ትቶ እኔን ማየት ጀመረ
"አባቴ ምነው በዚህ ብርድ"
ለነገሩ እላዩ ላይ ጣል ያደረጋትን ኩታ እያሳየኝ "አይበርድም የማዋያት ነገር ነበረኝ ሳታመልጠኝ ብዬ እኮ ነው አለኝ" አይኑን እኔን ለማየት ከነቀላት ጀንበር እየመለሰ፣
"እና አልጨረስክም በል ተነስ "እጄን ሰጥቼ እየደገፍኩት ወደቤት ገባን ፣
"አባቴ የማፈላልክን ቡና ታያለህ በዛውም ለጀንበሯ ስትነግራት የነበረውን ትነግረኛለህ"
"ቡናውን እስቲ ለጀንበሯ ግን ያወጋኋት ሚስጥር ነው ባይሆን ላንተ የማወጋህ አለኝ"
"እሺ የኔ ምርጥ አባት" በነገራችን ላይ እኛ ቤት የሴት የሚባል ስራ የለም ፣ አባቴ ወጥ እየሰራ ፣ ቤት ሲያስተካክል፣ እቃ ሲያጥብ፣ ልብስ ሲያፀዳ አረ እንደውም እንጀራ ሲጋግር ሴት ያስንቅ ነበር። ለዛም ነው እኔም በአባቴ ወጥቼ የሴት የምለው ስራ የለም የቻለውን ሁሉ እያደረገ ላሳደገኝ አባቴ ወጥ ሰርቼ አብልቼው፣ ቡና አፍልቼ አጠጥቼው አውቃለው፣ እኛ ቤት ሴትም የሴት የሚባል ስራም የለም ።
ከአባቴ ጋር ቡና እየጠጣን ነገ ባህርዳር ስለመሄዴ ነገርኩት በዛውም ከጊዜ ወዲህ ከአቅሜ በላይ እየሆነ ስላለው የማልዳ ፍቅር ነገርኩት፣
"እሷስ ምን ታስብ ይሆን ልጄ "አለኝ
"እንጃ የኔ አባት እኔ ግን ከፍቅር ያለፈ ያህል በሰኮንድ በሚያድግ ፍቅር ውስጥ ነው ያለሁት"
"የምን መልፈስፈስ ነው አንተው በርታ በል እንጂ ፍቅር ከተጃጃልክለት ያጃጅልሀል፣ ባይሆን እሷ ትምህርቷን እስክትጨርስ እንደምንም መቻል አለብህ፣ ካልሆነማ አንድ ሀሙስ እኮ ነው የቀረህ ምትመስለው"
"እሺ አባቴ"
በዚህ ሁኔታ ሰመከር የራሱን ታሪክ ሲነግረኝ አመሻሽተን ነበር የተኛነው።
ጉዞ ወደ ባህርዳር
ባህር ዳር ከተማ ከአዲስ አበባ ተነስተን 565 ኪሎ ሜትር ወደ ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ስንጓዝ የምትገኝ ከተማ ናት።
ባህ ርዳር ከተማ የአሁኑን ስሟ ልታገኝ የቻለችው በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው በአፄ ሠርጸ ድንግል ይህን ታቦት የት እናስቀምጥ ተብለው በተጠየቁ ጊዜ
"ከባህሩ-ዳር" አድርጉ እንዳሉና ከዚህም ተነስቶ ባሕር-ዳር ብለው ሥያሜ እንዳወጡላት ስለባህር ዳር የማውቀው ነው፣ ከዛም ባለፈ ባህርዳር በጣም ውብ የሆነ መልከአ ምድር የተጎናፀፈች ውብ ከተማ ናት ከተማዋን የሚያስውባት የጣና ሀይቅ ደግሞ ለከተማዋ ነዋሪዎች ልዩ ውበት ለጎብኝት ለሚመጡት ልዩ ተመስጦን ይሰጣል ፣
ከጣና ሀይቅ በቅርብ ርቀት ከሚገኘው ሁሌ ከመረንገናኝበት ካፌ ማልዳዬን አገኘኋት
"ባሌ" ሮጣ መጥታ ተጠመጠመችብኝ የኔ ቀበጥ በዙርያችን ያሉ ሰዎች በግርምት እስኪያዩን ነበር የተቃቀፍነው ፣
ማልዳዬ ቀይ መካከለኛ ቁመት ያላት ለአይን ሞልቶ የሚትረፈረፍ የሚያምር የሰውነት ቅርፅ ከሸንቃጣ ወገብ ጋር የሰጣት አይኖቿ ከአይን ሲገጥም ጥጣታቸው አይንን ያስከደነ ፣ በጣም የጠቆረ ሳላጋንነው ከወገቧ የሚደርስ ፀጉር ያላት፣ ስትስቅ ከሚሰረጉደው ጉንጯ ጋር ሲዳመር ፈጣሪ ተጠቦ የእሱን እፁብ ድንቅ ስራ እንድናደንቅ የሰራት ያስመስልበታል። ዛሬ ግን እንደዛ በጥቁረቱ ሀገር ያልቀናበት ፀጉሯ ወደቀይ የሚያደላ ቀለም ተቀብቶ ሳየው ደነገጥኩ፣ ግን ይባሱኑ አሳምሯታል፣ አለባበሷ ከባህርዳሩ ሙቀት ይሁን ለኔ ለመዋብ ሳላውቀው ሙሉ ውበቷን እንዳደንቅ ይጋብዛል፣ በቃ ማልዳዬ ስዕል መስላ መጣችልኝ ከእቅፏ ባልወጣ ተመኘው የተቀባችው ሽቶ መዐዛው ያውዳል፣ ሳልፈልግ ከእቅፏ ወጣው ተያይዘንወደ ጣና ሀይቅ፣ ሁሌም ስሄድ የምንዝናናው በጣና ሀይቅ ላይ በመርከብ ተንሳፈን ራሳችንን ከሀይቁ በሚወጣው እርጥብ አየር እያስመታን ነበር...
"ባሌ እንዴት ነክልኝ እንዴት እንደናፈኩክ"
"ማልዳዬ ሚስቴ እኔም እኮ በጣም ናፍቀሽኛል ስራ በዛ ላይ አባቴ ትንሽ አሞት.."
አልጨረስኩትም "አባቴ ምን ሆኑ ?አለችኝ እንደደነገጠች አባቴን አባቴ ብዬ ነው ምጠራው ለዛም ይሆናል የሆነ ደስ የሚል ስሜት የሚሰማኝ ለዛም ነው ስሜቴን የምትጋራኝ ማልዳ አባቴን አባቴ ብላ የምትጠራው፣
"አይ ትንሽ አስሙ ተነስቶ ነው "
"እሺ ሀኪም ቤት ሄዱ"
"አዎ አሁን ደህና ናቸው"
ማልዳን በፍቅር አይን እንደማያት እንዳታውቅብኝ በስስት ነበር ማያት ልክ ወደ እኔ ስትመለከት ወደሀይቁ እዞራለው፣
በጊቢ ውስጥ የገጠማትን ሁላ ስታወራልኝ ቆየን ፣ ዩንቨርሲቲ ከገባች ጊዜ ጀምሮ በየቀኑ ብል ማጋነን ካልሆነብኝ የፍቅር ጥያቄ ስለሚያዥጎደጉዱላት ወንዶች ትተርክልኛለች ፣ በዚያ ሰዐት የሚሰማኝ መዐት ቃላትም አይገልፁት እሷም አታውቀውም ፣ ቢሆንም ይሆናል ወይስ አይሆንም ብላ ስለማትጠይቀኝ ለኔ ስሜት ይኖራታል ብዬ እንዳምን አድርጎኛል፣ ያም ሆኖ ግን ለሷ ያለኝን ስሜት አንድም ቀን ልነግራት አስቤ አላውቅም ፣ ትምህርቷን ትጨርስና የእውነት ሚስቴ አደርጋታለው ብዬ ለራሴ ነገርኩት ፣ ለዛ ነው ውስጤን ጤና የነሳኝ ፍቅሯ ፊቴ ላይ እንዳያስታውቅ ፊቴን ከሷ ማሸሸው ፣ አሁንም ያንኑ በሳምንቱ ውስጥ ያስተናገደችውን የፍቅር ጥያቄዎች ፣ ከስልኳ ፣ በደብዳቤ የተሰጣትን ደግሞ ወረቀቱን እያሳየችኝ ልቤን ስታስጨንቃት ዋልን፣ ይሄን በነገረችኝ ቁጥር እሷን የማጣት ፍርሀቴ ሲበረገድ ለሷ ያለኝ ፍቅር እጥፍ ሲጨምር ለልቤ ራስ ምታት ሆነብኝ፣ ፊቴ አሁንም በፈገግታ እንደተሞላ ነው፣
"የኔ ሚስት እኮ የምትወደጅ ነሽ "አልኳት ስሜቴ ገንፍሎ ሚወጣ እየመሰለኝ ከራሴ ጋር እየታገልኩ፣
"ያንተ ሚስት ስለሆንኩ ነዋ" የኔ ቀበጥ እንደልጅነቷ ሙልቅቅ እያለች መለሰች
"ተይ ልቤን አታቅልጫት አልኩ በውስጤ እንዲህ ስትሆን ሳያት አንዳች ከደስታ ያለፈ የሀሴት ስሜት ውስጤን ይወረዋል።
"ግን እኔ ባልሽ እንዳለው አያውቁም እንዴ" የምሬን ነበር
"ያውቃሉ እንጂ" እየሳቀች መለሰችልኝ
ለካ ቀልድ ነው እንዲህ እያወራን የጣና ሀይቅ ላይ ብዙ ቆየን በመሀል የፃፈቻቸውን ግጥሞች ስታነብልኝ እኔም አለኝ የምለውን ሀሳብ ስሰጥበት ቆያየን ማልዳዬ
ግጥም መፃፍ ትወዳለች እኔ ደግሞ በጣም ነበር የምጠላው ነበር ነው ያልኩት ፣ ትዝ ይለኛል በተለይ 8፣9እና 10ኛ ክፍል ስንማር የፃፈችውን ሁላ ካላነበብኩልህ ስትለኝ እኔ እንቢ ቡኋላ እንኳን ካልኳት ቀኑን ሙሉ ነበር የምታኮርፈኝ እሷ እንዳታኮርፍ ባላዳምጣት እንኳን ሰማት ነበር ከዛ ግን ማዳመጥ ስጀምር ጎበዝ ፀሀፊ እንደሚወጣት አበረታታለው ፣ ከሷ ጋር ለማውራት እንዲመቸኝ ያነበበችውን መፅሀፍ ሁላ ሳነብ አለው እንግዲህ፣ አረ እንደውም ግጥም ለመፃፍም የሞከርኩባቸው አጋጣሚዎች አሉ ፣ በተለይ ፍቅር አቅም ሲያሳጣኝ ለሷ የፃፍኩላት ብዙ ግጥሞች አለኝ፣
"ሚስቴ"
"ወዬ ባሌ"
"ነግርካለው ያልሽኝን ሳትነግሪኝ"
"እሺ ነግርካለው በዛውም የማስተዋውቅህ ሰው አለ"
ልቤን አንዳች ነገር የመታው ያክል በፍጥነት ይመታ ጀመር ደነገጥኩ ለምን እንደሆነ እንጃ የሆነ ፍርሀት መላ አካሌን ሲቆጣጠር ይታወቀኛል
"ምን መሰለህ" ፊቷ ላይ የሆነ የሀፍረት ስሜት ይነበባል....
@zahkyu
Join us

♥️ ያደረ ፍቅር 📖
🦋 ክፍል ሶስት

በድንገት ስልኳ ጮኸ አንሺው የሚል ምልክት ሰጠኋት
" ወዬ ማርቲ"
ማርታ የዶርም አጋሯ እንደሆነች ነግራኛለች እንደውም አንድ ሁለት ጊዜ በጣም የምትወዳት ጓደኛዋን ሸዋን ጨምሮ አግኝቻቸዋለው፣
"ሸዊት ምን ሆነች "ከተቀመጠችበት ጀልባ ለመውደቅ እየቃጣት ፣ እጇን እየያዝኩ ምነው ብዬ በጥቀሻ ጠየኳት፣
"መጣው መጣው" እባክህ አዙርልኝ ለጀልባ ቀዛፊያችን ትዕዛዝ ሰጠች፣
"ምነው ሸዋ ደህና አይደለችም እንዴ"
"እንጃ ራሷን ስታ ሆስፒታል እየወሰድናት ነው እኮ ነው ምትለኝ"እንባ እየተናነቃት መለሰችልኝ እንዲህ ስትሆን ማየት ለኔ ሞት ነው ፣ ማልዳዬ ስትስቅ ስትቦርቅልኝ ካልሆነ የሀዘን ስሜት ሲነካት ማየት አልሻም፣
"እሺ እንሄዳለን ግን ተረጋጊ" እኔም ሀዘኗ እየተጋባብኝ፣
ተያይዘን ሸዋ ተኝታለች ወደተባለችበት ሀኪም ቤት ሄድን ፣እኛ ስንደርስ ሸዋ ራሷን አውቃ ነበር ፣ ማልዳ ሮጣ ሄዳ ተጠምጥማባት ማልቀስ ያዘች፣ ለሚያያቸው አብረው የሚኖሩ እህትማማች እንጂ ከተዋወቁ አመት የሆናቸው ጓደኛሞች አይመስሉም በፍቅራቸው ቀናው፣ የሸዋ ህመም ብዙም አያሰጋም ደሟ ዝቅ ብሎ ነው ተብሎ ቅዳሜን እዛው ሀኪም ቤት እንደምታድርና ነገ መውጣት እንደምትችል ተነገረን፣ ማልዳዬ እዚህ ማደሯ ነው፣ ሳልጠግባት ነገ ወደ አዲስ አበባ መመለስ ሊኖርብኝ ነው፣ እንደነገሩ ከነሱ ጋር አመሻሸውና ማልዳን ነገ እንደምሄድ ነግሬያት ሸዋን ተሰናብቼ መኝታ ለመያዝ ጉዞ በባህርዳር ጎዳናዎች ፣ የባህር ዳር ከተማ ሀይቅ ላይ እንደተመሰረተች ሀገር አይደለችም በጣም ትሞቃለች፣ ከተማዋ በማታ ለየት ያለ ውበት ይታይበታል ፣ የምሽቱን ውበት ለማድነቅ ግን አልታደልኩም፣ ውስጤ የሚመላለሰው ሀሳብ እረፍት ነሳኝ፣ ማልዳዬ ምን ልትነግረኝ ነበር ብዙ ነገር አሰብኩ እስከዛሬ ነግርካለው ብላ የነገረችኝ ነገር የለም ስለዚህ አንዳች አዲስ ነገር አለ፣
እንዲህ ከራሴ ጋር እያወራው ለማረፍ ያሰብኩበት ሆቴል ደረስኩ፣ እቅልፍ በአይኔ ውል ሳይል እኩለ ሌሊት ሆነ አሁንም ማልዳ በራሴ ተበሳጨው ፣ ምን የሚሉት ነው ከልክ በላይ ሰውን ማፍቀር፣
የተሳፈርኩበት አውቶቢስ ከውቢቷ ባህርዳር ለቆ ሲወጣ ገና ከማለዳው 1:00ሰዐት ነበር፣ ቢሆንም አዲስአበባ እንዳሰበሰኩት በጊዜ አልገባሁም፣ አዲስ አበባ እንደገባው ማግኘት የፈለኩት አምርን ነበር፣ አምር መርካቶ ካፈራችልኝ ምርጥ ጓደኞች አንዱ እና እንደ ወንድም የምቀርበው ሚስጥር ፣ ሀዘን፣ ደስታዬን የሚካፈለኝ ጓደኛዬ ሳይሆን ወንድሜ ነው፣ ሱቃችን አጠገብ ለአጠገብ ስለሆነ ውሎአችን አብሮ ነው፣ ደወልኩለት
"ወዳጄ"
"ወንድሜ መጣህ እንዴ"
"አሁን ገባው"
"እጅ ከምን?" ሁሌም ፍቅሯ አቅል እያሳጣኝ እንደሆነ ስለሚያምን ካልነገርካት እያለ ይጨቀጭቀኛል ፣ ቡኋላ አንዱ ላፍ ያደርግልህና ታርፈዋለህ ሲልም ማስፈራሪያ ያክልበታል፣ ለዛም ይመስለኛል አሁን የወረረኝን ፍርሀት ለማባረር እሱን ማግኘት የፈለኩት፣
"እሱን ሳገኝክ ነግርካለው የት ነህ?"
"ቤት ነኝ "
"በቃ መጣው"
ከአውቶብስ ተራ በሳር ቤት ወደ መካኒሳ አካባቢ ወዳለው የአምር ቤት አቀናው፣
አምር መካከለኛ ቁመት፣ ከመካከለኛ ውፍረት ፣ ከመካከለኛ ጥቁረት ጋር ያደለው ፀባየ ሸጋ እና መልከመልካም ልጅ ነው፣ ተጨባብጠን ሞቅ ያለ ሰላምታ ተሰጣጠን፣ ሻይ አፍልቶልኝ ቤት ያፈራው ነው ብሎ ሁሌም ከሱ ቤት የማይጠፋውን ፍርፍር አቀረበልኝ ፣ የሱ ፍርፍር ሁሌም ጨው ይበዛበታል ፣ እርቦኝ ስለነበር ጨውን እንኳን ሳላውቀው ጥርግ አድርጌ በላው፣
"እና ሳትነግረኝ ሳልነግራት መጣው ነው ምትለኝ? አለኝ የማወራለትን ሁላ ያለምንም መልስ ሲያዳምጥ ቆይቶ፣
"አዎ"በረዥሙ እየተነፈስኩ
"እኔ ነግሬካለው ቡኋላ......"
"ወንድሜ ተው ባክህ እኔ ሀሳቡ ሊገለኝ ነው፣ በዛ ላይ እንዴት እንዳማረባት ብታይ፣
"እኔም የምልህ እሱን እኮ ነው ፣ የምትሰማኝ ከሆነ እኔ ምመክርህ በቃ ንገራት፣ እሷም ጋር ስሜቱ ካለ እሰየው ካልሆነ እውነቱን መጋፈጥ ነው ሚሻለው ወዳጄ"
ከአምር ጋር ተሰናብተን ወደቤት ስሄድ አምር ያለኝን እያሰብኩበት ነበር ፣ አባቴ እራት አቅርቦ እየጠበቀኝ ነበር፣ "የኔ አባት እንዴት እንደናፈቅከኝ "ተጠመጠምኩበት ግንባሩን፣ እጆቹን፣ ጉልበቱን ሳምኩት፣
"እጅ ከምን?"አምር ያላትን ቃል እራሷኑ ደገማት ፣ የሆነውን ሁሉ አስረዳውት አባቴም ልነግራት እንደሚገባ ከዛ በኋላ የሚመጣውን መቀበል እንዳለብኝ ነገረኝ፣ መከረኝ፣
መንገር እንዳለብኝ ራሴን ለማሳመን ሁለት ቀን ፈጀብኝ፣ በመጨረሻም ልነግራት ደወልኩ ማታ ከ3:00 ቡኋላ ነበር
"ሄለው ማልዳዬ ሚስቴ"
"ሄለው ቡኋላ ልደውልልህ የሆነ ኘሮግራም ላይ ነኝ አለችኝ"
"እሺ" ስልኩ ቢዘጋም ከጆሮዬ ላይ አላነሳሁትም ነበር ፣ ማልዳዬ ላይብረሪ እንኳን ብትሆን እኔ ስደውልላት ወጥታ ታናግረኛለች ፣ ራሴን ለማረጋጋት ይሆናል ብዬ የማስበው ምክንያት ሁሉ ደረደርኩ ፣ ስልኬን አሁንም አሁንም አየዋለው አልደወለች 4:20 አካባቢ ደወለች
"ሄለው"
"ሄለው ባሌ"
"እንዴት ነሽ አሁን ገና ነው ብቻ እንዳትይኝ ዶርም የገባሽው?"
"አዎ አሁን ነው የገባሁት አመሸው አአ?"
"አረ በጊዜ ገባሽ" ቁጣዬንም ቅናቴንም በሚያስታውቅ ድምፀት፣
"ይቅርታ እሺ ባሌ አይለመደኝም"
"ለመሆኑ የት ከማን ጋር ነበርሽ?"
አሁንም ያው ድምፅ ነበር እሷ ግን የወንድምነቴን መስሏት ይሆን ልታረጋጋኝ ተለሳለሰች፣
"ባለፈው ነግርካለው ብዬክ እንደውም..." በዚህ ሰዐት ያ የመዐት ንዴት ተኖ በምትኩ ሀገር የሚያህል ፍርሀት ልቤን ሲያስጨንቃት ይታወቀኛል፣
"መች ነገርሽኝ ታዲያ"
"እንደውም የኛ ሲኒየሬ ነው ብዬ ፎቶውን ያሳየውህ ልጅ?"
ልቤን በአፌ ልተፋት ምንም አልቀረኝም አጠገቤ ሰው ቢኖር ልቤ ሲመታ ይሰማው ነበር፣
"ማን ነው እሱ ምን ሆነ?"
"ምንም አልሆነም ማለቴ ..በረጅሙ ተነፈሰች ማለቴ ፍቅረኛ ያዝኩ ኡፍፍፍ አለኝ ግልግል በሚል አተነፋፈስ፣
"ማለት ምን የምን ፍቅረኛ እንዴት "ተንተባተብኩ ተርበተበትኩ
"እንዴ አንተ ደግሞ የምን ፍቅረኛ ይባላል እንዴት በቃ በመቀራረባችን ውስጥ ሳላውቀው ፍቅር ይዞኝ አረፍኩት ከዛ.....
ይህንን የምሰማበት አቅም አልነበረኝም ስልኩን ከእጄ ለቀቅኩት......
#ይቀጥላል ክፍል አራት
💕🍃🌹🍃.......
😘JOIN & SHARE😘
@zahkyu
@Love pic's
Any comments
@nahom20
👒...........🍃🌹🍃............👒

🌹 ክፍል አራት

ጆሮዬን አላመንኩትም የምይዝ የምጨብጠው ጠፋኝ፣ ስልኬ መሬት እንዳለ ጮኸ ፣እሷ ነበረች የውስጤን በውስጤ ይዤ እንዳታውቅብኝ እየተጠነቀቅኩ ስልኩን አነሳሁት፣
"ሄለው ተቋረጠ አአ?"
" አው እና ካቆመችበት ቀጠለች " ብዙ ነገር ብታወራም ምንም አልሰማኋትም "አዎ" አረ "በጣም አሪፍ" ብዬ አድናቆትን ቸርኳት ፣ ውስጤ እሳት የተቀጣጠለ ያህል ሲጨስ ይታወቀኛል ፣ በቃ ተኚ ነገ እናወራለን አልኳትና ስልኩን ዘጋሁት፣ በቃ የሆነ ንዴትና ቅናት የተቀላቀለበት፣ ስቃይና እልህ ያንዘፈዘፈው ሰውነት አልጋውን ታክኬ እመሬት ላይ ዘጭ አልኩ ፣ እንዴ እያለቀስኩ ነው፣ አላመንኩም ካለቀስኩ ብዙ ዘመን አልፎኛል ለዛም ይመስለኛል ማልቀሴን እራሱ ከአይኔ የሚፈሰውን እንባ በእጄ ስነካው ነው ያመንኩት፣ ሌሊቱ አልነጋ አለ እዛው መሬት ላይ እንዳለው ከአይኔ የሚፈሰው እንባ ሳይደርቅ የሰፈራችን መስጂድ አዛን ለጆሮዬ ደረሰ፣ ከዛ የወፎች ጫጫታ ተከተለ ፣ የነሱን ድምፅ እማ ስሰማ እያበሸቁኝ ያለ ይመስል ተበሳጨው
"እሰይ እስይ ....ይበልህ ይበልህ..." ብዙ ብዙ የሚሉ መሰለኝ ጆሮዬን ያስኩ አሁንም ድምፃቸው ይሰማል፣ እንደምንም ራሴን ጎትቼ አልጋዬ ላይ ወጣው ፣ ትራሴን ጆሮዬ ላይ አድርጌ እንቅልፌን ተማጠንኩ...
ገና እንቅልፍ እየወሰደኝ እያለ የክፍሌ በር በሀይል ተንኳኳ
"ማን ነው በብስጭት ስሜት? ከእኔና አባቴ ቤት ውስጥ ማንም እንደሌለ አውቃለው፣
"እንዴ የኔ ልጅ ዛሬ ስራ የለም እንዴ አረ ሁለት ሰዐት ሊሆን ነው"
አሁን አይደል እንዴ የ11 ሰዐቱን አዛን የሰማሁት ወይስ
"አባቴ ትንሽ አሞኛል አርፍጄ ሄዳለው"
"እኔን አባትህን ልጄ ምን ሆንክብኝ ምን ነካህ ?" በሩን ማንኳኳቱን ቀጠለ
"አባ አሁን ልተኛ መተኛት ፈልጋለው "
"የምን መተኛት ነው ና በሩን ክፈትልኝ እንጂ ሀኪም ቤት እንሄዳለን"
"አባ በቃ ልተኛበት እስቲ! ሀይለቃል የተሞላበት ነበር፣ አባቴ ደንግጦ ይሁን ገብቶት ብቻ ዝም አለኝ፣
ሁፍፍፍፍ ድጋሚ እንቅልፌን እየተማጠንኩ ተኛው ከእንቅልፌ የነቃሁት ስድስት ሰዐት ሊሆን ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት ነበር እሱንም አምር ቤት መጥቶ የክፍሌ በር ሲንኳኳ
ገና በር እንደከፈትኩለት
"ምን ነካህ ወንድሜ? ምን ሆነህ ነው ደግሞ ካመመህ ሀኪም ቤት መሄድ ነው እንጂ ሀይ?"
በነገራችን ላይ አምር የድሬ ልጅ ነው ለዛ ነው በንግግሩ ውስጥ ሀይ የምትል ቃል ጣል የሚያደርገው፣
"ባክህ ትንሽ ነው አሁን ይሻለኛል"
"በሩን እየቀረቀረ ወዳጄ ነግረሀት ነዋ ምን አለች አቦ አታካብድ "የአልጋው ጠርዝ ላይ እየተቀመጠ
ለካ ልነግራት ነው ብዬ ነግሬው ነበር፣
"ባክህ እኔ ሳልሆን እሷ ናት የነገረችኝ" ሳላስበው እያለቀስኩ ኗሯል..
"እንዴ ወዳጄ እያለቀስክ እኮ ነው ምንድነው የነገረችህ?"
"እንባዬን ለመገደብ እየታገልኩ ፍቅረኛ አላት ማለቴ ፍቅር ይዟት "
"ማለት እንዴት እንዴ እሱን ነው ልትነግርህ የነበረው?"
አዎ በሚል ራሴን ነቀነቅኩት
"አቦ ቀረባታ በቃ አብሽህ ወንድሜ" ትከሻዬን ቸብ ቸብ አደረገ
"ይሄ ለኔ ሞት ነው ታውቃለህ እሷን ከሌላ ወንድ ጋር ማየት አይደለም መሳል ያማል ፣ይሄንን ማመን አልችልም ይሄን ከማይ ሞቴን እመርጣለው፣"
"ወዳጄ ይሄን ያህል እማ አታካብድ በቃ ላንተ..."
አላስጨረስኩትም " ስሞትልህ አምሬ ላንተ አላላትም እንዳትለኝ ማልዳዬ ለኔ የኔም ናት፣ ይሄ ታውቆኝ ነው ከልጅነቴ ማልዳ ሚስቴ ያልኳት እንዳትለኝ እንዳትለኝ "
"ሰውዬ ማመን አለብህ እንዴ ፍቅረኛ አለኝ አለችህ እኮ ሌላ ሰው ነው ምታፈቅረው፣"
"አይሆንም ተሳስታ ነው መስሏት ማልዳዬ ካፈቀረችም እኔን ነው"
"ወዳጄ ተረጋጋ በዚው ከቀጠልክ መጨለልህ እኮ ነው፣"
"አድርጎልኝ ነው ገላገለኛ ማልዳዬን ከሰው እቅፍ ከማያት የምሳሳለት ገላዋን ፣ የማልማቸው ከንፈሮቿን ... አይደረግም አይሆንም እባክህ በህልም ነው ተነስ በለኝ ይሄን አልችልም" እንባዬን አዥጎደጎድኩ ወንድ ልጅ በታሪክ እንዲህ ሲያለቅስ ታይቶ ሚታወቅ አይመስለኝም
" እንጄ አረ ተረጋጋ እሺ በቃ ተረጋጋ ተነስ እንደውም ሻወር ውሰድ የዙሁር አዛን ስላለ መስጂድ ደርሼ ልምጣ እስከዛ ተጣጥበህ ጠብቀኝ እንወጣለን፣"
እንቢ ልለው ብፈልግም አምር ካለ አለ ነው አይሰማኝም፣
"እሺ" አልኩት ዙሁን 7ሰዐት አካባቢ የሚሰገድ ሰላት ነው፣ አምር በሰላቱ እና በእናቱ ቀልድ አያውቅም ለዛም እሱ እስኪመለስ ሻወር ገባው፣
እንባዬ ከውሀው ጋር ይወርዳል ማመን አልቻልኩም ምናለ በህልሜ በሆነ ...
እዛው ሻወር እንዳለው አምር ተመልሶ መጣ ድምፁን ስሰማ እንደነገሩ ውሀ እላዬ ላይ አፍስሼ ወጣው፣
አባቴ እንደተጨነቀ ያስታውቅበታል ፣ አሁን ተሽሎኛል እሺ አባ ሀኪም ቤት እየሄድኩ ነው ፣ እንዲረጋጋልኝ ነው ለራሴ ያላመንኩትን ነገር ለሱ መንገር ከበደኝ፣
አምር ያስረሳዋል ያለውን ሁሉ ሲያወራ በየጌም ዞኑ እየሄድን ስንጫወት ብንውልም ህልም ህልም የሚመስለውን እውነት መጋፈጥ አልቻልኩም፣ እቤት ስገባ አባቴ ከጀንበሯ ጋር እያወራ ነበር ፣ አባ እንዴት አመሸህልኝ ፣ እጁን፣ ግንባሩን፣ ጉልበቱን እየሳምኩት፣
"እኔስ ደህና አንተስ ደግ ዋልክ ምን አሉህ ከሀኪም ቤት፣"
"ጥያቄውን አላሰብኩበትምና አስደነገጠኝ ምን እንትን ደም ማነስ እሱ ነው አሉኝ የሚያዞረኝ" አፌ ላይ የመጣልኝን ሁሉ ቀባጠርኩ፣
"እኮ ምግብ አትበላም ፈሳሽ አትወስድ እንዴት ደምህ አይጉደል ልጄ፣ ተው አንተ ብቻ ነህ ያለኸኝ ተው እንባውን በለበሰው ጋቢ ጫፍ ጠረግ ጠረግ ሲያደርግ አንጀቴን በላው፣
"አሁን ደህና ነኝ እኮ አባቴ ከዚህ ቡኋላ በደንብ እበላለው፣ ና በል እንግባ ፣ ደግሞ የምሰራልህ እራት ፣ ደግፌ ወደቤት አስገባሁት፣
"ደግሞ ማክዳ ደውላ ነበር ስልኩ ዝግ ሆነብኝ ስትለኝ እንዳመመህ ነገርኳት ደውልልኝ ብላሀለች"
"ለካ ስልኬ ዝግ ነው እሺ አባ ቡኋላ ደውልላታለው አሁን ላይብረሪ ትሆናለች፣"
እመኝታዬ ላይ እንዳለው ከፊት ለፊቴ ያለውን ሰዐት ስመለከት 3:15 ይላል ስልኬን ከፈትኩት ከአንድ አንድ ነበር የጠራው ማልዳ ናት ድምፄን ሞረድ ልቤን አፈን አድርጌ ስልኩን አነሳሁት፣
"ማልዳዬ ሚስቴ " ሚስቴ የሚለውን ቃል ሳወጣ እያነቀኝ ነበር
"አንተ ግን ሰው ያስባል አትልም እሺ ግን እያለቀሰች ነበር"
"እንዴ ምንም አልሆንኩም እኮ ደህና ነኝ እንዴ የምን ለቅሶ ነው?"
" ደህናማ አይደለህም አባባ እንዳመመህ ነግረውኛል ልምጣ እንዴ?"
"አረ ደህና ነኝ አሁን ተሽሎኛል ደህና ነኝ" ስለኔ ደህንነት ተጨንቃ ማልቀሷ ውስጤን ደስ አሰኘው አትጠላኝም ማለት ነው፣
#ይቀጥላል #ክፍል5
@zahkyu
Any comments
@nahom20
👒🍃........🌹.....🍃👒

🦋 ክፍል አምስት
"እእ ደህና ነኝ በቃ አሁን ትንሽ እረፍት ላርግ ጠዋት ደውልልሻለው ደህና እደሪ"
ላወራት ብፈልግም የሱን ስም ጠራችና ህመሜን ቆሰቆሰችው ደግሞ ለኔ አሳቢ አመሰግናለው ማልዳ እንቅልፌን አባረርሽው የትላንቱ ቀን ተደገመ ሳልተኛ ነጋ፣
ዛሬ ግን ስራ መሄድ አለብኝ ቤት ቁጭ ካልኩ ለራሴም ለአባቴም ጭንቀት ነው የምሆነው ብዬ ተነሳው፣
ካባድ ሁለት ወራት ለኔ በህይወቴ ካስተናገድኳቸው ለወደፊት ከማስተናግዳቸውም የከፉ ጊዜያት ነበሩ፣ እንቅልፍ የለ ፣ ምግብ የለም፣ ከቀን ወደቀን ክብደቴ እየቀነሰ መጣ፣ ዛሬ ከወትሮ የከበደኝ ቀን ነው እንጃ ምን እንደቀፈፈኝ አላውቅም ከሰሞኑን የከፋ ቀን እንደማላሳልፍ እርግጠኛ ነኝ፣ ለዛም መሰለኝ በጊዜ ሱቅ ዘግቼ ወደቤት አመራው፣ አባቴ እንደወትሮ ከጀንበሯ አጠገብ የለም፣ ግርምት ፈጥሮብኝ
"አባቴ ምነው ከጀንበሯ ተጠላቹ እንዴ ዛሬ ብቻዋን ናት"
ወደቤት ውስጥ እየገባው አባቴ ከተቀመጠበት ወንበር ተንሸራቶ እንደወደቀ ያስታውቃል ብቻ አባቴ ከመሬት ተዘርሯል አባቴ ጩኸቴን አቀለጥኩት
አምር መኪና ይዞልኝ መጣ አባቴን ሀኪም ቤት ስንወስደው ልቡ በዝግታ ትርትር እያለች ነበር፣
ሀኪሞች ተረባረቡበት ፣ የልብ ምቱ እንደቀነሰ እንዲሁም የደም መተላለፊያ ቱቦው እንደጠበበን ተነገረን ፣
ማልዳዬ ስልኬ ላይ ደጋግማ ደወለች አነሳሁላት
ሄለው ምነው ለምን ስልክ አታነሳም
ስራ በዝቶብኝ እኮ ነው
እኔ ደግሞ በጣም እፈልግሀለው ማወራህ ጉዳይ አለኝ
ይኼ ማወራህ ነገር አለህ ምትለዋ ቃል አትጥመኝም የሆነ ከባድ ህመምን ሰጥቶኝ የሚያልፍ ስለመሰለኝ ውስጤ ፈራ
"ምን መሰለህ ዛሬ የሲሱ ልደት ነው፣
ሲሳይ ፍቅረኛዋ ነው ሲሱ ብላ ማቆላመጧ ነው
"እና .."
"ማለት ጊፍት ምን ልሰጠው እንደምችል እንድታማክረኝ ነው፣"
በውስጤ ጥይት፣ ማላታይን ይገለዋል ያልኩትን ሁሉ አሰብኩ፣
"አንቺ ምን ልሰጪው አሰብሽ?"
"እንጃ ብቻ ምንም ባስብ ለሱ አልመጥነው አለኝ የሱን መወለድ ለኔ ያለውን ቦታ አልገልፅልሽ አለኝ
ጭራሽ!! ታዲያ እኔ ምን አገባኝ ውስጤ ጨሰ ለምን ልቤ በሷ ተስፋ መቁረጥ እንዳልቻለ አይገባኝም የሆነ ጩህ ጩህ የሚል ስሜት እየተሰማኝ ነው፣
"ምን አሰብኩ መሰለህ ቢያንስ የፍቅሬን መጠን ከገለፀለት ማታ አብሬው ላሳልፍ አስቤያለው?"
"ምን !"ድምፄ ሀይለቃልም እልህም ቅናትም ንዴትም በውስጡ ነበረው፣
"ማለት በቃ ..."
"እንዴ ከጋብቻ በፊት በጣም አልፈጠንሽም ማለቴ"
"አውቃለው ግን በቃ ከዛ የተሻለ ምንም ፍቅሬን አልገልፅልሽ አለኝ ለምትወደው ሰው ራስህን አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን የሚያስደስት ነገር አለ"
"ይሻላል ጥሩ ነዋ ወስነሽ ከጨረስሽ ቡኋላ ለኔ ለምን ነገርሽኝ ታዲያ"በድን ሆንኩ አሁን እየለየልህ ነው ትሰማኛለህ ትሰማታለህ " ለራሴ በለሆሳስ አንሾካሸኩ
"ምን አልከኝ?"
"አረ ምንም " ታዲያ ለኔ መንገር ምን አስፈለጋት እዛው እንደፈለገች አትሆንም ለምን ነፍሴን ታስጨንቃታለች ወይስ ብር አንባር ሰበረልዎ እንድጨፍርላት ነው ስልኩን ጆሮዋ ላይ ዘጋሁት፣
ጎበዝ ማልዳ ጥሩ አድርገሽ ማሳበድ ትችያለሽ
የዛን ምሽት እንቅልፍ ተውት ጤና አጥቼ አደርኩ በዚህ ሁኔታ እኔም ፍቅር አቅምም አቅልም እያሳጣኝ ፣
የስቃይ ሶስት አመታት አለፉ ፣ ፍቅር እንዲህ ያደርጋል ሲባል የምሰማውን ሁላ በኔ ላይ ተፈፃሚ ሲሆን ተመለከትኩ መኖሬ ለአባቴ ደስታ ብቻ ስለሆነ እተነፍሳለው፣ ማልዳዬ ልትመረቅ የአንድ ወር ጊዜ ብቻ ነበር የቀራት፣ የሆነ ቀን ድንገት ሱቅ በር ላይ መጥታ ሰርኘራይዝ ስትል ዘለለች፣
"እንዴ ናፍቃኝ ስለነበር ተጠመጠምኩባት መች መጣሽ የኔ ቀበጥ"
"ዛሬ ሰርኘራይዝ ላድርግህ ብዬ እኮ ነው ምን ሆነካል ደግሞ ጠቁረካል እኮ በዛ ላይ ከስተሀል" እያገላበጠች እየተመለከተችኝ፣
"አንቺ ደግሞ ቀልተሻል በዛ ላይ ወፈርሽ አምሮብሻል"
"አይደል?"
"አረ አዎ ሰላም ነሻ" አምር መምጣቷን ሲያይ ከኔ እኩል ደንግጦ እያያት ሰላምታ ሰጣት
"አለን አምርሻ እንዴት ነህ"
"እንዴት መጣሽ ማለት ትምህርቱስ?" አልኳት
"ለሆነ ጉዳይ ነው የመጣሁት ብታዬ ሰርኘራይዝ አለኝ"
"ምንድ ነው በእጇ ወደኋላ የደበቀችውን ለማየት እየጓጓው "
"የሰርግ ጥሪ ወረቀት ሰጠችኝ "
የማን ነው በሚን ስጠቅሳት ክፈተው የሚል ምልክት ሰጠችኝ አምር ለማየት እኔን ደገፍ ብሎ ወረቀቱ ላይ አፈጠጠ የሷ ይሆናል ብዬ ግን በፍፁም አላሰብኩም
የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን የልጃችን
ማክዳ ሳሙኤል
እና
ሲሳይ ማንያዘዋል
የጋብቻ ስነስረዐት የሚካሄደው ሐምሌ 10 ከቀኑ 6:30 ስለሆነ እርሶም ከ ጋር ተገኝተው የደስታችን ተካፋይ እንዲሆኑ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
ጠሪ ወላጅ እናቷ ወይንሸት እሸቴ
እና ወላጅ አባቷ ሳሙኤል ሹመቴ
#ይቀጥላል ክፍል ስድስት
💕🍃🌹🍃........
😘JOIN & SHARE😘
@zahkyu
Any comments
@nahom20
💕...........🍃🌹🍃............💞

🌹 ክፍል ስድስት🌹
👉እውነተኛ የፍቅር ታሪክ😍
👇
😭የመጨረሻ ክፍል😭

ከዚህ በኋላ ምን እያሰብኩ እንዳለው አላውቅም ህልምም መሰለኝ አሁን ከለሊቱ 9:00 ሰዐት ነው ይኼን ፅሁፍ ማለት ያደረ ፍቅር ያልኩትን ፅሁፌን ወይም ታሪኬን ማን እንደሚያነበው አላውቅም ግን በቀን በቀን የሚገጥመኝን እየፃፍኩ ነው ዛሬ የተሰማኝን ስሜት እንዲህ በግጥም ፃፍኩት....
"የተሸጠ እቃ አይመለስም"
ፍቅር ማነው ቃሉ..
ራስህን ገብረህ እሷነቷን መግዛት
ካንተ ህመም ቀድተህ ለሷ ደስታ መንዛት
ዝም ብሎ መመነን ከሷነቷ ገዳም ላይወጡ መከተት
ፍቅር እሷን ወዶ አንተነን ማጣት
ለሷው ነው መሰጠት
ልቤ ለፍቅርሽ ራሱን ሰጠልሽ
እንኪ ኑሬ ይድመቅ ደስታሽ
ከሌላ መዋልሽ ብያደማው
ከወዴት ይሸሸግ ምን ጥጋት ይጠልለው
ሸንጎ አልቀርብ ተካስሼ
ርስቴን አስወርሼ
ፍቅር እዳ ሆነብኝ ጤና ነሳኝ እረፍት አጣው፤
መልስ ካለሽ እስኪ ስጪ የኔን ፍቅር ከወዴት ጣልሽው፤
አንቺን ካስደሰተሽ ለኔ ሙሾው ይሁን
ከደስተሽ ላይ ተገኝቼ ብዘራው እንባዬን
ከፍቅርሽ መዳኛ ስጠማ ኖሬያለው
ይብላኝ እንጂ ላንቺ እኔ እንኳን ድኛለው
የሰጠሽ ጥሪ ለሀዘን ከሆነ
ሙሾ ልደረድር ከደጅሽ መጣለው፣
ላንቺ ሲጨላልም ለኔ ሲበራልኝ
በህልም አይቻለው፤
እንባ ያጣ ለቅሶ ሳቅ ያጣ ፈገግታ እንዲያ ነው ሚሰማኝ
ያ ነው ፍቅርሽ ለኔ በሳቅሽ ስደሰት ማጣቴ ሚያደማኝ
.
.
.
አላለቀም
ከዚህ በኋላ ታምር ያደረ ፍቅር ብሎ የሚፅፈውን ፅሁፍ መፃፍ አልቻለም ምክንያቱም ያን የሚያደርግበት አቅም አልነበረውም ጓደኛው አምር ነኝ ዶክተሮች ባዘዙኝ መሰረት የታምርን ክፍል ስፈትሽ ነበር ይኼን ፅሁፍ ያነበብኩት ለእናንተም ለማካፈል የሞከርኩት ከዚህ በኋላ ምን እንደሆነ እኔ ነግራቹሀለው፣ የማልዳን የሰርግ ወረቀት በእጁ እንደያዘ ወዴት እንደሚሄድ ሳይነግረኝ ከሱቅ እየሮጠ ሄደ፣ ቡኋላ እቤት እንደሄደ አባቱ ጋር ደውዬ አረጋገጥኩ ፣ ምን ሊሰማው እንደሚችል ለጥቂት ደቂቃዎች አሰብኩት ግን አልቻልኩም ፣ በጣም ከባድ ነበር፣ አብሬው መሆን እንዳለብኝ ስለገባኝ በደቂቃዎች ልዩነት ቤት ስደርስ በከፍተኛ ድምፅ ያለቅሳል፣ አባቱ አጠገቡ ቁጭ ብለው ከሱ ባልተናነሰ ለቅሶ እያጀቡት ዝም እንዲል ይማፀናሉ፣ ማንም ሊያረጋጋው አልቻለም፣ ጥቂት ሲቆይ ማልዳ መጣች፣ አስወጡልኝ እያለ መጮህ ጀመረ አባቱ የሱን ለቅሶ የሚያዩበት አቅም አልነበራቸውም ተዝለፍልፈው ወደቁ፣ አባቴ አንተም አንተም ከአባቱ የወደቀ ገላ ጋር እየታገለ ይኼን ብቻ ነበር ሚናገረው፣ አንቡላስ ጠርተን አባባን ወደሀኪም ቤት ብንወስዳቸውም፣ ሀኪም ጋር ሳይደርሱ ነበር ህይወታቸው ያለፈው፣ ቡኋላ ድንጋጤው ከከፍተኛ ልብ ህመማቸው ጋር ተዳምሮ ለዛ እንዳበቃቸው ተነገረን፣ ከዚህ ቡኋላ ጓደኛዬን መልሼ ማግኘት ከበደኝ፣ የአባቱን ሞት ካየ በኋላ መሳቅ ጀመረ
"አላልኳችሁም ሁሉም አስመሳዬች ናቸው"ሀሀሀሀሀሀሀ
"አባቴ አንተም አንተም እንኳን ደግ አደረክ"ሀሀሀሀ
"እኔን ማንም አይወደኝም እናቴም ብትሆን"
"እሷ ያልወደደችኝ ማን ሊወደኝ"
"ደግ አደረክ "
"አባቴ አንተም"
ጓደኛዬ ለእብደት የቀረበ እብደት ውስጥ ሆነ የአባቱ ቀብር ላይ እንኳን አልተገኘም፣
አሁን የአዕምሮ ህሙማን ማገገሚያ ይገኛል፣ ህክምና እየተከታተለ ቢሆንም ለማገገም ብዙ ጊዜያት እንደሚፈጅ ዶክተሮቹ ገንረውኛል።
ማልዳስ እንደማትሉኝ ተስፋ አለኝ......
.
.
ዛሬን እንፋቀር ይቅር ለነገ ያደረ
ፍቅር ከአቅም በላይ ደርሶ ከከረረ
ከማላታውቃት ንጋት ከነገ አትላተም
ከተሰጠህ ዛሬ ተፋቀር ግድ የለም
.
.
ፍቅር ካልከፈልከው ይከፍልሀል፣
ፍቅር ከከፈልክለትም ይከፍልሀል፣
ፍቅር ወይ ይከፋብሀል፣ ወይ ይከፋልሀል፣ ወይ ይክስሀል!!!!
.
.
.
🎀 ተፈፀመ 🎀
👉አሳዛኙ የፍቅር ታሪክ ይሄን ይመስላል.....ታሪኩ እውነተኛ ነው የተቀነሰም የተጨመረም ነገር የለም።
📩ሀሳባችሁን በ @nahom20 ላይ አድርሱኝ።
😘JOIN & SHARE😘
@zahkyu
Any comments
@nahom20
💕..........🍃🌹🍃...........💕