Telegram Web Link
#ሞርያ
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል 1

@zahkyu

አፎምያ እባላለሁ ህይወቴ ያሳየችኝን ልነግራቹ ወደድኩ
ከእኔ ህይወት ትማራላቹ ብዬ አስባለሁ በተለይ ሶሻል ሚድያ ለምትጠቀሙ ሁሉ ሁሌም ሰው ሰለ ራሱ መልካም ነገር ያስባል ነገ የተሻለ ቦታ መድረስ ይፈልጋል ግን ዛሬ የምንኖረው ኑሯችን ነገ ለምንመኘው ህይወት መንገድ መሆኑን እንዘነጋለን ሲበዛ የሶሻል ሚድያ ተጠቃሚ ነኝ አንድ ቀን ግን በህይወቴ ተፅኖ ያመጣል ብዬ አስቤ አላውቅም በህይወቴ ውስጥ ብዙ ወንዶች ይመጣሉ ይሄዳሉ እንግዲህ በዚህ መሃል ነው ሚክያስ ሚባል ወደ ህይወቴ የመጣው የተዋወቅነው በሶሻል ሚድያ ነው ሲበዛ ዝምተኛ ይመስላል አንዴ ከጀመረው

ግን ማያባራ ጫወታ ነው ሚያመጣው ኦንላይን ካለ እናወራለን ግን ብዙ ግዜ አይግገባም የሴት ጓደኞቼ ጋር ወንዶችን ማታለል ሆነ ማጨበርበር ስራ አድርገን ተያይዘነዋል ወንድ ልጅ በተለያዩ ኢንተርኔቶች ሴቶችን ወደድኩሽ አበድኩልሽ እንደሚሉ ሁሉ እኛም ከወንዶች የባስን አስመሳይ ሁነናል በርግጥ አንድ ቀን ይሄን ነገር ፈልገን አልገባንም ሄርሞን ምትባል ጓደኛችን በተለያየ ግዜ በወንዶች ተጎድታለች ወደድንሽ እያሉ ይቀርቡዋታል መጨረሻው ግን አያምርም እኛም በቀል መስሎን ብዙ ወንዶችን አስለቅሰናል እኔም በዚሁ ባህሪዬ ብዙዋች ጋር እንድቀራረብ አድርጎኛል አስመሳይነትን ተክኜበታለሁ ከምንም በላይ የገረመኝ ግን ብዙ ነገሮችን ሳደርግ

ሚኪን አንድም ቀን ዋሽቼው ሆነ አታልዬው አላውቅም ነገሮችን ገና ከመጀመሬ በንግግሮቼ ያውቅብኛል ይረዳኛል ምንም ይሁን ልደብቀው አልፈልግም ግን በሳምንት ውስጥ ሶስት ቀን ባገኘው ነው ጠፋህ ስለው ስራ ይዤ ነው ይለኛል በዚህ መሃል ከጓደኞቼ መሀል ረብቃ ምትባለዋ ልጅ ስለሱ አጥብቃ ጠየቀችኝ ሁላችንም በተገናኘን ቁጥር ሙድ ስለ ያዝንባቸው ወንዶች እናወራለን አንዳችን የአንዳችንን ስልክ እናያለን ረብቃ የእኔን ስልክ

ስትጎረጉር ወንዶች ጋር ቻት ባደረኩት ነገር ስትስቅ ቆይታ በመሃል ግን ዝም አለች ከደቂቃዋች በኋላ ምነው ዝም አልሽ ምን አይተሽ ነው ብዬ ጠጋ ብዬ ሳይ ሚክ ጋር የተፃፃፍነው ሚሴጅ ላይ አፍጥጣለች በግርምት ነው ምታነበው መጨረሻ ላይ ስለ ሚኪ አፋጣ ጠየቀችኝ ከምፃፃፋቸው ወንዶች ውስጥ አንዱ ነው ምንም የተለየ ነገር የለንም አልኳት አይመሰለኝም ብቻ ብላ እንደ መሳቅ ፈገግ አለች በዚህ መሃል ታላቋ እህቴ ለመምጣት ሳምንት እንደ ቀራት ነገረችኝ የምትኖረው ጀርመን ነው በጣም ነበር የደነገጥኩኝ እህቴ መጣች ማለት እኔ ጋር ውላ ስለ ምታድር ምፃፃፋቸውን ነገሮችን

ላቆም ነው እህቴ እንደዚህ አይነት ነገሮች አይመቻትም በርግጥ በእድሜም ቢሆን በሶስት አመት ነው ምትበልጠኝ በሰአቱ መምጣቷን ብፈልገውም ግን እንደ በፊት ነፃ የሆነ ሰአት አይኖረኝም ለጓደኞቼ ስነግራቸው ባህሪዋን ስለ ሚያውቁ ከአሁን ማቆም እንዳለብኝ ነገሩኝ ማታ ላይ በጣም ለምቀርባቸው እና ለምቀላለዳቸው ልጆች ይሄን ሰሞን ስራ ስላለብኝ አልገባም ብዬ ከነገርኳቸው በኋላ ልክ ልወጣ ስል ሚክ ትዝ አለኝ ልቤ ትንሽ ድንግጥ አለ ምን እንደ ሆነ ለራሴም አልገባኝም የሚገርመው እህቴ ልትመጣ እንደ ሆነ እውነቱን ግጥም አድርጌ ፃፍኩለት ለራሴ እስኪ ገርመኝ ድረስ ፅፌለት ወጣሁና ከሰአታት በኋላ ልክ ልተኛ አከባቢ ስገባ የባሰ ደነገጥኩ…
.
.
.
..
#ይቀጥላል
»»———— - ★ ———— - ««
• . ───── ❁ ❁ ───── . •


@Love pic's
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@nahom20
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
🤶🤶🤶💋💋😍😍
@nahom20
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄



#ሞርያ
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል2

@zahkyu

እህቴ ልትመጣ እንደ ሆነ እውነቱን ግጥም አድርጌ ፃፍኩለት ለራሴ እስኪ ገርመኝ ድረስ ፅፌለት ወጣሁና ከሰአታት በኋላ ልክ ለተኛ አከባቢ ስገባ የባሰ ደነገጥኩ
ሜሊ ልትመጣ ነው እንዴ አለ ገረመኝ እህቴን የት ሊያውቃት ቻለ ብዬ በጣም ተወዛገብኩ አንቺ ራስሽ

አደል እንዴ ከዚህ በፊት የነገርሽኝ ብሎ ሳቀብኝ እኔም መቼ እንደ ነገርኩት ትዝ ባይለኝም ይሆናል አልኩት እና ሲመቸኝ ሚሴጅ እልክለሃለው ስለው እኔ ደግሞ ከናፈቅሽኝ እደውላለሁ ብሎ ተሳስቀን ተለያየን የዛን ቀን እንቅልፍ ሳይመጣኝ አደር ከሌሎች ወንዶች ለየት አድርጌ ነው ማየው ታድያ ምን ይሁን ልቤ እንዲህ ሚደነግጠው ብዬ ግራ ገባኝ ይህ እንዳለ ቀኑ ደርሶ

እህቴ መጣች በጣም ነበር ደስ ያለኝ በጣም ናፍቃኝ ነበር የሚገርመው እህቴ ጋር ቁጭ ብዬ እያወራሁ ሃሳቤ ግን ሚክ ላይ ነው ግራ ቢገባኝ እንደ ምንም ብዬ ወደ ማታ አከባቢ እህቴ ከዘመዶቻችን ጋር የቀለጠ ወሬ ስትይዝ እኔም ክፍሌ ገባሁና በሩን ከዘጋሁ በኋላ ፀሎት የሚያደርግ ሰው ይመስል ቦታ መርጬ ለሚኪ

ደውልኩለት በመጀመርያው ጥሪ አላነሳልኝ አለ ልቤ ብዙ ነገር አሰበ መልሼ ደወልኩ ልክ አንስቶ ሄሎ እንዳለ እኔ መጥቼ ላንሳልህ ብዬ ወረድኩበት ከቻልሽ ነይና አንሺው አለኝ እረ ጥጋብ ማነው ግን እንዲህ የልብልብ የሰጠህ ለገና ለሶስት ቀን ጠፋች ብለህ ነዋ አልኩት ሳቁን አልቻለም የተወሰነ እንዳወራን ክለሴ ተንኳኳ

ነግሬው ቻው ብዬ ስልኩን ዘጋሁ ድምፁን ስለ ሰማሁ ደስ አለኝ ግን ወስጤ ሁሌም በፍረሀት ነው ያለው ምክንያቱ ደግሞ ሚክ በመልክ አያውቀኝም ድንገት በወሬ መሃል ፎቶሽን ላኪልኝ ካለ ስንገናኝ ነው ምታየኝ እለዋለሁ እስከዛ የኔንም ፎቶ እንዳታይው ይለኛል እየሳቀ በዚህ መሃል እህቴ ጋር ከሀገር ሀገር መዞር ጀመርን ያላት ሁለት ወር ብቻ ነው እህቴ ከድሮ ባህሪዋ ብዙ ነገሮቹዋ ተቀይረዋል በጣም ተጫዋች እና ቀልደኛ ሁናለች እኔ ነገሩ ግራ ቢገባኝም ግን ሀይለኝነቷ

እንዳሰብኩት አደለችም ዛሬ እኮ አንቺ ህፃን አደለሽም መካሪ እንጂ ተመካሪ አደለሽም ትለኛለች ከህፃንነቴ ጀምሮ የምትለኝን ሁሉ አድርጋለሁ ከቤተሰባችን እንደ እሷ ምፈራው ሰው የለኝም በዚህ መሃል እሁድ ቀን ጓደኞቿ እቤት መጠው ይዟት ወጡ እኔም ለሚኪ ልደውል ብዬ ደስ አለኝ ግን ሚኪ ስልኩ አይሰራም ረፋዱ ላይ የወጡትን ወደ ማምሻ አከባቢ መጡ በጣም ለቀቀ ብሎ ነው የመጡ ትንሽ ለው ብለዋል ማታ ላይ ልንተኛ አከባቢ እህቴ አንቺ ዛሬ የገጠመኝን ሳልነግርሽ አንድ ደስ የሚል ልጅ… .
.
.
... . . . ይቀጥላል

@zahkyu
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@nahom20
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
💋💋💋💋
#ሞርያ
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል3

@nahom20

እህቴ አንቺ ዛሬ የገጠመኝን ሳልነግርሽ አንድ ደስ የሚል ልጅ ተዋወኩልሽ አለችኝ ደስ ይላል ምን አይነት ልጅ ነው እንዴት ተዋወቃቹ የት ላይ ነው እያልኩ በጥያቄ አጣደፍኳት እሷም እየሳቀች ትነግረኝ ጀመር የሳምሪ ባል ምሳ ካልጋበዝኳቹ ብሎ አንድ ሆቴል ላይ ጠርቶን ሄደን ልክ ምሳ በልተን እንደ ጨረስን አንዱ ተጠቃሚ መሰለኝ እየወጣ እያለ ሚክያስ ብሎ ጠራውና ስለም ከተባባሉ በኋላ ተዋወቃቸው ብሎ አስተዋወቀን ገና ተናግራ ሳትጨርስ ወገቤ ቁምጥ ያለ መሰለኝ እናስ አልኳት ሁላችንንም ሰላም ካለን በኋላ እኔን

ትኩር ብሎ አየኝ ትንሽ ግራ ገባኝ ፊትሽ አዲስ አልሆነብኝም አለ እረ በጭራሽ ተሳስተህ ይሆናል አታቃትም አለች ሳምሪ ግን እንጃ ብቻ ብሎ ፊቴ ላይ ሚያውቀው ፈገግታ ያለ ይመስል አይኖቼ ላይ ፈለገ እኔም የልጁ እይታ ሳቄን አላስቻለኝም ካልተቀመጥክ ሲሉት አጠገቤ ተቀመጠ በቃ በሚያወራቸው ነገሮች ጥርሴን ሳልከድን መጣሁ እልሻለሁ ስትል በድንጋጤ መልስ አልሰጠኋትም ምነው ደበረሽ አለችኝ አቤት ብዬ ሳኩባት ደህና ለመምሰል ፈገግ አልኩ እዛን ቀን አዳሬን አልተኛሁም ሚክ ሊያፈጥባት የቻለው ደግሞ ከአመት በፊት ፎቶዋን ልኬለታለሁ ለዛ ነው የት እንደ ሚያውቃት ግር ያለው በሁለተኛው ቀን ስልኬን እነደ ከፈትኩ ሚሴጅ ልኮልኝ ነበር ሳየው በጣም ደስ አለኝ ደውዬለት ትንሽ

አወራን እሱ አንድም ቀን ስለ ፍቅር ህይወቱ አውርቶኝ አያውቅም ላውራ ብል እንኳ ያስቀይሰኛል ሲፈጥረኝ አንድ ነገር ባለቤቱ ራሱ ካልነገረኝ በስተቀር አፋጦ መጠየቅ ሚባል አልፈጠረብኝም ልክ በሳምንቱ ጓደኞቼ እቤት መጠው ይዘውኝ ወጡ እህቴ ከመጣች ጀምሮ አልተገናኘንም ልክ እንደ ወጣ እህቴ ደወለችልኝ የሆነ ቦታ እንሂድ ስትለኝ ከጓደኞቼ ጋር ነኝ ትንሽ ራቅ ብያለሁ አልኳት እሺ በቃ ሳምሪ ጋር እሄዳለሁ ብላ ስልኩን ዘጋች ለጓደኞቼ የሆነውን ሁሉ ነገርኳቸው በርግጥ ጓደኞቼም

ቢሆን ሚኪን ሀይ ይሉታል ግን ምንም ታክል ቢፅፉለት አይመልስላቸውም ማታ ለይ እህቴ ስትመጣ በቃ በጣም ደስ ብሏት ነበር የመጣች ምንድ ነው እንዲህ ጥርስ በጥርስ ያረገሽ አለኩ ሁኔታዋ ደስ እያለኝ ምን ይሄ ቀልደኛ ልጅ ነዋ እንዲህ አድርጎ የሰደደኝ አለች የልቤ ምቱ ተቀየር የሚወዱት ሰው ስም ሲጠራ ምን ያህል ልብ ላይ እንደ ሚከብድ የደረሰበት ያውቀዋል ሚኪ ነው አልኳት እእ ብላ ሳቀችብኝ እረ ሚክያስ ነው ምነው አቆላመጥሽውሳ ስትለኝ የድንጋጤ ሳቅ እንዴት ልቻል አንቺን እንደዚህ አድርጎ ፍልቅልቅ አድርጎ ልኮልኝ ባለ ቆላምጠው ነበር ሚገረመኝ አልኳት እየተሳሳቅን ወደ መኝታ ክፍል ገባን እኔ ግን እንቅልፍ ሚባል አጥቻለሁ ሁሉ ሃሳቤ እሱ ላይ ነው ምን እንደ ማደርግ አላውቅም በሶስተኛው ቀን ግን የፈራሁት አልቀረም

ዛሬ ማኪያቶ ካልጋበዝኩሽ እያለኝ ነው ተነሽ ልበሽና እንሂድ ስትለኝ ከድንጋጤ የተነሳ ተርበተበትኩ እኔ አሞኛል የትም መሄድ አልችልም አልኳት እረ ደህና ትቀልጃለሽ ደግሞ እኮ እህቴንም አስተዋውቅሃለው ብዬዋለሁ ስትል ከቆምኩበት ዝርግፍ ብዬ ቁጭ አልኩ ቆይ ከእኔ የደበቅሽኝ ነገር አለ እንዴ ወይስ ታቂዋለሽ ልጁን አለችኝ በቃ መልስ አሰጣችኝ እህ ምን ማለት ነው የት ነው ማውቀው ገና ሻወር ምናምን ገብቼ እሱ ነው ስልችት ያለኝ ብዬ በግድ እየሳኩ በውስጧ ሌላ ነገር እንዳታስብ አሳመንኳት ግን የት ቀረልኝና ከቤት ጨራርሰን ወጣን በቃ ካፌው አከባቢ ስንደርስ እግሬም አልታዘዘልኝ አለ የግዴን ተጎትቼ ገባሁ ሚኪ ጀርባውን ሰጦ ነበር የተቀመጠ ሚክያስ አለችው ዞር ሲል…

.
.
.

.

#ይቀጥላል

@zahkyu
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@nahom20
╚═══❖•🌺🌸•❖═══
Because
I love you
አንዱ ጀለሴ ክለብ ካገኛት ቺክ ጋር ወሲብ አድርገው ከጨረሱ በኃላ

እሷ~ይቺን ሚጢጢዬ ጊታር ይዘህ ታካብዳለህ? ስትለው
እሱ ምን ቢላት ጥሩ ነው

ስቴዲየም ላይ እንደምዘፍን ቀድመሽ አነግሪኝም ነበር
😀😀😀😀😀😀😀

Don't Forget .
👇
Share 😘 Share ቀን በቀን ለመሳቅ ይቀላቀሉን
ይቀላቀሉን
@zahkyu


@nahom20
💋💋💋💋
#ሞርያ
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል_4
@nahom20

ካፌው አከባቢ ስንደርስ እግሬም አልታዘዘልኝ አለ የግዴን ተጎትቼ ገባሁ ሚኪ ጀርባውን ሰጦ ነበር የተቀመጠ ሚክያስ አለችው ዞር ሲል ፊት ለፊት ተፋጠጥን ሰውነቴ ድንዝዝ ነበር ያለው ተነስቶ ሰላም አላት ታናሽ እህቴ ያልኩ እሷን ነው ተዋወቃት አለችው ነው ብሎ ፈገግ አለና ሚክያስ ሲል መልስ አለሰጠሁትም ስምሽን ብሎ ሳይጨርስ አፎምያ አልኩት እ … አለ እሷ ትክ ትክ አድርጋ አየችን ከመበላት ብዬ

ጠቀስኩት እ ቅዱስ ሚካኤል ያደነው አፎምያ አይሁን እንጂ አንቺን ለመተዋወቅ አይከብደኝም ብሎ አስቀየሰ የካህኑ ልጅ ሚክያስ አትሁን እንጂ እኔም እንዳንተው አልኩት እህቴ ምንድ ነው ምትፈላሰፉብኝ ብላ ተቀመጠች በሰአቱ ድንጋጤዬ ይሄ ነው ከምለው በላይ ነበር ማታ ላይ ደወለልኝ ገና ሄሎ ስል ሀይ አንቺ አጭቤ እንዴት ዋልሽ አለኝ ሳቅ ብዬ ሰላም አልኩት አይገርምም ጠርጥሬ ነበር

እህትሽ እንደምትሆን በዛ ላይ ስለሷ የነገርሽኝ ነገሮች በጣም እንድቀርባት አድርጎኛል አለኝ ውስጤ ቅር ቢለውም አዋ እህቴ ባህሪዋ እንደ ነገርኩህ ነው ለወደደችው ማች ናት አልኩት እሱን እናየዋለን አለ ምን አስበህ ነው አልኩት እረ ምንም ብሎ ሳቀብኝ ትንሽ እንዳወራን ነገ እደውልልሃለው ብዬ ዘጋሁበት እህቴ ማታ ላይ ወሬዋ ስለሱ ብቻ ሆነ እኔም ስለሱ መሆኑን መች

ጠላሁና ግን ነገሩ ግራ እየገባኝ ነው እህቴ በጥቂት ቀናት ውስጥ ሳትወደው አልቀረችም ነገሩን ለጓደኞቼ ነገርኳቸው እናጣላቸው አሉኝ ደነገጥኩ እህ ምን ብለን ነው ምናጣላቸው ያለምንም ነገር ደርሶ ማጣላት አይከብድም አልኩ ላንቺ እሱን ከማጣት ይሄ ቀላል ነገር ነው በዛለይ እህትሽ ተመልሳ ለመሄድ ሶስት ሳምንት ብቻ ነው የቀራት በኃላ ከማልቀስ አሁን ነው መፍቴውን መፈለግ ብሎ በወሬ ተስፋ ሞልቶ ላኩኝ ነገሩን ቆም ብዬ ማሰብ አልቻልኩም የገዛ እህቴ እኔ ላይ የተደረበች መሰለኝ ውስጤ እርር አለ በርግጥ እህቴ ስለኔ እና ስለሱ ግንኙነት ምታውቀው ነገር የላትም ውስጤ ግን ይሄን

ነገር አልቀበለኝ አለ እህቴ ሚኪን ካወቀችበት ቀን ጀምሮ ቤት አትቀመጥም አብዛኛውን ሰአት እሱ ጋር ነው ምታሳልፍ በጣም ደስተኛ አድርጓታል እንደ ምንም ብዬ
እህቴ እቤት ስትገባ ጠብቄ ለሚኪ ደወልኩለት ይመቸሃል እንገናኝ እለኩት እሁን እኮ እህትሽ ጋር ቆይቼ ወደ ስራ ቦታ ገባሁ አለኝ ካልተገናኘን ብዬ ግግም አልኩበት እሺ ነይ አለኝ ለጓደኞቼ ደውዬ ሚኪ ጋ እየሄድኩ እንደ ሆነ ነገርኳቸው መልሰን እንደ ውልልሻለን አሉኝ እኔም ብዙም ትኩረት አልሰጠኋቸውም ልክ ካፌው አከባቢ ስደርስ መልሰው ደውሉልኝ የት ነው የተቀጣጠራቹ አሉኝ እህ ምን ልትሆኑ ነው ምን አስባቹ ነው አልኳቸው ዝም ብለሽ ንገሪን ሲሉ ነገርኳቸው ልክ ካፌ እንደ ገባሁ ሚኪ

ከኋላዬ ተከተሎኝ ገባ ሳየው ልቤ ስንጥቅ አለ አንቺ አይጥ ብሎ ገንጬን ሳመኝና ቁጭ አልን ብዙም ደቂቃ ሳንቆይ ጓደኞቼ መጡ ሁለቶች ቀድሞ ገቡና ከኛ ራቅ ያለ ወንበር ላይ አንዷ በግራ አንዷ በቀኝ ተቀመጡ ትንሽ ተደናግጫለሁ ረብቃ ቀጥ ብላ ወደኛ መጣች ጠቀስችኝ እኔም ላለማስጠጣት ዝም አልኩ መጣ ሰላም ብላኝ ይሄ ልጅ ሚኪ ያልሽኝ እንዳይሆን አለች ደነገጥኩ ፈገግ ብዬ አዋ አልኩ ጓደኛዬ ናት ተዋወቃት አልኩት ተነስቶ ሰላም ሊላት ሲል እሷ በዛ ቅፅበት…
.
.
.
...
#ይቀጥላል

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@zahkyu
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
#ሞርያ
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል5
@nahom20

ረብቃ ቀጥ ብላ ወደኛ መጣች ጠቀስችኝ እኔም ላለማስጠጣት ዝም አልኩ መጣ ሰላም ብላኝ ይሄ ልጅ ሚኪ ያልሽኝ እንዳይሆን አለች ደነገጥኩ ፈገግ ብዬ አዋ አልኩ ጓደኛዬ ናት ተዋወቃት አልኩ ተነስቶ ሰላም ሊላት ሲል እሷ በዛ ቅፅበት አይኑን እያየች ሰላም ምትል መስላ እሱ ሚጠጣው ማኪያቶ ውስጥ የሆነ ነገር ጨመረችበት ደነገጥኩኝ ሰላም ብላን ወደ ጥግ ሂዳ አንዷ ጓደኛችን ጋር ቁጭ አለች ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ሚክ ጋር እያወራን ላብ በላብ ሆነ አንዴ መታጠብያ ክፍል ልሂድ ሞቀኝ ብሎ ሄደ ረብቃ ተከትላው ገባች እኔ ደንግጫለሁ አንቺ ምን ያደናብርሻል አለችኝ አንዷ

ጓደኛችን መልስ አልሰጠኋትም ከደቂቃዋች በኋላ ሲቆይብኝ ግዜ ወደ መታጠብያ ክፍል ስገባ መሬት ላይ ተዘልፈልፎ ወድቋል በቃ ማደረገውን ሁሉ አጣሁኝ ረብቃ አብራ ስትገባ አይቻለሁ ግን የለችም ስደውልላት ደርሻለሁ አለችኝ በቃ ከድንጋጤ የተነሳ መቆም አቃተኝ ወዲያው ረብቃ መጣች ሳዲዝ የሚባል የሰፈራችን ልጅ ጋር መጣች ለሁለት አንስተውት ይዘውት ወጡ እኔም ተከትያቸው ወጣሁ ልክ ካፌው በር ላይ ልወጣ ስል አስተናጋጇ ሂሳብ ብላ ያዘችኝ አናዳኝ መቶ ብር ሰጥቻት መልስ ሳልጠብቅ ተከትያቸው ኩንትራት ወደ ያዙት ላዳ ልገባ ስል አንቺ ወደ ቤት ሂጂ አለችኝ ቆይ አንቺ ምን አይነት ሃሳብ ነው እኔ ይሄ ነገር ምንም ደስ አላለኝ አልኳት እረ

ባክሽ ብላ አፌዘችብኝ እኔም ወደ ቤት ተመለስኩ በቃ አርፌ መቀመጥ አልቻልኩም ልክ በሁለተኛው ቀን ሚኪ ደወለልኝ በድንጋጤ እንዴት አድርጌ ላንሳው ስልኬን ብዘጋው ሊጠረጥር ይችላል ብዬ ፈራሁ ሊዘጋ ስል አነሳሁት ድምፁ ቀዝቀዝ ብሏል ሰላም ካለኝ በኋላ እኔምልሽ የተገናኘን ለታ ምንድ ነው የተፈጠረው አለኝ ላበት በላበት ሆንኩ ተመስገን አምላኬ እንኳንም በአካል አልሆነ አልኩ እየተርበተበትኩም ቢሆን እኔ ምን አውቃለሁ አንተን ልጠይቅህ እንጂ መታጠብያ ቤት ገብተህ በዛው የሄድክ አንተ አልኩት ምን አለኝ አዋ ቆይ

ግን ምን ሁነህ ነው አልኩት ሲበዛ አስመሳይነትን ተክኜበታለሁ ለእኔም ገርሞኛል ስነቃ ራሴን ያገኘሁት ሆቴል ውስጥ ነው ብቻ አላውቅም በቃ ይመችሽ እደውልልሻለሁ ብሎ ዘጋብኝ ተመስገን አልኩ በዚህ መሃል እህቴ ሚኪ ዘንድ እንሂድ አለችኝ እ አልኩ ደነግጬ ምነው ስትል አይ አንቺ ሂጂ እነ ረብቃ እየመጡ ነው ምንሄድበት ቦታ አለ አልኳት ከሆነ እሺ ብላ ሄደች ሚኪ ዘንድ ልሂድ ብላ ስትወጣ በጣም ነው ምናደደው ከቀን ቀን ለሚኪ ያለኝ ስሜት ከአቅሜ በላይ እየሆነ ነው በዚህ መሃል ወደ ባ/ዳር ለሶስት ቀን ልሄድ ነው አብረን እንሂድ አለችኝ ሚኪ ይሄዳል አልኳት እሱ አደል ሃሰቡን

ያመጣው አለችኝ እንደዛ ነው ነገሩ አልኩ በልቤ ካልደበረሽ ብቻቹን በትሄዱ ይሻላል ምክንያቱም አሪፍ ግዜ ታሳልፋላቹ አልኳት አንቺ ልጅ ግን እንዲህ በስለሻል እንዴ ብላ ሳቀችብኝ እኔ በልቤ በስዬ ባረርኩበት ሰአት እሷ ትቀልድብኛለች ነገውን ሊሄዱ ማታ ላይ ረብቃ ደወለችልኝ በጣም ደነገጥኩ ምን እንደነካኝ አላውቅም እንደ ምንም ብዬ ስልኩን አናሳሁ ሄሎ ከማለቴ አየሽው አለችኝ ምኑን አልኳት ዋት ሳፕ ላይ ልኬልሻለሁ አለችኝ ዳታዬን ከፍቼ ወደ ዋትስ አፕ ስገባ የላከችልኝን ፎቶ ሳይ ልቤ ለሁለት ስንጥቅ አለ

.
.
.
.
#ይቀጥላል

@zahkyu
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿»🌺̶̥✽̶┉┉┄┄
#ሞርያ
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል6

@nahom20

ረብቃ ደወለችልኝ በጣም ደነገጥኩ ምን እንደነካኝ አላውቅም እንደ ምንም ብዬ ስልኩን አናሳሁ ሄሎ ከማለቴ አየሽው አለችኝ ምኑን አልኳት ዋት ሳፕ ላይ ልኬልሻለሁ አለችኝ ዳታዬን ከፍቼ ወደ ዋትስ አፕ ስገባ የላከችልኝን ፎቶ ሳይ ልቤ ለሁለት ስንጥቅ አለ ሚኪ እርቃኑን ከሴት ጋር የሚያሳይ ፎቶ ላከችልኝ እጄ ተንቀጠቀጠ እህቴ እየጠራችኝ ወደ ክፍሌ መጣች እንዴት አድርጌ ስልኩን ላጥፋው እጆቼ አልታዘዘኝ አሉ በቃ በጣም ደነግጫለሁ እንደ ምንም ብዬ አልጋው ላይ በሆዴ ተኛሁ ተነሽ እንጂ እራት እንብላ ብላ እጄን

ይዛ ወጣች እህቴን አይኖቼን ሞልቼ ማየት አቃተኝ በጣም ነበር የከበደኝ ምን ላድርግ ሁሉም ነገር ከአቅሜ በላይ ሆነ ይሄን ሁሉ መዘዝ ያመጣሁ እኔነኝ ፍቅር በሀይል መስሎኝ በነገታው ሚኪ ጋር ወደ ባ/ዳር ሄዱ በቃ ምሆነው አጣሁኝ ቅናት አይሉት ጥላቻ አይሉት ብቻ የኔ ነገር የተለየ ነው በዚህ መሃል ረበቃ ደውላጠራችኝና ሄድኩኝ ስሄድ ጓደኞቼ አንድ ላይ ተሰብስቧል ትንሽ እንደ ተጫወትን ረብቃ የሜሊን ቁጥር ስጪኝማ አለች ማናት ሜሊ አልኩ እህ እህትሽ ናታ ስሟን ቀየረች እንዴ ሳንሰማ አለች እእ ለምን ፈለግሽው ብዬ ሰጠኋት በምን እንላክላት አለችኝ ደነገጥኩ የሚኪን ፎቶ እንደ ሆነ

ሲገባኝ እንደ ምንም ራሴን አረጋጋሁ ረብቃ አንዴ ከወሰነች ሰው ስለ ማትሰማ ቀስ ብዬ ይሄን ፎቶ ከእጇ ማውጣት አለብኝ ብዬ አሰብኩ ዘና ብዬ ቆይ አሁን አንልክላትም ላኪ ስልሽ ትልኪዋለሽ አልኳት አንድ ላይ ሲሆን አሪፍ ጥፊም እንዲቀምስ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ነው አልኳት አየሳኩ ሁሎችም ሳቁብኝ ሚኪ ቢናፍቀኝም መደውል ግን ፈራሁ በሶስተኛው ቀን ልክ እንደ መጡ እንዴት ነበር እያልኩ በወሬ አጣደፍኳት ፊቷን ላየ ሌላ ነገር ያስጠረጥራል በጣም ደስ ብሏታል በቃ ካደርግነው ይልቅ ያለደረግነውን ብጠይቂኝ ይቀላል አለች ፊቴ ተለዋወጠ አልገባኝም አልኳት በቃ አለአ ብላ

ክትክት ብላ ሳቀች ብቻ ደስ ይላል አለችኝ ይሄኔ ነገር ሁሉ ከአቅሜ በላይ ሆነብኝ በመሃከላቹ የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ እስቲ ከመጀመርያው ጀምረሽ ንገሪኝ አልኳት ይሄውልሽ የመጀመርያ ቀን አብረን ብናድርም ምንም የተፈጠረ ነገር የለም በሁለተኛው ቀን ትንሽ ሞቅ ብሎን ስለ ነበር በጣም ተላፋን እእ አልኳት ደንግጬ ምነው አለችኝ ፈገግ ብዬ እሺ ከዛስ አልኳት ሚጠጣ እሩም ድረስ አስመጣን እና አንድ ሁለት ማለት ጀመርን በቃ በትንሹ ይነካካኝ ጀመር እኔም ትንሽ ስለ ጠጣሁ ከእሱ ባስኩ በቃ ከመተሻሻት ወደ…
.
.
.
.
.
.
#ይቀጥላል

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@zahkyu
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
#ሞርያ
#እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ
#ክፍል7
#b

@nahom20


አንድ ሁለት ማለት ጀመርን በቃ በትንሹ ይነካካኝ ጀመር እኔም ትንሽ ስለ ጠጣሁ ከእሱ ባስኩ በቃ ከመተሻሻት ወደ መላፋት ገባን በሰአቱ ማለውቀው ደስታ ውስጥ ስለ ነበርኩ ምንም ነገር ማስታውሰው ነገር የለም ስነቃ ክንዱ ላይ ተኝቼ ነው ራሴን ያገኘው አለችኝ ልቤ ክው አለ ሁሉም ነገር አስጠላኝ ሳምንቱን እሱ ጋር አሳለፈች ልትሄድ አንድ ቀን ሲቀራት ብዙ ነገር አወራችኝ ብዙ ባህሪዬ እንደ ተቀየረባት የሆነ የደበኳት ነገር እንዳለ ሁሉ

ነገረችኝ እኔ ከድንጋጤ የተነሳ ምንም የደበኩሽ ነገር የለም ከማለት ውጭ ምንም ነገር አልተናገርኳትም ሲበዛ ነገሮች ሁሉ እሷ እንዳሰበችው እና እንዳልጠበቀች መሆኑን ነገረችኝ እኔም ሳላውቀውም ቢሆን ስሜቷን እንደ ጎዳሁ ገባኝ ነገውን እሷም ወደ ጀርመን ተመለሰች ሚኪ ከዛን ቀን ጀምሮ ባህሪው ሁሉ ተለወጠ በቃ እንደ በፊቱ ለምኖ አያወራኝም ደዋይ እኔ ብቻ ሁኛለሁ ሁሉም ነገር አስጠልቶኛል ልክ እህቴ

በሄደች በወሩ ክላሴን ሳፀዳ ልብስ ማስቀመጫ ባንኮኒ ውስጥ ጠረዝ ላይ የሆነ ወረቀት አየሁ ብዙም ትኩረት አልሰጠሁትም ሳልከፍተው አንስቼ መሳብያ ውስጥ አደረኩት ጓደኞቼ ጋር እንደ በፊቱ በየቀኑ መገናኘት ጀመርኩ የበፊት ጓደኞቼ ጋር ግኑኝነቴን አጠበኩ በዚህ መሃል ጓደኞቼ ጋር እያለሁ እህቴ ደወለች ደነገጥኩ

ብዙን ግዜ ማታ ማታ ብቻ ነው ምን ደዋወለው ትንሽ እንዳነገርኳት እመዬን አገናኚኝ አለች አሁን ወጥቻለሁ አልኳት ነገውንም እንደዚሁ ቀን ላይ ደወለች እመዬን አገናኘኚ አለች እየደበረኝም ቢሆን አሁን ነው ከቤት የወጣሁ አልኳት የእናቴ ስልክ ተበላሽቷል በዚህ መሃል ለሚኪ ደውዬ እንገናኝ አልኩት አይመቸኝም ትንሽ ስራ አለብኝ ነገ እንገናኝ አለ ረብቃ በጣም ተናደደች ማታ ላይ ደውላ በፌክ አካውንቷ ለእህቴ የሚኪን እርቃኑን ያስነሳችውን ፎቶ እንደ ለከችላት ነገረችኝ በጣም ነበር የደነገጥኩኝ ለሶስት ቀን ያህል ስልኬን ዘጋሁ በስራነው ስራ በጣም ተበሳጨሁ በሶስተኛው ቀን ስልኬን ስከፍተው እህቴ ጠፋሽ ብላ ሚሴጅ ልካልኛለች ምንም እንዳል ተፈጠረ ማስመሰሏ ነው ብዬ ትንሽ ግራ ተጋባሁ

ማታ ላይ የተወሰነ አወራን እና ተለያየን የእህቴ በሰላም እኔን ማውራት በጣም ገርሞኛል የሆነ ቀን ላይ ብዙ
ማይጠቅሙ ስህል እስልባቸው የነበሩ ወረቀቶችን ሳቀጥል አንዴ ከባንኮኒ ጠርዝ ላይ ያገኘውትን ወረቀት አይቼው ከፈትኩት እህቴ ነበር የፃፈችው በጣም ደነገጥኩ ማንበበ ስጀምር እጆቼ ተንቀጠቀጡ እህቴ ይሄንን ፁሁፍ ስታነቢ ሊሰማሽ የሚችለውን ነገር
አቃለሁ ግን እኔም ነገሮች ቃል በቃል መናገር ቢከብደኝም ላንቺም በዚህ ይቀልሻል ብዬ ነው
ይሄውልሽ አፎምያ ምን መሰለሽ ሚኪን…
.
.
.
.
.
.
.
#ይቀጥላል
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@zahkyu
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
2025/07/11 21:54:32
Back to Top
HTML Embed Code: