Telegram Web Link
ማኅበረ ቅዱሳን ለወጣቶች የሱስ ማገገሚያ ተቋም ለማቋቋም የሚያስችል ጥናታዊ የምክክር ጉባኤ አካሄደ

ግንቦት ፴/፳፻፲፯ ዓ.ም

"ማኅበራዊ ቀውስን በማከም ትውልድን እንታደግ"  በሚል መሪ ቃል ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደው ጉባኤ በማኅበረ ቅዱሳን ሙያ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት  ከባለድርሻዎች ጋር ሰፊ ጥናታዊ ሰነድን መነሻ ያደረገ ምክክር ተደርጓል።

በአሁኑ ወቅትም በአገራችን ኢትዮጵያ 46 ከመቶ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ለሱስ (በአልኮል፣ ጫት ወይም የሲጋራ) ተጠቂ ሁነዋል ተብሏል። በተመሳሳይ የንጥረ ነገርም ይሁን የባሕሪ ሱስ የተጋላጮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ስለመሆኑ ተነግሯል።

በዳሰሳ ጥናቱ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች በንጥረ ነገር ሱስ ከመጠቃታቸው ባሻገር ሲሶ የሚሆኑት የኢንተርኔት ሱስ ተጠቂ ናቸው ተብሏል። ይህም ብቻ ያይደለ በጥናቱ  የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎቹም ማኅበራዊ የመገናኛ አውታር መጠቀም የማይችሉበት አጋጣሚ ከተፈጠረ ጭንቀት እንደሚፈጥርባቸው አምነዋል ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጥናቱ 52 ከመቶ ገደማ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በተለያዩ የሱስ አምጭ ንጥረ ነገሮች አማካኝነት የሱስ ተጠቂ ሁነው መገኘታቸው የተገለጸ ሲሆን  ከቤተክርስቲያናችን ምእመናን ውስጥ 50 ከመቶ ገደማ የሚሆኑትም ለተለያዩ ሱሶች ተገዢ መሆናቸው ተጠቅሷል።

በማያያዝም ምእመናን በሱስ ምክንያት የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ለመፈጸም እንደሚቸገሩ ነው የተነሳ ሲሆን ቁጥር ልክ የሱሰኛ ወገኖቻችን ቁጥር መጨመሩ ለአገራችን እና ለቤተክርስቲያናችን እጅግ አሳሳቢ ነው ተብሏል።
የንጥረ ነገርም ይሁን የባሕሪ ሱስ ተጠቂ የሆኑ ግለሰቦች የአካልና የአእምሮ ጤናቸው ከመታወኩ ባለፈ ሱሰኝነት በማኅበራዊ ሕይወት ፤ በሰላም እና ደህንነት ብሎም በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳርፈው ጠባሳም ቀላል የሚባል እንዳልሆነ ተመላክቷል።

ታዲያ ለቤተክርስቲያናችን ብሎም በአገር ደረጃ አሳሳቢ ለሆነው ሱሰኝነት በጊዜ መፍትሔ ማስቀመጡ አግባብነት ያለው ተግባር መሆኑ ነው በምክክር መርሐ ግብሩ የተነገረው።

ማኅበረ ቅዱሳንም በሙያ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በኩል ለችግሩ መፍትሔ ብሎ ያስቀመጠው ቤተክርስቲያናችን ባሏት ገዳማትና አድባራት "የሱስ ማገገሚያ ማእከል" ማቋቋምን ሲሆን ለምክረ ሐሳቡ ተግባራዊነት ደግሞ ለእያንዳንዱ ሱስ የሚያስፈልገው የማገገሚያ ዓይነትና ተቋም የሚለያይ በመሆኑ ለሁሉም የሱስ ዓይነቶች ማገገሚያ ተቋም በአንድ ላይ እንዲሁም በተናጠል ማቋቋም በርከት ያለ ገንዘብ፣ ጊዜ፣ የሰው ኃይል ማሰናዳት ያስፈልጋል ተብሏል።


በቀጣይ ጊዜም ይህን ሥራ ወደ ተግባራዊ መፍትሔ ለመቀየር የሚቻልበት ዝርዝር መፍትሔዎችን ወደ ተግባር የሚቀየር ግብረ  ኃይል በማቋቋም ጉባኤው ፍጻሜውን አግኝቷል ተብሏል።
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚፈተኑ ተማሪዎች የሥነ ልቦና ዝግጅት ሥልጠና መሰጠቱን ጅማ ማእከል አስታወቀ።

ሰኔ ፩/፳፻፲፯ ዓ.ም

በጅማ ከተማ ከሚገኙ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለመጡ ከ150 በላይ ለሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ማኀበረ ቅዱሳን ጅማ ማእከል እና የጅማ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት  በጋራ በመሆን በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለሚፈተኑ ተማሪዎች ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም የሥነ ልቡና ዝግጅት ሥልጠና እና የማኅበር ጸሎት መርሐ ግብር በሀገረ ስብከት አዳራሽ አካሂደዋል።

በመርሐ ግብሩ ለብሔራዊ ፈተና ዝግጅት የማኅበር ጸሎት ተደርጓል።

ሥልጠናው የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተማሪዎች በቀሪ ጊዜያቸው በስነልቦና ዝግጁ እንዲሆኑ ያለመ ነው ተብሏል።

በተጨማርም በ25/09/2017 ዓ.ም ተመሳሳይ ወይም ይሄዉ ሥልጠና በተስፋ ተዋህዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚማሩ  ከ50 በላይ ለሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ ላይብረሪ አዳራሽ ተሰጥቷል።

በዕለቱ የሥልጠና ሂደቱ እንዲሳካ የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር መ/ር አማረ እና መምህራን ላደረጉት ትብብር ምሥጋናችን የላቀ ነው።

በመጨረሻም ተማሪዎቹ ከሥልጠናው በቂ ግንዛቤ እንዳገኙና ታስቦ ይህ ሥልጠና መዘጋጀቱ አበረታች እንደሆነ አሰተያየታቸውን ሰጥተዋል።
"ያለንበት ወቅት ከምንም በላይ የእውነተኛ እረኝነት ሐዋርያዊ ሕይወት የሚያሻበት፤ ቤተ ክርስቲያንንም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት የመምራት ጥበብ በእጅጉ የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው። “ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብ አፍሪካና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጾመ ሐዋርያትን አስመልክቶ መልእክት አስተላልፈዋል፤ የብፁዕነታቸው መልእክት ከዚህ እንደሚከተለው ይቀርባል።

"ወሰበኩ ከመ ይጹሙ ጾመ ቅድመ እግዚአብሔር፤ በእግዚአብሔር ፊት ጾም ዐወጁ።" ኤር ፴፮፥፱

በቸርነቱ ብዛት ኃጢአታችንን ይቅር ያለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለ፳፻፲፯ ዓ.ም ጾመ ሐዋርያት በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ።

ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን በተቀበሉ ማግስት ወደ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸው ከመሰማራታቸው አስቀድሞ በጾምና በጸሎት ተወስነው መቆየታቸውን ቅድስት ቤተ ክርስቱያን ታስተምረናለች።

በዚህ በጾመ ሐዋርያት ወቅት የእውነተኛ ሐዋርያዊነት እና አገልጋይነት መሠረቱ ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ በማስገዛት ክርስቶሳዊ በሆነ አካሄድ አገልግሎትን ለመጀመር መታመን መሆኑን የምንረዳበት ነው።

ተወዳጆች ሆይ !

ያለንበት ወቅት ከምንም በላይ የእውነተኛ እረኝነት ሐዋርያዊ ሕይወት የሚያሻበት፤ ቤተ ክርስቲያንንም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት የመምራት ጥበብ በእጅጉ የሚያስፈልግበት ጊዜ ነው። (ሐዋ ፳፥፳፰)

የሐዋርያት ሕይወት ስለ ክርስትናቸው የተቀበሉትን መከራ ብቻ ሳይሆን ከመንፈሳዊ አገልግሎት የሚገኝ ደስታን ለማግኘት መጓዝ የሚገባንን መንገድ የሚያስተምር ነው፤ ለዚህ ነው በመንፈሳዊ አገልግሎታችን ደስተኞች ሆነን የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን ለማገልገል መነሻችን ሊሆን የሚገባው እውነተኛ ክርስቲያንነት እና የክርስትናን ሕግጋት በሕይወት መኖር መሆኑን አበው የሚያስተምሩት።

በምንጾምበት ጊዜም ከጾሙ የምናገኘው በረከት የእግዚአብሔርን በጎ ምላሽ መሆኑን በማመን በልዩ ልዩ መንገዶች ቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተጋረጡ የሚመስሉን ችግሮች ከእግዚአብሔር ሁሉን አዋቂነት እና ሁሉን ቻይነት የማይሰወሩ አንዳቸውም መከራን እንድንቀበል ከማድረግ በቀር ቤተ ክርስቲያንን አሸንፈው ሊወጡ የማይቻላቸው ነገሮች መሆናቸውን መረዳት ይገባል።

በመጨረሻም :- በዚህ የጾም ወቅት በእግዚአብሔር ፊት በምናቀርበው ጸሎትና ልመና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንን በማሰብ በምንሰማራበት ሁሉ አገልግሎታችን ያማረና ለእግዚአብሔር የተመቸ መሆን እንዲችል አብዝተን ልንማጸን ይገባል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
+ አባ ሄኖክ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንየደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ሰኔ ፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
#ሰኔ_፲፪   በዓለ ተዝካሩ #ለቅዱስ_ሚካኤል ሊቀ መላእክት #ወቅዱስ_ላሊበላ 
#ቅዱስ_ሚካኤል_አፎምያንና_ባሕራንን_ያዳነበት_እለእስክንድሮስ_ቅዳሴ_ቤቱን_ያከበረበትና_የቅዱስ_ላሊበላ_ዕረፍቱ_ነው፡፡

   #ሰኔ_፲፪ #መከበሩ_ስለምንድን_ነው_ቢሉ_
ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር፤ ንሥረ አርያም የሚባል፥ ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ፥ ንዑድ ክቡር የሆነ ፥ የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ፭ት ነገሮችን የፈጸመበት እለት ነው  እንዲሁም  የሌሎችም ቅዱሳን መታሰቢያ ቀናቸው  (ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ያሳየበት) ፡፡ ሚካኤል ፭ት ነገሮችን የፈጸመበት እለት ነው  እነርሱም፤
   #share
፠፩. በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል፤
፠፪. ባሕራንን ያዳነበት፤
፠፫. የአስተራኒቆስ ሚስት ቅድስት አፎምያን ያዳነበት፤ በዓለ እረፍቷም በዚሁ እለት ነው፤
፠፬. በግብፅ ሃገር ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ ቅዳሴ ቤቱን ያከበረበት፤
፠፭. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ያሳየበት፤
፠ ሐናፄ መቅደስና በሰማያት ያለ ምሥጢርን የተመለከተ ቅዱስ ላሊበላ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በዓለ ዕረፍቱ ነው፤
፠67ኛ ሊቀ ጳጳስ ቄርሎስ ሊቀ ዻዻሳት ዘእስክንድርያ እረፍቱ ነው፤
፠የእስክንድርያ 6ኛ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ዮስጦስ (ወንጌላዊና ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ የክርስትና ጥምቀትን ያጠመቀው፥ ዲቁናና ቅስናን የሾመው) እረፍቱ ነው፡፡

ማብራሪያ፤
#፩. ቅዱስ ሚካኤል በፈቃደ እግዚአብሔር ከዲያብሎስ ጋር ተዋግቶ ያሸነፈበት፤ አምላክነትን ሽቶ በወደቀው በዲያብሎስ ምትክ ሊቀ መላእክት ሆኖ የተሾመበት እለት በመሆኑ ነው፡፡ ቀድሞ ከ100 ነገደ መላእክት ኃይላት የሚባሉ የ10 ነገደ መላእክት አለቃ ነበር፤ በዚህች ቀን ግን የኃይላት አለቅነቱን እንደያዘ አጋእዝት የተባሉትንና ሳጥናኤል(ሰማልያል) ይመራቸው ለነበሩት 10 ነገዶች በተጨማሪ አለቃ ኾኗል፤ እንዲሁም በአጠቃላይ ለሌሎችም 100 (99ኝ) ነገደ መላአክት አለቃ ሁኗል፡፡ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ያሰኘውም ይኸው ነው፡፡

#፪. ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት፤ ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ /312 - 326/ በግብፅ ሃገር ንግሥት ክሌዎፓትራ ‹‹ሳተርን›› ለሚባለው ያሠራችውንና ጣዖት ይመለክበት የነበረውን ቤተ ጣዖትን አፍርሶ በቦታው ላይ ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ ታቦተ ሚካኤልን አግብቶ በዓሉን በታላቅ ክብር ያከበረበት እለት ነው፡፡

#፫. ባሕራንን ያዳነበት
ሊቀ ጳጳሳት እለ እስክንድሮስ የተሠራውን የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ከሚያከብሩ ምእመናንን አንዱ የባሕራን አባት ነበር፡፡ እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራ ወር በገባ በየዐሥራ ሁለቱ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን የሚዘክርና ይልቁንም በኅዳር ፲፪ትና በሰኔ ፲፪ት ቀን በታላቅ ክብር የሚያከብር አንድ ሰው ነበር፤ በዚህ ሰው ላይ ላይ ጥላቻ ያደረበትና ርኅራኄ የሌለው አንድ ባለጸጋ ጐረቤት ነበረው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በሚያከብርበት ጊዜ ሁሉ ይዘብትበት ይሳለቅበት ነበር፡፡

    ይህ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውም በዚህ ዓይነት በጐ ሥራ ብዙ ጊዜ ከኖረ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ያርፍ ዘንድ የሞቱ ጊዜ ቀረበ። ሚስቱንም ጠርቶ ‹‹በጐ ስራ ከመሥራት ለድኃ ከመመጽወት ቸል አትበይ! የቅዱስ ሚካኤልንም በዓል በየወሩ ከማክበር አትቦዝኝ፤ ይልቁንም በኅዳር ፲፪ትና በሰኔ ፲፪ት  ቀን ከፍ ባለ ሥነ ሥርዓት እንድታከብሪ አደራ እልሻለው›› አላት፡፡ በሚሞትበትም ጊዜ ሚስቱ ፀንሳ ነበር። ይህም ደገኛ ሰው በሰላም ዐረፈና ፍጹም መንግሥተ ሰማያትን ወረሰ። ሚስቱም የመውለጃዋ ሰዓት በደረሰ ጊዜ ታላቅ ጭንቅ ላይ ኾነች እርሷም መልአኩን ቅዱስ ሚካኤል እንዲደርስላት ተማጸነችው በሰላምም ተገላገለች፡፡ መልኩ በጣም ያማረ ልጅ ወለደች። የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ያን ሕፃን ባረከውና ‹‹ቸርነት ርኅራኄ የሌለውን የዚህን ባለጸጋ ገንዘብና ሀብት እርሻውንም ሁሉ ይህ ሕፃን እንዲወርስ እግዚአብሔር አዟል›› አለ። ያን ጊዜ ያ ባለጸጋ በሴትዮዋ ቤት መስኮት አጠገብ ሆኖ ሁኔታውን ሁሉ ይመለከት ነበርና ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ልቡ በታላቅ ሐዘን ተነካ፤ ሕፃኑንም የሚገድልበትን ምክንያት ይፈልግ ጀመር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ብላቴናውን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀው ነበር።

ብላቴናውም ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ እናቱ በጣም ችግር ፀናባት፡፡ ባለጸጋው እኔ ጋር ተንከባክቤ ላሳድገው ብሎ ከእናቱ ከተቀበለ በኋላ፤ በልጅ ቁመት ልክ ሳጥን አሠርቶ ሕፃኑን በሣጥኑ ውስጥ አግብቶ በላዩ ላይ ቆለፈበትና ሣጥኑን ወስዶ ከባሕር ጨመረው፤ እንዲሁም የሣጥኑን ቁልፍ መክፈቻ አብሮ ወረወረው። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ያ ሣጥን ሳይሰጥም በባሕሩ ላይ እየተንሳፈፈ ከዚያች አገር ርቃ ወደምትገኝ የባሕር ወደብ ደረሰ።

በባሕሩ አካባቢ በጎቹን አሰማርቶ የሚጠብቅ አንድ ሰው ነበርና ያንን ሣጥን ባየው ጊዜ ከባሕሩ አወጣውና ወደ ቤቱ ወስዶ ሣጥኑን ቢከፍተው ያ ባለ ፀጋ ሊገድለው ያሰበውን ሕፃን በሣጥኑ ውስጥ አገኘው።  ባየውም ጊዜ እጅግ ተደስቶ በባሕር ውስጥ ስላገኘው ስሙን "ባሕራን" ብሎ ሰየመውና እንደ ልጁ አድርጐ ይንከባከበው ዘንድ ወሰነ፡፡

ከባሕራን ሀገር የበግ ጠባቂው አገር የዐሥር ቀን ጐዳና የሚያስኬድ ርቀት ነበረው። ከብዙ ዓመታት በኋላ ያ ባለ ጸጋ ሰው ለንግድ ከሀገሩ ወጣ፡፡ በጉዞውም ላይ ሳለ ፀሐይ ስትገባ ከዚያ የበግ ጠባቂው ዘንድ ደረሰ። በግ ጠባቂውንም ‹‹ወንድሜ ሆይ ባንተ ዘንድ የማድርበት ቢኖር ታሳድረኝ ዘንድ እለምንሃለው፣ ኪራዩንም እከፍልሃለው›› ብሎ ጠየቀውና ያ በግ ጠባቂ ወደ ቤቱ አስገባው። ባለጸጋውም ገብቶ ጥቂት ካረፈ በኋላ በግ ጠባቂው ያን ብላቴና ባሕራን ብሎ ሲጠራው በሰማ ጊዜ ‹‹ልጅህ ነውን?›› ብሎ ጠየቀው። በግ ጠባቂውም ‹‹አዎን ይህ አሁን ጐልማሳ ሆኖ የምታየው ወጣት ገና ሕፃን ሆኖ ሳለ በሣጥን ተከቶ ከባሕር ውስጥ ተጥሎ አግኝቼው ወስጄ አሳድጌዋለሁና ልጄ ነው›› አለው። ባለጸጋውም በባሕር ውስጥ የጣለው ሕፃን መሆኑንም ስላወቀ ይህንን ነገር በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደነገጠ፤ ይገድለውም ዘንድ ፈለገ፡፡ በበነጋውም መንገዱን ለመሄድ ሲዘጋጅ ልዩ ልዩ ምክንያት (ሰይጣናዊ ሐሳብ) በመፍጠር በግ ጠባቂውን ‹‹ወንድሜ ሆይ አንድ የማስቸግርህ ጉዳይ አለኝ ይኸውም በቤቴ የረሳሁት ነገር ስላለ ሄዶ መልእክት ያደርስልኝ ዘንድ ይህን ብላቴና እንድትሰጠኝ ነው የድካሙንም ዋጋ ሃያ ወቄት ወርቅ እከፍላለሁ›› አለው።

ያም በግ ጠባቂ ስለ ወርቁ ስጦታ ደስ በመሰኘት ያን ጐልማሳ ጠርቶ ‹‹ልጄ ባሕራን ሆይ ይህ ክቡር ሰው ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤቱ ሊልክህ ይፈልጋልና መልእክቱን አድርስለት እግዚአብሔር በሰላም ያግባህ›› ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም ‹‹እሺ መልካም ነው አባቴ ሆይ ያዘዝከኝን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁ ነኝ›› አለው። ከዚህም በኋላ ያ ባለጸጋ ‹‹ይህችን የመልእክት ደብዳቤ ይዞ ወደ አንተ የመጣውን ስሙ ባሕራን የተባለውን መልእክቷ በደረሰችህ ጊዜ ፈጥነህ ግደለው፤ ገድለህም ሬሣውን ከጉድጓድ ጣለው እኔ በሰላም ተመልሼ እስክመጣ ድረስ ማንም ማን ይህን ምሥጢር አይወቅ›› የሚል ጽሑፍ ለሹሙ ጽፎ አዘጋጀ፤ በአገልጋዩ (በሹሙ)ና በእርሱ መካከል የሚተዋወቁበትን ማኅተም በደብዳቤው ላይ አትሞ ለባሕራን ሰጠው፡፡ ለመንገዱም የሚሆነው ስንቅ ሰጥቶ ላከው።
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሰኔ 12 ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡

#፬. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ማሳረጉን፤ ወደፊት ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን እንደሚያንጽ ጌታችን የነገረውና የሕንጻዎቹን አሠራር ዝርዝር የነገረው በዚሁ እለት ነው፡፡


ባሕራንም መልእክቱን ለማድረስ ዘጠኝ ቀን ተጉዞ የአንድ ቀን ጎዳና ሲቀረው እነሆ ክቡር የሚሆን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በፈረስ ተቀምጦ ወደሱ ደረሰና ወዴት እንደሚሄድ ጠየቀው፡፡ ባሕራንም ‹‹ከአንድ ባለጸጋ ሰው የተጻፈ ደብዳቤ ይዤ እርሱን ለማድረስ ዕገሊት ወደምትባል አገር እሄዳለሁ›› አለው። ንዑድ ክቡር የሚሆን ቅዱስ ሚካኤልም "እስኪ የመልእክቱን ደብዳቤ አሳየኝ?" አለው፡፡ ባሕራንም ‹‹ጌታዬ ለማንም አታሳይ ብሎኛል›› አለው፡፡ መልአኩም ‹‹እሺ ያም ባይሆን እንደተጠቀለለ አሳየኝ›› አለው፡፡ ባሕራንም አሳየው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም በሞቱ ደብዳቤ ላይ እፍ ቢልበት የሞቱን ትእዛዝ አጥፍቶ የሕይወት ትዕዛዝ ጽፎበታል፡፡ በደብዳቤው ላይ የተጻፈውን የሞት መልእክት ደምስሶ ‹‹ከእኔ ከባለጸጋ ዕገሌ የተጻፈ›› ይልና ‹‹ይህን መልእክት ይዞ ለመጣሰው ዕገሊት የምትባለዋን ልጄን አጋቡት (ዳሩለት) በዱር የተሰማራውን ከብቴን ፥ በቤት ያለውን ሀብቴን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረቴን በሙሉ አውርሼዋለሁና እኔ እስክመጣ ድረስ አትጠብቁ በሄድኩበት ሀገር የምቆይበት ጉዳይ አለኝና፤ በቤቴና በንብረቴ ላይ ሙሉ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና የወደደውን ያደርግ ዘንድ አትከልክሉት ስለዚህም በእኔና በአንተ መካከል የምንተዋወቅበትን ምልክት አድርጌበታለሁ›› የሚል ጽሑፍ ጻፈበት "እንግዲህ ወደ ባለጸጋው ቤት ሂድና ይህን መልእክት አድርስ አለው፤ ባሕራንም ‹‹እሺ ጌታዬ እንዳዘዝከኝ አደርጋለሁ›› ብሎ ጉዞውን ቀጠለና የዚያን የባለፀጋ ቤት እየጠየቀ ከደረሰበት በኋላ ደብዳቤውን ለሹሙ ሰጠው።
ያም ሹም ደብዳቤውን ተቀብሎ ሲያነብ የታተመበት ማኅተም ዕውነተኛ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በቤተ ክርስቲያን ደንብ የባለጸጋውን ልጅ አጋባው፣ የሠርጉንም በዓል እስከ ፵ ቀን ድረስ በታላቅ ደስታ አከበሩ። ከሠርጉም በዓል ፍጻሜ በኋላ ያ ባለጸጋ ሰው ከሄደበት አገር ወደ ሀገሩ ተመልሶ ገባና በቤቱ አካባቢ ሲደርስ የደስታና የዘፈን ድምፅ ስለሰማ "ይህ የምሰማው ድምፅ ምንድነው?" ሲል ጠየቀ፡፡
ሰዎቹም ‹‹ባሕራን የተባለ ጐበዝ ካንተ ዘንድ ልጄን ዳሩለት የሚል ትእዛዝ አምጥቶ ልጅህን አግብቶ በሠርጉ ምክንያት ይዘፍናሉ ይደሰታ፤ እነሆ እየበሉና እየጠጡ በቀንና በሌሊት እየዘፈኑ ሲደሰቱ ፵ ቀን ሆኗቸዋል በመልእክትህም እንዳዘዝከው ገንዘብህን የወንድና የሴት ባሮችህን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረትህን ሁሉ በሙሉ አስረክበውታል›› አሉት። ያም ባለጸጋ ያህን ቃል በሰማ ጊዜ ከድንጋጤው የተነሳ በታላቅ ቃል በመጮኽ ከመሬት ላይ ተከስክሶ ሞተና ነፍሱን አጋንንት ተረክበው ወደ ሲኦል አወረዷት። ከዚህም በኋላ ባሕራን የተባለ ያ ጐልማሳ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በየወሩ እያከበረ ዝክሩን እየዘከረ ይኖር ጀመር። በዚያን ጊዜ በጉዞ ላይ ሳለ ተገልጾለት የሞቱን መልእክት ወደ ሕይወት የለወጠለት ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነም አወቀ ተረዳ። ንዑድ ክቡር የሚሆን የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ሊቈጥሩት የማይቻል ብዙ ስለሆነ በኛም ላይ ኃይለ ረድኤቱ አድሮብን ይኑር እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን፡፡

#፭. አፎምያን ያዳነበት
ቅድስት አፎምያ ሀገሯ ኪልቅያ ነው፡፡ ባለቤቷ አስተራኒቆስ መስፍነ ኪልቅያ ነበረ፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ ነበር፡፡
ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጕል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እርሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡ ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፤ ከሀብቷ ከንብረቷ እየሰጠች እየመጸወተች በጾም ፥ በጸሎት ተወስና ትኖር ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ደግ መነኵሴ መስሎ አጋንንትን መነኰሳይያት አስመስሎ መጥቶ ከደጅ ሆኖ አስጠራት፡፡

እርሷም ‹‹ከቤት ገብታችሁ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ፊት ጸልዩልኝ›› አለቻቸው፡፡ ሰይጣናቱም ‹‹እኛማ በነግህ ጸልየናል?›› አሏት፡፡ ቀጥሎም ሰይጣን ‹‹...እንደው አንቺ ግን ይህ ሁሉ ጾም ጸሎት ምን ያደርገልሻል? ሀብትሽን ሰጥተሸ መጨረስሽስ ስለምንድን ነው? በዚያ ላይ አንቺ ስትደክሚ የሚደግፍሽ ፥ ስታረጂ የሚጦርሽ ልጅ የለሽም ሁለተኛ ማግባት ኃጢአት መስሎሻልን? እነ አብርሃም እነ ዳዊት ከብዙ ሴቶች ብዙ ልጆች ወልደው የለምን? አሁንም ቤት ሰሪ፥ ጎመን ዘሪ ልጅ ያስፈልግሻልና ባል አግቢ፣ እሺ በይኝ›› አላት፡፡ ቅድስት አፎምያም ‹‹አባ ቆብህ መልካም ነበር ንግግርህ ግን ክፉ ነው፣ አትጹሚ፥ አትጸልዩ ያልከኝ፤ ጌታ ምጽዋትን መጽውቱ ብሎ የለምን? ሁለተኛ ባል አግቢ ማለትንስ ከምን አገኘኸው? ርግቦች እንኳን ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ከሌላ ወንድ አይቀርቡም፤ ታዲያ ጥንት በንጽሕና ሊኖር የተፈጠረ ሰው ሁለተኛ አላገባም ቢል ዕዳ ፍዳ ሊሆንበት ነውን?›› ብላ ሞገተችው፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ አይቷታልና ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡

ከላይ እንዳየነው በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ ሌላ ባል አግብታ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡ ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ እነርሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡  ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እርሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡

በሰኔ 12 ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?›› በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ
ጠየቀችው፡፡ ለጊዜው ‹‹በእኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም›› ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ። ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእርሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡  በመቀጠልም ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ሰይጣናዊ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን "ድረስልኝ" እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
ሕንፀተ ቤታ ለማርያም (ሰኔ ፳፩)
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ዓመታዊ በዓል አደረሰን አደረሳችሁ !!!
2025/06/29 18:12:42
Back to Top
HTML Embed Code: