Telegram Web Link
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋር በትምህርተ ሃይማኖት ኅብረት ካላቸው የአኃት አብያተ ክርስቲያን መካከል የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አንዷ ስትሆን ቀደም ሲል ሁለቱ አብያተ ክርስቲያን የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በመቀራረብ ሲያከናውኗቸው የነበሩት ተግባራትና ስብሰባዎች በመላው ዓለም ተከስቶ በነበረው የኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በተላለፉ ዓለም አቀፍ ክልከላዎች ተቋርጠው በመቆየታቸው የሁለትዮሽ ስብሰባዎቹን ለማስቀጠል እና በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ይቻል ዘንድ ከብፁዕ ወቅዱስ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ 3ኛ የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የተላኩት፤ ሜትሮፖሊታን ማር ዩሊዮስ እና ፋዘር ዶ/ር ጆሲ ያዕቆብን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

የልዑኩ መሪ  ሜትሮፖሊታን ማር ዩሊዮስ ከሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ፓትርያርክ የተላከውን መልእክትና ገጸ በረከት ለቅዱስነታቸው አቅርበው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሰላም፣ የሰው ልጆች ነጻነት፣ ፍትሕ በዓለም እንዲሰፍን በየጊዜው የሚያከናውኑትን አባታዊ ጥረት አድንቀው በዚህም የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተባባሪ መሆኗን ገልጸዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስነታቸውም በልዑካኑ ጉብኝት መደሰታቸውን፤ እንዲሁም የአብያተ ክርስቲያናት አንድነት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እንዲጠናከር የሚያስፈልግበት ጊዜ መሆኑን ገልጸው በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

በመጨረሻም ልዑካኑ በቅዱስነታቸው ለተደረገላቸው መንፈሳዊ አቀባበል አመስግነው፤ በቀጣይም የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ቅዱሳን ፓትርያርኮች በሀገራቱ ስለሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉዞ ያላቸውን ተስፋ ገልጸው፤ በቅዱስነታቸው ቃለ በረከትና ጸሎት የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የባሕር ዳር እና ሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሚመለከታቸው የመንበረ ፓትርያርክ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ፦የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ  የግብጽ ኦርቶዶክስ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጸ፡፡

ጥር ፳፬/፳፻፲፯ ዓ.ም

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበ ተክለ ሃይማኖት የግብጽ ኮፕቲክ ቤተርክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ታውድሮስ ሁለተኛ መልእክት ይዘው የመጡትን ሜትሮፖሊታን አምባ ቢመን የነጋዳን፣ ጉስ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሚካኤል ገዳም ሓላፊን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ጥር ፳፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም አነጋግረዋል፡፡

ሜትሮፖሊታን አምባ ቢመን ኮፕቲክ ቤተርክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ታውድሮስ ሁለተኛ ያመጡትን መልእክት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ያቀረቡ ሲሆን በዚህም  ቅዱስነታቸው የግብጽ ኮፕቲክ ልዑካንን ተቀብለው በማነጋገራቸው መደሰታቸውን ገልጸው፤ ይህም የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናትን  አንድነት የሚያሳይ ነው ብለዋል ፡፡

በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለው ግንኙነት የጥንት መሆኑን ያስረዱት ሜትሮፖሊታን አምባ ቢመን “በግብጽ በርካታ ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ፤ በዚያም ቤተክርስቲያን አላቸው ይጸልያሉ፡፡ የግብጽ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ለአማኞቿ አገልግሎት የምትሰጥበትን የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል  በጥሩ ሁኔታ ዕድሳት ተደርጎለት ተመርቆ ለአገልግሎት የሚጀምሩበትን ደብዳቤ ከቅዱስነታቸው መቀበላቸውን” አስረድተዋል፡፡

የሁለቱም አብያተ ክርስቲያንናት ግንኙነትም በጣም ጥሩ ነው ያሉት አቡነ ኤንገሎስ ኤልነጋዲ በኢትዮጵያ የግብጽ ቤተክርስቲያን ተወካይ እንደተናገሩት፤ በዚያም ቤተክርስቲያን አላቸው ይጸልያሉ፡፡ በኢትዮጵያም የግብጽ ቤተክርስቲያን አገልግሎቷን በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳምና በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ታካሂዳለች፡፡
በጾመ ፍልሰታ ስብሐተ ነግህ የሚባሉ የምእራፍ ዜማዎች
በመሪ ዘምስለ ተመሪ ከነንባቡ ጋር እነሆ ብለናል
ምዕራፍ መጽሐፍ ስብሐተ ነግህ ዘዘወትር ገፅ 216-219
በበዓለ ማርያም ዓቢይ ስብሐተ ነግህ ዘይእዜ በል
1)ተዓብዮ ነፍስየ
2)ይትባረክ እግዚአብሔር ግዕዝ
3) ይትባረክ እግዚአብሔር ዓራራይ
ማኅበረ ቅዱሳን በወላይታ ማእከል  የበገና ሠልጣኞችን አስመረቀ።

ጥር ፳፮/፳፻፲፯ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን በወላይታ ማእከል ፋይናንስና ልማት ተቋም ለ፱ኛ ዙር ያሠለጠናቸውን 34 የበገና ሠልጣኞች በወላይታ ሶዶ ኦቶና ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ጥር ፳፭/፳፻፲፯ ዓ.ም አስመርቋል።

በምርቃት መርሐ ግብሩ የደብሩ ዋና አስተዳዳር መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ ወልደ አማኑኤል ጃተና፣ አባቶች፣ የሠልጣኝ ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በልዩ ልዩ ቅኝቶች የተሰናዱ የበገና መዝሙራት በተመራቂዎችና ሌሎች መንፈሳዊ ዝግጅቶች ቀርበዋል።

በመጨረሻም ለሠልጣኞች በማኅበረ ቅዱሳን የተዘጋጀ የምስክር ወረቀትም ተሰጥቷል።
2025/07/14 02:57:25
Back to Top
HTML Embed Code: