Telegram Web Link
የዳግማዊ፡ ምኒልክ፡ መታሰቢያ፡ የመምህራን፡ እና፡ ቀሳውስት፡ ማሠልጠኛ፡ መንፈሳዊ፡ ት/ቤት
+++++++++++
ይኽ፡ አብነት፡ ትምህርት፡ ቤት፡ በዐዲስ፡ አበባ፡ 4 ኪሎ፡ ቤተ፡ መንግሥት፡ አጠገብ፡ ታዕካ፡ ነገሥት በአታ፡ ለማርያም፡ ገዳም፡ ውስጥ፡ የሚገኝ፡ አንድ፡ ምዕተ፡ ዓመት፡ ያስቆጠረ፡ አንጋፋ፡ ት/ቤት፡ ነው።
+++
"መታሰቢያ፡ ቤት"
+++++++++++++++++++
'መታሰቢያ፡ ቤት' እየተባለ፡ የሚጠራው፡ በሙሉ፡ ስሙ፡ የዳግማዊ፡ ምኒልክ፡ መታሰቢያ፡ የመምህራን፡ እና፡ ቀሳውስት፡ ማሠልጠኛ፡ መንፈሳዊ፡ ት/ቤት፡ በሊቀ፡ ሊቃውንት፡ አባ፡ ገብረ፡ አብ፡ መንግሥቱ (ኋላ፡ ብፁዕ፡ አቡነ፡ ፊሊጶስ)፡ በተባሉት፡ ታላቅ፡ የገዳሙ፡ አባት፡ አርቆ፡ አሳቢነት፡ እና፡ አሳሳቢነት፤ በግርማዊት፡ ንግሥተ፡ ነገሥታት፡ ዘውዲቱ፡ መልካም፡ ፈቃድ፤ ኋላም፡ ንግሥቲቱ፡ ሲያርፉ፡ በግርማዊ፡ ቀዳማዊ፡ ኀይለ፡ ሥላሴ፡ መመሪያ፡ ሰጪነት፤ በሊቀ፡ ሊቃውንት፡ አባ፡ ገብረ፡ አብ፡ አስተባባሪነት፡ ከ92 ዓመታት፡ በፊት፡ በ1925 ዓ.ም. ግንባታው፡ ተጠናቆ፡ አገልግሎት፡ መስጠት፡ ዠመረ።
+++
#የዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም የመምህራን እና ቀሳውስት ማሠልጠኛ አብነት ት/ቤት ሕንጻ የነበረው የፊትለፊት ክፍሎች በመንግሥት የኮሪደር ልማት ምክንያት ፈርሰዋል።

የት/ቤቱ የመማር ማስተማር ኺደትም እንደተቋረጠ እና በአብነት ት/ቤቱ ይኖሩ የነበሩ አባቶች መምህራን እና አዳሪ ደቀ መዛሙርት (ተማሪዎች) በጊዜያዊነት በት/ቤቱ አዳራሽ ተጠልለው እንደሚገኙ ተገልጿል። ቀጣይ መጠለያም ለማዘጋጀት በገዳሙ በኩል ጥረት እየተደረገ መኾኑን ማወቅ ችለናል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከገዳሙ አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር ዝርዝር መረጃዎችን በማጠናቀር በቅርብ ክትትል እያደረግን መኾኑን እያሳወቅን እስካኹን በደረሰን መረጃ በገዳሙ በኩል ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር ውይይቶች እየተካኼዱ እንደኾነ እና ክትትል እየተደረገ መኾኑን ተገልጾልናል። በዚኽም መሠረት እስካኹን በመንግሥት በኩል በኮሪደር ልማት ምክንያት ለተቀነሰው የገዳሟ ት/ቤት ይዞታ ምትክ የአብነት ት/ቤቱ አኹን ያለበት ግቢ ጀርባ የሚገኘውን ቦታ በካርታ በማካተት ለገዳሟ ሊያስረክብ እንደኾነ እና የፈረሰው የአብነት ት/ቤቱ ክፍል በዘመናዊ መልኩ ተጠናክሮ እንዲሠራ የሚጠበቅበትን ትብብር እንደሚያደርግ ተገልጿል። ከዚኽ በተጨማሪም ከዚኽ በፊት በፈረሰው የገዳሟ የዕጓለ ማውታ እና አረጋውያን መርጃ ማዕከል (ጡረታ ቤት) ቦታ ምትክ ካርታ አብሮ እንደሚያስረክብም በመንግሥት በኩል ቃል መገባቱን እና ሥራዎችም መዠመራቸውንም ገልጸውልናል።
+++
👉በቀጣይ በጉዳዩ ዙሪያ የሚኖሩ ዐዳዲስ መረጃዎችን ተከታትለን የምናደርስ መኾኑን እንገልጻለን።
በደብረ ዘመዳ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም ለሚገኙ 80 የአብነት ተማሪዎች ድጋፍ ተደረገ።

ታኅሣሥ ፳፮/ ፳፻፲፯ ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን

በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በራያ ቆቦ ወረዳ ስር ለምትገኘው ለደብረ ዘመዳ ቅድስት ማርያም አንድነት ገዳም ለሚገኙ 80 የቅዳሴ ጉባኤ ቤት ተማሪዎች የምግብ ቁሳቁስ በትናንትናው ዕለት ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል።

በማኅበረ ቅዱሳን የወልድያ ማእከል የጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ መለሰ አያሌው እንደገለጹት  ማእከሉ ከኢትዮጵያ ውጭ ከሚገኙ በጎ ፍቃደኛ ምእመናን የሰበሰበውን  ድጋፍ ማድረጉን  የገለጹ ሲሆን አሁን ካለው የኑሮ ውድነት እና የሰላም እጦት አንጻር ጉባኤ ቤቶች አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመሆናቸው በተጠናከረ ሁኔታ ተጨማሪ ድጋፎች ሊደረጉ ይገባል ብለዋል።

በተመሳሳይም መሰል ድጋፍ በጋዞ ወረዳ ቤተ ክህነት ስር ለሚገኘው የዋሮ ቅዱስ ሚካኤል ለ30 የዜማ ጉባኤ ቤት የአብነት ተማሪዎችም ተበርክቷል በዚህም በአጠቃላይ ለሁለቱም ጉባኤ ቤቶች 170‚000 (ከአንድ መቶ ሰባ ሺ ብር በላይ ወጭ መደረጉን ተገልጿል፡፡
‹‹ወልድ ተሰጠን›› (ኢሳ.፱፥፮)

እንኳን አደረሳችሁ!


ነቢየ እግዚአብሔር ልዑለ ኢሳይያስ የታነገረው ይህ ቃል ለጊዜው በምርኮ በጭንቅ ለነበሩ፣ በሰናክሬም ዛቻ፣ በብልጣሦር የግፍ አገዛዝ አስጨንቋቸው ምድራዊ ሕይወታች በመከራ አዘቅት ሰጥሞ ለነበሩት ለእስራኤላውያን ቢሆንም የመከራው ጊዜ አልፎ ከስደት እንደሚመለሱ፣ በተድላ ደስታ የሚኖሩበት መልካም ጊዜ እንደሚመጣ ሲሆንም ፍጻሜው ግን በጽመት አዘቅት ሰጥመው፣ በመከራ ፍኖት ተጉዘው ኑረውም፣ ሞተውም የዲያቢሎስ ምሮኮኞች የሲኦል ግዞተኞች ለነበሩ ለአዳምና ለልጆቹ የጽድቅ ፀሐይ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ተወልዶ፣ በሞቱ ሞትን አጥፍቶ ከዲያሎስ አገዛዝ ከጨለማ ሕይወት እንደሚያወጣቸው የተነበየው ነው:: (ኢሳ.፱፥፮ አንድምታ)

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ልዑለ ቃል ነቢየ ኢሳይያስ ‹‹ወልድ ተውህበ ለነ፤ ወልድ ተሰጠን›› በማለት እንደተናገረው ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ወልድ ሲወለድልን የጨለማው የሰው ልጆች ሕይወት በራ፤ ቤተ ልሔም አቅራቢያ መንጎቻቸውን ሲጠብቁ ለነበሩ እረኞች እስካሉበት ቦታ ድረስ ባሕረ የብርሃን ወንዝ (የብርሃን ጎርፍ) ፈሰሰላቸው፤ በአዳምና ሔዋን በደል ምክንያት በሰዎችና በቅዱሳን መላእክት መካከል የነበረው የጠብ ግድግዳ ፈርሶ፣ ሰላም ተመልሶ ፍቅር ነግሦ በአንድ ላይ ሆነው ምሥጋና የባሕርይው ገንዘቡ ለሆነ ፈጣያቸው በተፈጠሩበት ዓላማ መሠረት አዲስ ምሥጋንን አቀረቡ፡፡ ‹‹መላእክት ከኖሎት ኖሎት ከመላእክት ጋር አንድ ሆነው አመስግነዋል፡፡›› (ሉቃ ፪፥፲፬ አንድምታ)
ብርሃናውያን መላእክት በጨለማ ላለው አዳምና ልጆቹ ከጨለማ የሚያወጣቸው ወልድ በተሰጣቸው (በተወለደላቸው) ጊዜ ተደስተው ‹‹..ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ፡፡›› (ሉቃ.፪፥፲፫)

ውድ አንባብያን! ይህን የተቀደሰ ዕለት በደስታ፣ በፍቅርና በሰላም እናከብር ዘንድ ከጥልና ከጥላቻ ርቀን፣ በንስሐ ነጽተን፣ ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀን፣ በወንድማማችነት ፍቀር ተሰባስበን ይሁን!

መልካም በዓል!
2025/07/14 02:58:21
Back to Top
HTML Embed Code: