ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የግብጽ ኦርቶዶክስ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ልዑካንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገለጸ፡፡
ጥር ፳፬/፳፻፲፯ ዓ.ም
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበ ተክለ ሃይማኖት የግብጽ ኮፕቲክ ቤተርክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ታውድሮስ ሁለተኛ መልእክት ይዘው የመጡትን ሜትሮፖሊታን አምባ ቢመን የነጋዳን፣ ጉስ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሚካኤል ገዳም ሓላፊን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ጥር ፳፬ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም አነጋግረዋል፡፡
ሜትሮፖሊታን አምባ ቢመን ኮፕቲክ ቤተርክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ታውድሮስ ሁለተኛ ያመጡትን መልእክት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ያቀረቡ ሲሆን በዚህም ቅዱስነታቸው የግብጽ ኮፕቲክ ልዑካንን ተቀብለው በማነጋገራቸው መደሰታቸውን ገልጸው፤ ይህም የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናትን አንድነት የሚያሳይ ነው ብለዋል ፡፡
በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለው ግንኙነት የጥንት መሆኑን ያስረዱት ሜትሮፖሊታን አምባ ቢመን “በግብጽ በርካታ ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ፤ በዚያም ቤተክርስቲያን አላቸው ይጸልያሉ፡፡ የግብጽ ቤተክርስቲያን በኢትዮጵያ ለአማኞቿ አገልግሎት የምትሰጥበትን የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በጥሩ ሁኔታ ዕድሳት ተደርጎለት ተመርቆ ለአገልግሎት የሚጀምሩበትን ደብዳቤ ከቅዱስነታቸው መቀበላቸውን” አስረድተዋል፡፡
የሁለቱም አብያተ ክርስቲያንናት ግንኙነትም በጣም ጥሩ ነው ያሉት አቡነ ኤንገሎስ ኤልነጋዲ በኢትዮጵያ የግብጽ ቤተክርስቲያን ተወካይ እንደተናገሩት፤ በዚያም ቤተክርስቲያን አላቸው ይጸልያሉ፡፡ በኢትዮጵያም የግብጽ ቤተክርስቲያን አገልግሎቷን በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳምና በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ታካሂዳለች፡፡

በጾመ ፍልሰታ ስብሐተ ነግህ የሚባሉ የምእራፍ ዜማዎች
በመሪ ዘምስለ ተመሪ ከነንባቡ ጋር እነሆ ብለናል
ምዕራፍ መጽሐፍ ስብሐተ ነግህ ዘዘወትር ገፅ 216-219
በበዓለ ማርያም ዓቢይ ስብሐተ ነግህ ዘይእዜ በል
1)ተዓብዮ ነፍስየ
2)ይትባረክ እግዚአብሔር ግዕዝ
3) ይትባረክ እግዚአብሔር ዓራራይ
በመሪ ዘምስለ ተመሪ ከነንባቡ ጋር እነሆ ብለናል
ምዕራፍ መጽሐፍ ስብሐተ ነግህ ዘዘወትር ገፅ 216-219
በበዓለ ማርያም ዓቢይ ስብሐተ ነግህ ዘይእዜ በል
1)ተዓብዮ ነፍስየ
2)ይትባረክ እግዚአብሔር ግዕዝ
3) ይትባረክ እግዚአብሔር ዓራራይ
ማኅበረ ቅዱሳን በወላይታ ማእከል የበገና ሠልጣኞችን አስመረቀ።
ጥር ፳፮/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን በወላይታ ማእከል ፋይናንስና ልማት ተቋም ለ፱ኛ ዙር ያሠለጠናቸውን 34 የበገና ሠልጣኞች በወላይታ ሶዶ ኦቶና ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ጥር ፳፭/፳፻፲፯ ዓ.ም አስመርቋል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ የደብሩ ዋና አስተዳዳር መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ ወልደ አማኑኤል ጃተና፣ አባቶች፣ የሠልጣኝ ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በልዩ ልዩ ቅኝቶች የተሰናዱ የበገና መዝሙራት በተመራቂዎችና ሌሎች መንፈሳዊ ዝግጅቶች ቀርበዋል።
በመጨረሻም ለሠልጣኞች በማኅበረ ቅዱሳን የተዘጋጀ የምስክር ወረቀትም ተሰጥቷል።