ጥቂት ኦርቶዶክሳዊያን ባሉበት አከባቢዎች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማስቀጠል በሀገራችን የሚስተዋለው የሰላም እጦት እንቅፋት እንደሆነበት ማኅበረ ቅዱሳን የዜማና የኪነ ጥበባት ማእከል አስታወቀ።
ጥር ፳፯/፳፻፲፯ ዓ.ም
ማኅበረ ቅዱሳን የዜማና የኪነ ጥበባት ማእከል አገልጋይ ዲያቆን ዮናስ ተስፋዬ እንደገለጹት ጥቂት ኦርቶዶክሳዊያን ባሉበት አከባቢዎች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማስቀጠል በሀገራችን የሚስተዋለው የሰላም እጦት እንቅፋት እንደሆነባቸው ገልጸዋል።
ማኅበሩ ለበርካታ ዓመታት ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማከናወኑ የሚታወቅ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የመዝሙር ክፍል ሐዋርያዊ ጉዞዎችን በተለያዩ አከባቢዎች በተለይ ጥቂት ኦርቶዶክሳዊያን በሚገኙበት ሥፍራዎች በመንቀሳቀስ በበርካታ ቋንቋዎች አገልግሎቶችን በማከናወን ተደራሽ ማድረግ ችሏል።
በዚህም አገልግሎት “ወደ 54 ቋንቋዎችን በመዝሙር ተርጉመው እየሰሩ እንደሚኙ የገለጹት ዲ/ን ዮናስ አክለውም ምዕመናን በሚሰሙት ቋንቋ ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ” በሚል ዕቅድ ይዘው እየሠሩ የነበረ እንደሆነና አሁን ላይ የሀገሪቱ የሰላም እጦት አገልግሎቱን ተደራሽ እንዳያደርጉ እንቅፋት የሆነባቸውን ለመቅረፍ ማኅበሩ የተለያየ አማራጮችን እየተጠቀመ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፍቃድ ተሰጥቷችው መንፈሳዊ ሥራዎችን እያከናወኑ የሚገኙ ማኅበራትም ወደ ገጠራማና ጠረፋማ አከባቢዎች በመሄድ እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ምእመናንን የማስተማርና የማገልገል ሥራዎችን መስራት ቢችሉ በማለት ዲ/ን ዮናስ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በጾመ ፍልሰታ ዓቢይ ስብሐተ ነግህ የሚባሉ የምእራፍ ዜማዎች
በመሪ ዘምስለ ተመሪ ከነንባቡ ጋር እነሆ ብለናል
ምዕራፍ መጽሐፍ ዓቢይ ስብሐተ ነግህ ዘዘወትር ገፅ 234-236
1)ነአምን በአሀዱ አምላክ ዓራራይ
2)አቡነ ዘበሰማያት ዓራራይ
በመሪ ዘምስለ ተመሪ ከነንባቡ ጋር እነሆ ብለናል
ምዕራፍ መጽሐፍ ዓቢይ ስብሐተ ነግህ ዘዘወትር ገፅ 234-236
1)ነአምን በአሀዱ አምላክ ዓራራይ
2)አቡነ ዘበሰማያት ዓራራይ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
@zemariian
#የቤተክርስቲያን_ይትበሀል
፩) ዘመነ ክረምት
፪) መፀው
፫) ሐጋይ
፫. ሐጋይ
ሐጋይ፦ ማለት ደረቅ ፀሐይ ማለት። እርሱም ከታኅሣሥ ፳፮ እስከ መጋቢት ፳፭ ድረስ ያለው ጊዜነው። ስለዚህ የቤተክርስቲያን ሥርዓት የሚባለው '' ወለእመ ፈቀድከ ታእምር ክፍለ ዘመኑ ለሐጋይ፣ ትወጥን አመ ፳ወ፮ ለታኅሣሥ ወትፌጽም አመ፳ ወሐሙሱ ለመጋቢት ወኁልቈ እሉ ዕለታት ተሰዓ ውእቱ ወእምዝ ኢየሐፅፅወበውስቴቶሙ ሀለዉ ንዑሳን አዝማን ፬ቱ ዘውእቶሙ ዘመነ ልደት ፤ ዘመነ ናዝሬት ፤ ዘመነ ጥምቀት ወአስተርእየ፤ ወዘመነ ጾም ዘመነ ልደት ትዌጥን አመ ፳ወተሱዑ ለታኅሣሥ ወትፌጽም እስከ አሐቲ ሰንበት።''
ዘመነ ናዝሬት ትዌጥን ድኅረ አሐቲ ሰንበት። ወበሳኒታ ሰኑይ ትዌጥን ወትፌጽም አመ ፲ ለጥር ዘውእቱ ጥምቀት ገሃድ ለእመ ኮነ ልደት በሰኑይ ፭ተ ዕለተ
በሠሉስ ለእመ ኮነ ፮ተ ዕለተ
በረቡዕ ለእመ ኮነ ፯ተ ዕለተ
በሐሙስ ለእመ ኮነ ፰ተዕለተ
በዓርብ ለእመ ኮነ ፱ተ ዕለተ
በቀዳዊት ለእመ ኮነ ፱ተ ዕለተ
በእሑድ ለእመ ኮነ ፲ተ ወ፩ደ ትረክብ ናዝሬት። ለቡ ዘንተ በተጠናቅቆ ዘመነ ጥምቀት ወአስተርእዮ ትዌጥን አመ ፲ወ፩ ለጥር ወትፌጽም አመ ፴ሁ ለጥር ወኁልቈ እሉ ዕለታት ፳ ውእቱ ዘይከውን በርዕደቱ ለጾም ለእመ የዓርግ ጾም ኃበ ላዕላይ ቀመር ዘመነ አስተርእዮ ይበጽሕ እስከ ሠሉሱ ለመጋቢት፤ ወኁልቈ ዕለታት ፶ወ፫ ውእቱ እምዝ ኢየሐፅፅ ወኢይትዌሰክ።
@zemariian
®ዲ.ን ሱራፊ

ጾመ ነነዌ፤ ከየካቲት 3-5 (ከሰኞ-ረቡዕ)
#ነነዌ
በጤግሮስ ወንዝ ምሥራቃዊ ቆሬ፥ ከዛሬዋ የሞሱል ከተማ በተቃራኒ ከባግዳድ በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 350 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የነበረች ታላቅ ከተማ ነች፡፡
ነነዌን በመጀመሪያ የቆረቆራት ናምሩድ ነው፡፡ /ዘፍ. 10፥11/
በጣም ሰፊ ነበረች “የቅጥሯም ዙሪያ በእግር የሦስት ቀን መንገድ ያህል ነበረ” /ዮና. 3፥3/
እግዚአብሔር አምላካችን ነነዌን “ታላቂቱ ከተማ” በሚል ቅጽል ጠርቷል፤ /ዮናስ 3፥2፤ 4፥11/
ስለ መጥፋቷ ነቢዩ ሶፎንያስ “...ነነዌንም ባድማ እንደ በረሃም ደረቅ ያደርጋታል” በማለት ትንቢት ተናግሮባታል፡፡ /ትን. ሶፎ 2፥13/፡፡ እንደ ነቢያቱ ትንቢት ታላቋ ነነዌ ከ300 ዓመታት በኋላ ጠፍታለች፡፡
የነነዌ ሰዎች በስብከተ ዮናስ አምነው፥ ንስሐ ገብተው ድነዋል፤ በዚህም ጌታችን በወንጌል ላይ ስለ ንስሓቸውና ስለ እምነታቸው /‹‹...የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፡፡›› በማለት አመስግኗቸዋል፡፡ ማቴ 12፥41/
#ዮናስ_ነቢየ_አሕዛብ_ወሕዝብ
ዮናስ ማለት ርግብ፥ የዋኅ ማለት ነው፡፡
በዳግማዊ ኢዮርብአም ዘመነ መንግሥት /825-784 ቅ.ል.ክ./ በሰማርያ የነበረ ነው፡፡ /2ነገሥ. 14፥25/፡፡
ቊጥሩ ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው፡፡
ነገዱ ከነገደ ይሳኮር ወገን ሲሆን፤ #አባቱ_አማቴ_እናቱም_ሶና(የሰራፕታዋ ደግ ሴት የሆነችውና ቅዱስ ኤልያስን በዚያ በረሃብ ዘመን የመገበችው ናት)፡፡
ኤልያስ በረሃቡ ዘመን ወደ ሰራፕታዋ መበለት ቤት በመሄድ "ውኃ አጠጪኝ ጥቂት ቁራሽም አምጪልኝ" አላት፡፡ ‹‹ሕያው እግዚአብሔርን እፍኝ ዱቄት አለችኝ ጋግሬያት አንተም እኔም ልጄም (ዮናስ) በልተናት እንሞታለን›› አለችው፡፡ ኤልያስም "የረሀቡ ዘመን እስኪያልፍ ይበርክት" አላት፤ ከቤቷ ብትገባ ዱቄቱ በማድጋው፣ ዘይቱ በማሰሮው መልቶ አገኘች፡፡ ከጥቂት ጊዜም በኋላ ልጇ ዮናስ ታሞ ሞተ፡፡ እናቱም ሄዳ ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስን "ሳይገባኝ ከቤቴ ገብተህ ኀጢአቴን ተመራምረህ ልጄን ትገድልብኝ?" አለችው፡፡ ነቢዩ ኤልያስም ወደ አምላኩ ሰባት ጊዜ ጸሎት አድርሶ ዮናስን ከሞተ በኋላ አስነሥቶታል፡፡
ዮናስ ትንሽ ከፍ ባለ ጊዜም ከነቢያት ጓደኞቹ አብድዩና ኤልሳዕ ጋር ሆነው የታላቁ ነቢይ የኤልያስ ደቀ መዛሙርት ሆኑ፡፡ /1ነገ.17፥1-24፤ 18፥10-24/ ነቢዩ ኤልያስ ካረገ በኋላ ደግሞ ሁሉም በተሰጣቸው አገልግሎት ተሠማርተው እግዚአቤሔርን አገለገሉ፡፡ ነቢዩ ዮናስ አርባ ዓመት ሲሞላው ሀብተ ትንቢት ተሰጥቶት ማስተማር ጀመረ፡፡
የሰማርያውን ንጉሥ ኢዮርብአምን ጠቃሚ ምክር በመለገስ የእሥራኤልን ድንበር ከሔማት እስከ ዐረብ ባሕር ድረስ እንዲይዝ አድርጎታል፡፡ /2ነገሥ. 14፥25/፡፡
ነቢዩ ዮናስ ምንም እንኳን የእስራኤል ነቢይ ቢኾንም ከምድረ እስራኤል ውጪ በነነዌ ስላስተማረ #ነቢየ አሕዛብ ወሕዝብ ይባላል፡፡ የትንቢት መጽሐፉም ዋና መልእክት እግዚአብሔር የእስራኤል ብቻ ሳይሆን የአሕዛብም አምላክ እንደሆነና በንስሐ ወደ እርሱ የተመለሱትን ሁሉ በምሕረት እንደሚጐበኝ ማሳየት ነው፡፡
#ዮናስና_ነነዌ_
የነነዌ ሰዎች ኀጢአት ከመሥፈርቱ በማለፉ፤ የእግዚአብሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ መጣ “ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የክፋታቸውም ጩኸት ወደ ፊቴ ወጥቷልና ለእነርሱ ስበክ” አለው፤ ዮናስ ግን የፈጣሪው መሐሪነት፥ ቸርነት መስፈርት እንደሌለው ያውቃልና፤ እርሱ ቢምራቸው ማን ለቃሉና ለትንቢቱ ይገዛል፤ እኔም ሐሰተኛ ነቢይ ልባል አይደለምን? ብሎ አልሔድም አለ፤ እግዚአብሔር እየደጋገመ ሲናገረው ግን ዮናስ የዋሕ ነበረና እንዲህ የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል ብሎ ከፊቱ ለመሰወር ወደ ተርሴስ በመርከብ ኮበለለ፡፡
ዮናስ ወደ መርከብ ገብቶ ጕዞ ከተጀመረ በኋላ በእርሱ ምክንያት ታላቅ ማዕበል ተነሳ፤ በመርከቡ ውስጥ የተሣፈሩትም ሊያልቁ ሆነ፤ ሌሎች እንዲያ እየተናወጡ እርሱ ግን የእምነት ሰው፥ የዋሕና ቅን ስለሆነ ተረጋግቶ በመርከቡ ውስጥ ተኝቶ ነበር፡፡ መርከበኞቹም እጅግ ሲጨንቃቸው እያንዳንዳቸው ወደ አምላካቸው ጮሁ፤ መርከቢቱም እንድትቀልላቸው በውስጧ የነበረውን ዕቃ ሁሉ እያወጡ ወደ ባሕር ጣሉ፡፡ ባሕሩ ጸጥ ሊል ስላልቻለ ዮናስንም ቀስቅሰው “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንዳገኘን እናውቅ ዘንድ፤ ኑ ዕጣ እንጣጣል ተባባሉ፡፡” /ዮናስ 1፥7/፡፡ እጣ ቢጥሉ በዮናስ ላይ ወጣ፤ ዮናስም በራሱ ተጠያቂነት፤ ‹‹የእኔ ጥፋት ስለ ሆነ ወደ ማዕበሉ ጣሉኝ›› አላቸው፡፡ መርከበኞች ግን ዮናስን ለመታደግ የሚችሉትን ሁሉ አደረጉ፡፡ መርከቢቱ ወደ ምድር ትጠጋላቸው ዘንድ አብዝተው ቀዘፉ፤ የእርሱ ወደ ባሕር መጣል ፈቃደ እግዚአብሔር ስለሆነ ልፋታቸው ሁሉ ከንቱ ሆነ፡፡ ሁሉም አንድ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡ “አቤቱ! አንተ እንደ ወደድህ አድርገሃልና ስለዚህ ሰው ነፍስ አታጥፋን፤ ንጹሕ ደምንም አታድርግብን፡፡” በማለት እያዘኑ በሐምሌ 15 ቀን ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም ከመናወጥ ጸጥ አለ፡፡
ነቢዩ ወደ ባሕር ቢጣልም የእግዚአብሔር ጥበቃ አልተለየውምና ዮናስን ይውጠው ዘንድ ታላቅ ዓሣ አንበሪን አዘዘለት፡፡ ነቢዩ ዳዊት ‹‹እግዚአብሔር የቀባውን እንዳዳነው ዛሬ ዐወቅሁ›› እንዳለ /መዝ. 19፥6/ የመረጠውን ነቢይ ለማዳን ዓሣ አንበሪን አዘጋጀለት፡፡
*ዮናስም በአሣ አንበሪ ሆድና በማዕበል ውስጥ ሆኖ ለ3 ቀናት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ በመጽሐፍ ቅዱስም በዓሣ ሆድ ተጕዞ ያስተማረ፥ ትንቢትም የተናገረ የመጀመሪያ ነቢይ ሆነ፡፡ ዓሣ አንበሪው ዮናስን በሆዱ ቋጥሮ የሦስት ቀን ጎዳና በባሕር ውስጥ ገስግሶ በ3ኛው ቀን ነነዌ ዳር ደረቅ መሬት ላይ አራግፎ ተፋው፡፡ /ዮናስ 1፥4-16፤ 2፥1-11፣ መዝ. 138፥7-10/፡፡
ዮናስ በግዙፉ አሣ አነበሪ ውስጥም ያለ እንቅልፍ በጾም፥ በጸሎትና በምስጋና ለ3 ቀናት መቆየቱ ለክርስቶስ ትንሣኤ ምሳሌ ነው፤ ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ 3 ቀን 3 ሌሊት ኑሮ፥ ሙስና (ጥፋት) ሳያገኘው መውጣቱ አዳምና ልጆቹን ለማዳን የመጣው ጌታችንም 3 መዓልትና 3 ሌሊት በከርሠ መቃብር አድሮ ከሙታን ተለይቶ የመነሣቱ ምሳሌ ነው፡፡ ለዚህም ራሱ ጌታችን በወንጌል ‹‹ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፡፡ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም፡፡ ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ 3 ቀንና 3 ሌሊት እንደ ነበረ፤ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ 3 ቀንና 3 ሌሊት ይኖራል፡፡ የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፡፡ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፡፡ እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ፡፡›› /ማቴ. 12፥39/
**እግዚአብሔር አምላክም ለሁለተኛ ጊዜ ዮናስን ወደ ነነዌ እንዲሄድ አዘዘው፤ “ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የነገርሁህንም የመጀመሪያውን ስብከት ስበክላት” አለው፡፡ ዮናስም እንቀድሞው ሳያንገራግር ወደዚህች ከተማ ገብቶ እንዲህ እያለ ‹‹እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታእ ነነዌ ዐባይ ሃገር›› (እስከ ሦስት ቀን ድረስ ነነዌ ትገለበጣለች) ንስሐን ሰበከ፥ አስተማረ፡፡

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
የነነዌ ሰዎችም ኃጢአታቸውን አምነው (ከኃጢአቱ የሌሉበትም ቢሆን መከራው ስለማይቀርላቸው) ከመሪ እስከ ተመሪ፤ እንደ አንድ ልብ መካሪ፥ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሁነው፤ ንጉሡም በከተማዋ የጾም አዋጅ አስነግሮ፥ ከዙፋኑ ወርዶ፤ ሕዝቡም ማቅ ለብሰው፥ አመድ ነስንሰው፥ በፍጹም ልባቸው አዝነው አልቅሰው፥ ሕፃናት ከጡት፥ ከብቶችም ከሣር መሠማራት ተከልክለው፥ ያለምግብ በበረት ተዘግተው፤ ጾሙንም በልባዊ ጸጸት፥ ራስን ዝቅ በማድረግና በማዋረድ ንስሓ ገቡ /“የነነዌ ሰዎችም እግዚአብሔርን አመኑ” ዮናስ 3፡5 ‹‹... ለጾም ዐዋጅ ነገሩ፤ ከታላቁም ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ማቅ ለበሱ፡፡ ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ ደረሰ፡፡ እርሱም ከዙፋኑ ተነሥቶ መጎናጸፊያውን አወለቀ፤ ማቅም ለበሰ፤ በአመድም ላይ ተቀመጠ...” ዮናስ 3፥5-9፡፡/ እንዳለ ከአምላካችን ምሕረትን አገኙ፡፡
ነቢዩ ዮናስም ይህን አይቶ በየዋሕነቱ ‹‹እንግዲህማ ሊምራቸው ነው፣ እኔም ሐሰተኛ ነቢይ ልባል ነው›› ብሎ እያዘነና ከሕይወት ሞት ይሻላል ነፍሴን ከእኔ ውሰድ እያለ ከከተማ ወጥቶ ዳስ ሠርቶ ተቀመጠ፡፡ እግዚአብሔርም በውኑ ትቆጣ ዘንድ ይገባሃልን አለው፡፡ /ዮናስ. 4፥3-11/ አምላካችን መሐሪ በመሆኑ /አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል ፍጥረታቸውን እሱ ያውቃልና መዝ. 102፥8-14፡፡ ጥበብ 3፡፡/ ብለዋል፤ አምላካችንም /እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ በሰማይ ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን አይሰጣቸው ብሏል ማቴ. 7፥12/ ቀጥሎም ነቢዩ ዮናስ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት ተኝቶ ቢነቃ ከራስጌው ቅል በቅላ ፀሐይ ስትከለክልለት አየና እጅግ ደስ አለው፡፡ ሁለተኛም ተኝቶ ቢነሣ ቅሏ ጠውልጋ፥ ደርቃ አገኘና አዘነ፡፡ እግዚአብሔርም ‹‹አንተ ላልተከልካትና ውኃ ላላጠጣሃት ቅል እንዲህ ስታዝን እኔስ በዝናም አብቅዬ፥ በፀሐይ አብስዬ ለምመግባቸው ሕዝቤ አላዝንምን?›› አለው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የዮናስን ፈቃዱን ይፈጽምለት (ሐሳዊ ነቢይ እንዳይሉት) ለምልክት እንዲሆን በሦስተኛው ቀን እሳት ከሰማይ ወርዶ ከፍ ከፍ ያሉትን ዕፅዋት ጫፍ ጫፋቸውን በልቶ ተመልሷል፡፡
ነቢዩ ቅዱስ ዮናስ በቀሪ ዘመኑ ፈጣሪውን እያገለገለ ኑሮ፤ በመልካም ሽምግልና በ170 ዓመት እድሜም መስከረም 25 አርፏል፡፡ ዮናስ በሕይወት ሥጋ ሣለ ሰማርያንና ነነዌን ብቻ ነበር ያስተማረው፤ ከሞተ በኋላ ግን ዛሬ ዓለምን የሚያስተምር ነቢይ ነው፡፡
ከጾሙ ረድኤት በረከት ይክፈለን፤
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

ዘወረደ
እንኳን አደረሳችሁ!
ዘወረደ ማለት "ከላይ የመጣ፣ የወረደ'' ማለት ነው። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን "ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእመሩ እግዚአ ኩሉ ዘየሐዩ፤ አዳምን ለማዳን ከሰማይ የወረደውን አምላክ አይሁድ ሰቀሉት፤ የሰማይ ሥልጣን ያለው የሁሉ ጌታ እንደሆነም ምንም አላወቁም" እያለች በሰንበት ዋዜማ ዜማውን መሐትው (መግቢያ) አድርጋ የሳምንቱን ዜማ በማስተጋባት የጌታችንን ከሰማይ መውረድ ታመሠጥርበታለች፤ ታመሰግንበታለች። (ጾመ ድጓ፥ ዘዘወረደ ዋዜማ)
ይህን ሳምንት በልዕልና በዘለዓለማዊ ቅድስና እና በማትመረመር ጥበብ ራሱን ሰውሮ የሚኖር አምላክ በገሃድ ለሰው ልጅ የተገለጠበትን፣ ዘለዓለማዊ አምላክ ሰውን ከተደበቀበት ለመፈለግ ብሎ ''ኦ አዳም አይቴ ሀሎከ- አዳም ሆይ ወዴት ነህ" እያለ በማያልቅ የፍቅር ድምፅ ፍለጋ ወደ ዱር (ወደ ዓለም) የገባበትን ሳምንት የምንዘክርበት ነው። አምላካችን እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ምን ያህል በበዛ ፍቅሩ እንደሚፈልገው፣ ከፍ ላለ ዓላማውም እንዳጨው ያሳየበት፣ ከሁሉም ደግሞ በሕሊና ሊታሰብ የማይችለውን የሰማይ አኗኗሩን ትቶ በሚታይ የአዳም ሥጋ የተገለጠበት፣ መጋረጃው እሳት፣ ዙፋኑ እሳት፣ ልብሱ እሳት የሆነው አምላክ በሚበሰብስ ሥጋ የተገለጠበት፣ በጨርቅ፣ ያንን የሚያስደነግጥ መለኮታዊ ክብሩን ስለ ሰው ልጅ መዳን ተጨንቆ በሕፃን አምሳል ተገልጦ በበረት የተገኘበትን ሳምንት እናስብበታለን። ቅዱስ አትናቴዎስ የእግዚአብሔር ልጅ ለሰው ልጅ ድኅነት ሲል መወለዱን እንዲህ በማለት ይገልጠዋል፡፡ "ለዚሁ ዓላማ (ለሰው ልጅ ድኅነት) የማይበሰብስ፣ የማይሞት አካል ያለው የእግዚአብሔር ልጅ ወደዚህ ዓለም ገባ" (On the Incarnation: Saint Athanasius page 6)
ዘወረደ ከዚህ ትርጉም ባለፈ የአዳም ሳምንት ተብሎ ይጠራል። አዳምን ከጠፋበት ሊፈልግ፣ ከወደቀበት ሊያነሣ፣ ከገባበት ሊያወጣ የትንቢቱ ጊዜ በደረሰ ሰዓት ከብላቴናይቱ ድንግል ተወልዶ ተስፋ አዳም ተፈጽሞበታልና። “ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤" እንዲል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ (ገላ.፬:፬)።
ሠለስቱ ምዕት በጸሎተ ሃይማኖት "ዘበእንቲአነ ለሰብእ ወበእንተ መድኃኒትነ ወረደ እምሰማያት፤ ተሰብአ ወተሰገወ እመንፈስ ቅዱስ ወእማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ስለ እኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ" (ጸሎተ ሃይማኖት) እንዲሉ በሥጋ የአዳምን ዘር ለማዳን ሰው ሆኖ ለአዳም የገባውን ኪዳን ፈጸመ። የሥጋ ዘመዳችንም ሆነ። (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ)
ሌላኛው ይህ ሳምንት ጾመ ሕርቃል በመባል ይታወቃል። ይህም በ፮፻፲፬ ዓ.ም የፋርስ ንጉሥ ኪርዮስ ኢየሩሳሌምን ወርሮ፣ አብያተ ክርስቲያናትን ዘርፎ እና መዝብሮ ክርስቲያኖችን ማርኮ ንግሥት ዕሌኒ ካሠራችው ቤተ መቅደስ የክርስቶስን መስቀል ዲያቆናትን አሸክሞ በምርኮ ወሰደ። ከምርኮ ያመለጡ ክርስቲያኖች ወደ ሮሙ ንጉሥ ከ፲፬ ዓመት በኋላ በ፮፻፳፰ ዓ.ም ለንጉሥ ሕርቃል ጩኹታቸውን ያሰማሉ፤ እርሱም በፋርሱ ንጉሥ በኪርዮስ ላይ ድል አግኝቶ መስቀሉን መለሰላቸው። በሕገ ቤተ ክርስቲያን ‹‹ሰው የገደለ ዘመኑን ሁሉ ይጹም›› የሚል በሐዋርያት ስለተደነገገ የንጉሡን ዕድሜ ተከፋፍለው አንድ ሳምንት ደርሶባቸው ስለ ንጉሡ ጾመወለታል፤ በዚህም የእርሱ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ይህ ሳምንት ጾመ ሕርቃል በመባል ይጠራል። እኛም ይህንን ዋቢ አድርገን እንጾማለን። (ምንጭ፡- ስንክሳር ዘወርኀ መጋቢት ፲)
ዘወረደ ከአርብዓው ዕለት የሚካተት ባይሆንም ቤተ ክርስቲያን ትእዛዝ አድርጋ ከአርብዓው ዕለታት ጋር ደምራ እንድንጾም ሕግ ሠርታለታች። እኛም እንደ ፈቃድ ሳይሆን እንደ ትእዛዝ ተቀብለን እንጾማለን።
ቅዳሴ፡- ቅዳሴ እግዚእ
"ዘበእንቲአነ ለሰብእ ወበእንተ መድኃኒትነ ወረደ እምሰማያት፤ ተሰብአ ወተሰገወ እመንፈስ ቅዱስ ወእማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ስለ እኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ፡፡" ወንጌል (ዮሐ.፫፥፲-፩፬)
ምስባክ ዘነግህ:- (መዝ.፪፥፲፩) "ዘበእንቲአነ ለሰብእ ወበእንተ መድኃኒትነ ወረደ እምሰማያት፤ ተሰብአ ወተሰገወ እመንፈስ ቅዱስ ወእማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ስለ እኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ"
ምስባክ ዘቅዳሴ:- (መዝ.፪፥፲፩) “ተቀነዩ ለእግዚአብሔር፤ ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ፤ አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐዕ እግዚአብሔር፤ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፤ በረዓድም ደስ ይበላችሁ፤ ጌታ እንዳይቆጣ ተግሣጹንም ተቀበሉ፡፡”
መልእክታት:-
ሠራኢ ዲያቆን ዕብ.፲፫፥፲፯
ንፍቅ ዲያቆን ያዕ. ፬፥፮- ፍጻሜው
ንፍቅ ካህን የሐዋ. ፳፭፥፲፫-ፍጻሜ
ስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን!

ቅድስት
ቤተ ክርስቲያናችን በሠራችልን የጾም ሥርዓት መሠረት ሁለተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት “ቅድስት” በመባል ይጠራል። ይህም ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጾም ከፋፍሎ በዜማ ደርሶ ባስቀመጠልን መሠረት ነው። ሳምንቱ የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ይሁን እንጂ ጌታችን በገዳመ ቆሮንቶስ ለጾመው ጾም ወይም ጾመ ዐርብዓ የመጀመርያው ሳምንት ነው። ቅድስት ስንል "የተመረጠች፣ ልዩ የሆነች፣ የከበረች" ሳምንት እያልን ነው። (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ መዝገበ ቃላት ገጽ ፯፻፹፬) ቅዱስ ያሬድም ይህችን ሳምንት ቅድስት ብሎ መጥራቱ፡-
፩. ጌታችን ጾሙን የጀመረባት የመጀመሪያዋ ሳምንት በመሆንዋ ነው። በዮርዳኖስ ወንዝ የጥምቀትን ሕግ ከሠራልን በኋላ በመብል ምክንያት የመጣውን የሕግ መተላለፍ ጾሞ የረኃብን፣ የስስትን እና የትዕቢትን ፈተናዎች ያጠፋልን ዘንድ ከሰው ርቆ በበረሃ ለዐርብዓ ቀን እና ሌሊት ጾሞ፣ ጸልዮ ከክብሩ ዝቅ ያለውን የሰው ልጅ ሊያከብረው የጾመበትን ሳምንት ለማዘከር ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ ሳምንቱን “ቅድስት” ብሎ ጠርቶታል። (ማቴ.፬፥፩-፲፩)
፪. ሰንበት ላይ በመዋሉ ነው፤ አምላካችን እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን በነቢዩ ሙሴ በኩል ከሰጣቸው ዐሥርቱ ትእዛዛት መካከል አንዷ ክብረ ሰንበትን እንዲጠብቁ ነው። "የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ" እንዲል፡፡ (ዘጸ.፳፥፰) ይህን ያልንበትም ምክንያት በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ነው። የመጀመሪያው ፈጣሬ ፍጡራን፣ አምጻኤ ዓለማት ቅዱስ እግዚአብሔር ይህችን ዓለምና በውስጧ የሚኖሩትንም ፍጥረታት ከአለመኖር ወደ መኖር በቃሉ ፈጥሮ፣ የሰውን ልጅም በእጁ ከምድር አፈር አበጃጅቶ ከጨረሰ በኋላ ከሥራው ሁሉ ያረፈባት ዕለትና ለእስራኤል ዘሥጋ እንዲጠብቋት የተሰጠች የዕረፍት ቀን በመሆንዋ ነው፡፡ (ቀዳሚት ሰንበት) (ዘፍ.፪፥፫)
ይህችውም ዕለት በአይሁድ ዘንድ እጅግ የተከበረች እና ልዩ የዕረፍት ቀን ተደርጋ ትከበራለች። በዚች ዕለት ከቆሙ ሳይቀመጡ፣ ከዘረጉ ሳያጥፉ ሥራቸውን ሁሉ በመካተቻይቱ ቀን (ዓርብ ዕለት) ፈጽመው በዚህች ቀን ያርፉ ነበር። እስራኤል ዘነፍስ ለሆንን ለሐዲስ ኪዳን ምእመናንም ይህችን ዕለት ከሥጋ ዕረፍት እናርፍባት ዘንድ ሕግ ተሠርቶልናል።
ሁለተኛዋ የዕረፍት ቀን ደግሞ የትንሣኤያችን በኩር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሞትን መውጊያ ሰብሮ፣ የመቃብርን ሆድ ባዶ አስቀርቶ፣ ሰላም አጥቶ በእሳት ዛንዥር ይሠቃይ ለነበረው ለአዳም እና ለልጆቹ የሰላም ስብከት በሰበከበት፣ በትንሣኤውም ሞትን ድል ባደረገበት፣ በሚመጣውም ዓለም በትንሣኤ ዘጉባኤ ዳግሞኛ ለፍርድ በሚመጣባት የሐዲስ ኪዳኗ ሰንበት “ሰንበተ ክርስቲያን” ላይ ይህ የጌታ ጾም ስለሚጀምር የመጀመሪያዋን ሳምንት “ቅድስት” ብሎ ጠራት። ይህች ዕለት ከዕለታት ሁሉ የከበረች፣ ከፍ ከፍም ያለች ናት። ጥንቱን ዓለም በእርሷ መፈጠር ጀምረ፤ የሰው ልጅ ትንሣኤውን በእርሷ አየ፤ ፍጻሜውም (ህልቀተ ዓለም) በእርሷ ይሆናል። በዚያችም ቀን ወደ ተዘጋጀችልን የደስታ መኖሪያችን ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር እንገባባታለን።
የዕለቱ ምስባክ፦ “እግዚአብሔርሰ ሰማያተ ገብረ አሚን ወሰናይት ቅድሜሁ ቅድሳት ወዕበየ ስብሐት ውስተ መቅደሱ፤ እግዚአብሔር ግን ሰማያትን ሠራ፤ ምስጋና እና ውበት በፊቱ ነው፤ ቅዱስነት እና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።” (መዝ.፺፭(፺፮)፥፭)
ወንጌል፦ ማቴ.፮፥፳፭
ቅዳሴ፦ ቅዳሴ ዘኤጲፋንዮስ
መልእክታት
ዲያቆን (ገባሬ ሰናይ) ፦ ፩ኛ ተሰ፣፬፥፲፫
ንፍቅ ዲያቆን፦ ፩ኛ ጴጥ.፩፥፲፫-ፍጻሜው
ንፍቅ ካህን ፦ ሐዋ.፲፥፯-፴

ምኵራብ
የቤተ ክርስቲያን እንዚራ ቅዱስ ያሬድ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ምኵራብ መግባት አይቶ በወንጌል የተጻፈውን ተርጒሞ ሳምንቱን በዜማ ያንን ቤተ መቅደስ የገባበትንና ቤተ መቅደሱ ውስጥ ይሸጡ ይነግዱ የነበሩ ወንበዴዎችን ያባረረበት ቅጽበት አንሥቶ ለጾሙ ሳምንት ምኵራብ ብሎ አርእስት ሰጥቶታል።
ምኵራብ “ቤተ አዳራሽ፣ ኮረብታ፣ ተራራ የሚያህል ታላቅ ሕንጻ፣ ሰቀላ መሰል አዳራሽ” ማለት ሲሆን ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን ወርሮ ቤተ መቅደሱን ባፈረሰበት ሰዓት እና ሕዝቡንም በምርኮ ወደ ባቢሎን በአግአዘ (በአፈለሰ) ወቅት በምርኮ ሀገር ሆነው እግዚአብሔርን የሚያመልኩበት፣ ለጸሎት እና መሥዋዕት ማሳረጊያ ይሆናቸው ዘንድ ባገኙት ቦታ ድንኳን ይተክሉ (የጸሎት ቤት ይሠሩ)ነበር። (ሕዝ.፲፩፥፮፣ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ ፷)
በዚያ ምኩራብም መጻሕፍትን ያነቡ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ይማሩ፣ የአምልኮ እና የጸሎት ሥርዓት ይፈጽሙ ነበር፤ ከሕግና ከነቢያት፣ ከዳዊት መዝሙራትም ይዘምሩ ነበር፥ ስብከት እና ቡራኬም ነበር፤ሕግ ያፈረሱትን በፍርድ የሚቀጡበትም ቤት ነው። ይህም የሚሆነው በሰንበት ቀን ነበር። (ማቴ.፬፥፳፫፣ ሐዋ.፮፥፱፣ ፱፥፪፣ ዮሐ.፱፥፴፬፣ ፪ኛ ቆሮ. ፲፩፥፳፬፣ ሉቃ.፬፥፲፮)
ጌታችንም በሰንበት ቀን እየሄደ ሕዝቡን ያስተምር፣ ድውያንን ይፈውስ፣ አንካሳውን እንዲራመድ ያደርግ ነበር፤ ሽባውን ይተረትር፣ ለምጻሙንም ያነጻ ነበር። ከነቢያት መጻሕፍትን ከመዝሙርም እየጠቀሰ ያስተምራቸው ነበር። (ማቴ.፳፩፥፲፬፣ ማር.፩፥፳፩፣ ፭፥፴፭፣ ሉቃ.፬፥፲፮)
ይህን አይቶ ቅዱስ ያሬድ በድጓው እንዲህ አለ፤ "ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ቃለ ሃይማኖት ለአይሁድ ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕተ፤ አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምሥያጥ፤ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ ቦአ ምኩራቦሙ ወገሠጾሙ ያርምሙ አንከሩ ምሕሮቶ ሞገሰ ቃሉ ወጣዕመ ነገሩ ወሣዕሣዓ አፉሁ፤ ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገባ፤ የሃይማኖትም ቃል አስተማረ፡፡ ከመሥዋዕት ይልቅ ምጽዋትን እወዳለሁ፤ የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባትዋ እኔ ነኝ አላቸው፡፡ የአባቴን ቤት የሸቀጥ ቦታ አታድርጉት፡፡ ቤቴ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራል፡፡ ወደ ምኵራብ ገብቶ ተቈጣቸው፡፡ ዝም እንዲሉም ገሠጻቸው፡፡ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩንም ጣዕም፣ የንግግሩንም ርቱዕነት አደነቁ፡፡" (ጾመ ድጓ ዘምኩራብ ዘሰንበት)
የሊቁን ሐሳብ ይዘን ብንመረምር ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን እናገኛለን። በዋናነት ግን ሁለት ዐምድ የሆኑ ጉዳዮችን እናገኛለን። የመጀመሪያው ጌታችን ወደ አይሁድ ምኵራብ ገብቶ እንዳስተማረ፤ የሃይማኖትንም ቃል እንደነገራቸው ስለ ምጽዋት፣ ስለ ሰንበት ጌትነቱ፣ ስለ ምሕረት እንዳስተማራቸው የምናገኝበት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አንጽሆተ ቤተ መቅደስ ያደረገበትን ቦታ እናገኛለን። ቅዱስ ያሬድም ጌታችንን ወደ ምኵራብ የገባበትን እና ቤተ መቅደሱን ያነጻበትን ምክንያት በማድረግ ሳምንቱን ምኩራብ ብሎ የጠራው። እስኪ ሁለቱን ሐሳቦች አንድ በአንድ እያነሣን እንመልከታቸው፡-
የመጀመሪያውን በተመለከተ ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ምኵራብ መሄዱን እና የሄደበት ጊዜ ደግሞ ፋሲካቸው መዳረሻ አካባቢ እንደሆነ እንዲህ በማለት ይነግረናል። “ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፥ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ። የአይሁድ ፋሲካም ቀርቦ ነበር፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።" (ዮሐ.፪፥፲፪-፲፫)
አይሁድ በምኵራባቸው በሰንበት ቀን እንደ ልማዳቸው መሠረት ጸሎት መጸለይ፣ ትምህርት መማር፣ መጻሕፍትን ማንበብ ያዘወትሩ ነበር። ኢየሱስም የተገኘው በዚሁ ዕለት ነው። ያን ጊዜ ደግሞ የአይሁድ ፋሲካ ነበር። ወንጌላዊው ይህን ፋሲካ ከእግዚአብሔር ፋሲካ ሲለይ የአይሁድ ፋሲካ ብሎ ጠራው። (ዘዳ.፲፪፥፲፩)
ነቢዩ ኢሳይያስ የአይሁድ ፋሲካን ከእግዚአብሔር ፋሲካ መለየቱን እና እግዚአብሔርም እንዳልተደሰተበት የሚነግረን “መባቻችሁንና በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ ሸክም ሆነውብኛል፥ ልታገሣቸውም ደክሜያለሁ።" (ኢሳ.፩፥፲፬)
እግዚአብሔርን የኃጢአተኞች ድግስ ደስ አያሰኘውም። የእርሱን ፋሲካ የሚያርጉት ግን እግዚአብሔር ወደዚያ እንዲመለከት ያደርገዋል። መጽሐፍ "ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። የተቀደሰ ጉባኤ ብላችሁ የምታውጁአቸው በዓላቶቼ፥ የእግዚአብሔር በዓላት፥ እነዚህ ናቸው" የሚለው ለዚህ ነው። (ዘሌ.፳፫፥፪)
በዚህም አይሁድ ከተሠራላቸው ሕግ እንደራቁ፣ ከአምልኮተ እግዚአብሔር ይልቅ በወግ አጥባቂ ሕግ እንደታወሩ መረዳት ይቻላል። ጌታችንም ወደ ምኵራብ በገባ ጊዜ የልቡና ዓይናቸው እንዲገለጥ፣ የዕውቀት ብርሃናቸው እንዲበራ ብሎ ያስተማረውን ትምህርት ነው፤ ቅዱስ ያሬድ "ወደ አይሁድ ምኵራብ ገባ፤ የሃይማኖትን ቃል አስተማረ" የሚለው ነው።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጀመሪያ ቤተ መቅደስ የገባው በዐሥራ ሁለት ዓመቱ ነበር። ያን ጊዜ ከመምህራን ትምህርትን ሊማር፣ ሊጠይቅ እንጂ ሊያስተምር አልነበረም። (ሉቃ.፪፥፵፪-፶፪) ከዚያ በኋላም ግን ለማስተማር፣ መጻሕፍትን ያውቁ ዘንድ (ሉቃ.፬፥፲፮) የእውነትን ምሥጢር ይገልጥላቸው ዘንድ ስለ አባቱ ጌትነት፣ ስለ እራሱም የባሕርይ ልጅነት፣ ስለ መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ ሕይወትነት ሊያስተምራቸው፣ ከሃይማኖት ይልቅ በወግ አጥባቂ ሕግ ታንቀው ነበርና ያንን ያፈርስ ዘንድ፤ ጾምን፣ ምጽዋትን፣ ወንድማማችነት ሊሰብክ ወደ ምኵራብ ገባ። እነርሱ ግን አላወቁም። የእነርሱንም ድንቁርና አልተረዱም። ይልቁንም የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን ጣዕም፣ የንግግሩንም ርቱዕነት ያደንቁ ነበር እንጂ።
አይሁድ ግን የእጁን ተአምር እያዩ፣ የቃሉን ትምህርት እየሰሙ ክፉ ቅንዓት ይዟቸው ነበር። እንዲያውም የምኵራብ መሪዎች እነርሱን እና ቤተ መቅደሱን የሚያዋርድ ይመስላቸውም ነበር። (El Khoury paul Elfaghali: The Gospel of Saint John, The Writhing Syndicate, 1992, page 15)
እግዚአብሔርም ግን በፍቅሩ ስቦ ወደ ቅዱስ መቅደሱ በክብር ያቆመናል። እኛም በእርሱ፣ በአባቱም ፊት ባለሟልነትን እናተርፋለን። ለዚያም ክብር ያብቃን፤ አሜን!
ስብሐት ለእግዚአብሔር፤አሜን!

Forwarded from ዘማሪት ፋሲካ ፍሥሐ (Fasika Fisseha)
YouTube
🔴የንስሀ ዝማሬ"ፊትህን መልስ"ዘማሪት ኢንጂነር ፋሲካ ፍሥሐ| Official Video@Zemarit_Fasika_fisseha#የመድኃኔዓለም መዝሙሮች#mahtot
Ethiopian Orthodox Tewahdo Mezmur by Zemarit Engineer Fasika Fissha "Fitehn Mels" @Zemarit_Fasika_fisseha
ፊትህን መልስ እባክህ ይቅር በለኝ
ጌታ ከአንተ እርቄ መሸሸጊያም የለኝ
ፊትህን መልስ እባክህ ይቅር በለኝ
ጌታ ከአንተ እርቄ መሸሸጊያም የለኝ
መዝሙረ ዳዊት በግዕዝ ውርድ ንባብ https://youtu.be/rZa46SyyxF8?si=sUDybiEoQGycyS5K
YouTube
#መዝሙረ_ዳዊት_ውርድ_ንባብ_ከአድህነኒ_እስከ_አምላክዬ
#መዝሙረ_ዳዊት_ውርድ_ንባብ
#መዝሙር_፲፩፦ አድኅነኒ እግዚኦ እስመ ኀልቀ ኄር
#መዝሙር_፲፪፦ እስከ ማዕዜኑ
#መዝሙር_፲፫፦ ይብል አብድ በልቡ
#መዝሙር_፲፬፦ እግዚኦ መኑ የኀድር
#መዝሙር_፲፭፦ ዕቀበኒ እግዚኦ
#መዝሙር_፲፮፦ እግዚኦ ስምዐኒ ጽድቅየ
#መዝሙር_፲፯፦ አፈቅረከ እግዚኦ በኃይልየ
#መዝሙር_፲፰፦ ሰማያት ይነግራ ስብሐተ እግዚአብሔር
#መዝሙር_፲፱፦ ይስማዕከ እግዚአብሔር
#መዝሙር_፳፦…
#መዝሙር_፲፩፦ አድኅነኒ እግዚኦ እስመ ኀልቀ ኄር
#መዝሙር_፲፪፦ እስከ ማዕዜኑ
#መዝሙር_፲፫፦ ይብል አብድ በልቡ
#መዝሙር_፲፬፦ እግዚኦ መኑ የኀድር
#መዝሙር_፲፭፦ ዕቀበኒ እግዚኦ
#መዝሙር_፲፮፦ እግዚኦ ስምዐኒ ጽድቅየ
#መዝሙር_፲፯፦ አፈቅረከ እግዚኦ በኃይልየ
#መዝሙር_፲፰፦ ሰማያት ይነግራ ስብሐተ እግዚአብሔር
#መዝሙር_፲፱፦ ይስማዕከ እግዚአብሔር
#መዝሙር_፳፦…
#መዝሙረ_ዳዊት_ውርድ_ንባብ
መግቢያ
ነዓ ሃቤየ አምላከ ዳዊት ንጉሠ እስራኤል በዓለ መዝሙር ሰናይ ወጥዑመ ቃል ታለብወኒ ነገረ ወፍካሬ ኩሉ አምሳል ከመ እወድሳ ለማርያም ድንግል እንዘ እፀርህ ወእብል መዝሙረ ዳዊትሰ ትመስል ገነተ አንተ ትፀጊ ጽጌያተ ወታፈሪ ፍሬያተ ወታበፅህ በረከተ ወትሰድድ አጋንንተ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም።
#መዝሙር_፩፦ ፍካሬ ዘፃድቃን
#መዝሙር_፪፦ ለምንት አንገለጉ
#መዝሙር_፫፦ እግዚኦ ሚ በዝኁ
#መዝሙር_፬፦ ሶበ ጸዋዕክዎ
#መዝሙር_፭፦ ቃልየ አጽምዕ
#መዝሙር_፮፦ እግዚኦ በመዓትከ ኢትቅስፈኒ
#መዝሙር_፯፦ እግዚኦ አምላኪየ ብከ ተወከልኩ
#መዝሙር_፰፦ እግዚኦ እግዚእነ ጥቀ ተሰብሐ
#መዝሙር_፱፦ እገኒ ለከ እግዚኦ
#መዝሙር_፲፦ በእግዚአብሔር ተወከልኩ