ሰሙነ ሕማማት
@zemariian
ረቡዕ የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰብስበው ጌታችንን ኢየሱስን እንዴት እንደሚይዙትና እንደሚያስገድሉት ምክር የጀመሩበት ዕለት ነው፡፡ ነገር ግን የፋሲካ በዓል ቀርቦ ስለነበር ሁከት እንዳይፈጠር እንዴት መያዝ እንዳለበት ሲጨነቁ ከጌታችን ደቀ መዛሙርት መካከል ይሁዳ ከምክራቸው በመቀላቀሉ ጥያቄአቸውን አቀለለላቸው፡፡ (ማቴ. ፳፯፥፫-፭፣ሉቃ. ፳፪፥፩-፪፣ማር.፲፬፥፩-፪) እንዲሁም እንዲሞት የወሰኑበት ዕለት ነው፡፡ (ማቴ. ፳፮፥፫-፭)
ምንጭ:- ማኅበረ ቅዱሳን ድኅረ ገጽ

እለተ ሐሙስ
በዚህች ዕለት ጌታችን በፍጹም ትሕትና የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበበት፣ ከሐዋርያት ጋር ግብር የገባበትና የክርስትና ሕይወት ማሕተም የሆነውን ምሥጢረ ቁርባን ያከናወነበት ዕለት ነው፡፡
ጌታችን በዚህ ዕለት ‹‹እናንተ ለወንድሞቻችሁ እንደዚህ አድርጉ›› በማለት የደቀ መዛሙርቱን እግር ያጠበበት ነው። ይህም የሚያሳየው ‹‹እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለው፤ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም፤መልክተኛም ከላኪው አይበልጥም፤ ይህን ብታውቁ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ›› በማለት ትሕትናውን አሳይቷል፡፡ (ዮሐ.፫፥፮-፯)
አባቶችንም በዚህ ዕለት ጌታችንን አብነት አድርገው በቤተ ክርስቲያን የምእመናኑን እግር ያጥባሉ፤ እኛም ከጌታችን ትሕትናን እንማራለን፤ በሕይወታችን ታዛዦች፣ትሑት፣ቅን ልሆንና ከእርሱ እንድንማር ባስተማረን መሠረት አርአያውን ልንከተል ይገባል፡፡

ከበሮ፣ጸናጽል፣መቋሚያና ከ፲ በላይ ቅዱሳት መጻሕፍትን የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በቅጂና ተዛማች መብቶች ሥራ ተመዝግቦ ከሚያዚያ ፫ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አእምሯዊ ንብረት መሆኑ ተረጋግጧል።
ከዚህ ቀደምም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ በአእምሯዊ ንብረት ዐቢይ ኮሚቴ አማካኝነት በርካታ የቤተክርስቲያን ንብረቶች ተመዝግበው እውቅና ማግኘታቸውን የመምሪያው ኃላፊ መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ ገልጸዋል።
ምንጭ ፦ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

#ግብረ_ህማማት_ዘመሀትወ_ሆሳእና_ከኢየሱሰ_ክርስቶስ_እስከ_ተአምረ_ኢየሱስ #ኢየሱሰ_ክርስቶስ
ኢየሱስ ክርስቶስ ጥዑመ ስም ለዘይጼውዖ
ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብስተ ሕይወት ለዘይበልዖ
ኢየሱስ ክርስቶስ በግዐ መድኃኒት ለዘይሠውዖ ከመ ይባርኩነ ይፈኑ አርዳኦ ለጸባኢነ ይጸብኦ ወልታሁ ነሢኦ።
#ተአምረ_ኢየሱስ
በንባብ ቤት

*መዝሙር ዘሌሊት ሰንበተ ክርስቲያን ቅድስት እንተ ቆመ ባቲ በዓለ ሆሳዕና።
* መዋሥዕት ዘሆሣዕና ዘ፻፳ወ፩ ተፈሣሕኩ እስመ ይቤሉኒ ቤተ እግዚአብሔር ነሐውር።
* ትዕዛዝ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ንዌጥን በረድኤተ እግዚአብሔር በጽሑፍ ዘአንበርዎ አበዊነ።
* ድርሳነ ዘቅዱስ ወክቡር ስምዖን አምዳዊ ዘይትነበብ በሌሊት ሰንበተ ክርስቲያን ቅድስት ዘኮነ ባቲ በዓለ ሆሣዕና።

ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቅድስት ድንግል ማርያምን በማስመልከት ባስተላለፉት ትምህርት ዙሪያ ተወያየ !
ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
ቋሚ ሲኖዶስ ዛሬ ማለዳ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ባሳለፍነው አርብ በስቅለት ዕለት በፍኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በቅድስት ድንግል ማርያም ዙሪያ ያስተላለፉትን ትምህርት በተመለከተ ውይይት አድርጓል።
በብፁዕነታቸው የተላለፈውን ትምህርት ዝርዝር ሁኔታን በመመርመርም ውሳኔ ለማስተላለፍ ይቻል ዘንድ ሁሉም የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምልዓት በተገኙበት ለአርብ ሚያዚያ 17 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ ተይዞል።
በተያያዘ ዜና የሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ በሆኑት በፖፕ ፍራንሲስ ሥርዓተ ቀብር ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ቤተ ክርስቲያናችንን በመወከል እንዲገኙ ተወስኗል።

ብቻህን ማሰብ ስትጀምር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የብቻችን የሆነ ትምህርት የለም። በማኅበር እንማራለን ፤ በማኅበር እንጸልያለን ፤ አንድ ሆነን የተዘጋጀልንን ማዕድ ቅዱስ ቊርባን እንቀበላለን ፤ በመጨረሻም የተዘጋጀልንን የተስፋ አገር እንቀበላለን።
ክርስቶስ ያስተማረ በጉባኤ ነው ፤ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ምንጊዜም ጉባኤአዊት ሆና ትቀጥላለች እንጅ ማንም ምንም ቢሆን የራሱን ትምህርት አምጥቶ ሊያስተምር የሚችልበት ዕድል የለውም።
የብቻው የሆነ ክርስቶስ ስለሌለው የብቻው የሆነ ትምህርትም ሊኖረው አይችልም።
ብቻህን ማሰብ ከጀመርህ ከጉባኤው የተለየ አስተምህሮ ማምጣትህ ስለማይቀር “ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኵሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት” የሚለውን የሃይማኖት መግለጫ አስቀድመን እንድናውቅ መደረጉ ስለዚህ ነው።
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚኖር ማንም ቢሆን ቤተ ክርስቲያን ካስተማረችው ትምህርት የወጣ እንደሆነ መዐርጉ ፣ የዕውቀት ደረጃው ፣ የወገኑ የሀብቱ ብዛት ሊያድነው አይችልም። በመጀመሪያ ከቃሉ የሰሙ ሰዎች “የተናገርኸውን ትምህርት አስበኸው ከሆነ አትናገረው ተናግረኸውም ከሆነ አትድገመው” ብለው ይመክሩታል። ምክራቸውን ሰምቶ በዚህ ካቆመ ይተዉታል፤ ምክራቸውን አልሰማ ብሎ ከቀጠለ ግን ወደ መምህራን ያደርሱታል፤ መምህራንንም አልሰማ ካለ ወደ ጉባኤ {ሲኖዶስ} ይቀርባል። ሲኖዶሱን ካልሰማ ተወግዞ ይለያል።
በሰሞኑ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የሰጡትን ትምህርት በቪዲዮ አንዲት ወዳጄ ልካልኝ ተመለከትሁት፤ ምናልባት ከባልንጀሮቻቸው ጋር ተማክረውበት ከበታቾቻቸውም ጋር ተከራክረውበት የነበረ ጉዳይ ከሆነ “አስበኸው ከሆነ አትናገረው ተናግረኸውም ከሆነ አትድገመው” ሊሏቸው ይገባ ነበር።
አሁን ግን በሹክሹክታ ሳይሆን በሰገነት ላይ የተሰበከ የስሕተት ስብከት ስለሆነ ጉዳዩ ከዚህ ያለፈ ይመስለኛል። ከረፈደም ቢሆን ባየሁት መረጃ መሠረት ብዙ ሊቃውንት ሀሳብ ሰጥተውበታል ፤ ይሄ ለብፁዕነታቸው መልካም ዕድል ነው ብየ አምናለሁ። ሀሳባቸውን የገለጹ ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን በሊቅነታቸው የምታምንባቸው ሊቃውንት እንደመሆናቸው መጠን ምክሩን ይቀበሉታል ብየ ስለማምን ነው። ሀሳቡን ሳይንቁ በቶሎ በሰገነት ላይ ያጠፉትን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት በሰገነት ላይ ወጥተው ቤተ ክርስቲያኒቱን ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል። “አትደንግጡ” ብለውናል እንዳንደነግጥ ያድርጉን።
ይህንን ትምህርት አባቶቻችን አልነገሩንም መጻሕፍቶቻችን ላይ ተጽፎ አላገኘነውም።
ብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ መጻሕፍቶቻችንን አባቶቻችንን ተቃውመዋል። ዛሬ መልስ አልጽፍም፤ ምክንያቱም መልሱን ከብፁዕነትዎ ስለምጠብቅ ነው።
ሊቀ ሊቃውንት ስምዓ ኮነ መልአክ