Telegram Web Link
የሳርዶ ቅድስት ማርያም አዳሪ አብነት ትምህርት ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ 9 ደቀ መዛሙርትን አስመረቀ።

በኢሉ ባቡር ሀገረ ስብከት በኖኖ ሰሌ ወረዳ ቤተ ክህነት በ2013 ዓ.ም የተመረቀው ዘመናዊ አዳሪ አብነት ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ዙር በንባብና ቅዳሴ 9 የሚሆኑ ደቀ መዛሙረትን ግንቦት 11 ቀን 2016 ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት አስመርቋል።

በምረቃው መርሐ ግብር ላይ ተመራቂ ደቀመዛሙርቱ ወርብ ያቀረቡ ሲሆን በሁለት ዓመት የትምህርት ቆይታቸው ከአብነት ትምህርቱ ጎን ለጎን የትምህርተ ሃይማኖት የኮርስ ሥልጠና ሲሰጣቸው እንደነበር ተገልጿል ።

በማኀበረ ቅዱሳን የገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ዋና ክፍል ም/ኃላፊ ዲ/ን ደረጀ ጋረደው ፣ የኢሉ ባቡር ሀገረ ስብከት ተወካይ ቀሲስ ጌቱ ሠይድ፣ የኖኖ ሰሌ ወረዳ ሊቀ ካህናት ቄስ ደረጀ ፈጠነ ፣ እንዲሁም የአካባቢው ህዝበ ክርስቲያን በመረሐ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።

ዲ/ን ደረጀ ጋረደው እንደተናገሩት ሀገረ ስብከቱ የአገልጋይ ካህናት እጥረት ያለበት መሆኑና በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ቀዳሽ አጥተው ተዘግተው ያሉበት በመሆኑ የእነዚህ ደቀመዛሙርት መመረቅ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ያሉ ሲሆን አብነት ትምህርት ቤቱ ለሌሎች ክልሎች አጎራባች ስለሆነ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ማፍራት እንደሚችል ጠቁመዋል።

የተማሪዎችን ሙሉ የቀለብ ወጭ የሸፈነው ማኅበረ ቅዱሳን ሲሆን ለዚህም ከ 700 ሽህ ብር በላይ ማድረጉም ተገልጿል።
ቅዱስነታቸው የደቡብ አፍሪካ ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ።
******

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ
ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዮንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣የደቡብ ኦሞና
አሪ ዞኖች ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ የዳውሮ-ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች በደቡብ አፍሪካ ሲያካሒዱት የቆዩትን ሐዋርያዊ አገልግሎት አጠናቀው ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ቅዱስነታቸውና ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ወደ ደቡብ አፍሪካ የተጓዙት የልዑካን ቡድን አባላት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣የባህርዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ክቡር መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ፣የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገው
ላቸዋል።

በመቀጠልም በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል መርሐ ግብር የሚካሔድ ሲሆን በዚሁ መርሐ ግብር ላይም ቅዱስ ፓትርያርኩ ትምህርተ ወንጌል፣ቃለ ምዕዳንና ቃለ ቡራኬ ሰጥተው የአቀባበል መርሐ ግብሩ የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ምንጭ: የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወ/ቂርቆስ ታመዋል"

ብዙዎቻችንን ወደ መንፈሳዊ መንገድ የመራን፣ በሐጢአት የገገረውን ዓለት ልባችንን በመንፈሳዊ መዝሙሮቹ ያቀለጠልን፣ ልንጠፋ ጫፍ ስንደርስ በሚስረቀረቅ ድምፁ የመለሰን፣ በአገልግሎቱ አዋጅ ነጋሪ የሆነ፣ መዝሙሩ ወደ ጸሎት ያደገለት ታላቁ አባታችን ሊቀ መዘምራን ኪነ ጥበብ ወልደ ቂርቆስ ሕክምና ይፈልጋል።

ጠንካራ ቤተ ክህነት ቢኖረን ኖሮ ይህ የቤተ ክርስቲያን ባለውለታ መታከሚያ ባላጣ ነበር። ዳሩ ግን...ሆድ ይፍጀው። እኛ የመዝሙራቱ ተጠቃሚዎች ግን ባለውለታችንን አንተውም። ዘማሪ ኪነጥበብ ወልደ ቂርቆስን ለማሳከም እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ....እነሆ በረከት!
መርዳት የማትችሉ በማጋራት ተባበሩ።

ድጋፋችንን አድርገን ወዳጅነታችንን እንግለጥ

CBE
1000481007287
KINETIBEB W/KIRKOS W/MESKEL
CMC Michael Branch
ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ያላቸው አስተዋፅኦ

ክፍል አንድ


በሐዋርያት ትምህርት ላይ የተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዋናው ተልእኮዋ የምሥራች ቃልን ለዓለም ማዳረስ ነው። ይህን የምሥራቹን ቃል ለማዳረስም በተለያየ ዘመን ብዙ ፈተናዎች ገጥሟታል፡፡ ፈተናዋን በጸሎት እና በዘመኑ በነበሩ አበው ምእመናን ጥብዓት ተሻግራ አሁን ካለንበት ዘመን ደርሳለች። ከአባቶቻችን የተረከብናትን ቤተ ክርስቲያን ከእነ ሙሉ ክብሯ ለመጠበቅ ትምህርት ላይ መሥራት ለነገ የማይባል ሥራ መሆኑ የሚያጠራጥር ባይሆንም ነገር ግን አሁን ባለንበት ዘመን ያለውን የትምህርት አሰጣጥ ሁኔታ ስንገመግመው ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሐዋርያት የተቀበለችውን ትምህርት ለማስተማር ከምትጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ ልጆቿን በሰንበት ትምህርት ቤት መዋቅር ውስጥ እንዲታቀፉ በማድረግ አስፈላጊውን ትምህርት እንዲያገኙ በማስቻል ነው። በመሆኑም የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች መጠንከርም ሆነ መድከም ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ያለው ተጽዕኖ ቀላል ይሆናል ተብሎ አይታሰብም። በዚህ አጭር ጽሑፍ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ያላቸውን አስተዋፅኦ ለማየት እንሞክራለን።

ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት ምን ማለት ነው?

ሰንበት ትምህርት ቤት ማለት በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ሥር ታቅፈው በበዓላት፣ በዕረፍት ቀናት (በሰንበታት) በመገኘት ትምህርተ ሃይማኖት የሚማሩ ተማሪዎች ስብስብ ማለት ነው።

የአገልግሎት ትርጕም

የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሲባል ገና ተጋድሎዋን ያልፈጸመችው እና የሚደርስባትን መከራ በጸጋ በመቀበል ክርስቶስን በመከራ ለመምሰል ሥርዓተ አምልኮዋን ዘወትር የምታከናውን ሲሆን ነው፡፡ “እግዚአብሔር የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ እንማልዳለን” ብላ በዐጸደ ነፍስ ካሉ ቅዱሳን እንዲሁም ዘወትር ያለማቋረጥ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት ጋር አንድ የሚያደርጋት አገልግሎት ተብሎ ሊገለጽ ይችላል።
ይቆየን!
በአዲስ አበባ የዘነበ ወርቅ ደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ እና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ፈለገ ሰላም ሰንበት ት/ቤት ማኅበረ ቅዱሳን ለሚያከናውነው ሐዋርያዊ አገልግሎት ድጋፍ አደረገ::

ድጋፉም በደቡብ ቤንች ወረዳ ለምትገኘው እና ለአዳዲስ አማንያን መገልገያነት ለታነጸችው ለካቡል ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ነው::

ሰንበት ትምህር ቤቱ 62ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ መለገሱ የተገለጸ ሲሆን ለ24 ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ልብሰ ስብሐት እና 5 መጽሐፍ ቅዱስ አስረክቧል::

የሰንበት ተ/ቤት ተማሪዎች በሃይማኖታቸው እንዲበረቱ፣ ቁጥራቸው እንዲጨምር የማደረግ ጥቅም የሚኖረው ሲሆን ሌሎች ሰንበት ት/ቤቶችም በእንደዚህ አይነት አገልግሎት መሳተፍ እንዳለባቸው የትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ኃላፊ የሆኑት ዲ/ን ኃይሌ አርአያ በርክክቡ ወቅት ገልጸዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ የማኅበረ ቅዱሳን ተወካዮች፣ በአካባቢው በቤንችኛ እና ሸክኛ ቋንቋዎች የሚያገለግሉት መጋቤ ኃይማኖት ቀሲስ ደመላሽ አማኑኤል ጨምሮ የፈለገ ሰላም ሰንበት ት/ቤት አገልጋዮች ተገኝተዋል::

ሰንበት ት/ቤቱ በዚሁ ዓመት በቤንች ወረዳዎች ለሐዋርያዊ ተልእኮ የሚሠማሩ 25 ሰባክያነ ወንጌልን ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመሆን አሰልጥኖ መላኩ ይታወሳል፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን አስተባባሪነት አገር አቀፍ የደም ልገሳ መርሐ ግብር እየተከናወነ ይገኛል።

ማኅበረ ቅዱሳን ከኢትዮጵያ የደም ባንክ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የደም ልገሳ መርሐ ገብር በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ እየተከናወነ ይገኛል።

አዲስ አበባ በሚገኘው የማኅበሩ ዋና ማእከል ጽ/ቤት በተከናወነው የደም ልገሳ መርሐ ግብር ላይ በርካታ ምእመናን ተገኝተው በመለገስ ላይ ይገኛሉ።
2024/05/27 08:21:10
Back to Top
HTML Embed Code: