Ayehugn behelme_Ermias begena.mp3
Unknown Artist
መምህር ኤርምያስ በገና a
ኬብሮም የዜማ መሣርያ ማሠልጠኛ እና ማምረቻ ተቋም ባለቤት
@zemarian
Audio
ድንቅ ወቅታዊ ዝማሬ
በዘማሪት መስከረም ወልዴ
ቻናሉን ለመቀላቀል
ይጫኑት
👇👇
@zemarian
የጉልባን ታሪክ
@zemarian
➛ ጉልባን ከባቄላ ክክ ከሰንዴ ወይም ከተፈተገ ገብስ እና ከሌሎችም ጥራጥሬዎች ጥሬውን ወይም ከክቶ እንደ ንፍሮ ተቀቅሎ የሚዘጋጅ ምግብ ነው ። የዕለተ ሐሙስ ሥርዓተ ጸሎት ከተፈጸመ በኋላ ምእመናን ወደ ቤታቸው ሄደው ጉልባን ሠርተው ይመገባሉ ። ለዚህም ሁለት ትውፊታዊ መሠረት እንዳሉት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ያስረዳሉ እንመልከት፦ ፩ የኦሪት ምሳሌ ለመፈጸም እስራኤል ለ215 ዓመታት በግብጻውያን በባርነት ተይዘው በግፍ ተጨቁነው መኖራቸው ይታወቃል የእግዚአብሔር ፍቃድ ሁኖ እግዚአብሔር ሙሴን ፈርኦንን ህዝቤን ልቀቅ ብሎሀል ብለህ ንገረው ብሎት ነበር ። ሙሴም ፈርኦንን እግዚአብሔር ህዝቤን ልቀቅ ብሎሀል አለው ፈርኦንም እስራኤል እለቅ ዘንድ እግዚአብሔር ማነው ? እግዚአብሔርን አላቅም እስራኤንም ደግሞ አለቅም በማለት አሻፈረኝ ብሎ ነበር ። እግዚአብሔርም የኃይል ስራውን በሙሴ አሳየ በመጨረሻም እምቢ ሲል እግዚአብሔር ከእንስሳትም ከሰውም ወገን በመልአክ በሞተ በኩር ግብጽ ተቀሰፈች በዚህም ፈርኦን ደንግጦ ሕዝበ እስራኤል ለመልቀቅ ተገዷል ። በዚህ ጊዜ ህዝቡ ለመውጣት ስለቸኮሉ በቤት ያለውን እህል ያልተፈጨውን ንፍሮ ቀቅለው የተፈጨውን ቂጣ ጋግረው በልተው ነው ጉዞ የጀመሩት ። እስራኤልም ከግብፅ ከወጡ በኋላም የነጻነት በዓላቸውን ሲያከብሩ ያልቦካ ኪጣ ጋግረው ንፍሮ ቀቅለው በግ አርደው ከባርነት በወጡበት ዕለት የነበረውን ሁኔታ ያስቡ ዘንድ ታዘዋል ። (ዘጸ ፲፫ ፥፩) ፋሲካ የሚለውም '' ፓሢሕ '' ከሚለው ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ማለፍ መሻገር ማለት ነው ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሴተ ሐሙስ በአልዓዛር ቤት ተገኝቶ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ይህን በዓል አክብሯል ። እኛም አሰቀድሞ በሙሴ ላይ አድሮ ሕገ ኦሪትን የሠራ ሕዝቡንም መርቶ ከነዓን ያደረሰው እርሱ ራሱ እግዚአብሔር የሰውን ስጋ ለብሶ ክርስቶስ ተብሎ መገለጡን በማመን ፤ ክርስቶስ ራሱ አዲሱን ሕግ ከመሥራቱ አሰቀድሞ ከደቀመዛሙርቱ ጋር በዓለ ፋሲካን እንዳከበረ ሁሉ እኛም አዲስ ኪዳን ጥላ /ምሳሌ/ የሆነውን ሥርዐት እኛ ጉልባን በመመገብ ለመታሰቢያ እናደርጋለን ።
፪ የኀዘን ሳምንት መሆኑን ለማጠየቅ ፦ እንደ ሀገራችን ባሕል ንፍሮ እንባ አድርቅ ይሉታል ። ብዙ ጊዜም ለለቀስተኞች ይሠራል ። አንድም ሞት ተናግሮ አይመጣምና ሞት በድንገት ሲመጣ ለእንግዳ መሸኛ ቶሎ ሊደርስ የሚችል ምግብ ንፍሮ ስለሆነ በተለይም በገጠራማ አካባቢዎች ለልቅሶ ቤት ንፍሮ የመቀቀል ልማድ አለ ።
➛ በሰሙነ ሕማማት ወቅት ምዕመናን በጌታችን መከራ ፣ ሞት እና በድንግል ማርያም ኀዘን ምክንያት ኀዘንተኞች ስለሆኑ ይህንኑ ለማመልከት ጉልባን ይመገባሉ ። የጉልባን ክርስቲያናዊ ትውፊት ይህንን ይመስላል እኛ ምዕመናን በቤተችን እንዲሰራ በመጠየቅ በመስራት ይህን ትውፊት ማስቀጠል ይኖርብናል ።
+ ከማቁሰል የከፋ መሳም +

​ይሁዳ ጌታችንን ያለ ፍርሃት ቀርቦ ሳመው፡፡ መሳም የጥልቅ ፍቅር መግለጫ ነው ፤ ይሁዳ ግን በመሳሙ የልቡን ጥላቻ የሚገልጽ ተንኮል ሠራበት፡፡ በዚህ ምክንያት ይሁዳ ክፋትን በልባቸው ይዘው የውሸት ፍቅርን ለሚያሳዩ ሁሉ ምሳሌ ሆኖ ቀረ፡፡ ቅዱስ አምብሮስ ይሁዳን እንዲህ ይለዋል፡፡ ‹‹የመሳምን ትርጉም የማታውቅ ይሁዳ ሆይ ጌታችንን ልትስመው ቀረብህ! የሚፈለገው ትልቁ ነገር ግን በከንፈር መሳም አይደለም፡፡ የልብና የነፍስ መሳም ከሁሉ ይበልጣል›› ይሁዳ በዚህ ድርጊቱ ከርሱ ከቀደሙ ክፉዎች ጋር ተመሳሰለ፡፡ አሳቢ መስሎ የሰይጣን ማደሪያ የሆነውን ዕባብ ፣ በፍቅር መሳም አታልላ ሶምሶንን አሳልፋ የሰጠችው ደሊላ ፣ አባቱ ላይ ጠላት አስተባብሮ ሊወጋ የተነሣው አቤሴሎም ፣ ለወንድሙ ዮሴፍ አዛኝ መስሎ እንዲሸጥ ሃሳብ ያቀረበው ይሁዳ በአስመሳይነታቸው የአስቆሮቱ ይሁዳ ቀደምት የግብር ዘመዶች ናቸው፡፡

​የይሁዳ መሳም ለጌታችን ከችንካር የከፋ ነው፡፡ ‹‹የወዳጅ ማቁሰል የታመነ ነው ፤ የጠላት መሳም ግን የበዛ ነው›› እንደሚል ይሁዳ ጌታን ጠላቱ ሆኖ ለማስመሰል አብዝቶ ከሚስመው ይልቅ ፍቅርን ተሞልቶ ወዳጁ ሆኖ ቢያቆስለው ይሻል ነበር፡፡ (ምሳ. ፳፯፥፮) ቅዱስ ጄሮም እንዳለው የይሁዳ መሳም ‹የቃየን መሥዋዕት› ሆነ፡፡ ቃየን ንቀት በተሞላ ልብ መሥዋዕትን እንዳቀረበ ይሁዳም በጥላቻ ተሞልቶ የፍቅርን መሥዋዕት አቀረበ፡፡
​ጌታችንን በዕለተ ዓርብ አቁስለውት የዳኑ አሉ ፤ ይሁዳ ግን ጌታችንን ስሞት ተኮነነ፡፡

የዲማው ሊቅ አለቃ ውድነህ እሸቴ ፡-
‹‹ስዒመ ከናፍር ትእምርተ ፍቅር ወረጊዘ ገቦ ትእምርተ ሞት ፤
ባሕቱ ፍሉጥ ለስቅለትከ ሥርዓት ፤
ስዒመ ይሁዳ እስመ ለኀጉል ወረጊዘ ለንጊኖስ ለሕይወት››

‹‹በከንፈር መሳም የፍቅር ምልክት ነው ፤
ጎንን መውጋት ደግሞ የሞት (ጥላቻ) ምልክት ነው፡፡
ጌታ ሆይ የስቅለት ግን ሥርዓቱ የተለየ ሆነ፡፡
የይሁዳ መሳም ለጥፋት ሲሆን
የለንጊኖስ በጦር መውጋት ግን ለሕይወት ሆነ››
ብለው የሳመው ይሁዳን የጌታን ጎን ከወጋው ወታደር ጋር አነጻጽረው ተቀኝተውበታል፡፡

ጌታችን ይሁዳ በተንኮልና በውሸት ሊስመው እንደመጣ እያወቀ እንኳን ‹እንዳትነካኝ› ብሎ አላስደነገጠውም፡፡ እንደ ሌባ ሊያስይዘው መጥቶ ክፋትንና ተንኮልን በተሞሉ ከንፈሮቹ ሲስመው ታገሠው ሊያስይዘው በመጣበት ሰዓት ለትዕግሥቱ ወሰን የሌለው ጌታ የይሁዳን መሳም ተቀበለ፡፡ እሱ ቢከዳውም ጌታችን ግን ለይሁዳ ያለውን ፍቅር ያሳየበት የመጨረሻው ቅጽበት ሲስመው መቀበሉ ነበር፡፡

እኛ ብንሆን ምን እናደርግ ነበር? ኢትዮጵያዊው ሊቅ ርቱዐ ሃይማኖት በዓሥራ አራተኛው ክፍለ ዘመን በጻፈው ድንቅ ድርሰቱ እንዲህ ይጠይቀናል ፡-
​‹‹አንተ ሰው ሆይ! የጌታን ትሕትናውንና ቸርነቱን ተመልከት፡፡ አንተ እንደ ክርስቶስ ሥልጣን ቢኖርህ ኖሮ ይህን ጊዜ ምን ታደርገው ነበር? እንደሚመስለኝ ሥጋውን በበላኸው ደሙንም በጠጣኸው ነበር! ጎስቋላው ይሁዳ የሰማዩን ንጉሥ ያስገድለው ዘንድ የሽንገላ መሳምን በሳመው ጊዜ እንቢ አላለውም፡፡ ‹ወዳጄ ሆይ መጣህን› ብሎ መሳምን አስቀደመ እንጂ፡፡ ታላቁንና የሚሻለውን ነገር ለዘመድ ወዳጆቻችን ፤ ታናሹንና የሚከፋውን ነገር ደግሞ ለጠላቶቻችን የምንሠጥ እኛ በዚህ ዘመን ብንኖር ኖሮ ይህንን አድርገን የምንተው አልነበረም፡፡ የሚወድቁበትን መንገድ እስከምናገኝ ድረስ እንጸናባቸዋለን እንጂ፡፡

‹‹አቤቱ ጠላቶቻችንን እንደ ትቢያ እንረግጣቸው ዘንድ ማሸነፍን ሥጠን›› ብለንም እንጸልያለን፡፡ በይሁዳ ከንፈሮች የተሳመው አምላካችን ይህንን ስንል በሰማ ጊዜ በልቦናችን ስላደረው ክፋት ምን ይል ይሆን? በእርግጥም ይህንን ዓይነት ምግባር ካልተውን በቂም በበቀል እያለን በሽንገላ የምንሳሳም ከሆነ ዕጣችን ከጎስቋላው ይሁዳ ጋር ይሆናል›› (ርቱዐ ሃይማኖት ፲፬፥፩)
ሊሸጠው እንደመጣ እያወቀ ይሁዳ በሐሰት ፍቅር ሲያቅፈው ጌታችን ልቡን ምንኛ አሳዝኖትና አምሞት ይሆን? እርሱ ግን ይህንን ሕመም ታገሦ ተቀበለ፡፡ ይሁዳም እንደ ጠላቱ እየሸጠው እንደ ወዳጁ አቅፎ ሳመው፡፡ ጌታችን ‹‹በሩ እኔ ነኝ ፤ በእኔ የሚገባ ይድናል›› ብሎ ሲናገር ቢሰማም ይሁዳ ግን በሩን ጌታን ስሞ ተሳልሞ ወደ ውስጥ በመግባትና በመዳን ፈንታ ወደ ሲኦል ገሠገሠ፡፡ ከውጪ ተሳልሞ መመለስ ይኼው ነው ትርፉ! (ዮሐ. ፲፥፱)

የክርስቶስ አካል የሆነች ቤተ ክርስቲያናችን የጌታዋ ሕመም ዘልቆ ስለሚሰማት የይሁዳን በመሳም አሳልፎ መስጠት በማሰብ በሕማማት ሳምንት ልጆችዋ ምእመናንን በመሳሳም ሰላምታ እንዳይለዋወጡ ትከለክላለች፡፡ በዓመት ውስጥ ሦስት መቶ ስድሳ አንዱን ቀናት ‹‹ተአምኁ በበይናቲክሙ በአምኃ ቅድሳት›› ‹‹እርስ በእርሳችሁ በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተለዋወጡ!›› እያለች የቅዱስ ጳውሎስን የሰላምታ አዋጅ በቅዳሴዋ የምታውጀው ቤተ ክርስቲያን በሕማማቱ ሳምንት ግን እንዳይሳሳሙ ታስቆማቸዋለች፡፡

‹ይህ ሳምንት መድኃኒታችሁ ስለ እናንተ በሽንገላ መሳምን የታገሠበት ሳምንት ነው ፣ ይህ ሳምንት የፍቅር ምልክት የሆነው መሳሳም የጥላቻ ምልክት የሆነበት ሳምንት ነው›› ብላ ሰላምታ ይቅርባችሁ ትላለች፡፡ ምእመናንም በዚያ ሳምንት ውስጥ ሰላምታ ሊለዋወጡ ከጀመሩ በኋላ ሕማማት መሆኑን አስታውሰው ቆም ሲሉ በዚያው መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በይሁዳ መሳም ተላልፎ መሰጠቱን ለቅጽበት ያስባሉ፡፡

​ጌታችን ይሁዳ ከሳመው በኋላ ‹‹ወዳጄ ይሁዳ ሆይ ለምን ነገር መጣህ? በመሳም የሰውን ልጅ አሳልፈህ ትሠጣለህን?›› በማለት እንደተናገረ ሁለቱ ወንጌላውያን የጻፉትን ገጥመን በማንበብ መረዳት እንችላለን፡፡ (ማቴ. ፳፮፥፵፰፤ሉቃ. ፳፪፥፵፰)

‹‹ወዳጄ ይሁዳ ሆይ ለምን ነገር መጣህ? በመሳም የሰውን ልጅ አሳልፈህ ትሠጣለህን?›› የሚለው የጌታ ንግግር ‹ጠላቶቻችሁን ውደዱ› ለሚለው ቃል ተግባራዊ ምስክር ነው፡፡‹‹ጠላቱ ሲሆን ጠላቴ አላለውም ወዳጄ አለው እንጂ፡፡ በቀልን የሚተው ልቡናው ትሑት ፣ ጠላቱን ወዳጅ ነውና›› ፍቅርም የተጓደለውም በይሁዳ በኩል እንጂ በጌታችን በኩል አልነበረም፡፡

ሊቃውንት ‹የሰውን ልጅ አሳልፈህ ትሠጣለህን› የሚለውን ቃል ጥልቅ ነገረ መለኮታዊ መልእክትም ያለው ነው ይላሉ፡፡

‹‹ጌታችን የተሰወሩ ምሥጢራትን በመግለጥ ይሁዳ በትክክል አሳልፎ የሰጠው ማንን እንደሆነ ተናገረ፡፡ ‹የሰውን ልጅ› በማለት ማንን እንደከዳ አስረዳው፡፡ የሰው ልጅ በማለቱ ሥጋን በመልበሱ እንጂ በመለኮታዊው ባሕርይው ተላልፎ ሊሠጥም ሆነ ሊያዝ እንደማይችል አስረዳ››

‹የሰውን ልጅ አሳልፈህ ትሠጣለህን?› የሚለው ቃል ደግሞ ከላይ እንዳየነው የክርስቶስን አምላክነት ለሚጠራጠረውና ‹ጌታ ሆይ› ብሎ ሊጠራው ላልወደደው ይሁዳ ምፀታዊ ትርጉምም የሚሠጥ ንግግር ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹መምህርህን ወይም ብዙ ነገር ያደረገልህ ጌታህን አሳልፈህ ትሠጣለህን? አላለውም›› በማለት ካስተዋለ በኋላ የጌታችንን ንግግር ሲያብራራም ‹‹ጌታህና መምህርህ ባልሆን እንኳን ኖሮ ንጹሕ የሰውን ልጅ አሳልፈህ ትሠጣለህን? በከዳኸው ቅጽበት ትስመዋለህ? መሳምን አሳልፎ የመሥጫ ምልክት ታደርገዋለህ?›› ሲለው ነው ብሏል፡፡

ይህ ንግግር በፍጥረቱ መዳን ተስፋ የማይቆርጠው ጌታ ለይሁዳ ያቀረበው የመጨረሻ የሚያራራ ትምህርት ነበር፡፡ በዚህች ልብ የምትነካ ጥያቄ ይሁዳ ሊመለስ ይገባው ነበር፡፡
‹‹የምንሰጠው ምክር ፍሬ አልባ ቢመስለንም እንኳን ወንድሞቻችንን ከመምከር ማቋረጥ የለብንም፡፡ የምንጭ ውኃ የሚጠጣው ሰው ባይኖርም እንኳን መፍሰሱን አያቆምም፡፡ ዛሬ የማይሰማ ነገ ይሰማ ይሆናል፡፡ ዓሣ አጥማጅ ቀኑን ሙሉ ባዶ መረብ በባሕር ውስጥ ጥሎ ሊውል ይችላል፡፡ በመጨረሻዋ ቅጽበት ግን ዓሣ ሊያጠምድ ይችላል፡፡ ለዚህ ነው ጌታችን ይሁዳ እንደማይሰማው እያወቀ እንኳን እስከተያዘበት የመጨረሻ ሰዓት ድረስ ምክርን መሥጠቱን አላቋረጠም፡፡›› ይላል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፡፡
አዎን ጌታችን የይሁዳን ነፍስ ወደ ቅድስና መረብ አጥምዶ ለማስቀረት ሦስት ዓመታት ሙሉ ያለማቋረጥ እጁን ዘረጋ፡፡ ተይዞ ሊሔድባት ባለባት ምሽት እንኳን ይሁዳን ለመመለስ በፍቅር ቃል አናገረው፡፡
‹‹የወደዳቸውን እስከ መጨረሻው ወደዳቸው›› ይላልና፡፡ (ዮሐ. ፲፫፥፩)

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሕማማት /ገፅ55)
++ ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ++

ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ፊት በዚያች ምሽት በጭንቀት ቆመዋል፡፡ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሠጠኛል ብሎ ነግሯቸዋል፡፡ ስለዚህ ተጨንቀዋል፡፡ ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? እያሉ ዐሥሩ ደቀ መዛሙርት ተራ በተራ ጠየቁት፡፡

የቀሩት ሊሸጠው ተስማምቶ የመጣው ይሁዳና ወንጌላዊው ዮሐንስ ናቸው፡፡ ይሁዳ እኔ እሆንን ማለቱ ልቡ እያወቀ ስለነበር ከዐሥሩ ጋር አብረን አንቆጥረውም፡፡ ዮሐንስ ደግሞ ለጌታ ካለው የፍቅር ጥልቀት የተነሣ እኔ እሸጠው ይሆን? የሚል ሥጋት ስላልነበረበት ‘’ጌታ ሆይ አሳልፎ የሚሠጥህ ማነው?’’ አለ እንጂ እኔ እሆንን አላለም፡፡ የሐዋርያቱ የጭንቀት ጥያቄ በማግሥቱ መልስ አግኝቷል፡፡ ሆኖም ይህንን ትሕትና የተሞላ ጥያቄያቸውን ለእኛ ሳይበጅ አይቀርም፡፡

በዙሪያችን ለተደረጉ ፣ ለሚደረጉ ክፉ ነገሮች ሁሉ ምክንያቱ ምንድር ነው? ጥፋቱ የማን ነው? መነሻው ምንድርን ነው? ብንባል ሁላችንም ጣት የምንቀስርበት ሰው አናጣም፡፡
አዳም ዕጸ በለስን ለመብላቱ ‘’ም ክን ያቴ ሔዋን ናት ‘’ አለ
ሔዋን ‘’ዕባብ አሳተኝ ‘ አለች
ዕባብም ጠያቂ ቢያገኝ ሰይጣን ማለቱ አይቀርም ነበር፡፡
አንዳቸውም ‘’ጌታ ሆይ እኔ እሆንን?’’ ማለት አልቻሉም፡፡ እንደ ዳዊት ‘’እኔ መተላለፌን አውቃለሁ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊትህ ነው’’ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ለሚሆኑ ነገሮች ሁሉ የምንከስሰው ሰው አናጣም:: መፍትሔው ግን ራስን ማየት ነው:: "እስመ አዕይንቲሁ ለጠቢብ ዲበ ርእሱ" (የጠቢብ ዓይኖቹ በራሱ ላይ ናቸው) እንዲል

ቅዱሳን በምንም ነገር ራሳቸውን ይወቅሱ ነበር:: በገድላቸው ብዛት በሚጸልዩበት ሥፍራ ዶፍ ዝናብ እየወረደ ሳለ እርሳቸውን እንዳይነካቸው በቆሙበት ሥፍራ እንዳይዘንም ያደረገላቸው ዳግማዊው ኤልያስ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያሉትን እናስታውስ:: በቆሙበት ሥፍራ ዝናም እንዳልዘነመ ሲያዩ "ይህችን መሬት በኃጢአቴ ዝናም አስከለከልኳት" ነበር ያሉት:: ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ማለት ይህም አይደል?

የሙሴ ወንድም አሮን በእስራኤል ግፊት ጣኦት ሠራ፡፡ ከወርቅ አቅልጦ ጥጃ አምላክ አድርጎ ሠራላቸው፡፡ ከሠራ በኋላም መሥዋዕት ለጣኦቱ አቀረበ፡፡
ሙሴ መጥቶ ሲቆጣ ሲያይ ግን አሮን ፈራና በሕዝቡ አሳበበ የራሱን ድርሻ በተመለከተ ግን እንዲህ አለ
‘ወርቅ ሰጡኝ በእሳት ላይ ጣልሁት ይህ ጥጃ ወጣ’ {ዘጸ 32፡24}
ራሱ ከእጃቸው ተቀብሎ በመቅረጫ ቀርጾ የሠራውን ጣኦት ‘ስጥለው ጥጃ ሆነ’ አለ፡፡ ራሱ ሕዝቡን ‘ስድ ለቅቋቸው’ የነበረ በመሆኑ ‘’ጌታ ሆይ እኔ እሆንን?’’ ብሎ ራሱን ሊከስስ ይጠበቅበት ነበር፡፡

በትምህርት ቤት ሕይወታችን የማይረሱ ቀናት ግሬድ የሚለጠፉባቸው ቀናት ናቸው፡፡ ከብዙ የመታወቂያ ቁጥር መካከል ውጤቱን ያየ ተማሪ በዚያ የትምህርት ዓይነት A እንዳገኘ ሲያውቅ ለጓደኞቹ ‘’A አገኘሁ እኮ’’ ይላል፡፡ በተቃራኒው ‘F’ ያገኘ ከሆነ ‘’F ሠጠኝ’’ ይላል እንጂ ‘F አገኘሁ’ አይልም፡፡ A ከሆነ ያገኘው ተማሪው ነው ፤ F ከሆነ ግን በድክመቴ አገኘሁ ከማለት ይልቅ ጥፋቱ የመምህሩ ይሆናል፡፡ ነገሩን አልኩ እንጂ ሀገር ሰላም ብሎ የቆመ በር ጋር ስንጋጭም ‘በሩ መታኝ’ እንጂ መታሁት አንልም፡፡
እናም በሕይወታችን ለሆኑትና ለሚሆኑት ነገሮች ‘ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ማለት ትልቅ ጸሎት ነው፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 20 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ
ሊሸጠው እንደመጣ እያወቀ ይሁዳ በሐሰት ፍቅር ሲያቅፈው የጌታችን ልቡን ምንኛ አሳዝኖት ና አሞት ይሆን?እርሱግን ይህንን ሕመም ታግሦ ተቀበለ ይሁዳም እንደ ጠላቱ እየሸጠው እንደወዳጅ አቅፎ ሳመው ።ጌታችን <<በሩ እኔ ነኝ በእኔ የሚገባ ይድናል >>ብሎ ሲናገር ቢሰማም ይሁዳ ግን በሩን ጌታን ስሞ ተሳልሞ ወደ ውስጥ በመግባትና በመዳን ፈንታ ወደ ሲኦል ገሠገሠ። ከውጪ ተሳልሞ መመለስ ይኼው ነው ትርፉ !(ዮሐ 10፥9)
የክርስቶስ አካል የሆነች ቤተክርስቲያናችን የጌታዋ ሕመም ዘልቆ ስለሚሰማት የይሁዳን በመሳም አሳልፎ መስጠት በማሰብ በሕማማት ልጅችቿ ምዕመናንን በመሳሳም ሰላምታ እንዳይለዋወጡ ትከለክላለች ።በዓመት ውስጥ 361ዱን ቀናት <<እርስ በራሳችሁ በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተለዋወጡ! >
እያለች የቅዱስ ጻውሎስን የሰላምታ አዋጅ በቅዳሴዋ የምታውጀው ቤተክርስቲያን በሕማማቱ ሳምንት ግን እንዳይሳሳሙ ታስቆማቸዋለች ። ይህሳምንት መድሐኒታችሁ ስለ እናንተ በሽንገላ መሳምን የታገሰበት ሳምንት ነው ይህ ሳምንት የፍቅር ምልክት የሆነው መሳሳም የጥላቻ ምልክት የሆነበት ሳምንት ነው።ብላሰላምታ ይቅርባችሁ ትላለች ምዕመናንም በዚያ ሳምንት ውስጥ ሰላምታ ሊለዋወጡከጀመሩ በኃላ ሕማማት መሆኑን አስታውሰው ቆም ሲሉ በዚያው መድኃኔዓለም ክርስቶስ በይሁዳ መሳም ተላልፎ መሰጠቱን ለቅጽበት ያስባሉ ።

#ከማቁሰል የከፋ መሳምከሚለው ርዕስ የተቀነጨበ

#ሕማማት መጽሐፍ ገፅ55-62)

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
_NEW_በርባን_እኔ_ነኝ_ዘማሪት_ትዕግስት_ስለሺ_1080_X_1072_.mp4
64.6 MB
{በርባን እኔ ነኝ )

ድንቅ ዝማሬ

ዘማሪት> ትዕግሥት ስለሺ
ግጥም> ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
ዜማ >ዘውዱ ጌታቸው
#ዓርብ
#የስቅለት_ዓርብ_ይባላል
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።

#መልካሙ_ዓርብ_ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።

@zemarian
20230405-1328_Recording 53.wav
5.8 MB
ኪራላይሶ
በዘማሪ ብርሃኑ ጫኔ
ክራር ኢዮሲያስ አበራ
@zemarian
#ቅዳሜ
#ቀዳም_ስዑር_ትባላለች
ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።

#ለምለም_ቅዳሜ_ይባላል፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።

#ቅዱስ_ቅዳሜ_ይባላል፡-
ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።

@zemarian
Audio
አለምን ለማዳን
ዘማሪ ወንደሰን
ክራር ኢዮሲያስ አበራ
@zemarian
Audio
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ዘማሪ👉 ዘለቀ አስናቀ
በገና 👉ዳዊት ችሮታው

@zemarian
Audio
ዘማሪ ዲያቆን ፍጹም
ክራር ኢዮሲያስ አበራ
@zemarian
Audio
ጌታ ተነስቷል
በዘማሪ ስንታየሁ ሞገስ
ክራር ኢዮሲያስ አበራ
@zemarian
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሐይማኖት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

ሚያዝያ 26 ቀን 2016 ዓመተ ምህረት ንቁ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የጸሎትና የንስሐ መርከብ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
++++++++++++++++++++++++
- ቅዱስነታቸዉ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሳኤ ስናስብ የእኛን ትንሳኤ እያሰብን ሊሆን ይገባል በማለት ገልፀዋል።
- በዕምነት ትንሳኤ በአምልኮተ እግዚአብሔር ትንሳኤ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመመላለስ መሆን አለበት ብለዋል።
- ቅዱስነታቸዉ ከዚህ በማስቀጠል ከህገ እግዚአብሔር በመራቅ ከቅድስት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ዉጭ በሆነ ዝሙት ምክንያት በኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ የሚሞተዉ ሰዉ ሀገርንና ድንበርን ለመጠበቅ በየጦር ሜዳዉ ከሚያልቀዉ ሰዉ አይተናነስም በማለት ምዕመናን ከዚህ አፀያፊ ተግባት እንዲታቀቡ አባታዊ መልዕክትን አስተላልፈዉ በመላዉ ዓለም ለሚገኙ ምዕመናን ለ2016 ዓመተ ምህረት የትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የቅዱስነታቸዉ በረከት ይደርብን።
2024/05/06 12:08:49
Back to Top
HTML Embed Code: