Telegram Web Link
• ጀምረናል…

ገባገባ በሉማ…

• አላችሁ አይደል…?
"…ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ፥ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል? ለሚሉ ወዮላቸው! ኢሳ 29፥15 

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
ሌላ የአፈና ዜና…

"…የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት የሆኑ ጥንታውያን ገዳማትና አድባራትን በማስጎብኘት፣ ሕዝብ አስተባብሮም የፈረሰውን በማሳነጽ የሚታወቀው፣ የማኅበረ ወይንዬ አቡነ ተክለሃይማኖት መንፈሳዊ ማኅበርና ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ትውልድን ከግበረ ሰዶም እንታደግ የተሰኘው ማኅበር መሥራቹ የአደባባይ ሰው መምህር ደረጄ ነጋሽ (ዘወይንዬ) በዛሬው ዕለት ምሳ ሰዓት አካባቢ ሰዓሊተ ምህረት ኢትዮ ቻይና ኮሌጅ ፊት ለፊት ከሚገኘው ቢሮው ውስጥ በሥራ ላይ እንዳለ ታርጋ ቁጥሩ ኮድ ② አአ 64813 በሆነ መኪና በመጡና የደኅንነት ሰዎች እንደሆኑ የገለጹ አካላት አፍነው ይዘውት እንደሄዱ በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ለዘመድ ሚዲያ ገልፀዋል።

"…በጎጃም አራት አይናው ሊቅ የኔታ ይባቤ በታፈኑ፣ በምሥራቅ ሸዋ የዝቋላ መነኮሳት በታረዱና በተጨፈጨፉ ማግሥት በዛሬው ዕለት ደግሞ ደፋሩ፣ ፊትለፊት የግንባር ሥጋ የሆነው፣ ለተጎዱ፣ ለተጠቁ ሁሉ ያለመሳቀቅ በድፍረት ከፊት ረድፍ ተሰላፊው፣ በሀገሩ በኢትዮጵያና በሃይማኖቱ በተዋሕዶ ድርድር የማያውቀው መምህር ደረጄ ነጋሽም ዕጣው ደርሶት መታፈኑ ተገልጿል። ቤተሰቦቹ ፍለጋ ላይ ቢሆኑም እስከአሁን እኔ ጋር ነው የሚል ተቋም እንደሌለም ነው የተገለጸው።

"…በሌላ ዜናም በደብረ ከርቤ ግሸን ማርያም፣ በደብረ ሮሀ ቅዱስ ላሊበላ ራሳቸው ጠላ ጠምቀው፣ ዳቦ ደፍተው፣ እንጀራ ጋግረው፣ ራሳቸው ቆመው ነዳያንን በማብላት የሚታወቁትና በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የታላቁ የአርበሐራ መድኃኔዓለም ገዳም አባት የሆኑት አባ ገብረመድህን አበበም ያለፈው አርብ ለሥራ ጉዳይ አዲስ አበባ መጥተው ለገጣፎ አካባቢ የመንግሥት ኃይሎች ነን በሚሉ አካላት ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ እስከአሁን የት እንዳሉ እንዳልታወቀም ተሰምቷል።

• ማነህ ባለ ሳምንት…?
የግድያ እና የአፈና ዜና…!

"…በፎቶው ላይ የሚታዩት ቄስ ዮሐንስ ግርማ የተባሉና በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ሀገረ ስብከት በሸገር ሀገረ ስብከት የዓለም ገና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ካህን ባለፈው ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ለአገልግሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ላይ ሳሉ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ደጃፍ ላይ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ በተባሉ ኃይሎች በጩቤ ተወጋግተው መገደላቸውን ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ ዘግቧል።

"…በዚያው በሸገር ሲቲ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በሚያስተዳድሩት ሀገረ ስብከት የቦሌ አራብሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም የስብከተ ወንጌል ሓላፊ እና የአንድ ልጅ አባት የሆኑት መምህር ብርሃነ መስቀል የካቲት 16/2017 ዓም ምሽት 4:00 ሰዓት ላይ በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ ምንም ዓይነት መለዮ ባልለበሱና የፖሊስ ፓትሮል በያዙ በቁጥር ስምንት በሚሆኑ አፋኞች ታፍነው የደረሱበት ከጠፋ እነሆ አምስት ወር እንደሆናቸው ተነግሯል።

"…በተያያዘ ዜና በዛሬው ዕለት ከሥራ ቦታው የታፈነው መምህር ደረጀ ነጋሽ (ዘወይንዬ) ከዜናው መበተን በኋላ በስተመጨረሻ ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ በሚገኘው የእስረኞች ማቆያ ውስጥ እንደሚገኝ የመረጃ ምንቼ አድርሰውኛል። የእስሩም ምክንያት መምህሩ በጤና ባለሙያዎቹ የደሞዝ ጥያቄ ዙሪያ በሠራው ቪድዮ ምክንያት በጠቅላይ ሚንስትሩ በአቢይ አሕመድ ቀጥተኛ ትእዛዝ ምክንያት ለምርመራ መወሰዱ ነው የፖሊስ ምንጮቼ የገለጹልኝ።

"… የሰኔ የደም ግብርም ያለእንከን እየተፈጸመ ነው። ከኦሮሚያና ከሸገር ሲቲም ካህናት መነኮሳትም እየጸዱ ነው። አቡነ ሳዊሮስ እና አቡነ ዲዮስቆሮስም ሥራቸውን አገዛዙን ደስ በሚያሰኝ መንገድ እየፈጸሙ ይመስላል። የኔታ ይባቤም እስከአሁን ድረስ አልተፈቱም። እዚያው ባሕርዳር መኮድ ጨለማ ቤት እንደታሰሩ ነው።

• ማነህ ባለ ሳምንት…?
"…እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? መዝ 25፥12

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
የሰማእትነት ዜና…

"…በሶሪያ ደማስቆ በቅዱስ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሥርዓተ ቅዳሴ ላይ በነበሩ የሶርያ የግሪክ ኦርቶዶክስ አማኞች ላይ የሶሪያ ጽንፈኛ የእስልምና አሸባሪዎች በፈጸሙት የአጥፍቶ መጥፋት የቦንብ ጥቃት ወደ 25 ያህል ምእመናን፣ ካህናት እና ዲያቆናት ሕፃናት ጭምር ሲሞቱ ወደ 80 ያህሉ ደግሞ ቆስለው ወደ ሆስፒታል ገብተው ህክምና በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ከሥፍራው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

"…ወዲያው ነው የአንጾኪያው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኤፍሬም ፪ኛ እና በዱሊያ የማር ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ፲ኛ በደማስቆ ዱሊያ አካባቢ ወደሚገኘውና ጥቃቱ ወደደረሰበት የቅዱስ ኤልያስ ቤተክርስትያን በመሄድ ለሞቱት ጸሎተ ፍትሃት፣ ለቆሰሉትና በህክምና ላይ የሚገኙትን ደግሞ በሆስፒታል በመሄድ ሲያጽናኑ፣ ሲያበረቱና ሲጸልዩላቸው እንዳረፈዱ የተነገረው።

"…በኢትዮጵያ ይሄ ይናፍቅህሃል። በዝቋላ ለታረዱ አባቶች የቤተ ክርስቲያኒቱ ቴሌቭዥን ሳይቀር የሀዘን መግለጫ እንኳ የሰጠው አሁን ከደቂቃዎች በፊት ነው። በሸገር ዙሪያ አቡነ ሳውሮስ ሀገረ ስብከት እየታረዱ ስላሉት ካህናት የተነፈሰ የለም። የኔታ ይባቤ ታፍነው አቡነ አብርሃም፣ አባ ገብረ መድህን ታፍነው አቡነ ቀለሜንጦስ ትንፍሽ አላሉም። የቲክቶክ ሐዋርያቱ እነ አኬም እንኳ የዝቋላው እርድና ጨፍጫፊ ሳይታያቸው የሶሪያውን አራጅ እስላም ጠቅሰው ሲወበሩ እያየሁ ያሁኔያ… ለማንኛውም የሰማዕታቱ በረከታቸው ይደረንብን…!

"…የዘማሪት ዮርዳኖስ ደረጀን ጉዳይ በተመለከተ ሓሳቤን በነገው ዕለት አቀርባለሁ። የኔታ ይባቤ እስከአሁን እዚያው መኮድ ናቸው፣ አባም እስከአሁን የትእንዳሉ አልታወቀም። ደረጄ ዘወይንዬም ፍርድቤት አልቀረበም እንጂ ሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ እንደሚገኝ ታውቋል።

• ምኑን አረፍኩት ግን…?
• ስለ የኔታ ይባቤ
     አጭር መረጃ

"…በእነ ዳንኤል ክብረት እልህ፣ በእነ ፓስተር ምስጋናው አንዱዓለም ጉትጎታ ዘመነ ካሤን ትነግሣለህ ብለው የቀቡት እርሳቸው ናቸውና እርሳቸውን ይዘን አስረን ስናበቃ የኔታ ለእነ አርበኛ ዘመነ ካሤ ደውለው ትግሉን እንዲያቆሙ እናደርጋለን በሚል የፌደራሉ አገዛዝ የኦሮሙማው ብልጽግና መከላከያ ሠራዊቱን ልኮ ከገዳማቸውና ከጉባኤ ቤታቸው ወስዶ ባህርዳር መኮድ ግቢ እንዳሰራቸው መግለጼ ይታወሳል።

"…የኔታ ይባቤን እነ ዳንኤል ክብረት ወደ አዲስ አበባ መጥተው በዚህ ምርመራ እንዲፈጽማባቸው አዘው ነበር ቢባልም ከመካከለኛው እስከ ከፍተኛው አመራር ድረስ ያሉት የብአዴን አመራሮች ሂደቱን በመቃወማቸው ምክንያት ሊቁ ወደ አዲስ አበባ ሳይላኩ ቀርተዋል። በመሃልም የሀገሬው ሕዝብ በግልጽ ሳይፈራ፣ ሳይሳቀቅ በሰላማዊ ሰልፍ ብልፅግናን "አባታችንን በአስቸኳይ ልቀቁልን በማለት እስከመጠየቅ ደርሷል።

"…በመጨረሻም የአገው ተወላጆች የሆኑ የአገው ሸንጎ አባላት ሊቁን እንዲከሱ ከላይ ከፌደራል ጫና የተደረገ ቢሆንም የአገው ሸንጎ አባላቱም በዚህ ጉዳይ ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ነው የተነገረው። በመጨረሻም ከቤተ ክህነቷ በቀር ሕዝቡ ውስጥም ከውጭም የኔታ ይፈቱ የሚለው ጥያቄ እየበረታ በመምጣቱ የክልሉ ብልጽግና ብአዴን ከፌደራል እጅ ተቀብሎ ሊቁን ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለምርመራ በሚል በፓሊ እና ጋምቢ መሃል በቀበሌ 12 በሚገኘው 2ኛ ጣቢያ አስገብተዋቸዋል።

• ይልቅ አይበጃችሁም እና ሊቁን ያለምንም ቅድመ ሆኔታ ልቀቋቸው።

• እኔማ ምኑን አረፍኩት…?
😂😂😂

• ደኅና እደሩልኝ
"…ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ ደግሞ፡— የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል። 2ኛ ጴጥ 2፥22

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
2025/07/05 08:49:11
Back to Top
HTML Embed Code: