👆④✍✍✍
6ኛ፦ የአፋጎ መሪዎች ሃይማኖተኛ ወታደር እንዳዘዙት አይሆንም በሚል መርህ ታች ያለውን የፋኖ አባል እምነትም ሕይወትም እንዳይኖረው እየሠሩበት ነው። እነአስረስ በደንብ የቀረቡትን የብርጌድ መሪ ሴት እስከ መጋበዝ ድረስ ያደርጉታል። ተዋጊው ወታደር ትምህርት እንዳያገኝ በተለያየ መንገድ አጥረው ይይዙታል። የፖለቲካ መኮንን ተብለው እየዞሩ ያስተምሩ የነበሩትን ሳይቀር አስረስ መዓረይ ወዲያው ነው ያስቆማቸው። "ወታደር አድርግ አታድርግ እንጂ ትምህርት አያስፈልገውም" በማለት ነው ለምን ብለው እንዳይጠይቁ፣ እንዳይማሩ፣ እንዳያውቁ ያደረጓቸው። በተለይም ለሃይማኖቴ፣ ለማዕተቤ ብሎ የወጣውን ስለሚፈሩት በሩቁ ተሸማቆ እንዲኖር ያደርጉታል። ፋኖ ዮሐንስን ጨምሮ የተገደሉት፣ የተወገዱት ምሑራን ፋኖዎች፣ ቀለም ገብ ፋኖዎች በሙሉ ባለማዕተብ የተዋሕዶ ልጆች ናቸው። ከጠጪ፣ ከሠካራም፣ ከቅባቴና ከጴንጤዎቹ አመራሮች እስከአሁን እንኳን ሊሞቱ፣ ሊገደሉ እንቅፋት ጭምር የመታቸው የሉም።
7ኛ፥ ከክፍለ ጦር ጀምሮ እስከ ብርጌድ ሻለቃ ድረስ በየጊዜው ሪፎርም በማድረግ በመገለባበጥ ያማስሉታል፣ የትግሉን ሥነ ባህርይ የለመደው ለምን ብሎ መጠየቅ እንዳይችል አርፎ እንዲቀመጥ ያደርጉታል። በአዲስ የተሾመውም የላይኛውን እያየ እንዳያወርዱት በሥጋት ዝም ጭጭ ብሎ የመሪዎችን ፎቶ እየተቀባበለ "ጀግናው፣ ሙሴያችን፣ ቶማስ ሳንካራችን፣ የትውልዱ መሪ፣ የእኛ ባትሆን ኑሮ፣ አንተኮ ትለያለህ.."እያለ የውዳሴ መአት ሲያወርድ ይኖራል። ልብ ሊባል የሚገባው ከላይኛው መሪዎች ግን ሪፎርምም ግምገማም ተደርጎ አያውቅም። አንድ የብርጌድም ሆነ የክፍለ ጦር መሪ ዕቅድ ሳይኖረው፣ ሥልጠና ሳያገኝ፣ ክትትል ሳይደረግለት ያጥፋ አያጥፋ በምን ይለካል? የሚመጣውም እንዲሁ ነው። በቅንነት ለፊፎርም ሥራ የሚደክሙ ሰዎች ግን ቅን ሓሳባቸውና ቁርጠኛ ድካማቸው የሚዘነጋ አይደለም።
8ኛ፦ ዐማራዊ አንድነቱ ሁለት ሦስት ጊዜ እንዳይሳካ ያደረጉት የአፋጎ መሪዎች ናቸው። ለምን ብሎ የሚጠይቃቸው አባል እንዳይኖር በሚድያ አፎቻቸው በኩል አፉን ለማዘጋት ይሞክራሉ። የውስጥ ሥራችንን እስክንጨርስ ድረስ ጄነራል ተፈራ ማሞ ለ6 ወር ይምራን፣ ከ6 ወር በኋላ አርበኛ ዘመነ ካሤ ይረከበው ብለው ፊርማቸውን ካኖሩ በኋላ በውጭ ያለው ቀጣሪያቸው በፍጹም አይደረግም በማለቱ ስምምነቱን ትተነዋል ብለው ራሳቸው ያመጡትን ራሳቸው ያሮጡት እነ አስረስ መዓረይ እና አርበኛ ዘመነ ካሤ ናቸው። አሁን ደግሞ ከጎንደር፣ ከሸዋ እና ከወሎ ጋራ አንድነቱ ካልተሳካልን ከህወሓት፣ ከጉምዝ ነጻ አውጪ እና ከኦሮሞ ነጻ አውጪው ከኦነግ ሸኔው ከጃልመሮ ጋራ ሁነን አንድ የስምምነት ድርጅት ፈጥረን መጓዝ አለብን ብለው ወዲያ ወዲህ እየተደዋወሉ በመላላጥ ላይ ናቸው። አንዳንዳን የኦነግና የወያኔ ሰዎች በግልጽ ከአፋጎ መሪዎች ጋር መደዋወል መጀመራቸውም ነው የሚሰማው። ከጎንደር፣ ከሸዋና ከወሎ ዐማራ ይልቅ እንዴት እነዚህ ሊቀርቧቸው እንደቻሉ ፈጣሪ ይወቀው።
"…ተመልከቱ ጎንደርን "ሞዐ ተዋሕዶ የሚል ስም ሰጥተው ነው የሚወቅጡት። እነ ፓስተር ምስጋናው አንዷለም፣ እነ አያሌው መንበር ሁላ በዚህ ስምም ሆነው ነው ጎንደርን የሚወቅጡት። ወሎን ደግሞ ቲም ገዱና ምዐ ተዋሕዶ የሚል የዳቦ ስም ሰጥተው ነው የሚወርዱበት። ከገዱ አንዳርጋቸውና ከስብሀት ነጋ ጋር፣ ከጃዋር መሀመድም ጋር ቁጭ ብለው የተወያዩት እነርሱ ሆነው ሳሉ ወሎንና ጎንደርን ላም ባልዋለበት ኩበት ካልለቀማችሁ ብለው ፍዳ ያበሏቸዋል። ሸዋን ደግሞ በእስር ቤት እስኳድ (በዶክተር ወንድ ወሰን) ፈርጀው ዋይ ዋይ እያሉ ነው። ደፍራችሁ ተወያዩ።
9ኛ፥ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ወሳኝ እስትራቴጅስት አመራሮች ከሚባሉት መካከል እነ ፓስተር ተሰማ ካሳሁን የአብን አመራር የነበረ እና አባቱ ከአቢይ አሕመድ ጋር በአንድ የጸሎት ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ፣ እሱም የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አማኝ ወጣቶች ሊቀመንበር እንዲሆን ከታጨ በኋላ ወደ ዐማራ ፋኖ በጎጃም ይቀላቀል ዘንድ በተመስገን ጥሩነህ ተልኮ ጎጃም የከተመውና በብሔራዊ ደኅንነት መሥሪያ ቤት ይሠራ በነበረው ፓስተር ዳዊት መሀሪ ናቸው። ለእነዚህ ደግሞ ከብልፅግና ወንጌል የተሻለ የጌታ መንግሥት የላቸውም። ባለፈው በበቋራ ቃል ኪዳን ወቅት ተሰማ ያለውን ሰምታችኋል "በዚህ 6ወር ሥራ እንሠራበታለን አንድነቱን እንቢ በሉ"ሲል የነበረው ለዚሁ ዓላማ ነበር። በጎን "እኔ የአብን መስራች ነበርሁ አብንን የሸጡብን ጎንደሬዎች ናቸው ዛሬም ከጎንደር ጋራ አንድ ብንሆን ትግሉን ይሸጡብናል፣ እንሁን ከተባለም እንኳ ወሳኝ ወሳኝ የመሪነት ቦታዎችን መያዝ ያለብን እኛ ጎጃሞች ነን" በማለት ብዙ ሰዎችን ሸውዶና አሳምኖም አንድነቱ እንዲቀር አድርጓል። ጎጃም አሁን በይፋ ከአፋብኃ እንደወጣ ይቆጠራል።
10ኛ፦ በማርሸት እና በአስረስ በኩል የጎጃም ዳብል ኤጀንት ባለሀብቶች አሉ። ብአዴኖች እነ ተመስገን ጥሩነህ በሚረጩት ገንዘብና ከፋፋይ አጠራጣሪ መረጃ ምክንያት አሁን የጎጃም ፋኖ ትልቅ አደጋ ውስጥ ነው ያለው። ይሄ ቲም ማስወገድ ያለበትን ያስወግዳል መጥቀም ያለበትን ይጠቅማል። ዐማራን ነጻ የማውጣት አይደለም ዐማራ የመሆን ዕድል የለውም። ለሚፈልጉት አስወጋጅ ቲምና ብርጌድ ዲሽቃም፣ ስናይፐርም፣ ብሬንም ተተኳሽም ገዝተው ያቀርባሉ። በማርሸት በኩል ብቻ አንደኛው ባለሀብት እስከ አሁን የተለቀቀው ብር 135 ሚልዮን ብር መድረሱን ነው የሰማሁት። ይሄ ካራሱ ከማርሸት የተገኘ መረጃ ነው። ማርሸት እንደሚታወቀው ይቅማል፣ ያጨሳል፣ ይጠጣል፣ ጋንጃ ይስባል ሲመረቅን መረጃዎችን በሀላል ይናገራል። ይሄ ሁሉ ገንዘብ ለፋኖ ትግል የዋለ ሳይሆን ለትግል ማኮላሻ የዋለ ነው። በሌሎች በኩል ምን ያክል ብልጽግና ገንዘብ እንደረጨ ይሄንን ተከትሎ ማሰብ አይከብድም። ነገርየውን አቅልላችሁ እንዳትመለከቱት።
11ኛ፥ እውነት ለመናገር አርበኛ ዘመነ ካሴ የአስረስ መዓረይን ያህል ብስል ፖለቲካ ዐዋቂ አይደለም። እንዴት እንደሚመቱት እና እየመቱት እንደሆላም እንኳ ብዙም ዐያውቅም አይረዳውምም። አርበኛ ዘመነ ካሴ አንደበተ ርቱዕ ነው። በዚህም ተሰጥኦው ምክንያት መናገር እና መቀስቀስ ይችላል እንጂ እስትራቴጅስት ፖለቲከኛ ግን አይደለም። ከአጃቢዎቹ መካከል የተሻለ ደህና አማካሪ እንኳ የለውም። እነ አስረስ መዓረይ የአርበኛ ዘመነ ካሤን ሥነ ልቡናውን በደንብ ስላጠኑት ከላይ ከላዩ በአጃቢዎቹ በኩል ፎቶ እያስነሱ አንተኮ ትለያለህ እያሉ ይፖስቱለታል። እሱም እንደ ሚወዱት አምኖ ይኖራል። የዐማራው ንጉሥ አንተነህ የሚል ቲሸርት ሳይቀር አሠርተው አምጥተው አልብሰው ፎቶ አንስተው ይፖስቱታል። King የሚል ቲሸረት ገዝተው አምጥተው ወንዝ ውስጥ አቁመው ራሳቸው በሌላ ገጽ የውዳሴ ኮሜንት እየጻፉ እሱን ለማስደሰት ጥረት ያደርጉለታል። የዘመነን የዋህነት ተጠቅመው ብዙ ጊዜ ማኖ እያስነኩት ነው። ለትልቅ የተባለውን ዘመነን ወደ ትንሽ እንዲወርድ እያንደረደሩት ነው። ፈጣሪ ይሁነው። እኔ ራሴ እኔና ዘመነ በግል፣ በምስጢር ያወራነውን፣ የነገረኝን እያሰብኩ እሰጋለታለሁ።
12ኛ፥ በመጨረሻም ሁልጊዜ ከገንዘብ ለቀማ ስር፣ ከሴት ቀሚስ ስር፣ ከውስኪ ስር፣ በፍየል ቁርጥ ሥጋ ስር፣ ፎቶ እየለቀቁ ከማያዩት ከኮሜንት ውዳሴ ስር የሚልከሰከስ የዕዝ መሪ ዐማራን አይደለም መንደሯን ነጻ ማውጣት ይቅርና ራሳቸውም ከከባድ ሱስ ነፃ የሚያወጣቸው ያስፈልጋቸዋል። እነዚህ ጉደኞች የጎጃም ዐማራን መርተውና አዋግተው አራት ኪሎ ያደርሱናል ብለው ተስፋ…👇 ④✍✍✍

👆⑤ ✍✍✍ …የሚያደርጉ ፋኖዎች ካሉ በጊዜ መንቃት አለባቸው ባይ ነኝ። ይሄንን የመሰለ ታላቅ የበላይ ዘለቀ ልጆች ኃይል በማይመጥኑት ፀረ ዐማራ ብአዴንን በሚያስንቁ ሰዎች መመራት ስለሌለበት ዕዙ ሪፎርም ያስፈልገዋል! ብለው መጠየቅና ማስተካከል አለባቸው። እነ ማርሸት፣ እነ አስረስ፣ እነ ተሰማ የሚመሩት ድርጅት አይደለም ለዐማራ፣ አይደለም ለጎጃም ከጎጃምም ራሱ ለጎንቻም ሆነ ለሜጫም አይጠቅምም።
"…በየትኛውም መድረክ ቅቡልነታቸው የወረደው እነ አስረስ መዓረይ አሁን በሕዝብም፣ በሠራዊቱም ዘንድ ተወዳጅ በሆነው በሻለቃ ዝናቡ በኩል ለመገለጥ ይላላጣሉ። ደጋ ዳሞት ከትናንት እስከዛሬ ድረስ ያልተቋረጠ ተጋድሎ እያደረገ ያለ አካባቢ ነው። ምሥራቅ ጎጃምን ለብአዴን አስረክቦ በምዕራቡ የጎጃም ክፍል የከረመው የእነ አስረስ መዓረይ ቡድን አሁን የእነ ዝናቡን ተጋድሎና ጀግንነት ተጠቅሞ የፕሮፓጋንዳ ሥራውን ይጀምራል። እነ መሳይ መኮንን፣ እነ ደረጄ ሀብተወልድ፣ እነ ፋሲል የእኔዓለም አሁን ሻለቃ ዝናቡን በቃለ መጠይቅ ልቡን ያፈርሱታል። ለብልጽግና ግብአት የሚሆን መረጀ አስፈልፍለው ያስወጡታል። ጎጃም ይዋጋል፣ ይሞታል ይገድላል፣ እዚያው ጭቃውን ሲያቦካ ይኖራል። ዐማራን አሸናፊ የሚያደርገው አንድነት ብቻ ነው። ትግሬ እንኳ 17 ዓመት ታግላ ማሸነፍ ሲያቅታት ኢህአዴግ ብላ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ካሳተፈች በኋላ ነው ጎንደርን ወሎና ወለጋን አልፋ ወደ መሃል ሀገር የገባችሁ። እናርጅ እናውጋ ላይ ብቻ ስትታኮስ ውለህ ብታድር የኦሮሙማው አገዛዝ ምኑ ነው የሚጎዳው? ሁለት ሚሊሻ ማረክን፣ አንድ ልዩ ኃይል ገደልን፣ ሦስት መከላከያ ስበን አስከዳን ብለህ ዜና ሠርተህ ስታበቃ እግረ መንገድህን የአረመኔው ብራኑ ጁላ ጦር በጎጃም እንዲህና እንዲያ ቦታ ላይ ትምህርት ቤት አወደመ፣ ጤና ጣቢያ አቃጠለ፣ ገበሬ ገደለ፣ መንደር አቃጠለ ብለህ ማለቃቀስ ፋርነት ነው። የራስህን አባት ሚሊሻ ገደልህ ፎክረህ፣ 3 መከላከያ ስቤ አስከዳሁ ብለህ ፎክረህ ስታበቃ ወደምኩ፣ ተቃጠልኩ ብሎ ማላዘን አይነፋም። ኦሮሙማው እንደሆነ ትግሉ ዓባይን እስካልተሻገረ ድረስ እዚያው እንደ ጋዛ እያነደደህ፣ እያደቀቀህ፣ ትምህርትና ጤና ጣቢያ እያወደመብህ፣ በበሽታም፣ በጥይትም እየፈጀህ በቢኖር ለእሱ ደስታው ነው። ከፈለገም እናትህንና አባትህን ሰልፍ አስወጥቶ እያስወገዘህ መሳቂያ መሳለቂያ እያደረገህ ይኖራል። የምትጎዳው አንተና ሕዝብህ ናቸው። አሁንም ስርነቀል ግምገማ ተካሂዶ የጎጃም ፋኖ አመራሮች ወደመስመር ካልመጡ በስተቀር የጎጃምም፣ የዐማራም መከራ አያበቃም።
"…እኔ የምጽፈውም፣ የምናገረውም ሲያነቡትም ሆነ ሲሰሙት ይደብራል፣ ይመርራል፣ ይጎመዝዛል። ውዳሴ ከንቱ፣ የውሸት ሰበር ዜና፣ መሬት ላይ የሌለ የድል ዜና ሸላይ በላዩ መጋት የለመደ ጆሮ እንደኔ ዓይነቱን ኮመጠጥ ያለ ራስህን ለካህን አስመርምር፣ ንስሀ ግባ የሚል ጠንከር ያለ ቃል መስማት ያሳምምሃል። ራስህን በራስህ ማርካት የለመድክ አንተ ሳሙናህን ስቀማህና ሚስት አግብተህ በተፈጥሮ መንገድ ተደሰት፣ ዘርተካ ስልህ ልማድህ ትዝ እያለህ ታለቃቅስብኛለህ፣ ትውርድብኛለህ፣ ትሰድበኛለህ። መፍትሄው የእኔ መንገድ ነው። አቢይ አሕመድ ሟች ወታደር አላጣም። የደቡብን ሕዝብ መቀነስ ስለሚፈልግ ከኦሮሚያ እንኳ ሰው ቢያጣ ከደቡብ በገፍ አምጥቶ ይለቅብሃል። ይቀጠቅጥሃል። ያወድምሃል። ከደቡብ እንኳ ሰው ቢያጣ በራሱ በአማራው ሚሊሻ፣ በቅማንትና በአገው ሸንጎ ታጣቂዎች እርስ በእርስ ያፋጅሃል። አንተ ነፃ ባላወጣኸው ከተማና መንደር ውስጥ ያሉትን ሕዝብ በሙሉ የሚያዝባቸው አገዛዙ ነው። ተነሥ፣ ተኛ፣ ታጠቅ፣ ዝመት የሚለው አገዛዙ ነው። ሰልፍ ውጣ፣ ፋኖን አውግዝ ቢለው ከመታዘዝ ውጪ ሌላ ምንም ማድረግ አይችልም። ከሠልፉ ማግስት አገዛዙ ዐውቆ ወደ ኋላ ያፈገፍግና ፋኖ ወደ ከተሞቹ እንዲገባ ያደርጋል። ፋኖም ከተማ እንደገባ ባለፈው ሰልፍ የወጣው ማነው ብሎ የገዛ ሕዝቡን ያስራል፣ በገንዘብ ይቀጣል፣ የሚሊሻና የአድማ ብተና ሰዎችን ደግሞ ይገድላል። ማን ተጎዳ? አቢይ አህመድ? ብራኑ ጁላ? በፍጹም። የምትጎዳው አንተ ነህ። የአንድ ሚሊሻ ሞት ብዙ ቤተሰብ ያለ ወላጅ ነው የሚያስቀረው። አሁን ብዙ ወንዶች በዐማራ ክልል እየሞቱ ነው። መሬት ጦሙን እያደረ ነው። የፋኖ አመራሮች ራሳቸውም፣ ቤተሰቦቻቸውም ኑሮአቸውን ባህርዳር፣ ማርቆስ፣ አዲስ አበባ፣ ዱባይ፣ ኡጋንዳ፣ አውሮጳ፣ አሜሪካና ካናዳ ዘጭ ብለው እየኖሩ ነው። እየተጎዳ ያለው ሕዝቡ ነው። አምርረህ ተሟገት። ፕሮፓጋንዳው ይብቃ። ህመምህን ተናግረህ ፈውስ የሚሰጥህን መድኃኒት በቶሎ ውሰድ። የእነ ፕሮፌሰር ሀብታሙ ምክር ጎጃምን በአናቱ ነው የሚተክለው። ብትፎክር፣ ብትሸልል፣ እሱ መፍትሄ አይሆንም። መፍትሄው ከጎንደር፣ ከወሎና ከሸዋ ወንድሞችህ ጋር አንድ ሆነህ ስትታገል ነው። የሚዘረፈው ሲጠፋ፣ ገበሬው ምርቱ ሲቀዘቅዝ ገንዘቡ እንጀራ አይሆንህም እኮ ጎበዝ። ዘንድሮ ገበሬው ማዳበሪያ አላገኘም። እናም መጪው ጊዜ ይከብድብሃል።
• እስከመስከረም እዚያው ጎጃም ነኝ። ከጎጃም አልወጣም፣ ከጮቄም አልወርድም። የእውነት ይሁን የውሸት ወያኔ ከሻአቢያ ጋር ሆና ለውጊያ እየተዘጋጀች መሆኗ እየተነገረ ነው። በጦርነቱ ተጎጂው አሁንም ዐማራው ነው። በዚህ ጊዜ ዐማራ አንድ ሆኖ ተዘጋጅቶ እንዳይጠብቅ ደግሞ የአፋጎ አመራሮች ከወያኔም በላይ፣ ከኦሮሙማውም በላይ ጠላት ሆነው ተሰልፈዋል። የትግሬ ኮሎኔሎችን፣ አዋጊዎችን ፈትቶ የላከው የአስረስ መዓረይ ቡድን ዐማራ አንድ እንዳይሆን ሽብልቅ ነው የገባበት። ነገርየው ከባድ ነው። ከ5 ሴቶች 4ቱ ጥቁር ከል የኀዘን ልብስ የለበሱበት የጎጃም ዐማራ ትግል በጥቂቶች አፈር ደቼ እየበላ ነው። ዝናቡ መሳይ ጋር ሄዶ በግድ በሚመስል መልኩ የሰጠውን ቃለመጠይቅም አይቼዋለሁ። ዝናቡን በሚገባ ዐውቀዋለሁ። የገባበትና የከረሙበትንም ዐውቃለሁ። ይሕቺን ክረምት በሥልጠና ሰበብ አሳልፈው ዐማራን በበጋው ደቼ ሊያበሉት ነው የሚፈልጉት። ይሄ ደግሞ ለኦሮሙማውም የተመቸ ነው። በእኔ በኩል ለዛሬ ይህን ጽፌአለሁ። እናንተ ደግሞ አንብባችሁ ስትጨርሱ የራሳችሁን ሓሳብ ጻፉ። በጨዋ ደንብም የወያዩ። አመሰግናለሁ።
• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!

መልካም…
"…ከወትሮው ዛሬ ይሻላል… ወደ 20 ፍሬ የሚደርሱ ሰዎች 😡 ጓ ብው ብለው አይቻቸዋለሁ። እነዚህ ሰዎች የርእሰ አንቀጹ ተቃዋሚዎች ናቸው ማለትም አይደለም። ባነበቡት ነገር ብስጭት የገባቸውም ሰዎች ይሄን የብስጭት፣ የንዴት 😡 ኢሞጂ ስለሚጠቀሙ ነው።
"…ለማንኛውም እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ዛሬ በጻፍኩት ርእሰ አንቀጽ ላይ በጨዋ ደንብ መወያየት እንጀምራለን። እየቆየሁ ስመጣ አገዛዙ እጅ ሰጥተውት የነበሩትን እነ መንግሥቱን እጃቸውን ጠምዝዞ እስከ አፍንጫቸው ድረስ አስታጥቆ ወደ ጫካ መመለሱን ካልሰማችሁ ሰሞኑን እነግራችኋለሁ። ሌላው አንደጊዜ የተከበሩት አቶ ክርስቲያን ታደለ ጀምረውት የነበረውና በጊዜ የተቃጨው ጎንደርና ጎጃምን የሚያቃቅር አጀንዳም በእነ አስረስ በኩል እንዲንቀሳቀስ ተደርጎ ሰሞኑን ጎንደርና ጎጃም የሚነታረኩበት አጀንዳ ይለቀቃል። መጠበቅ ነው።
• ሓሳባችሁን መስጠት ጀምሩ። እኔም ቁጭ ብዬ ማንበቤን እቀጥላለሁ። ጀምሩ…✍✍✍ ጻፉ።
• ማስጠንቀቂያ…
"…ተቃውሞ እንኳን ቢኖራችሁ በጨዋ ደንብ ሓሳባችሁን ግለጹ። መብታችሁ ነው። በርእሰ አንቀጹ ብትናደዱ እንኳ በመሳደብ ሳይሆን በጨዋ ደንብ በመተንተን ተቃወሙ። ይሄ በጣም ተላላቅ ሰዎች የሚሳተፉበት ገፅ ስለሆነ የመንደር ዱርዬ ጋጠወጥ ስድብ በገጼ አይስተናገድም። ብስጭታችሁን ዋጥ አድርጋችሁ ተሳተፉ። ባለጌ ይቀሰፋል። ሰምታችኋል!

"ርእሰ አንቀጽ"
"…አቢይ ውሸታም ነው። ብልፅግና ጨፍጫፊ ነው። ፓርላማው እንቅልፋም ነው። መከላከያው ጨፍጫፊ ነው። አገዛዙ ፀረ ሕዝብ፣ ፀረ ሰው፣ ፀረ ሃይማኖት፣ ፀረ ባሕል፣ ፀረ ኢትዮጵያ ነው ወዘተረፈ ብሎ እሱ ፓርላማ ቀርቦ በተበጠረቀ ቁጥር፣ ራሱ ጠያቂ ራሱ መላሽ በሆነበት የቴሌቭዥን መስኮት ዲስኩሮቹ በተሰራጩ ቁጥር፣ አሰፍስፎ ጠብቆ እሱን በማሳጣት ለእሱ ግብረ መልስ ለመስጠት በሚል ሰበብ፣ ሱፍና ከረባት ገጭ አድርጎ፣ በቴሌቭዥን፣ በዩቲዩብ፣ በቲክቶክና በፌስቡክ ቀርቦ አቢይ እንዲህ አለ፣ እንዲህ ዋሸ፣ ቀጠፈ ብሎ ሲተነትኑ መዋል ማደር እንዴት ያለ ሰገጤነት፣ ምን የሚሉት ዥልጥ ጅልነትስ ነው? እንዴት ሰው ሰባት ዓመት ሙሉ የአንድ በሃላል ማንነቱ በዓለሙ ሁሉ የታዋቀን፣ ሁሉ ሰው የተረዳውን ሰው የተገለጠ ውሸቱን መልሶ መላልሶ ችክ እስኪል ድረስ ሲተነትን ይኖራል? ጥቅሙ ነው ያልገባኝ።
"…ይሄን ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሥርዓት ገርስሶ፣ ለውጥም አምጥቶ የተሻለ ሥርዓት፣ እውነተኛ ሕዝባዊ መንግሥት መመስረት ነው የሚሻለው ወይስ የአያልቄን የአባ ሳክሶን የሐሰት ዲስኩር በየደቂቃው ልተንትነው ብሎ አየር ይዞ መበጥረቅ ነው የሚሻለው? በቃ ሕዝቡ እኮ ሁሉን ዐወቀ፣ ሁሉንም ተረዳ፣ እንኳን ሰፊው ሕዝብ ይሄን የአገዛዙን ክፋት፣ አረመኔነትና ውድቀት ራሳቸው የአገዛዙ ሚዲያዎች መመልከት በቂ ነው። የአቢይ አሕመድን የማኅበራዊ ሚዲያ የፌስቡክ ገፁን የአስተያየት መስጫ ሰንዱቅ ማየቱ ብቻ በቂ እኮ ነው። ሕዝቡ ምንያህል እንደተጠየፈው፣ እንደናቀው ለማወቅ አይደለም በሰውየው፣ በራሱ ደጋፊ የፓርቲ አባላት፣ በሚዲያ ሠራዊቶቹ በካድሬዎቹ ጭምር ምን ያህል እንደተናቀ መመልከት ይቻላል። እናም ቀባሪ ያጣን አንድ ግለሰብና ፓርቲን በየጊዜው እያነሱ እንዲህና እንዲያ አለ ብሎ ማላዘን፣ እንደ ጋማ ከብት መልሶ መላልሶም ማመንዠክ ጥቅሙ አይታየኝም።
"…ይልቅ ይሄን ሥርዓት ለማስወገድ ጫካ ገብቶ ነፍጥ ያነሣውን አካል በደከመው እያበረቱ፣ ጠንክሮ እንዲወጣም እያበረታቱ፣ ተግዳሮቶቹን በድፍረት እየቀረፉ፣ ሾተላይ ሴረኞቹንም ኮምጨጭ እያሉ እየገሰፁ፣ እየነቀሉም ወደፊት እንዲመጣ ማድረግ ነው እንጂ የምን በሞተ እና ቀባሪ ባጣ አስከሬን ፊት ቆሞ ማላዘን ነው? በለስ ቀንቷቸው ቢመጡ፣ ሥልጣን ላይ ቢወጡ ከአቢይ አሕመድ የባሰ ጨፍጫፊ፣ ዘራፊ የመሆን ባሕሪያቸው ከወዲሁ ፈጥጦ የወጣባቸውና የተገለጠባቸውን እንደ ዐማራ ፋኖ በጎጃም ከፍተኛ አመራሮች ያሉትን ዓይነቶቹን አደብ የሚገዙበትን መስመር ማመቻቸት፣ መፍትሄ መፈለግም እንጂ አቢይ ነዳጅ አወጣለሁ ብሎ ዋሸ፣ ሙፈሪያት ከሚል የጠራችው ቁጥር እና አቢይ አሕመድ የጠራው ቁጥር የተለያየ ነው ወዘተ እያሉ ቁጥር አይፈሬን የሆነን ግለሰብ አስር ጊዜ እኮ አይደለም 7 ዓመት ሙሉ ስሙን እየጠሩ ችክ ምንችክ ብሎ ማላዘን ጥቅሙ ምንድነው? ፐ እገሌ እኮ አቢይን እርቃኑን አስቀረው ብሎ እርቃኑን በቆመ ሰው ላይ ሲንዘባዘቡ መዋልም ልክ አይመስለኝም።
"…አሁን የሕዝብ ጥያቄ እኮ አንተ አክቲቪስቱ፣ አንተ ቦለጢቀኛው፣ አንተ ጋዜጠኛው፣ አንተ ታጋዩ፣ አንተ ተንታኙ ልክ እንደ ሕዝቡ፣ ሕዝቡ የመረረውንና ያንገሸገሸውን ይሄን መርግ ማን ከላያችን ያንሣልን ብሎ የሚያለቅስበትን ጉዳይ መልሰህ፣ መላልሰህ አዲስ ግኝት ያገኘህ ይመስል እንድትዘበዝበው አይደለም። ነዳጅ በሊትር 120 ብር ገባ፣ ምስር በኪሎ 300 ብር ገባ(አሁን ይሄን ከጻፍኩ በኋላ 350 መግባቱን ሰማሁ)፣ አንድ ኪሎ ኮሮሪማ 3ሺ ብር ገባ፣ አንድ ደረቅ እንጀራ 35 ብር ገባ፣ የአንድ ዶላር ምንዛሪ 160 ብር ደረሰ፣ ከአዲስ አበባ ወደ ክፍለ ሀገር በመኪና መሄድ ከባድ ሆነ፣ የቤት ኪራይ ጣራ ነካ፣ ሀኪሞች፣ መምህራን እና የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ በወር 71$ ነው፣ በኑሮ ውድነቱ ምክንያት ፍቺ እየበዛ ነው። ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች እየወደሙ ነው፣ ገበሬው ማረስ፣ ማምረት አልቻለም ወዘተረፈ እያሉ ሀገር ምድሩ የሚያውቀውን፣ በድርጊቱ ተማርሮ መፍትሄ ያጣበትን ጉዳይ ልክ እንደ አዲስ ግኝት ፀዳ ኮስተር ብሎ ከሕዝቡ ጋር መልሶ መላልሶ ማልቀስ እንደ አስለቃሽ ደረት አስመቺ ሴት ሕዝብን ያለምንም መፍትሄ ዋይ ዋይ ማስባል ምን ይሉታል?
"…በዕድሩ ድክመት ምክንያት ቀባሪ አጥቶ ከሞተ የቆየውን የሞተ፣ የገማ፣ የከረፋ አረመኔ ሥርዓት አስር ጊዜ እያነሳህ እንደ ቡና ከምትወቅጠው ከዚያ ይልቅ እየመጣ ስላለው ራብ፣ እየመጣ ስላለው ደም አፋሳሽ ጦርነት፣ እየተበራከተ ስላለው ፍልሰት፣ ስደት፣ ዘረፋ፣ እገታ፣ ጭፍጨፋ አድምቶ መወያየት፣ መምከር፣ ስለ የመብራት፣ የውኃ ዋጋ መናር፣ የገበሬው ማዳበሪያ እጦት፣ የምርት መቀነስ ወዘተረፈ የመፍትሄ ሓሳብ ማምጣት አይሻልም። ጨክነህ ስለ ፋኖ ጎታች፣ ሾተላይ፣ ሰልቃጭ፣ ደፍጣጭ ፋኖ መሳይ ፍናፍንቶች ብትወያይ አይሻልም? ሚዲያን ያህል ትልቅ መሣሪያ ይዘህ ስታበቃ ሁልጊዜ አቢይ ውሸታም፣ ዋሾ ነው እያልክ አየር ከምትይዝ ደፍረህ ይሄን አገዛዝ ሊቀይር ይችላል ብለህ ተስፋ የጣልክበትንና የሕፃን ጨዋታ እየመሰለ የመጣውን የዐማራ ፋኖ ትግል መስመር ስለ ማስያዝ ብትመክር አይሻልም? ይሄ ሥርዓት እንደሁ ፋኖም ባይመጣ እንኳ በራሱ ሽግር መውደቁ፣ ተገርስሶ መውደቁ እንደሁ አይቀርም። ከወደቀ በኋላ ታዲያ እነ ዘመነ ካሴና እነ ሀብቴ፣ እነ ምሬ፣ እነ ደሳለኝ፣ በአንድ በኩል እነ እስክንድር፣ እነ መከታው፣ እነ ሙሀቤ፣ እነ ደረጄ በሌላ በኩል ሆነው አራት ኪሎ ሲጨቃጨቁ ሌላ ደም መፋሰስ ከመከሰቱ በፊት ከወዲሁ እንደ ትልቅ ሰው ተሰባስበህ በጊዜ ብትመክር፣ ብትመካከር አይሻልም?
• 3 :1 ።