• ኧረ ጻፉ…!
"…እስቲ ነገ በዕለተ አርብ ከምስጋናው በኋላ ጦማሪዎች እንዲጦምሩ፣ ጸሐፊያን እንዲጽፉ የሚጎተጉት አጭር ጦማር ወደ እናንተ አደርሳለሁ።
"…በዩቲዩብ፣ በፌስቡክ፣ ወላ በቲክቶክ በለው በቴሌግራም ብዞር፣ ብዞር፣ ብሽከረከር አንድም የሚያከራክር፣ የሚያመራምር፣ የሚያወያይ ጦማሪ ነው ያጣሁ። እግሬ እስኪቀጥን ነው የዞርኩት። የምታውቁ ጠቁሙኝ።
"…በተረፈ እኔ ዘመዴ የእረፍት ጊዜዬን በአግባቡ እየተጠቀምኩ ነው። በዓመት ለሆኑ ቀናት ብቅ ብላ ጥፍት የምትለዋን የአውሮጳ ፀሐይ ቫይታሚን D ን ትተካለች ብለው ስለነገሩኝ ሳታመልጠኝ በብዛት እየወሰድኳትም ነው። 😁 እዚህ ፀሐይ መታኝ አይሠራም።
• ሻሎም…! ሰላም…!

"…ጻፉ እንጂ ጎበዝ…!
"…ምንድነው ይሄ ሁላ ዝምታ፣ ጭጭ ጮጋም ማለት? ኧረ ምንሼ ኖ…? ጻፉ እንጂ! ያውም የሚያሟግት፣ የሚያከራክር፣ የሚያወያይ፣ የሚያነጋግር፣ የሚያረጋጋም፣ ተስፋንም የሚጭር፣ ደሀ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ የሚል፣ ሾተላዮችን፣ ሌቦችን፣ ዘራፊዎችን፣ ነፍሰ ገዳይ ጨፍጫፊ ዘር አጥፊዎችን፣ የጭቃ ውስጥ እሾህ፣ ሱፋጮችን፣ የሳር ውስጥ ኮብራ እባቦችን የሚያጋልጥ ጠንቋይ ቀላቢ አስማተኞችን፣ መናፍቃን ትግል ጠላፊዎችን የሚያጋልጥ ድማሚት የሆነ ጦማር ጦምሩ እንጂ። መረጃ ፈልፍላችሁ እያመጣችሁ፣ ማስረጃም በየዘርፍ በየዘርፉ እያቀረባችሁ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ በትበት በሉ እንጂ። በዩቲዩብ፣ በፌስቡክ፣ በቴሌግራም መንደር ድሮም እንደምታውቁት እግሬ ቀጭን ነው አሁን ደግሞ ጦማሪዎች ካሉ ብዬ ያው እግሬ እስኪቀጥን የውስጥ ዓይኔም እስኪላጥ ድረስ ብዞር፣ ብሽከረከር ወደላይ ወደታችም ብንጦሎጦል ወፍ የለም ሆነብኝ። ምነው? በሰላም ነው…?
"…በአይተ ኢሳይያስ አፈወርቂ "ኦሮሙማ" በሚለውን ቃል መጠቀም ምክንያት ኦሮሙማዎቹ ለምን ከወትሮው በተለየ መልኩ ከዳር እስከዳር እንደተንጫጩ አንድም ሰው የሚነግረን እንዴት ይጠፋል? ዐማራን ነፍጠኛ የሚል ታፔላ ለጥፎበት የኢትዮጵያውያን ሁሉ ጠላት ያደረገው ሻአቢያ ለኦሮሞውም ሆን ብሎ ቀደም ሲል ፍሮፌሰር ሐሰን መሀመድ በመጽሐፍ የፈጠረውን፣ ኤርሚያስ ዋቅጅራ ደግሞ በፌስቡክ ገጹ፣ በኢሳትና በኢትዮ 360 ሚዲያዎች ከመጠን በላይ ፕሮሞት ያደረገውን የጨፍጫፊውን የኦሮሞ ቦለጢቀኞች መለያ ኮድ የሆነውን ኦሮሙማ የሚለውን የዳቦ ስም ጠቅሶ ለምን እንዳንጫጫቸው ጻፉ እንጂ። ነገርየው እኮ ከባድ ነው ጎበዝ። ከነፍጠኛ ወደ ኦሮሙማ…
"…ሰው ተርቧል አይገልጠውም። የሚጽፍ ግን የለም። የሚናገርም የለም። በሰሜን ሸዋም ሆነ በሌሎች ክልሎች ዘንድሮ በኢትዮጵያ ያልታረሰው ጦም ያደረው መሬት ብዙ እንደሆነ እየተነገረ ነው። በጎጃም ገበሬዎች በመንግሥት ትእዛዝ ዘንድሮ በቆሎ እንዳይዘሩ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ፣ ፋኖዎች ደግሞ ማዳበሪያ ከመንግሥት የገዛ ገበሬ እረሽናለሁ በማለታቸው በሚቀጥለው ዓመት ከወዲሁ ምርት እንዳይጠበቅ መደረጉም ነው እየተነገረ ያለው። በተለይ የራቡ ነገር እጅግ የሚያስፈራ እንደሆነ ነው የሚነገረው። ወረርሽኙም ቢሆን ማለትም የዝንጀሮ ፈንጣጣ የተባለው በሽታ ታየ ከተባለበት ከኦሮሚያዋ ሞያሌ በአንደዜ ዘሎ እንዴት መተማና ባህርዳር እንደገባ፣ አዲስ አበባም ጭምር ታይቷል ቢባልም ጮጋ ዝምጭጭ መባሉን ሰምታችሁ የማትጽፉ፣ የማትነግሩን ለምንድነው? ኧረ የምን ዝም፣ ጭጭ ነው? ጻፉ፣ ኧረ ጻፉ።
"…ስለ ቲክቶከር ስመኝ ገብሩ ሻቲ መልበስ አለመልበስ ይሄን ሁላ መቸክቸክ ምኑ ነው የሚጠቅምህ? እነ ልደቱ አያሌው እነ ጃዋር ተጠቃቅሰው ውኃ ስለቸለሱበት ስለ ሐኪሞቹ ዐመጽ ከምን እንደደረሰም ለምን አትጽፉልንም? ስለ እነ አቦይ ስብሐትም፣ ስለ እነ ልደቱ አያሌው አብሮነት፣ ስለ እነ አሉላ ሶሎሞን እና ስለ እነ ጃዋር ጥምረት፣ ስለ እነ መዓረይ ከእነ መከታው እና ከእነ እስክንድር ጋር ለመጣመር አልፎም ለመዋሐድ እየተነጋገሩ ነው ተብሎ ስለሚታማው ነገርም እስቲ ጻፉ። ስለ አፋብኃ አሁናዊ ሁኔታ፣ ስለ የአሩሲና የሐረርጌ ኦሮሞዎች በሰይፍ በገጀራ መጨፋጨፍ፣ ስለ የኦሮሞ እስላሞችና የኦሮሞ ዋቄፈናዎች ቤተ አምልኮዎቻቸውን ተራ በተራ በእሳት እያቃጠሉ፣ ወጣቶችንም በጅምላ እየረሸኑ በበቀል እንዴት እየተወዳደሙ እንዳሆነም ጻፉ እንጂ። እንዴት አንድም ሰው ነፍስ ስላለነው ጉዳይ የሚተነፍስ ይጠፋል? ዞርኩ፣ ዞርኩ፣ ምንም አጥቼ ሲደከመኝ ጊዜና ወደመጠየቁ መጣሁ።
"…የአቢይ አሕመድ ቅቡልነት መቀነሱ ያሳሰባቸው፣ ከመጪው ሐምሌ ነሐሴ ጀምሮ አይኤምኤፍን ለማስደሰት ሲሉ ከሚጨምሩት ታክስ እና ግብር፣ ከወረርሽኙ ጋር ተያይዞ የሚመጣው ክረምት ምስቅልቅል ከወዲሁ ቀድሞ የታያቸው የኦሬክሱ የብልፄ ካድሬዎችና አክቲቪስቶች፣ የብልፅግና መንግሥታቸውን ለማዳን ሲሉ የቅቡልነት ማጣት አጀንዳውን ለማስቀየስ ሲሉነእንደተለመደው መጀመሪያ በገመዳ ሾው በኦሮሚኛ ቋንቋ፣ በገመዳ ሾው አልጮህ ሲል በሰይፉ ሾውና በሌሎች የብልፅግና የአጀንዳ ማስቀየሻ ማሽኖች አማካኝነት የተከፈተውን የ"አይዞሽ ገለቴን" አጀንዳ ተቀላቅለህ ከምትጮህ፣ ከምትነፈርቅ ለምን ስለ አሳሳቢው ሀገራዊ ጉዳይ አትጽፍም፣ አትወያይምም። ጻፍ አልኩህ አንተ። ጻፍ እየመጣ ስላለው አደጋ ጻፍ። በዳይ የተባለው ሰው ድምጹ ሳይደመጥ፣ ሳይሰማ፣ ዘመናዊ የኦሮሞ ፓስተር ተብዬ ጠንቋዮች እንደፈረንጅ ላም አልበው፣ እጥብ አድርገው የጋጧትን ምስኪን ጴንጤ የኦሮሞ ሯጭ ሴትን አጀንዳ ተከትለህ ስትጃጃል የራስህን አጀንዳ እንዳትዘነጋ እየነገርኩህ ነው። ንቃ።
• በነገራችን ታች…
"…እኔ ለጥቂት ጊዜ ከቴሌግራም ጦማር ገሸሽ ያልኩት እረፍት መውሰዴ እንዳለ ሆኖ ከእናንተም ወገን አዳዲስ መረጃዎችን በማስረጃ አስደግፈው ክሽን አድርገው የሚያቀርቡ፣ ግሩም የሆነ አሳማኝ፣ አስተማማኝም የሆነ ጦማር በግሩም አማርኛ ሆሄያትን ጠብቀው፣ ፊዳላቱን በአግባቡ ተጠቅመው የሚጽፉ፣ የፌስቡክም ሆነ የዩቲዩብ ቤታቸውን በር ለውይይት፣ ለሙግት፣ ለክርክርም ክፍት አድርገው ሰዎች ሁሉ በጨዋ ደንብ እንዲተነፍሱ የሚያደርጉ፣ ከእውነት ጋር የቆረቡ፣ ፊት ዓይተው የማያደሉ፣ በመልክ፣ በሃይማኖት፣ በጾታ፣ በዘመዳ አዝማድ አሳበው ሃቅን የማይቀብሩ፣ ለገንዘብ ሟች ነውረኛ ጋለሞታም ያልሆኑ፣ ይሄ እኮ ከዘሬ ነው፣ ያኛው ጓደኛ አብሮአደጌ ነው፣ ወገኔም ነው፣ ቤተሰቤም ነው ብለው ማንንም ከመውቀስ፣ ከመምከር ወደ ኋላ የማይመለሱ፣ ወደኋላም የማይሉ፣ ሁሉን እኩል በእኩል ዓይን የሚመለከቱ፣ የማይም ጥርቅም ጫጫታ፣ የዴየደብ መንጋ የስድብ፣ የካድሬዎች፣ የአቃጣሪ እወደድ ባዮች የዛቻ ብዛት ከእውነት ሚዛናቸው ዝንፍ የማያደርጋቸው፣ ጠንካራም የሆነ የዝሆንም ሆነ የአዞ ቆዳን የተላበሱ፣ ሁል ጊዜም ደሀ ተበደለ ፍርድም ተጓደለ የሚል መርሕ አንግበው የሚንቀሳቀሱ፣ ለማንም ለምንም ሸብረክ፣ በርከክ የማይሉ፣ እምነትም፣ ሃይማኖት ያላቸው፣ ሀገራቸውንና ሕዛባቸውን የሚወዱ፣ አጭበርባሪ፣ ቀጣፊ፣ ዋሾ፣ ዋልጌ፣ ጋለሞታ ያለሆኑ፣ ሱሳም፣ አረቄያም፣ ሆዳም ያልሆኑ፣ ለሁሉም ዜጋ እኩል ሳያበላልጡ የሚጮሁ፣ ድምፅ የሚሆኑ፣ ቀለባቸው ላይክና ሼር ያልሆነ፣ እገሌ ቄስ ነው፣ እገሌም ጳጳስ ነው፣ እገሌ ሼህም ፓስተርም ነው ብለው ፈርተው እውነትን የማይቀብሩ ጦማሪዎች ካሉ እስቲ እኔም ልስማቸው፣ ላንባቸው፣ ልከታተላቸው ብዬ ነው መጥፋቴ። እባካችሁ ካያችሁ ጠቁሙኝ። ዘመዴ እገሌን ተከታተለው ብላችሁ ጠቁሙኝማ። ስሞት ስቀበርላችሁ። እስከዛሬ እኔ ብቻዬን አየሩን ሁሉ ይዤ፣ ሌሎች ይኑሩ አይኑሩ እንኳ ሳላውቅ በዚያ ላይ ቢኖሩም ወደፊት እንዳያልፉ አንቄ የያዝኩ፣ የጋረድኳቸውም ስለመለለኝ እስቲ እኔም ዝም ልበል፣ ካሉም ልከታተላቸው፣ ላነብባቸው፣ ልሰማቸውም ብዬ ነው መጥፋቴ። ግን ወፍ የለም። ጭራሽ የሚጽፉት ቢያጡ ነው መሰል እኔን እና መምሕር ፈንታሁን ዋቄን አጀንዳ አድርገው ጃል ቆቱ ምናምን እያሉ ሲያላዝኑ አያቸዋለሁ። ምስኪን ቅባቴ አገው ሸንጎ እኮ ሲያሳዝን። ከምር።…👇①✍✍✍

👆②✍✍✍ "…ለማንኛውም ሁለት ሚሊሻ ተቀላቀለን፣ ቁጥራቸው የማይጨምር የማይቀንሰው 60 ፍሬ ባለ ቀይ ቦኔቶቹን ኮማንዶ አስመረቅን የሚለውን ዋቴ ተወት አድርጉና ጠንከር ስለሚለው ከራቡ በፊት ስለ Biological Weaponsም ስለ ዝንጀሮ ፈንጣጣውም ጻፉልን። ከአሕፋድ ከእስክንድር ነጋ ጦር ስንት ሰው ሞተ፣ ስንቱስ ከዳ ጻፉ እንጂ። ጻፉ። እንዴት ጥቂት አርቆ የሚያስብ የወደፊቱን እየተነበየ ካለፈው ጋር እያነጻጸረ የሚጽፍ የተስተማረ ሰው ይጠፋል? …እኔ እኮ አለመማሬ እኮ የሚነደኝ፣ የሚበሰጨኝ በዚህ ጊዜ ነው። ብማር ብስተማር ኖሮ እልና ደግሞ ሳስበው ብማር ብስተማር ኖሮማ እኔም ሆዳም፣ ፈሪ፣ ቅዘናም፣ ሽንታም፣ ቦቅቧቃ፣ መስሎ አዳሪ፣ አቃጣሪ፣ የቤት ቀጋ የውጭ አልጋ፣ አስመሳይ፣ እስስት፣ ደካማ፣ እወደድ ባይ፣ አሽቃባጭ፣ አፈጻድቅ እሆን ነበር። አለመማሬ እኮ ነው የሌለ ደፋር የሚያደርገኝ። ብቻ ለማንኛውም ጻፉ። ጸሐፊዎች ጻፉ። ጻፉና አስደምሙን። አወያዩን፣ አከራክሩን፣ አመራምሩን እንጂ…! ሃኣ…።
"…ክሬሚያ ጅቡቲ ናት ወይስ አሰብ…? ጻፉ እስቲ ስለእሱ። …ምንአልባት የውስጥ ቅጥረኛ ከፋፋዮች ባይኖሩና የ6 ወር የተንኮል፣ የክፋት፣ የሴራ ትብታብ ተብታቢዎች ባይኖሩ ክረምቱን ለአገዛዙ ያስፈራል ተብሎ የነበረው የመጪው ክረምት የፋኖ ማንሰራራት ግምት እንዳይሳካ ባለ አጀንዳዎቹ፣ አጀንዳ ፈጣሪ፣ አምራች፣ አከፋፋዮቹ በቀጣይ ምን ያደርጋሉ? የሚለውንም ከወዲሁ እየቀደማችሁ በመጻፍ አንቁ እንጂ። ከወዲሁ በቅርቡ ከፍ ባለ ድምጽ ጥቅሴዎቹ ተጠቃቅሰው ስለሚያጮሁት…
• የፕሪቶሪያ ስምምነት አልተከበረም!
• እስከ ሰኔ 30 ብለን የነበረውን የፋኖን ድምሰሳ እስከ ነሐሴ 30 እንጨርሰዋለን!
• ኤርትራን ልንገጥም ነው። ወደብ ልናስመልስ ነው!
• ኤርትራም ትዝታለች፣ "ኦሮሙማ" እያለች ትናቆራለች።
• ሕወሓት ተከፋፈለ፣ ተጣላ፣ ሊታኮስ ነው።
• ስለ አቶ ጌታቸው ረዳም ወሮ ስምረት ፓርቲ ከፍ ብሎ ይጮሃል፣ አንተም አብረህ ትጮሃለህ። እንከፎ። እርግጥ ነው ዓለሙ ሁሉ ጭንቅ ላይ ነው። ኢራንና እስራኤል፣ እስራኤልና ፍልስጤም፣ ሶሪያ፣ የመን፣ ሩሲያና ዩክሬን፣ በአሜሪካም፣ በካናዳም ዓለም ጭንቅ ላይ ነው። ሆኖም ግን ስለ እኛም ጻፉልን። በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን መርቲ ወረዳ ጎልጎታ ቀበሌ ውስጥ ስለተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝም ጻፉ፣ ስለ።ዝንጀሮ ፈንጣጣውም ጻፉ። ጻፉ… 10 ብር ሳይኖርህ ከ10 ሺ ብር በላይ ከባንክ ውጪ መግዛት መሸጥም አትችልም ተባልኩ ብለህ አታለቃቅስ። በ3 ብር ፌስታል 5 ሺ ብር ልቀጣ ነው ብለህ አትንቦቅቦቅ፣ ለገለቴ ቡርቃ እንደሁ የአንተ ማለቅለቅ ሳያስፈልጋት ፌስታል አንደኛ ኦሮሞነቷ፣ ሁለተኛ፣ ጴንጤ መሆኗ ብቻ ይበቃታል። እ? ቀድሞ ያለቀሰ የሚታዘንለትን የዘመኑን ፍርደ ገምድል አጀንዳ ተወውና ይልቅ ጻፍ፣ ስለመጪው ጊዜ ምከር፣ ተመካከር፣ ተጨቃጨቅ፣ ተወያይ።
"…ኧረ ጻፉ… ምንኡኖው ኖ የሚጽፉ የጠፉት?

"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር
"…በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት ልክ 1:00 ደቂቃ ላይ በዘመድ ቴቪ መርሀ ግብሩ ይጀምራል። እንደተለመደው ገባ ገባ በሉና ጠብቁን።
• ZemedTv 👉 zemedtv.com
• በትዊተር (×) 👉 https://x.com/i/broadcasts/1YqJDZBDkYaKV
• በራምብል 👉 https://rumble.com/v6utldt--zemede-june-15-2025.html?e9s=src_v1_upp
• በሳታላይት ቴሌቭዥን 👉
Yahsat 52.5° East
11977 H 27500 • ላይ ይከታተሉን።
"…በተረፈ የእኔን የስልክ ወጪን ጨምሮ አገልግሎቴን ለመደገፍ የምትፈቅዱ።
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል መለገስ ትችላላችሁ። ሁላችሁም ተመስግናችኋል።
• ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁን…!

"…ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ። ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤
"…የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና። ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም የተጣሉ ሰዎች ሆነው፥ እውነትን ይቃወማሉ።
"…ዳሩ ግን የእነዚያ ሞኝነት ደግሞ ግልጥ እንደ ሆነ፥ ሞኝነታቸው ለሁሉ ይገለጣልና ከፊት ይልቅ አይቀናላቸውም። …ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች፥ እያሳቱና እየሳቱ፥ በክፋት እየባሱ ይሄዳሉ። አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤ ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል። 2ኛ ጢሞ 3፥ 1-15
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"…እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

ማስታወሻ፦
"…አይደለም በኢትዮጵያ በዓለሙ ሁሉ ላይ የሚሰማውና የሚታየው ነገር ሁሉ ምኑም ደስስ አይልም። ከጥቂቶች በቀር አብዛኛው ሰው ግን እየተካሄደ ያለው ነገር ሁሉ የገባው አይመስልም። ወይም ገብቶት ሳለም ዐውቆ የገባው ላለመምሰል የሚጥርም ነው የሚመስለው። ማወቅ መረዳት ያለብን ነገር ግን በየትኛውም የምድራችን ክፍል ላይ ለምንኖር የሰው ልጆች በሙሉ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ከሌለ በቀር ከፊታችን የሚመጡት ወራት ከባድ፣ እጅግም ፈታኝ ወራት ይመስላሉ። ነገሮች ከሸማኔ መወርወሪያ ይልቅ በፍጥነት እየተወረወሩ ዓለሚቱን ወደ ከባድ አዘቅት የሚያመሯት ነው የሚመስለው።
"…የኢራንና የእስራኤል ጦርነትን እንደ ቀላል የሚያዩ፣ ጭራሽ የሃይማኖት ጦርነት መስሏቸው ግራና ቀኝ ቆመው ለእስራኤልና ለኢራን ድጋፍ ለመስጠት ጎራ ለይይተው የሚሰዳደቡ፣ የሚበሻሸቁም ኢትዮጵያውያንንም እያየሁ ነው። ኢራን እንድታሸንፍ ቆሞም ተቀምጦም ዱአ የሚያደርግ እንዳለ ሁሉ እስራኤልም እንድታሸንፍ እንዲሁ የሚነታረክ እያየሁ ነው። ከኢራን ወደ እስራኤል የሚወነጨፉ ሚሳኤሎችን በሞባይሉ እየቆጠረ አላህ ወአክበር እያለ የሚጨፍር አረብ አይቼ ዞር ስል በእስራኤል ሚሳኤል ከፈራረሰ ሕንጻ ውስጥ የሚለቀም የኢራናዊ አስከሬንም እያየሁ ነው። የሁለቱ ሀገር ጦርነት በአንድም በሌላም ዳፋው የሚተርፈው ከሁለቱ ሀገራት አልፎ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊም አፍሪካዊና አውሮጳዊ ቤትና ጓዳ ላይ ነው። እናም ቲፎዞነቱ ለጊዜው አቆይተን በጸሎቱ ብንበረታ።
"…አሁን አውሮጳ ጭንቅ ላይ ነው። አሜሪካም ቢሆን ከሕገወጥ ስደተኞቹ ጋር ተያይዞ ዝብርቅርቋ እየወጣ ነው። ካናዳ ስላለህ፣ እስያ ወይም መካከለኛው ምሥራቅ ስለምትኖር ያለስጋት፣ ያለ ጭንቅ መኖር የማይታሰብ ነው። በየትኛውም የምድራችን ክፍል የሰላም አየር መተንፈስ እንደ ሜርኩሪ ብርቅ እየሆነ ነው። በኢራን የቴህራን ከተማ ነዋሪዎች፣ በእስራኤል የቴልአቪቭ ከተማ ነዋሪዎች ቤታቸውን፣ ከተሞቻቸውን በሙሉ ለቅቀው እንዲወጡ ኢራንም፣ እስራኤልም ዐዋጅ አስነግረዋል። አሜሪካም ዜጎቿን ቴህራንን ለቀው እንዲወጡ አሳስባለች። ሩሲያ፣ ቻይና፣ እስራኤልና ኢራን አራቱ ሀገራት ዜጎች ቴልአቪቭን ለቅቀው እንዲወጡ አሳስበዋል። ከማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያው ቀጥሎ እንግዲህ የሚከሰተው ያው ውድመት ነው። ሥልጣኔ በሉት መሰረተ ልማት ሁሉ ይወድማል። ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት፣ ቤተ እምነቶች፣ ታሪካዊና ጥንታዊ ቅርሶች በሙሉ ይወድማሉ። ለትዝታ የሚሆን ነገር ይጠፋል። በጋዛ፣ በኢራቅ፣ በየመን፣ በሊቢያና በሱዳን፣ በሶሪያም የታየው ምስቅልቅል ሁሉም ይከሰታል። የአላስቃ መስጊድም በግርግር ምን እንደሚገጥመው አይታወቅም። ከምር ምኑም ደስስ አይልም።
"…ይሄ ሁሉ ሩቅ ስለሆነ ከእርሱ ጋር የሚደርስ የማይመስለው ሰው ካለ ትልቅ ስህተት እያደረገ ነው። በሩቅ ነው ያልነው መከራም ወደ እኛ ይቀርባል። በተዘዋዋሪ እንጎዳለን። የነዳጅ ዋጋ ይጨምራል። ኑሮው ሁሉ አሁን ካለበት በእጥፍ ጣራ ይነካል። ወረርሽኝ ይከሰታል፣ አሁንም የዝንጀሮ ፈንጣጣ የሚሉት ወረርሽ መከሰቱ እየተነገረም ነው። መድኃኒት ይወደዳል። ምስቅልቅል ነው የሚወጣው። በዚህ ላይ ሌሎች ኃያላን ሀገራት ጦርነቱን ከተቀላቀሉ ደግሞ አስቡት። እጅግ ከባድ ነው። ደግሞም ሳይቀላቀሉ አይቀሩም። የሌሎቹን እንጃ እንጂ አሜሪካ ዳር ዳር እያለች ነው። ፈረንሳይም ቃሏን ሰጥታለች። ኢራንም ሆነች እስራኤል ከጎናቸው የሚሰለፍ የትየለሌ ነው። አሁን በአሜሪካ መኖር እኮ እረፍት የሚሰጥ አልሆነም። በኢትዮጵያም፣ በአውሮጳም፣ በመካከለኛው ምሥራቅም በየትኛውም የዓለማችን ክፍል መኖር እፎይ የሚያሰኝ አይደለም። ችግሩን ደግሞ የምታዩት በኪሳችሁ እና በፍሪጃችሁ ውስጥ ነው። በአውሮጳና በአማሪካ ባለመኪኖች ነዳጅ ሊትሩን በሳንቲም መቅዳት ከተዉ እኮ ዓመታት እየተቆጠሩ ነው። ሱፐርማርኬቶች የዋጋ ጭማሪያቸው አስደንጋጭ ነው። ማንጎራጎር እንጂ ጸሎት ግን የለም።
"…ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው የብልፅግናው አገዛዝ በወንጀል ጠርጥሮ የያዛቸውን ዜጎች ከመግደል ውጪ ያለውን አሰቃቂ የምርመራ ዘዴዎች ብልት ላይ ሃይላንድ ማንጠልጠልን ጨምሮ በማኅጸን ውስጥ ብረትና እንጨት ከትቶ፣ በእሳት፣ በውኃ አፍኖ መመርመር የሚያስችለውን ፈቃድ በዐዋጅ ያጸደቀለት። ሳናጣራ አናስርምን ውኃ በላት። በነገራችን ላይ ስለ ሂሊኮፕተሯም ሰሞኑን ጊዜ ሳገኝ እንዲሁ በጥቂቱ እተነፍሳለሁ። በተለይ ዜናውን ስላጮሁት በሸዋ እና በጎንደር ስላሉት የትግሬ ፋኖዎች የሆነች ነገር እላችኋለሁ። ስለ ትግሬዎቹ ብቻ ሳይሆን ብአዴኖች ሞቱ ብለው ነጠላ ዘቅዝቀው ኃዘን ተቀምጠው ስለነበሩት ጥቂት የሸንጎና የቅማንቴ የዐማራ አክ እንቲቪስቶችም የሆነች ጦማር እለቅባችኋለሁ።
• ሻሎም… ሰላም…!

ግርግር ለሌባ ያመቻል…
"…ወዳጄ በአሁኑ ጊዜ ያውም ሰሚም፣ አድማጭም በሌለበት በዚህ ዘመን እንደ ትናንቱ ዛሬም በወለጋ፣ በጎጃም፣ በሸዋና በወሎ በአቢይ አህመድ ተጨፈጨፍኩ ብለህ አትጩህ። ማን ሊሰማህ ነው የምትጮኸው? እንዲያውም አሁን ነው ሰሚም፣ ተመልካችም የለም ብሎ ሳይብስበት ነቃ ብሎ ግራ ቀኙን፣ ዙሪያ ገባውን፣ ፊትና ኋላህን ሁሉ መጠበቅ። አሁን ነው ከበፊት ይልቅ ንቁ መሆን እንዝህላልነትን ሁሉ ትቶ፣ ዳተኝነትን፣ ስንፍናንም ሁሉ አስወግዶ በንቃት መንቀሳቀስ። አሁን ነው ወዳጄ።
"…አንተማ በሰላሙ ቀን ስትጨፈጨፍ፣ በዘርህ ተለይተህ ስትገደል፣ ስትዘረፍ፣ ስትገፈፍ፣ በሃይማኖትህ ተመርጠህ ስትገፋ፣ ስትደፋም ያልሰማህ፣ ያልደረሰልህ፣ ዞር ብሎም ያላየህ ዓለም አሁን ላይማ የፈለገ ነገር ቢፈጸምብህ፣ ቢደረግብህም ደንታውም አይሆን። እናም ወዳጄ እዬዬውን ትተህ ከበፊቱ ይልቅ በርታ፣ ንቃ ጠንክረህም ራስህን ጠብቅ።
"…በሰላሙ ጊዜ ለራብህ ስንዴና ዘይት፣ ዶላርም፣ ዱቄትና ብስኩት፣ ለእልቂትህ ጥይትና ቦንብ ይለግሱህ የነበሩት አካላት አሁን በራሳቸው የውስጥ ጉዳይ ስለተወጠሩ ተራብኩ ብትልም አይሰሙህም። ፍግም ብትልም ዞር ብለው አያዩህም። ለራሳቸው ከሚሳኤል ጥቃት ለማምለጥ፣ ለመትረፍም በየምድር ዋሻው እየተንከራተቱልህ ነው። እናም ራስህን አድን። ስለራስህ አስብ።
"…በሰላሙ ጊዜ ጆሮ ያልሰጡህ፣ መጨፍጨፍህ ልክ አይደለም ብለው መፍትሄ ያልሰጡህ አካላት አሁን በዚህ ቀውጢ የጦርነት ቋያ ውስጥ ሆነው ገዳዬን፣ ጨፍጫፊዬን ያስታግሱልኛል ብለህ እንዳታሳብ። እንዲያውም ግርግር ለሌባ ይመቻል አይደልስ የሚባለው ከነተረቱ። አዎ በግርግር በኃይል እንዳትበላ ተጠንቀቅ። እነርሱ በራሳቸው ጉዳይ ሲወጠሩ አጅሬው አንተን እንዳይወጥርህ አንተም ከቻልክ ራሱኑ መልሰህ ወጥረው።
"…እኔ 8 ዓመት ሙሉ ላንቃዬ እስኪሰነጠቅ ድረስ ከነገርኩህ የተለየ ኦቦ ታዬ ደንድአ ምንም የሚነግርህ አዲስ ነገር እንደሌለም ዕወቅ። እየተፈራረቁ ጆርህ ላይ መስማት የምትፈልገውን እየነገሩህ ራስህን በራስህ እያረካህ በመከራ እንድትኖር አያድርጉህ። ስንትና ስንት መላእክት የነገሩህን ትተህ አንድ ሰይጣን ውሉደ ሰይጣን በሚነግርህ የርኩሰት ምስክርነት አትመሰጥ። ሰይጣን ሰይጣን ነው አለቀ። ታየኝ እኮ ኦነጉ ፀረ ዐማራው ታዬ ደንደአ ዐማራና ትግሬን ወድዶ አዲስ ምስጢር ሲነግርህ። ያውም ደግሞ በኦነጉ ሚዲያ ላይ። አትጃጃል።
"…ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ተናግረናል። ዐማራን እንደ ነገድ፣ ኦርቶዶክስን እንደ ሃይማኖት ለማጥፋት የመጣ ሥርዓት ነው ብለን ጩኸናል። ጩኸታችንን የሰሙ ፈዛዞች ሲሰድቡን፣ ሲወቅሱን፣ ጩኸታችንን የሰሙ ብልሆች ግን የመጣውን የጥፋት ኃይል ለመመከት ቀድመው ዱር ቤቴ ብለው ገብተዋል። እነዚያ ናቸው ዛሬ የዐማራን የጅምላ እልቂት መክተው፣ ገትረው፣ ባለበት ያስቆሙት። መከራ በሁሉም ቤት ይገባል ብለን ጩኸናል። የሚተርፍ፣ የሚቀር የለም ብለን እሪሪ ብለናል። ካልነውና ከተናገርነው አንድም የቀረና የጎደለ የለም። አሁን ደግሞ የመንግሥት ሠራተኛ የሆነ ሁሉ ይባረራል። ይቀነሣል። አሪታው ይበረታል። ትበላለህ። ዘንዶው ይውጥሃል። የሚምረው የለም። ውቧ ቴህራን፣ ቆንጅዬዋ ጋዛና ቴላቪቭም ለመውደም ደቂቃ አልፈጀባቸውም። ሰምተሃል።
"…አሁን ላይ የሁሉም ሰው ዓይን ቴላቪሽና ቴህራን ላይ በተተከለበት በዚህ ዘመን የኦሮሙማው አገዛዝ ድምጹን አጥፍቶ ቶሎ ቶሎም ብሎ የሚፈልገውን የጀመረውን የዘር ጭፍጨፋ በወለጋም ሆነ እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ከመፈጸም ወደ ኋላ አይልምና መፍትሄው አሁንም ትርኪ ምርኪውን ትተህ በአንድነት ቆመህ በኅብረት መጋፈጥ፣ በቅንጅት መመከት ብቻ ነው። ይልቅ በግርግሩ እንዳትበላ ነቅተህ ራስህን ጠብቅ። መቶ ሺ ሠራዊት ላለው አገዛዝ ሁለት ሚሊሻ ማረክሁ፣ ሁለት ወታደር አስኮበለልኩ እያልክ በሰበር ዜና ሕዝቡን ማዛግህን ተወውና ይልቅ በፍጥነት አንድነት ፈጥረህ ለህልውናህ ታገል። አባው ወሬ ቀንስ፣ ጩኸት እዬዬህን ቀንስ፣ ለተግባር ፍጠን። አድምጠኝ፣ ልብ ብለህም ስማኝ ልንገርህ አይደል? የዘንድሮው ክረምት አያምልጥህ። ነግሬሃለሁ። ይሄ ክረምት አያምልጥህ።
"…አንድ ኪሎ ኮረሪማ 3ሺ ብር፣ ኩንታሉ 300 ሺ ብር ማለት ነው አይደል?

ጉድ እኮ ነው…
"…እረፍትም ላይ ሆኜ እኮ ምንም እረፍት የሚያሰጥ፣ ዝም፣ ጭጭ ጮጋም የሚያስብል ነገር ተገኝቶ ዝም ለማለት አልተቻለም። መቼም ዘንድሮ እኮ አይሰማ ነገር ጉድ የለም። የነገ ሰው ይበለንማ። የመድኃኔዓለም ያለህ።
• በሉ እስኪ ደህና እደሩልኝ…

"…በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሣል፤ ሕዝብም ከሆነ ጀምሮ እስከዚያ ዘመን ድረስ እንደ እርሱ ያለ ያልሆነ የመከራ ዘመን ይሆናል፤ በዚያም ዘመን በመጽሐፉ ተጽፎ የተገኘው ሕዝብህ ሁሉ እያንዳንዱ ይድናል። በምድርም ትቢያ ውስጥ ካንቀላፉቱ ብዙዎች ይነቃሉ፤ እኵሌቶቹ ወደ ዘላለም ሕይወት፥ እኵሌቶቹም ወደ እፍረትና ወደ ዘላለም ጕስቍልና። ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ። ዳን 12፥ 1-3
በዛሬው ዕለት ሰኔ 12
"…የከበረ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር የተሾመበት፣ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር ንሥረ አርያም የሚባል ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ ንዑድ ክቡር የሆነ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ቅድስት አፎምያን ያዳነበት፣ ዳግመኛም ይኽች ዕለት የቅዱስ ባህራን ቀሲስ የሞት ደብዳቤ ቀዶ እርሱን ለታላቅ ክብር ያበቃበት ቀን ናት፡፡ በተጨማሪም ካህን እና ንጉሥ፣ ጻድቅ እና ንጹሕ የሆነ ቅዱስ ላሊበላም ያረፈው በዛሬው ዕለት ነው።
"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?
"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼