Telegram Web Link
በሆለታ ከተማ አንዲት  አህያ ፈረስ መውለዷ ተሰማ

በሆለታ ከተማ አስተዳደር ገልገለ ኩዩ ቀበሌ ውስጥ አንዲት አህያ ፈረስ መገላገሏን የከተማው አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ገልጿል ።

በሆለታ ከተማ ገልገለ ኩዩ የተባለ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት የአቶ ብርሀኑ ጐዳ ንብረት የሆነች የጭነት አህያ ፈረስ መውለዷ ተገልጿል ።

የአህያዋ ባለቤት የሆኑት አቶ ብርሀኑ ጐዳ  እንደገለጹት ከአስር ዓመት በፊት የጭነት አህያዋን ከኤጀሬ ከተማ መግዛታቸውን ገልጸዋል።  ከዚህ ቀደም ባልታሰበ መንገድ በስድስተኛዋ እርግዝና ሆዷ ተልቆ የታየ እና  ከዚህ ቀደም ግን አምስት አህዮችን ስትወልድ የተለየ የሰውነት አቋም እና ባህሪ እንዳልነበራት ተጠቁሟል።

የጭነት አህያዋ በስድስተኛ ወሊድዋ ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋት ሶስት ሰዓት ላይ ግን መጠኑ ከአህያ ውርንጭላ በአቋሙ የተለየና ሙሉ በሙሉ የፈረስ ዝርያ ያለው ውርጭላ መውለድዋን ተናግረው አጋጣሚው ግርምት እንደ ጫረባቸው አውስተዋል።

የሆለታ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ማዕከል  አጠቃላይ የእንስሳት ጤና አጠባበቅ ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ቤክሲሳ ኡርጌ እንደገለጹት በዘረ መል ምርመራ ሂደት የፈረስ እና የአህያ ክሮሞዞም  ተመሳሳይነት ያለውና  የአንደኛው የዘር ፈሳሽ የሚፈጠር ፅንስ ሲሆን በተለምዶ አህያ ከፈረስ ጋር የማዳቀል ሂደት በቅሎ የሚወለድ ይሆናል ማለታቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

አህያ ፈረስ የመውለዱ ሂደት የተለመደ ባይሆንም  በሳይንስ የተረጋገጠ ቁጥር ባይኖርም አህያ ፈረስ መውለድ እንደሚችልና የተወለደውም በሽታን የመቋቋም አቅሙ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

በአሁኑ ጊዜ  የተወለደው ፈረስ ጤንነቱ ሙሉ ለሙሉ የተረጋገጠ እንደሆነና እናቱም በፍቅር ጡቷን እያጠባችው እንዳለ ተረጋግጧል።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
😁6426🤔11🤷‍♂3😱1
በባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ባለፋት አስር ዓመታት በሰዉና ዝሆን ግጭት 66 ሰዎች የሞት እና የአካል ጉዳት አደጋ አጋጥሟቸዋል ተባለ

በባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ በሰዎችና በዝሆኖች መካከል በተፈጠሩ ግጭቶች ባለፋት አስር ዓመታት 66 ሰዎች ለህልፈትና የመቁሰል አደጋ አጋጥሟቸዋል ሲል የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።

በባለስልጣኑ የጥበቃ ቦታዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ አቶ ካሳዬ ዋሚ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት እኤአ ከ2016እስከ 2025 ድረስ በመጠለያው 86 የዝሆን ዝርያዎች እንደሞቱ ጥናቶች ያሳያሉ።ሰዎች ለእርሻና ለሌሎች ተግባራት በሚል በሚፈጥሩት ህገወጥ እንቅስቃሴ ምክንያት የህገወጥ ሰፈራ መበራከት ለችግሩ መፈጠር ከሚጠቀሱት ምክንያቶች መካከል ተጠቃሽ መሆኑ ተገልጿል።

በዚሁ መጠለያ ያሉት ዝሆኖች ከሰዎች ጋር በሚፈጥሩት ግጭት ሳቢያ ሰዎች ህይወታቸውን ሊያጡና የአካል ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችል የገለፁት አቶ ካሳዬ  በባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ ቁልፍ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ባለስልጣኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማካሄዱን ተናግረዋል።

ከኦሮሚያ እና ሱማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የመጠለያው አዋሳኝ ከሆኑ ዞኖች፣  ወረዳዎች እና ቀበሌዎች እንዲሁም ከሀሮማያ እና ጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ  ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይቱ መካሄዱ ታውቋል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
20😁16
1
አርኤስኤፍ በሊቢያ ድንበር አቅራቢያ ቁልፍ ቦታ መያዙን ገለጸ

የሱዳን ፈጣን ድጋፍ ሰጭ ኃይሎች ሰኞ እለት በሰሜን ሱዳን ግዛት ከሊቢያ እና ግብፅ ድንበሮች አቅራቢያ የሚገኘውን ኦሳይስ የተሰኘውን ስተራቴጂክ ቦታ መያዙን ገልጿል፣ ይህ እርምጃ የፓራሚሊታሪ ቡድኑ የአቅርቦት መስመሮቹን ለማጠናከር ይረዳል ተብሎለታል። አርኤስኤፍ ሀገሪቱን ለመቆጣጠር ከሁለት አመት በላይ በዘለቀው ጦርነት ከሱዳን ጦር ጋር እየተዋጋ ነው።

የአርኤስኤፍ አማካሪ መሀመድ ሙክታር ለሱዳን ትሪቡን እንደተናገሩት ኃይላቸው በጀበል አርኬኑ ተራራ ክልል አቅራቢያ የሚገኘውን “ካርብ አል ቱም” የተሰኘውን የባህር ዳርቻ ተቆጣጥረዋል። የተያዙት አከባቢዎች በሱዳን፣ ሊቢያ እና ግብፅ መካከል መገናኛ መስመር በሆነው ስልታዊ "ትሪያንግል" አካባቢ መያዙን ተከትሎ ነው።

በአካባቢው የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊት ጥምረት ቃል አቀባይ ስለጉዳዩ ምላሽ ማግኘት አልተቻለም ተብሏል። ይህ የጦር ግስጋሴ የመጣእ የRSF መሪ ጄኔራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳግሎ ጁን 2 በቪዲዮ ወደ ሰሜናዊ ግዛት ኃይላችን እየገባ እንደሆነ ከተናገሩ በኋላ ሲሆን ሰላማዊ ዜጎች በቤታቸው እንዲቆዩ አስጠንቅቀዋል።

በቀረጻው ላይ፣ ዳግሎ፣ RSF በአካባቢው “የISIS ታጣቂዎች” በማለት የገለጻቸውን የሱዳን ታጣቂዎች መረጃ እንዳላቸውና “ህጋዊ ኢላማ” እንደሆኑም ገልፆል።  ዘመቻው በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት እንደማያደርስም ተናግረዋል።

ተንታኞች እንደሚሉት አርኤስኤፍ በኮርዶፋን እና በዳርፉር አካባቢዎች የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማጠናከር ከሊቢያ የሚወስደውን የአቅርቦት መስመር ለማስጠበቅ እየሞከረ ነውም ተብሏል። በዳርፉር ክልል የሰራዊቱ የመጨረሻ ምሽግ በሆነው በኤል ፋሸር ላይ የ RSF ጥቃት ከተጠናከረበት ጋርም ይገጣጠማል።

በመሬት ላይ ያሉ ምንጮች እሁድ እለት በከተማይቱ ላይ የ RSF ጥቃት እጅግ በጣም ኃይለኛ ሆኖ እንደቀጠለ ገልፀዋል ይህም ከበባውን ለማጠናከር የተደረገው ጥረት አካል ነው ብለዋል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
18👎2😁1
😁28👍24
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሕግ አገልግሎት መምሪያ በአቶ ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ መሰረተ።

የቤተክርስቲያናችን ሕግ አገልግሎት መምሪያ ለኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባቀረበው ክስ የወንጀል ምርመራ ተደርጎ የምርመራ መዝገቡ መብቱ ለሚፈቅድለት የዐ/ሕግ ዘርፍ እንዲተላለፍለፍ ጠይቋል።

በወንጀል ተጠርጣሪ /ተከሳሽ - አቶ ትዝታው ሳሙኤል
ተጠርጣሪ /ተከሳሹ ነዋሪነቱን በውጪ ሃገር በማድረግ የቤተክርስቲያኒቱ የበላይ ውሳኔ ሰጪ አካልን ለማዋረድ፣
ለመስደብ እና የምዕመኑን ስሜት ለመንካት ብሎም በሀገሪቱ ውስጥ ሁከትና ብጥብጥ እንዲነሳ በማሰብ በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ መንገዶች እና ከ5000 በላይ ተከታዮች ባሉት የራሱ የዪቲዩብ ቻናል በመጠቀም ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

በማያያዝም ግለሰቡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን አባቶችን፣ በየገዳማቱ ውስጥ የሚገኙ ገዳማውያን መነኮሳትና አገልጋዮችን <<ግብረ ሰዶማውያን ናቸው>> በማለት፣እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን <<የመተት እና ጠንቋይ ቤት ናት >>በማለት፣ሲቀሰቅስ የቆየ መሆኑን የገለጸው መምሪያው ግለሰቡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የምትገለገልባቸውን ሃይማኖታዊ የፀሎት፣የታሪክ ፣የገድላትና ድርሳናት መጻሕፍትን <<ድውያን መጽሐፍት ናቸው መጥፋት አለባቸው>>ማለቱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በቅድስናየምታ
ከብራቸውንና የምትዘክራቸውን ቅዱሳን አባቶች እና እናቶችን << ጣኦታትና ጣኦት አምላኪ>> ናቸው በማለት ግለሰቡ የፈጸመውን የወንጀል አድራጎት በመጥቀስም ክስ መስርቶበታል።

መምሪያው በአጠቃላይ ሰባት ነጥቦችን ያካተቱ የወንጀል ዝርዘርሮችን በመግለጽም ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል ቀርቦ ግለሰቡ በሕግ ተጠያቂ እንዲደረግ ባቀረበው አቤቱታ ገልጿል።

#ዳጉ_ጆርናል
👍95😁4726👎13🤷‍♂3🤔2
በአዲስ አበባ ሿሿ የሚሰሩ ወንጀለኞች ተያዙ

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በመምሰል በተለምዶ የሿሿ የተባለውን ወንጀል የሚፈፅሙ ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

በተለምዶ ሿሿ የሚባለውን ወንጀል ለመከላከልና አጥፊዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል በጥናት ላይ በመመስረት እና ማስረጃ በማሰባሰብ ባደረገው እንቀስቃሴ ከዚህ ቀደም በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በቂርቆስ፣ በቦሌ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በልደታ እና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች በልዩ ልዩ ስፍራዎች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ በመምሰል በተለምዶ ሿሿ የሚባለውን ወንጀል የሚፈፅሙ አስራ አንድ አባላት ያሉት ሁለት ቡድኖችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ መቀጠሉን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ወንጀል ለመፈጸም ይገለገሉባቸው የነበሩ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ 53234፣ ኮድ 3 ኦ/ሮ 50777 እና ኮድ 2 አ/አ B 50438 ተሽከርካሪዎችን መያዙንና ከዚህ ቀደም በፈፀሙት የሿሿ ወንጀል አስፈላጊው ማስረጃ ተሰብስቦ አራት የምርመራ መዝገብ እንደተደራጀባቸው ፖሊስ መምሪያው ገልጿል፡፡

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በግለሰቦቹ ላይ ምርመራውን አጠናክሮ እንደቀጠለና አስፈላጊውን ማስረጃ እያሰባሰበ በመሆኑ ከዚህ ቀደም በእነዚህ ተሽከርካሪዎች የሿሿ ወንጀል የተፈፀመበት ማንኛውም ግለሰብ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በግንባር በመቅረብ ወንጀል ፈፃሚዎቹን በመለየትና በመምረጥ ማስረጃ መስጠት የሚችል መሆኑን ጥሪውን አስተላልፏል።

#ዳጉ_ጆርናል
31👏24👍4🤔4😁1😭1
በአጣየ ከተማ ትምህርት ላልጨረሱ የ8 እና የ12 ክፍል ተፈታኞች በሁለተኛ ዙር ከነሃሴ በኋላ ፈተናው እንሚደሚሰጣቸው ተነገረ

በአጣየ ከተማ በተለያዩ ጊዜያት  ተቋርጦ በነበረ የትምህርት አገልግሎት ምክንያት ትምህርት ላልጨረሱየስድስተኛ እና የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች በሁለተኛ ዙር ፈተናው እንደሚሰጣቸው የአጣየ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሱፐርቫይዘር የሆኑት አቶ  ማሙሽ ሲከፋኝ  ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

የመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች ባለፈው ሳምንት ፈተናቸውን ያጠናቀቁ መሆኑን በመግለጽ የሁለተኛ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች እስከ ነሃሴ 2 ድረስ ትምህርት እንዲጨርሱ ከተደረገ በኋላ ክልሉ በሚያስቀምጠው ቀን ፈተናውን እንደሚወሰዱ ተገልጿል ።በሌላ በሉል በአካባቢው ካሉ አራት   ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሁለቱ በመጀመሪያ ዙር ሰኔ 23 ፈተናውን እንደሚወስዱ ተጠቁሟል።

ይሁን እንጂ ዘግይቶ ትምህርት መስጠት የጀመረው ጋሊለበር ትምህርት ቤት ከነሀሴ በኋላ በተመሳሳይ ትምህርት ሚኒስቴር  በወሰነው ቀን ፈተናውን እንደሚሰጣቸው ይጠበቃል። ቀሪው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአካባቢው በነበረ ግጭት ምክንያት  በዘንድሮ የትምህርት ዓመት ምንም አይነት ተማሪ አለመቀበሉን እና አገልግሎት አለመስጠቱ ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል ።

በመሆኑም በመጀመሪያ ዙር ፈተናውን ለሚወሰዱ ተማሪዎች በጥሩ ሁኔታ ዝግጅቱ መጠናቀቁ እና ከዚህ ቀደም እንደነበረው ያቋረጠ  ተፈታኝ አለመኖሩንም አቶ ማሙሽ  ሲከፋኝ ብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
19🙏1
6
በቴህራን የደረሱ ፍንዳታዎች በነዋሪዎች ላይ ፍርሃት እና ቁጣ ቀስቅሰዋል

በከተማው ውስጥ ከሚኖሩ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች እና ከ14 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሌሎች በርካታ ከተሞችን ባካተተው ሰፊው የቴህራን ግዛት ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች ከፍተኛ ድንጋጤ ዉስጥ ይገኛሉ፡፡በነዋሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ጭንቀት እና ፍርሃት አለ። ነገር ግን የሚገርመው፣ በዋና ከተማው ውስጥ በአብሮነት የመቆየት ስሜትም አለ።

በአንጻሩ እስራኤል ለደረሰባት ፍንዳታ እና ተደጋጋሚ የማስጠንቀቂያ መልእክቶች ምላሽ ለመስጠት ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የህዝቡ ክፍል ቴህራንን ለቆ መውጣትን መርጧል።በተለይ ኢላማ በተደረገባቸው ሰፈሮች ውስጥ የሚኖሩ፣ ጥልቅ የሆነ የንዴት ስሜት ነበር።ነዋሪዎቹ ከኒውክሌር መርሃ ግብሩም ሆነ ከወታደራዊ ተቋማት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው እና አሁን በነዚህ ክስተቶች ህይወታቸው በቀጥታ እየተጎዳባቸው ያሉ ተራ ዜጎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

መቀመጫውን በቴህራን ያደረገው የኢራን ጉዳይ ተንታኝ አባስ አስላኒ እስራኤል በኢራን ውስጥ "የሥነ ልቦና ጦርነት" በግድያ እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በሚሄድ ዛቻዎች እያካሄደች ነው ብለዋል።በመካከለኛው ምስራቅ ስትራቴጂክ ጥናት ማዕከል ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት አስላኒ ኢራን ለእስራኤል ጥቃቶች ምላሽ እንዳትሰጥ ለማስቆም እስራኤል "ህዝቡን ለማስፈራራት እና የዛቻ ደረጃን ለመጨመር እየሞከረች ነው" ብለዋል ። እውነታው ግን ኢራን እስካሁን ድረስ በሙሉ ኃይል አልመጣችም ምክንያቱም ዩናይትድ ስቴትስ በዚህ ግጭት ውስጥ ልትሳተፍ የምትችልበትን እድል ክፍት ነዉ ብለዋል።

የእስራኤል ጥቃቶች እና ዛቻዎች ፍርሃትን ወይም ትርምስን ከማስነሳት ይልቅ በኢራን ውስጥ ጠንካራ የብሄራዊ አንድነት ስሜት ፈጥረዋል ብለዋል ።የእስራኤል ጥቃት ኢራንን ምላሽ ከመስጠት አያግድም ሲሉ አክለዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
74👎12😁7👍2🤔1
በ2018 በጀት ዓመት የመድኃኒት የግዥ የቆይታ ጊዜን በመቀነስ አቅርቦቱን ለማሻሻል መታቀዱ ተገለፀ

የአገልግሎቱ የግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አወል ጀማል በ2018 በጀት ዓመት የተሻለ የመድኃኒት አቅርቦት ለማከናወን የአሠራር ፍጥነትን በመጨመር የመድኃኒት ግዥ ቆይታ ግዜን ወደ 120 ቀናት ለማውረድ መታቀዱንና እያንዳንዱ ሠራተኛ ተጠያቂ የሚሆንበት ስርዓት መዘርጋቱን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጽያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የፋርማሲዩቲካል የግዥ አስተዳደር ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ተከተል አሃዱ በሰርቶ ማሳያው ሁሉም ሠራተኛ ወጥ በሆነ መልኩ በተመሣሣይ ገፅ በጋራ እቅዶቹን ማዘጋጀቱ በአቅርቦቱ ላይ እንዲሁም ከተጠያቂነት አንፃር ኃላፊነት እንድንወስድ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

በእለቱ የግዥ ስርዓት መከታተያዎች የተዘጋጁ ሲሆን በ2018 በጀት ዓመት ለሚፈፀሙ ግዥዎች ሊገጥሙ የሚችሉትን ተግዳሮቶች አስቀድመን በመለየትና በማቀድ የመድኃኒት አቅርቦቱን በማፋጠን ፈጣንና ምላሽ ሠጪ ተቋም ልንገነባ እንደሚገባ በአፅንኦት ተገልጿል፡፡

የኢትየጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት መድኃኒቶችንና የህክምና ግብዓቶችን ግዥ ለማከናወን ከማንዋል የግዥ አሠራር በመውጣት ወደ ኤሌክትሮኒክ ወይንም EGP የግዥ ስርዓት መድኃኒቶችን በማቅረብ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም. የፀደቀው አዲሱ 1066/2017 የመድኃኒትና የህክምና መገልገያዎች የግዥ መመሪያም ለአቅርቦቱ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልፆል።

በሰመኃር አለባቸው
#ዳጉ_ጆርናል
14👎5🙏1
የኢራን እና የእስራኤል ግጭት አሜሪካ እሳቱን በማራገብ እያባባሰች ነዉ ስትል ቻይና ከሰሰች

የዩናይትድ ስቴትስ መሪ የቴህራን ነዋሪዎችን "ወዲያውኑ ለቀው እንዲወጡ" ካስጠነቀቁ በኋላ ቻይና በኢራን እና በእስራኤል መካከል እየተባባሰ ባለው ግጭት ላይ "እሳት በማቀጣጠል" ትራምፕን ከሰሰች ።

“እሳቱን ማቃጠል፣ ነዳጅ ማፍሰስ፣ ማስፈራራት እና ግፊት መጨመር የሁኔታውን መባባስ ለማርገብ አይረዳም ነገር ግን የበለጠ እንዲባባስና ግጭቱን ያሰፋዋል” ሲሉ የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጉኦ ጂያኩን በመደበኛ የዜና ኮንፈረንስ ላይ ስለ ትራምፕ አስተያየት ሲጠየቁ ተናግረዋል ።በእስራኤል የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ ማክሰኞ እስራኤል እና ኢራን ከባድ ጥቃት ዉስጥ መግባታቸዉን ተከትሎ ዜጎቹ “በተቻለ ፍጥነት” ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አሳስቧል።

"በእስራኤል ውስጥ ያለው የቻይና ተልእኮ ቻይናውያን በተቻለ ፍጥነት በመሬት ድንበር ማቋረጫዎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አሳስቧል፣ ይህም ለግል ደህንነታቸው ዋስትና እንዲሰጡ ቅድመ ሁኔታ ነው" ሲል ኤምባሲው በዊ ቻት ላይ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።"በዮርዳኖስ አቅጣጫ መሄድ ይመከራል" ሲል አክሏል፡፡የቤጂንግ ኤምባሲ ማክሰኞ እለት ግጭቱ “መባባሱን ቀጥሏል” ብሏል።

"በርካታ የሲቪል መሰረተ ልማቶች ተበላሽተዋል፣ የዜጎች ጉዳት እየጨመረ ነው፣ የጸጥታው ሁኔታም አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል" ብሏል።የኢራን እና እስራኤል ጥቃቱ ከበፊቱ ያነሰ ቢሆንም ለአምስተኛ ቀን የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን ከመካከለኛው ምስራቅ የሚወጡ ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡እስራኤል በምዕራብ ኢራን ውስጥ በርካታ “ወታደራዊ ኢላማዎች” በአንድ ሌሊት የመታች ሲሆን ከምሽት ወደ ላይ የሚተኮሱ ሚሳኤሎች እና የድሮን ማከማቻ ቦታዎችን ደብድባለች፡፡

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
🕊3528👍13🤣5👎4👏2💯2🤔1
ሚኪያስ ጎማ ፣ ባትሪና ከመነዳሪ አከፋፋይ 

#ለቪትስ
#ለያሪስ
#ለዲዛየርና ስዊፍት
#ለኮሮላ
#3L & 5L እንዲሁም ለከባድ ተሽከርካሪዎች የሚሆኑ ጎማዎች እና ባትሪዎችን ይዘዙን ካሉበት እናደርሳለን

👉የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ጎማዎች (ትሪያንግል ፣ ስፖርትራክ ፣ ኮምፈርሰር ፣ አፖሎ ፣ ብሪጅስቶን እና ሌሎችም)

👉 የተገለገሉበት ጎማ ን ዋጋ ተምነን በአዲስ እንቀይርሎታለን

👉 በስልክ ቁጥር 📞...+251-913-701702 / +251-975293297 ይደውሉልን አልያም ተክለሀይማኖት ከሚገኘው ሱቃችን ይምጡ በደስታ እናስተናግድዎታለን
16👍6
ኢራን ፋታህ-1 ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤልን ወደ ቴል አቪቭ ማስወንጨፏን አስታወቀች

የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ጓድ(አይአርጂሲ) ዛሬ ማምሻውን ፋታህ-1 ‘hypersonic’ ሚሳኤልን በእስራኤል ማስወንጨፉን አስታውቋል። ኢራን እ.ኤ.አ ኦክቶበር 1 ቀን 2024 በእስራኤል ልልይ በፈጸመችው ጥቃት፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ፋታህ-1 ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል አስወንጭፋለች። ሆኖም ይህ የፋታህ ሚሳኤል በአሁኑ ጦርነት ጥቅም ላይ ሲውል ይህ የመጀመሪያው ይመስላል።

ፋታህ ሚሳኤል ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በ2023 ሲሆን የተሰየመው በኢራን ጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኒ ነው። አይአርጂሲ ሚሳኤሉን “እስራኤል-አጥቂ” ሲል የጠራው ሲሆን ይፋ ባደረገበት ወቅት በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን ውስጥ “400 ሰከንድ ወደ ቴል አቪቭ” የሚል መልእክት የያዘ ትልቅ ባነር ተጭኗል። ምንም እንኳን ኢራን ፋታህ ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ነው ብትልም ወታደራዊ ባለሙያዎች ግን ስለ ትክክለኛው ሃይፐርሶኒክ ችሎታው ጥርጣሬ አላቸው።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
65🤣11👍7👏2😱1
ትራምፕ ያለ ቅድመ ሁኔታ ኢራን እጅ እንድትሰጥ ጠየቁ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቴህራን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እጅ እንድትሰጥ ቢጠይቁም በሁለቱ የረጅም ጊዜ ጠላቶች መካከል የአየር ጦርነት ስድስተኛ ቀኑን አስቆጥሯል። ኢራን እና እስራኤል አዲስ የሚሳኤል ጥቃት ፈፅማዋል። የእስራኤል ጦር ረቡዕ ጠዋት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰዓታት ውስጥ ሁለት የኢራን ሚሳኤሎች ወደ እስራኤል መተኮሱን አስታውቋል። በቴል አቪቭ ላይ ፍንዳታዎች ተሰምቷል።

እስራኤል በቴህራን ደቡብ ምዕራብ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች የአየር ሃይሉ የኢራንን ወታደራዊ ተቋማት ስለሚመታ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቃለች። የኢራን የዜና ድረ-ገጾች እስራኤል ከመዲናዋ በምስራቅዊ ክፍል ከኢራን አብዮታዊ ጥበቃዎች ጋር በተገናኘ ዩኒቨርሲቲ ላይ ጥቃት ሰንዝራለች።የኢራን የዜና ድረ-ገጾች እስራኤል በሀገሪቱ ምስራቅ ከሚገኙ የኢራን አብዮታዊ ጥበቃዎች ጋር ግንኙነት ያለው ዩኒቨርሲቲ እና በቴህራን አቅራቢያ የሚገኘውን የኮጂር ባላስቲክ ሚሳኤል ተቋም ላይ ጥቃት እየሰነዘረች ነው ብለዋል ።

የዩናይትድ ስቴትስ የብሄራዊ መረጃ ዳይሬክተር ቢሮ ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ትልቁን የባልስቲክ ሚሳኤሎች መታጠቋን አስታውቋል። ኢራን የባለስቲክ ሚሳኤሎቿ በዩኤስ፣ በእስራኤል እና በሌሎች ቀጣናዊ ኢላማዎች ላይ ወሳኝ መከላከያ እና አጸፋዊ ሃይል እንዳላቸው ገልጻለች።

ትራምፕ ማክሰኞ ዕለት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የአሜሪካ ትዕግስት ቀጭን ለብሶ ነበር ሲሉ አስጠንቅቀዋል። የኢራን መሪ አያቶላ አሊ ካሜኔይን ለመግደል ምንም ሀሳብ እንደሌለ ቢናገሩም የሰጡት አስተያየቶች የአሜሪካን ተሳትፎ የለኝም የሚለውን አቋም ማጠናከር አለመቻሉን በኢራን ላይ የበለጠ ጠብ አጫሪ አቋም እንዳላቸው ጠቁሟል ። በትሩዝ ሶሻል ላይ “‘ከፍተኛ መሪ’ እየተባሉ የሚጠሩትን የት እንደተደበቁ በትክክል እናውቃለን” ሲሉ ትራምፕ ጽፈዋል። "አሁን አንገድላቸውም ግን ትዕግሥታችን አብቅቷል" ሲሉ አክለዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
😁5431👎11👍5🤣2
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (....)
ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሰናል በቀጣዩ አመት የፕሪሚየር ሊግ ዘመን በመጀመሪያ ጨዋታ ይገናኛሉ

🚨🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 OFFICIAL: የ2025/26 የውድድር ዘመን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሙሉ መርሀግብር ይፋ ሆኗል።🔥🔥

በሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ ከአርሰናል በኦልድ ትራፎርድ ያገናኛል። 

በሌሎች የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታዎች የአምናው ሻምፕዮን ሊቨርፑል በአንፊልድ ከበርንማውዝ ፣ቶተንሀም ከበርንሌይ ፣ቼልሲ ከክሪስቲያል ፓላስ እንዲሁም ማንቸስተር ሲቲ ከወልቭስ ይገናኛሉ።

ቀሪዎቹን መርሀግብሮች ከታች መመልከት ትችላላችሁ።

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
22🔥5
2025/07/09 11:03:05
Back to Top
HTML Embed Code: