Telegram Web Link
በህገ- ወጥ መልኩ ከ2 ሺህ በላይ ፕላምፕሌት ይዞ የተገኘ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በሰቆጣ ከተማ በህገ- ወጥ መልኩ ፕላምፕሌት ከመጋዝን ውስጥ ይዞ የተገኘ ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት አስታወቀ።

የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤልያስ አስፋ  ነዋሪነቱ በሰቆጣ ከተማ 01 ቀበሌ ሲሆን ተከሳሽ አቶ ወንድሙ ቢክሰኝ በ2012 ዓ.ም የወጣው የኢፌድሪ ምግብና መድኃኒት አሥተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2012 አንቀጽ 67/4/ የተደነገገውን በመተላለፍ በምግብ እጥረት ለተጎዱ ህጻናት የመጣን 2ሺህ 1መቶ 83 ፕላምፕሌት ሚያዚያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡ 00 ሰዓት አካባቢ መጋዝን ውስጥ ይዞ  መገኘቱን ተከትሎ ክስ ተመስርቷል።

የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት የወንጀል ጉዳዮች ሥራ ሂደትም ከፖሊስ ተጣርቶ የቀረበለትን የምርመራ መዝገብ  በመያዝ በተከሳሽ  አቶ ወንድሙ ላይ ክስ መስርቶ  የሰቆጣ ወረዳ ፍርድ ቤት የፍርድ ብያኔ እንዲሰጠበት ጉዳዩን ሲከታተለው መቆየቱን አቶ ኤልያስ  ገልጸዋል።ፍትህ ጽ/ቤቱ በተከሳሽ አቶ ወንድሙ ላይ ያቀረበውን ክስ የሰቆጣ ወረዳ ሲያከራክር ቆይቶ ሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን ጥፋተኛ በማለት 2 ዓመት እስራትና 5ሺህ ብር እንዲቀጣና በኢግዚቪት የተያዘው 2ሺህ 1መቶ 83 ፕላፕሌትም ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ተወስኗል ሲሉ አቶ ኤልያስ ተናግረዋል።

የፍትህ ጽ/ቤት የተቋቋመው የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው ያሉት አቶኤልያስ ወንጀል ፈጽሞ ከህግ መሰወር የማይቻል መሆኑንም አስረድተዋል። በጤና ባለሙያዎች ከታዘዘለት ግለሰብ ውጭ ፕላምፕሌት ይዞ  የተገኘም ሆነ ሌሎች ወንጀሎችን የተፈጸሙ ማንኛውም ሰው በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን አውቆ ወንጀል ከመፈጸም ሊቆጠብ ይገባል ሲሉ ኃላፊው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል
ወደ ሰሜን ኮርያ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሩዝ እና ዶላር ሊልኩ የነበሩ አሜሪካውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ

የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት 1,300 የሚገመቱ የፕላስቲክ ጠርሙሶችን በሩዝ፣በዶላር እና በመፅሀፍ ቅዱስ በመሙላት ወደ ሰሜን ኮሪያ በባህር ሊልኩ ሲሞክሩ የነበሩ ስድስት የአሜሪካ ዜጎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የዜና ዘገባዎች አመልክተዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች የተያዙት አርብ ማለዳ ላይ ጠርሙሶቹን ከሰሜን ኮሪያ ጋር በተከለከለው የፊት ለፊት ድንበር አካባቢ አቅራቢያ ከሚገኘው ከጓንግዋ ደሴት ወደ ባህር ለመልቀቅ ሲሞክሩ ከተያዙ በኋላ ነው ሲል የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣን ዮንሃፕ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ስድስቱ ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት አካባቢውን የሚጠብቅ የባህር ዳርቻ ወታደራዊ ክፍል ለፖሊስ ካሳወቀ በኋላ ነው። ደቡብ ኮሪያ ከሰሜናዊ ድንበር አቋርጠው የሚመጠ የፕላስቲክ ጠርሙሶች ወይም የሚበር ፊኛዎች ላይ የሚላኩ ቁሳቁሶች በኮሪያ ልሳነ ምድር ላይ ውጥረት ፈጥረዋል። ዮንሃፕ እንዳለው ፀረ ፒዮንግያንግ ፕሮፓጋንዳ ወደ ሰሜን እንዳይጀምር የሚከለክል አስተዳደራዊ ትእዛዝ ለአካባቢው ተግባራዊ ሆኗል ።

እ.ኤ.አ. በ 2023 ፣ የደቡብ ኮሪያ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት የ 2020 በራሪ ወረቀቶችን እና ሌሎች እቃዎችን ወደ ሰሜን ኮሪያ መላክን ወንጀል የሚያደርግ ህግን የሻረ ሲሆን የመናገር ነፃነትን ከመጠን በላይ ይገድባል ብሏል ። ነገር ግን በጁን መጀመሪያ ላይ ስልጣን ከያዙ ወዲህ የፕሬዚዳንት ሊ ጄ-ሚንግ አዲሱ የሊበራል መንግስት ከሰሜን ኮሪያ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ለማስቀረት እና የግንባር ቀደምት የደቡብ ኮሪያ ነዋሪዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ እንዲህ ያሉ የሲቪል ዘመቻዎችን ከሌሎች ከደህንነት ጋር በተያያዙ ህጎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ እየሞከሩ ይገኛል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እስራኤል በዌስት ባንክ 'የግዳጅ ማፈናቀል' እየፈፀመች ነው አለ

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) በዌስት ባንክ ውስጥ በሚገኘው ማሳፈር ያታ አካባቢ በ3 የፍልስጤም ማህበረሰቦች የሚኖሩባቸው ሁሉም ህንፃዎች እንደሚወድሙ የእስራኤል ጦር ማሳሰቢያ አውጥቷል። ቢያንስ 1,200 ሰዎች፣ ከ500 በላይ ህጻናትን ጨምሮ፣ አሁን ወታደሮቹ ያቀዱትን የማፍረስ ተግባር ከፈጸሙ “በግዳጅ የመፈናቀል” ስጋት ላይ ናቸው ሲል ኦቻ ገልጿል።

በዌስት ባንክ ውስጥ ለፍልስጤማውያን የከፋ ሁኔታ በተመለከተ የቅርብ ጊዜ የኩነት ዘገባ እንዳመናከተው፣ ኦቻ ከሰኔ 13 እስከ 23 ባለው ጊዜ ውስጥ የእስራኤል ወታደሮች 240 የፍልስጤም ቤቶችን እንደ ወታደራዊ መጠለያ እና የምርመራ ማዕከላት ለመጠቀም ለጊዜው “እንደያዙ” ዘግቧል። የቤቶቹ ባለቤቶች በግዳጅ ተፈናቅለዋል ወይም ታስረዋል ሲልም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በወታደራዊው የቤት ወረራ ወቅት ገልጿል።

በዌስት ባንክ ቱልካሬም እና ኑር ሻምስ የስደተኞች መጠለያ ካምፖች 100 የሚጠጉ ግንባታዎች በተለይም ቤቶች በዚህ ወር በእስራኤል ወታደሮች ፈርሰዋል። በምስራቅ እየሩሳሌም ውስጥ ደግሞ 320 የሚጠጉ ነዋሪዎች በሶስት የፍልስጤም ማህበረሰቦች ውስጥ እንደገና የመፈናቀል እና የማፍረስ ዛቻዎች ተደቅኖባቸዋል ሲል ኦቻ አስታውቋል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
ኢትዮጵያ  ከፍተኛ ኃይል ከሚያመነጩ አስር የአፍሪካ ሀገራት ተርታ በሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ተባለ

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ኃይል እያመነጩ ካሉ አስር የአፍሪካ ሀገራት መካከል በሰባተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

በአገልግሎቱ ፕሮሰስ እና ኳሊቲ ማኔጅመንት ስራ አስፈፃሚ አቶ እሱባለው ጤናው ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በዘርፋ ከምርጥ አስር የአፍሪካ ሀገራት ተርታ ተመድባ ባታውቅም ከህዳሴ ግድብ ወዲህ ግን ኃይልን ከማመንጨት አንፃር የ7ኛ ደረጃን ይዛለች።

ከአፍሪካ ሀገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ ለዜጎቿ በፈረቃ ኤሌክትሪክን የምታዳርስ መሆኗን አንስተው እንደ ግብፅ፣ሞሮኮና አልጀሪያ ያሉ ሀገራት ደግሞ የተሻለ እና የተረጋጋ ኤሌክትሪክን ለዜጎቻቸው ከሚያዳርሱት መካከል ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።

ምንም እንኳን ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ከምርጥ አስር የአፍሪካ ሀገራት ተርታ ብትመደብም ካላት ሰፊ የህዝብ ቁጥር አንፃር እንዲሁም ወደ ኢንዱስትሪው ዘርፍ ለመሸጋገር ከምታደርገው ጥረት አኳያ የኤሌክትሪክ ዘርፋን ማሳደግ ይጠበቅባታል ሲሉ ስራ አስፈፃሚው  ጨምረው ተናግረዋል።በተለይም ደግሞ በቀጣይ ያላት የህዝብ ቁጥር እየጨመረ በሚመጣ ወቅት ኃይል የማመንጨት አቅሟን ይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባት ተጠቁሟል።

ቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ሰር ዴቪድ ቤካም ከ 23 አመት በፊት ለደረሰበት ጉዳት የቀዶ ህክምና አደረገ

ሰር ዴቪድ ቤካም ከ 23 አመት በፊት እንግሊዝ ከደቡብ አፍሪካ ባደረጉት ጨዋታ ለደረሰበት ጉዳት ከአመታት በኋላ የቀዶ ህክምና አድርጓል። ቤካም በእጁ ላይ በደረሰዉ በወቅቱ በጨዋታው ተቀይሮ ለመዉጣት የተገደደ የነበረ ቢሆንም ህክምናዉን ግን ከ 23 አመታት በኋላ ነዉ ያደረገዉ።

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
ዩናይትድ ስቴትስ ከጥቃቱ ምንም አላተረፈችም ሲሉ የኢራን ከፍተኛ መሪ ተናገሩ

የኢራን ጠቅላይ መሪ ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ማክሰኞ ዕለት ከተደረሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረጉት ንግግር አሜሪካ በቴህራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ በከፈቷቸው ጥቃቶች “ምንም ስኬት አላስገኘችም” ሲሉ አጥብቀው ተናግረዋል ። ጥቃቱ የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር ለማደናቀፍ ምንም አይነት ፋይዳ አላስገኘም ያሉት አያቶላህ አሊ ካሜኒ፣ በኳታር የሚገኘው የአሜሪካ የአየር ጦር ሰፈር ላይ የወሰድነው አጸፋም “ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት” ገልጸዋል። ኢራንን ይህንን ትበል እንጂ ጥቃቱ የኢራንን የኒውክሌር ምኞቷን በእጅጉ ጎድቷል ስትል ዋሽንግተን መናገሯ ይታወሳል።

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ፔት ሄግሥት በዩናይትድ ስቴትስ እና በእስራኤል የተሰበሰቡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ኦፕሬሽኑ "የኒውክሌር መርሃ ግብሩን በእጅጉ በመጎዳቱ ለአመታት ወደኋላ ኢራንን እንድትመለስ አድርጓል" ብለዋል።ከዚህ ቀደም የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ውስጥ በሦስት ቁልፍ የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን የገለፁ ሲሆን ጉዳቱ ከተጠበቀው ያነሰ ሊሆን እንደሚችል ስማቸው ያልተጠቀሰ የአሜሪካ ባለስልጣናት ተጠቅሶ የተሰራውን ዘገባ በቁጣ የሀሰት ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሃሙስ ማለዳ ላይ በፔንታጎን ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከከፍተኛ ጄኔራል ዳን ኬይን ጋር ንግግር ሲያደርጉ ሄግዝ እንደተናገሩት ተልእኮው “የኢራንን የማበልጸጊያ ተቋሞች ከስራ ውጪ ያደረጉ ታሪካዊ ስኬት” ነው ብለዋል። ካሜኔይ ትራምፕ የኒውክሌር ጣቢያ ጥቃቶች ያስከተለውን ተጽእኖ በተመለከተ የተናገሩት “የተጋነኑ” መሆናቸውን በመግለጽ “ምንም ነገር ማከናወን አልቻሉም እና አላማቸውን ማሳካት አልቻሉም” ብለዋል። በኳታር የሚገኘው የአሜሪካ የአየር ጦር ሰፈር ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በመጥቀስ ካሜኒ “ይህ ክስተት ወደፊትም ሊደገም የሚችል ነው፣ እናም ማንኛውም ጥቃት ቢደርስ ለጠላት እና ለአጥቂው የሚያስከፍለው ዋጋ በጣም ከፍተኛ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም” ብለዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በደቡብ ጎንደር ዞን ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ እንዳልተፈታ ተገለፀ

በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ መካነ ኢየሱስ ከሰሞኑን የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ በመቆየቱ ህብረተሰቡ ለከፍተኛ እንግልት  ተጋልጦ እንደነበር  የመካነ-ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ተጠሪ ጽ/ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።በዞኑ የኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ እሱባለው መስፍን ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በአካባቢው ተቋርጦ የነበረው የትራንስፓርት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ አልተፈታም።

በሁሉም አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ የትራንስፖርት ሊቋረጥ የቻለው በፀጥታ ችግር እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን  ይህም አሽከርካሪዎች ለከፍተኛ ድብደባ  ፣ግድያ እና እንደተጋለጡ ተነግሯል። ባለሀብቶች በንብረታቸው ማዘዝና በገንዘባቸው መጠቀም፤ ነጋዴዎች ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ ሸቀጣ ሸቀጥ ማቅረብ አለመቻላቸውም ተጠቅሷል።

በተጨማሪም የትራንስፖርት አገልግሎቱ በመቋረጡ የተነሳ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና ለማደናቀፍ ጥረት መደረጉን አቶ እሱባለው ገልፀው አሁን ላይ ተማሪዎች ፈተናው ወደ ሚሰጥበት ማዕከል መሄድ የሚችሉበት ሁኔታ መፈጠሩን ለጣቢያችን አስረድተዋል።እንደዚሁም የከተማው አስተዳደርና የወረዳው አመራሮች ከባለሀብቶችና አሽከርካሪዎች ጋር  ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
ኢራን በስለላ ወንጀል የተጠረጠሩ ተጨማሪ ሰዎች ማሰሯን አስታወቀች

የኢራን ሆርሙዝ ግዛት ባለስልጣናት ከእስራኤል ጋር ለ12 ቀናት በዘለቀው ጦርነት በስለላ ወንጀል ተሳትፎ የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፖሊስ ቃል አቀባይን ጠቅሶ የእስልምና ተማሪዎች የዜና አገልግሎት (ኢስና) ዘግቧል። ተጠርጣሪዎቹ በሆርሞዝጋን የስለላ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር የዋሉት በሀገሪቱ ውስጥ ሊነጣጠሩ ስለሚችሉ የጥቃት ለመምከር ከውጪ አካላት ጋር በመገናኘት ነው ሲል የፖሊስ ቃል አቀባይን ጠቅሶ ኢኤስኤንኤ ዘግቧል።

ወንድ እና ሴት ተጠርጣሪዎቹ መዋቢያዎችን በማስመጣት እና የሳተላይት ስልኮችን ለመጠገን በሚል ስም ተግባራቸውን ደብቀው እንደነበር የገለፀው ዘገባው፥ ለሥራቸውም “ከፍተኛ ገንዘብ” እንደተከፈላቸው ገልጿል። “መደበቂያ ቦታቸው” ላይ በተደረገ ፍተሻም የቴሌኮሙኒኬሽን መሳሪያዎች፣ እንዲሁም ጂፒኤስ እና ሳተላይት ስልኮች መገኘቱን ኢስና ዘግቧል።

የኢራን ባለስልጣናት በመላ ሀገሪቱ ሰፊ የጸጥታ ሃይሎችን በማሰማራት ከ700 በላይ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል በሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ላይ ስጋት ፈጥሯል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
የእስራኤል መከላከያ አዛዥ ነፍሰ ገዳዮች አያቶላህ ካሚኔይን ለመግደል ሲፈልጓቸው ነበር አሉ

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ ለእስራኤል ህዝብ በቀጥታ ስርጭት ባስተላለፉት መልእክት ቢቻል ኖሮ ወታደሮቹ የኢራንን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሚኒን ከቴህራን ጋር ለ12 ቀናት በዘለቀው ግጭት ውስጥ ይገድሉ እንደነበር ገልፀዋል።

ከእስራኤል ቻናል 13 ጋር ባደረጉት የተለየ ቃለ ምልልስ፣ ካትዝ የእስራኤል ኦፕሬተሮች ካሜኔን “ብዙ ፈልገዋል” ነገር ግን ጥቃት ለመፈጸም “የአሰራር እድል” ማግኘት አልቻሉም ብለዋል። የኢራን ባለስልጣናት ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ደካማ የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረግም እስራኤል ካሚኔይን ለመግደል እየፈለገች ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

በተጨማሪም ካትዝ ለቻናል 13 እንደተናገሩት "ኢራን የኒውክሌር መስሪያ ቤቶችን ዳግም የምታስጀምርበት ሁኔታ አይታይም" በዩናይትድ ስቴትስ እና በእስራኤል ሃይሎች ጥቃት ሳብያ ቴህራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የመገንባት አቅሟ "በአጠቃላይ ወድሟል" ብለዋል። ሆኖም ካሜኒ ከተኩስ አቁም ስምምነቱ በኋላ ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግራቸው የዩናይትድ ስቴትስ ጥቃቶች ለኢራን የኒውክሌር ፋሲሊቲዎች ምንም አይነት ፋይዳ አላሳዩም ብለዋል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (....)
ፒኤስጂ ሊዮንን ወደ ሁለተኛ ዲቪዚዮን እንዳይወርድ ለማዳን እየረዳ ነዉ ተባለ

ፒኤስጂ ሊዮንን ወደ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ከመውረድ ለማዳን እየረዳው ስለመሆኑ ተሰምቷል።

ክለቡ ብራድሌይ ባርኮላን በ 45+5 ሚሊዮን ዩሮ የፈረመውን የዝውውር ሂሳብ ቀደም ብሎ ከፍሏል።

ይህ እርምጃ ሊዮን የፋይናንስ አቋማቸውን እንዲያሻሽሉ አስችሎታል ተብሏል። ሊዮን ከሰሞኑ ባጋጠመዉ የፋይናንስ ቀዉስ ከፈረንሳይ ሊግ እንዲወርድ ተወስኖ ነበር።

የክለቡ ደጋፊዎችም በክለቡ ባለቤት አሜሪካዊዉ ባለሃብት ጆን ቴክስተር ላይ ተደጋጋሚ ተቃዉሞ ሲያሰሙ ነበር። ባለሃብቱ ከወራት በፊት ክለቡ እስከመዉረድ አይደርስም እንታደገዋለን ብለዉ የነበረ ቢሆንም ቃላቸዉን ሳይጠብቁ መቅረታቸዉ የሊዮንን ደጋፊዎች አስከፍቷል።

ክለቡ ይግባኝ አቅርቧል የተባለ ሲሆን ወደ ሊግ 1 እንደሚመለስ ተስፋ አድርጓል።

በስምኦን ደረጄ

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
ቅዳሜን ከእኛ ጋር" ፕሮግራም በተወዳጁ ብስራት ኤፍ.ኤም 101.1 ዛሬ ይመለሳል፤ ስንመለስ...

[ ] በልዩ ፕሮግራም ቅዳሜን ከእኛ ጋር ዛሬ የሬዲዮ ሞገዳችሁን 101.1 ላይ ካደረጋችሁ አብረን እንቆያለን።

[ ] የእስራኤል የረጅም ጊዜ መሪ ቤንያሚን ኔታንያሁ(ቢቢ) ማን ናቸው? በአክራሪ ብሄርተኝነታቸው የሚታወቁት ቢቢ ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ይስሃቅ ራቢን ግድያ ጋር በተያያዘ ለምን ስማቸው ይነሳል?

[ ] በራሪው ተወዳጁ የአዙሪ የግብ ዘብን ጂአንሉጂ ቡፎንን እናነሳለን።

[ ] የቅዳሜ ወሬዎችን እያነሳሳን እንቆያለን ምርጥ ምርጥ ሙዚቃ ትጋበዛላችሁ፤ ተረክም አለ ፣ ስፖርታዊ ጥንቅር ከወቅታዊ መረጃዎች ጋር ተዘጋጅቷል።

ስፖንሰሮቻችን ፦
👉 ዘመን ባንክ
👉 ቨርጂኒያ ፋርማሲውቲካልስ
👉 ጣዕም ዳቦና ኬክ ቤት-ሻወርማን ይቅመሱ
👉 ጃፋር የመፅሃፍት መደብር
👉ዲያፕላንትስ - ፍቱን የባህል ህክምና
👉 አውት ዲተርጀንት -የፅዳት መላ

ሁሌም ቅዳሜያችሁን ከ 5 እስከ 7 በተወዳጁ ጣቢያ ብስራት ኤፍ.ኤም 101.1 ላይ እንጠብቃችኃለን።

#ቅዳሜን ከእኛ ጋር
ለአዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎች ቴሌግራም ቻናላችንን #ዳጉ_ጆርናል ይቀላቀሉ
ሊንክ :- @zena24now
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
የቤኒቶ ሙሶሎኒ የልጅ ልጅ በቀጣይ አመት በጣሊያን ሴሪኤ ይጫወታል

የ22 አመቱ ሮማኖ ፍሎሪያኒ ሙሶሎኒ የውድድር ዘመኑን ከላዚዮ በሴሪ ቢ ጁቬ ስታቢያ በውሰት ተሰጥቶ አሳልፎ ነበር።

ተከላካዩ በአስደናቂ የውድድር ዘመን አሳልፏል የተባቤ ሲሆን ለጁቬ 37 ጨዋታዎችን አድርጓል።

በስታቢያ አስደናቂ የውድድር ዘመን ካሳለፈ በኋላ ክለቡ ላዚዮ የዉሰት ዉሉን በማቋረጥ ወደ ክለቡ እንዲመለስ አድርጓል። ጁቬ የመግዛት አማራጭ ባለዉ የዉሰት ዉላቸዉ መሰረት ተጨዋቹን ለመግዛት ጠይቀዉ ነበር። ሆኖም ላዚዮ ጥያቄዉን አልተቀበለውም።

ሙሶሎኒ ወደ ላዚዮ መንገዱን ከማግኘቱ በፊት በሮማ ወጣቶች አካዳሚ ውስጥ ጊዜ አሳልፏል።

እ.ኤ.አ. በ1943 ከስልጣን መመውደቁ እና በኋላም በ1945 ከመገደሉ በፊት የጣሊያን ፋሺስታዊ ገዥ ከነበረዉ ቅድመ አያቱ ተጨዋቹ እራሱን ለማራቅ ደጋግሞ ሞክሯል።

ስሙንም እስቀመቀየር ተገዶ እንደነበር ከዚህ ቀደም ዳጉ ጆርናል ስፖርት መረጃ አድርሷል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
የእግረኞች መንገድ ላይ በመኪና ሲያሽከረክር የተገኘው ግለሰብ 100 ሺህ ብር ተቀጣ

ትላንትና ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02፣ ቦሌ ማተሚያ ቤት አካባቢ በተገነባው የእግረኞች መንገድ ላይ በመኪና ሲነዱ የተገኙ ሁለት አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከእነዚህ ውስጥ አንዱ አሽከርካሪ 100,000 ብር ሲቀጣ፣ የሌላኛው ተሽከርካሪ ምርመራና ማጣራት እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል። ይህ የተደረገው ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር ሲሆን፣ መረጃው የተገኘውም ከህብረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ለህብረተሰቡ ላደረገው ትብብር ምስጋና ያቀረበ ሲሆን፣ በከተማዋ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ እና ደንብ የሚጥሱ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ህብረተሰቡ ጥቆማውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው::

#ዳጉ_ጆርናል
2025/07/01 12:54:51
Back to Top
HTML Embed Code: