Telegram Web Link
በደቡብ ጎንደር ዞን ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ እንዳልተፈታ ተገለፀ

በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ መካነ ኢየሱስ ከሰሞኑን የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ በመቆየቱ ህብረተሰቡ ለከፍተኛ እንግልት  ተጋልጦ እንደነበር  የመካነ-ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ተጠሪ ጽ/ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።በዞኑ የኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ እሱባለው መስፍን ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በአካባቢው ተቋርጦ የነበረው የትራንስፓርት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ አልተፈታም።

በሁሉም አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ የትራንስፖርት ሊቋረጥ የቻለው በፀጥታ ችግር እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን  ይህም አሽከርካሪዎች ለከፍተኛ ድብደባ  ፣ግድያ እና እንደተጋለጡ ተነግሯል። ባለሀብቶች በንብረታቸው ማዘዝና በገንዘባቸው መጠቀም፤ ነጋዴዎች ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ ሸቀጣ ሸቀጥ ማቅረብ አለመቻላቸውም ተጠቅሷል።

በተጨማሪም የትራንስፖርት አገልግሎቱ በመቋረጡ የተነሳ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና ለማደናቀፍ ጥረት መደረጉን አቶ እሱባለው ገልፀው አሁን ላይ ተማሪዎች ፈተናው ወደ ሚሰጥበት ማዕከል መሄድ የሚችሉበት ሁኔታ መፈጠሩን ለጣቢያችን አስረድተዋል።እንደዚሁም የከተማው አስተዳደርና የወረዳው አመራሮች ከባለሀብቶችና አሽከርካሪዎች ጋር  ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
ኢራን በስለላ ወንጀል የተጠረጠሩ ተጨማሪ ሰዎች ማሰሯን አስታወቀች

የኢራን ሆርሙዝ ግዛት ባለስልጣናት ከእስራኤል ጋር ለ12 ቀናት በዘለቀው ጦርነት በስለላ ወንጀል ተሳትፎ የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፖሊስ ቃል አቀባይን ጠቅሶ የእስልምና ተማሪዎች የዜና አገልግሎት (ኢስና) ዘግቧል። ተጠርጣሪዎቹ በሆርሞዝጋን የስለላ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር የዋሉት በሀገሪቱ ውስጥ ሊነጣጠሩ ስለሚችሉ የጥቃት ለመምከር ከውጪ አካላት ጋር በመገናኘት ነው ሲል የፖሊስ ቃል አቀባይን ጠቅሶ ኢኤስኤንኤ ዘግቧል።

ወንድ እና ሴት ተጠርጣሪዎቹ መዋቢያዎችን በማስመጣት እና የሳተላይት ስልኮችን ለመጠገን በሚል ስም ተግባራቸውን ደብቀው እንደነበር የገለፀው ዘገባው፥ ለሥራቸውም “ከፍተኛ ገንዘብ” እንደተከፈላቸው ገልጿል። “መደበቂያ ቦታቸው” ላይ በተደረገ ፍተሻም የቴሌኮሙኒኬሽን መሳሪያዎች፣ እንዲሁም ጂፒኤስ እና ሳተላይት ስልኮች መገኘቱን ኢስና ዘግቧል።

የኢራን ባለስልጣናት በመላ ሀገሪቱ ሰፊ የጸጥታ ሃይሎችን በማሰማራት ከ700 በላይ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል በሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ላይ ስጋት ፈጥሯል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
የእስራኤል መከላከያ አዛዥ ነፍሰ ገዳዮች አያቶላህ ካሚኔይን ለመግደል ሲፈልጓቸው ነበር አሉ

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ ለእስራኤል ህዝብ በቀጥታ ስርጭት ባስተላለፉት መልእክት ቢቻል ኖሮ ወታደሮቹ የኢራንን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሚኒን ከቴህራን ጋር ለ12 ቀናት በዘለቀው ግጭት ውስጥ ይገድሉ እንደነበር ገልፀዋል።

ከእስራኤል ቻናል 13 ጋር ባደረጉት የተለየ ቃለ ምልልስ፣ ካትዝ የእስራኤል ኦፕሬተሮች ካሜኔን “ብዙ ፈልገዋል” ነገር ግን ጥቃት ለመፈጸም “የአሰራር እድል” ማግኘት አልቻሉም ብለዋል። የኢራን ባለስልጣናት ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ደካማ የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረግም እስራኤል ካሚኔይን ለመግደል እየፈለገች ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

በተጨማሪም ካትዝ ለቻናል 13 እንደተናገሩት "ኢራን የኒውክሌር መስሪያ ቤቶችን ዳግም የምታስጀምርበት ሁኔታ አይታይም" በዩናይትድ ስቴትስ እና በእስራኤል ሃይሎች ጥቃት ሳብያ ቴህራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የመገንባት አቅሟ "በአጠቃላይ ወድሟል" ብለዋል። ሆኖም ካሜኒ ከተኩስ አቁም ስምምነቱ በኋላ ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግራቸው የዩናይትድ ስቴትስ ጥቃቶች ለኢራን የኒውክሌር ፋሲሊቲዎች ምንም አይነት ፋይዳ አላሳዩም ብለዋል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (....)
ፒኤስጂ ሊዮንን ወደ ሁለተኛ ዲቪዚዮን እንዳይወርድ ለማዳን እየረዳ ነዉ ተባለ

ፒኤስጂ ሊዮንን ወደ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ከመውረድ ለማዳን እየረዳው ስለመሆኑ ተሰምቷል።

ክለቡ ብራድሌይ ባርኮላን በ 45+5 ሚሊዮን ዩሮ የፈረመውን የዝውውር ሂሳብ ቀደም ብሎ ከፍሏል።

ይህ እርምጃ ሊዮን የፋይናንስ አቋማቸውን እንዲያሻሽሉ አስችሎታል ተብሏል። ሊዮን ከሰሞኑ ባጋጠመዉ የፋይናንስ ቀዉስ ከፈረንሳይ ሊግ እንዲወርድ ተወስኖ ነበር።

የክለቡ ደጋፊዎችም በክለቡ ባለቤት አሜሪካዊዉ ባለሃብት ጆን ቴክስተር ላይ ተደጋጋሚ ተቃዉሞ ሲያሰሙ ነበር። ባለሃብቱ ከወራት በፊት ክለቡ እስከመዉረድ አይደርስም እንታደገዋለን ብለዉ የነበረ ቢሆንም ቃላቸዉን ሳይጠብቁ መቅረታቸዉ የሊዮንን ደጋፊዎች አስከፍቷል።

ክለቡ ይግባኝ አቅርቧል የተባለ ሲሆን ወደ ሊግ 1 እንደሚመለስ ተስፋ አድርጓል።

በስምኦን ደረጄ

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
ቅዳሜን ከእኛ ጋር" ፕሮግራም በተወዳጁ ብስራት ኤፍ.ኤም 101.1 ዛሬ ይመለሳል፤ ስንመለስ...

[ ] በልዩ ፕሮግራም ቅዳሜን ከእኛ ጋር ዛሬ የሬዲዮ ሞገዳችሁን 101.1 ላይ ካደረጋችሁ አብረን እንቆያለን።

[ ] የእስራኤል የረጅም ጊዜ መሪ ቤንያሚን ኔታንያሁ(ቢቢ) ማን ናቸው? በአክራሪ ብሄርተኝነታቸው የሚታወቁት ቢቢ ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ይስሃቅ ራቢን ግድያ ጋር በተያያዘ ለምን ስማቸው ይነሳል?

[ ] በራሪው ተወዳጁ የአዙሪ የግብ ዘብን ጂአንሉጂ ቡፎንን እናነሳለን።

[ ] የቅዳሜ ወሬዎችን እያነሳሳን እንቆያለን ምርጥ ምርጥ ሙዚቃ ትጋበዛላችሁ፤ ተረክም አለ ፣ ስፖርታዊ ጥንቅር ከወቅታዊ መረጃዎች ጋር ተዘጋጅቷል።

ስፖንሰሮቻችን ፦
👉 ዘመን ባንክ
👉 ቨርጂኒያ ፋርማሲውቲካልስ
👉 ጣዕም ዳቦና ኬክ ቤት-ሻወርማን ይቅመሱ
👉 ጃፋር የመፅሃፍት መደብር
👉ዲያፕላንትስ - ፍቱን የባህል ህክምና
👉 አውት ዲተርጀንት -የፅዳት መላ

ሁሌም ቅዳሜያችሁን ከ 5 እስከ 7 በተወዳጁ ጣቢያ ብስራት ኤፍ.ኤም 101.1 ላይ እንጠብቃችኃለን።

#ቅዳሜን ከእኛ ጋር
ለአዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎች ቴሌግራም ቻናላችንን #ዳጉ_ጆርናል ይቀላቀሉ
ሊንክ :- @zena24now
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
የቤኒቶ ሙሶሎኒ የልጅ ልጅ በቀጣይ አመት በጣሊያን ሴሪኤ ይጫወታል

የ22 አመቱ ሮማኖ ፍሎሪያኒ ሙሶሎኒ የውድድር ዘመኑን ከላዚዮ በሴሪ ቢ ጁቬ ስታቢያ በውሰት ተሰጥቶ አሳልፎ ነበር።

ተከላካዩ በአስደናቂ የውድድር ዘመን አሳልፏል የተባቤ ሲሆን ለጁቬ 37 ጨዋታዎችን አድርጓል።

በስታቢያ አስደናቂ የውድድር ዘመን ካሳለፈ በኋላ ክለቡ ላዚዮ የዉሰት ዉሉን በማቋረጥ ወደ ክለቡ እንዲመለስ አድርጓል። ጁቬ የመግዛት አማራጭ ባለዉ የዉሰት ዉላቸዉ መሰረት ተጨዋቹን ለመግዛት ጠይቀዉ ነበር። ሆኖም ላዚዮ ጥያቄዉን አልተቀበለውም።

ሙሶሎኒ ወደ ላዚዮ መንገዱን ከማግኘቱ በፊት በሮማ ወጣቶች አካዳሚ ውስጥ ጊዜ አሳልፏል።

እ.ኤ.አ. በ1943 ከስልጣን መመውደቁ እና በኋላም በ1945 ከመገደሉ በፊት የጣሊያን ፋሺስታዊ ገዥ ከነበረዉ ቅድመ አያቱ ተጨዋቹ እራሱን ለማራቅ ደጋግሞ ሞክሯል።

ስሙንም እስቀመቀየር ተገዶ እንደነበር ከዚህ ቀደም ዳጉ ጆርናል ስፖርት መረጃ አድርሷል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
የእግረኞች መንገድ ላይ በመኪና ሲያሽከረክር የተገኘው ግለሰብ 100 ሺህ ብር ተቀጣ

ትላንትና ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02፣ ቦሌ ማተሚያ ቤት አካባቢ በተገነባው የእግረኞች መንገድ ላይ በመኪና ሲነዱ የተገኙ ሁለት አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከእነዚህ ውስጥ አንዱ አሽከርካሪ 100,000 ብር ሲቀጣ፣ የሌላኛው ተሽከርካሪ ምርመራና ማጣራት እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል። ይህ የተደረገው ከትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር ሲሆን፣ መረጃው የተገኘውም ከህብረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ለህብረተሰቡ ላደረገው ትብብር ምስጋና ያቀረበ ሲሆን፣ በከተማዋ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ እና ደንብ የሚጥሱ አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ህብረተሰቡ ጥቆማውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው::

#ዳጉ_ጆርናል
የ6ኛ ክፍል ተማሪ ሳለች ለእናቷ የገባችውን ቃል ያሳካችው ተመራቂ

የአብስራ ሽፈራው ትባላለች። የ6ኛ ክፍል ተማሪ ሳለች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በእናቷ ምርቃት ላይ ተገኝታ ነበር።

ያኔ ታዲያ "በዚህ ግቢ ተምሬ እመረቅበታለሁ" ስትል ለእናቷ ቃል ገብታላት ነበር።

እንሆ ዛሬ የአብስራ ያን ቃሏን አሳክታለች። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሳይኮሎጂ ትምህርት ክፍል 3.5 በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ በዲግሪ ተመርቃለች።

አካል ጉዳተኝነት ያልበገራት የአብስራ በመምህሮቿ የተመሰገነች ታታሪ ተማሪ ስትሆን፤ ለዚህ ስኬቷ ደግሞ የእናቷ አበርክቶ ትልቅ ድርሻ ይወስዳል።

በ4 ዓመታት የዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ እናቷ እርሷን በማመላለስ እና በማበረታታት ለዚህ አብቅታታለች።

የአብስራ እናት፥ "ልጆቻችን አካል ጉዳተኞች ናቸው ብለን በየቤቱ ደብቀን ይበልጥ ከምንጎዳቸው፤ መስዋዕት ከፍለን ካሰቡበት እናድርሳቸው" ስትል ለወላጆች መልዕክት አስተላልፋለች።

Via EBC
#ዳጉ_ጆርናል
በእስራኤል ኢራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ይመልከቱ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/W3o-tvV6238?si=TUJiSWsTiBjKxizo

#ዳጉ_ጆርናል
2025/06/30 00:48:49
Back to Top
HTML Embed Code: