Telegram Web Link
ዝክረ ሃጫሉ ሁንዴሳ...

ሃጫሉ ሁንዴሳ ተወልዶ ያደገው ከአዲስ አበባ በስተምዕራብ አንድ መቶ ኪሎ ሜትሮች ርቃ በምተገኘው አምቦ ከተማ ውስጥ ነው።

እናቱ ወይዘሮ ጉደቱ ሆራ፣ ሃጫሉ ከልጅነቱ ታሪክን መስማትና የመንገርና ዝንባሌውንና ችሎታውን ጠንቅቀው ተረድተውት ስለነበር ከመጀመሪያው አንስቶ ያበረታቱት እንደነበር በተደጋጋሚ ሃጫሉ ያስታውሳል።

አባቱ አቶ ሁንዴሳ ቦንሳ ደግሞ ልጃቸው ሃጫሉ በትምህርቱ ዓለም ገፍቶ ዶክተር ወይም የዩኒቨርሲቲተ መምህር እንዲሆንላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ነበራቸው።

ሃጫሉ ግን ገና ከልጅነቱ ጀምሮ በፍቅሯ ለወደቀላት ሙዚቃ ነበር መላው ትኩረቱ። በአስራዎቹ እድሜው ላይ እያለ እንኳን የበርካቶችን ስሜት የሚኮረኩሩ ሙዚቃዎችን ይጫወት ነበር።

ሃጫሉ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሳለ በ1995 ዓ.ም የ17 ዓመት ታዳጊ እንዳለ ታስሮ ለአምስት ዓመታት አምቦ በሚገኘው እስር ቤት አሳልፏል።

ፖለቲካዊ መልዕክት ያላቸውና ተወዳጅ የኦሮሞ የትግል ሙዚቃዎችን ማቀንቀኑን እንዲያቆም ለማድረግ መታሰሩን ሃጫሉ ይናገራል።

ነገር ግን መታሰሩ እንደውም ይበልጥ በሥራው እንዲገፋበትና በሰዎች ላይ የሚደርሰውን ግፍ እና ጭቆና የበለጠ እንዲገባው ማድረጉን በአንድ ወቅት ተናግሮ ነበር።

በእስር ላይ ሳለም ነበር የሙዚቃ ግጥሞችን ዜማዎችን መጻፍ የጀመረው። ከአምስት ዓመታት በኋላ ሲለቀቅ የደረሰበትን በደል ለመቃወምና ለሚሊየኖች ድምጽ ለመሆን ወስኖ እንደወጣ ይናገራል ሃጫሉ።

በአጭር ጊዜም በኦሮምኛ ተናጋሪው ሕዝብ ዘንድ ብቻ ሳይሆን በመላዋ አገሪቱ ተወዳጅ የሆነለትን 'ሳኚ ሞቲ' የተሰኘውን አልበሙ አቀረበ። የዚህ የሙዚቃ ስብስብ አብዛኛዎቹ ግጥሞችና ዜማዎች ሃጫሉ በእስር ላይ እያለ የሰራቸው እንደነበሩ ይነገራል።

በወቅቱ በሃያዎቹ መጀመሪያ የእድሜ ክልል ውስጥ የነበረው ሃጫሉም በዚህ አልበሙ በተለይ ደግሞ የአልበሙ መጠሪያ በነበረው ሙዚቃው ቋንቋውን በማይችሉ ሰዎች ዘንድም ታዋቂነትን ለማትረፍ ችሎ ነበር።

ከጥቂት ዓመት በኋላም ወደ አሜሪካ የሙዚቃ ሥራዎቹን ለማቅረብ በሄደበት ጊዜ ሁለተኛውንና "ዋኤ ኬኛ" አልያም "የእኛ ነገር" የሚል ትርጉም ያለውን አልበሙን ለቀቀ።

በወቅቱ አልበሙ አማዞን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ በመሸጥ ከፍተኛ ትኩረትን አግኝቶ የነበረ ሲሆን፤ የሃጫሉ ተወዳጅነትም የበለጠ እየተጠናከረ መጣ።

ሃጫሉ እንደሚለው "ሙዚቃ ለእኔ ህይወቴ ነው። ውስጤ ነው ያለው። የሕዝቤን የአኗኗር ዘዬ የማሳውቅበት፣ የሆዴን የምገልጽበት ነው። ሙዚቃ ሁሉ ነገሬ ነው፤ ዘመድም ጠላትም ያፈራሁበት።"

ሃጫሉ ተወዳጅ የሆኑ የኦሮሞ የሙዚቃ ስልቶችን ከዘመናዊው ሙዚቃ ጋር በማጣመር በሚያቀርባቸው ሥራዎቹ ብዙዎችን ጆሮና ቀልብ ለመማረክ አስችሎታል። በአገሪቱ የሚገኙ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ጣቢያዎችም ሙዚቃዎቹን በተደጋጋሚ በማጫወታቸው በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ዘንድ አድናቆትን ማግኘት ችሏል።

ከሦስት ዓመት በፊት በአገሪቱ ተቀስቅሶ ከነበረው የመንግሥት ተቃውሞ ጋር በተያያዘ በተለይ በኦሮሚያ ክልል ሲካሄድ በነበረው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ወቅት የሃጫሉ ያወጣው 'ማላን ጂራ' የተሰኘው ነጠላ ሙዚቃው ከፍተኛ ተወዳጅነትን ከማትረፍ አልፎ የእንቅስቃሴው መነቃቂያ ሆኖ ነበር።

ሃጫሉ የመንግሥት ባለስልጣናት በሚገኙባቸውና በቀጥታ በቴሌቪዥን በሚቀርቡ በትልልቅ የሙዚቃ መድረኮች ላይ በመገኘት ሙዚቃዎቹን በሚያቀርብበት ጊዜ ያለፍርሃት የሚሰማውን ፖለቲካዊ ጉዳዮችንም በማቅረብ በድፍረቱ ይታወቃል።

ባለትዳርና የሦስት ልጆች አባት የነበረው የ36 ዓመቱ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሰኞ ሰኔ 22/2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ በተፈጸመበት ጥቃት ህይወቱ አልፏል።

ሃጫሉ ህይወቱ ባለፈበት ወቅት በተነሳ ግርግር እና ረብሻ የበርካታ ኢትዮጵያዊያን ህይወት ማለፉም ይታወቃል።

Via Fast Mereja Showbiz
#ዳጉ_ጆርናል
#ጥቆማ

በዳጉ ጆርናል ዘገባዎች ላይ ሀሳብ እና አስተያየት ካላችሁ እንዲሁም ለዜና ጥቆማ ከፈለጋችሁን #በኢንስታግራም ገጻችን ላይ ባሻችሁ ሰዓት ብትፅፉልን ፈጣን ምላሽ እንሰጣለን

👇👇👇👇👇

https://www.instagram.com/sima_dereje?igsh=MmVtNHJmeW1qZnow

User Name - sima_dereje

#ዳጉ_ጆርናል
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
በተደረጉት 48 የአለም ክለቦች ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች ከ1 ሚሊየን በላይ ባዶ የስታዲየም መቀመጫዎች ነበሩ።

አጠቃላይ ከ 2.95 ሚሊዮን ተመልካቾችን የመያዝ አቅም ካላቸዉ ስታዲየሞች እስካሁን 1.67 ሚሊዮን ተመልካቾች ብቻ ተገኝቷል።

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስተር ቤንያሚን ኔታንያሁ ማን ናቸው?

በጋዜጠኛ ስምኦን ደረጄ


👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/yV_2fQu6dUc?si=_xpza7_TeE5B-_X8

#ዳጉ_ጆርናል
እኛ የምንላችሁን ካልተቀበላችሁ በቦንብ እንደበድባችኃለን ማለት የጫካ ህግ ነው ስትል ኢራን አስታወቀች

የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንደተናገሩት ዩናይትድ ስቴትስ ከኢራን ጋር ዲፕሎማሲያዊ ድርድር ለመቀጠል ከፈለገች ተጨማሪ ጥቃቶችን ማስቀረት አለባት ሲሉ ተደምጠዋል። ማጂድ ታክት ራቫንቺ የትራምፕ አስተዳደር ለኢራን በአስታራቂዎች በኩል ወደ ድርድር መመለስ እንደሚፈልግ ቢገልፅም ንግግሮች እየተካሄዱ ባለበት ወቅት ተጨማሪ ጥቃቶችን ስለመፈፀም ያላቸውን "አቋማቸውን ግልጽ አላደረጉም" ብለዋል። በሰኔ 13 መጀመሪያ ላይ የጀመረው የእስራኤል ወታደራዊ ዘመቻ፣ ከሁለት ቀናት በኋላ በሙስካት ሊካሄድ የነበረውን ስድስተኛ ዙር ቀጥተኛ ያልሆኑ ድርድር እንዳይካሄድ አፍርሷል።

ባለፈው ሳምንት ዩናይትድ ስቴትስ በእስራኤል እና በኢራን መካከል በተነሳው ግጭት ውስጥ በቀጥታ የተሳተፈች ሲሆን ሶስት የኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎችን በቦምብ አጥቅታለች።ታክት ራቫንቺ በተጨማሪም ኢራን ሰላማዊ ናቸው ላለችበት ዓላማዋ ዩራንየምን ማበልጸግ እንደምትችል ታምናለች በማለት ኢራን በድብቅ የኒውክሌር ቦምብ ለማምረት እየተንቀሳቀሰች ነው የሚለውን ውንጀላ ውድቅ አድርገዋል። ኢራን ለምርምር መርሃ ግብሯ "የኒውክሌር እቃዎችን እንዳታገኝ ተነፍጋለች"ና ስለዚህ "በራሳችን ላይ መታመን" አለብን ብለዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ "በዚህ ደረጃ መነጋገር ይቻላል፣ አቅሙን መወያየት ይቻላል፣ ነገር ግን ማበልጸግ አትችሉም ወይም ዜሮ ማበልጸግ በሚለው ካልተስማማችሁ ደግሞ በቦምብ እንመታችኋለን ማለት የጫካ ህግ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በአሜሪካ ጥቃት በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ላይ የደረሰው ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ ግልጽ ያልሆነ ሲሆን ታክት ራቫንቺ ትክክለኛ ግምገማ መስጠት እንደማይቻል አክለዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
2025/06/30 07:03:35
Back to Top
HTML Embed Code: