Telegram Web Link
ሐጫሉ አዋርድ የአንዱዓለም ጎሳን ሽልማት ነጥቆ ይቅርታ እንዲጠይቅ ተጠየቀ

የሐጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ አዘጋጅ የሆነው ሐጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳን ከሸለመ በኋላ በህዝቡ ቅሬታ አጋጥሞታል። በተለይ የሞዴል ቀነኒ አዱኛ ህይወቷ ከማለፉ በፊት ጥቃት ይደርስባት እንደነበር የሚያመለክቱ ምስሎች ከወጡ በኋላ በህዝቡ ዘንድ ቁጭት እና እልህ የታከለበት እንደ አዲስ ጉዳዩ እንዲነሳ ሆኗል።

የሞዴል ቀነኒ አዱኛ እጮኛ የነበረው ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ የተሸለመው ሽልማት ተነጥቆ ፋውንዴሽኑ በ24 ሰዓት ውስጥ ለህዝቡ መግለጫ እንዲሰጥ ዘመቻም ተጀምሯል።

Via ፋስት መረጃ
#ዳጉ_ጆርናል
አሜሪካ፤ ኢራን ከ አለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ጋር የነበራትን ትብብር ለማቆም ያሳለፈችው ​​ውሳኔ 'ተቀባይነት የለውም' አለች

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኢራን ከዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ተቆጣጣሪ ጋር ያላትን ትብብር ለማቆም መወሰኗ ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል። ውሳኔው የተሰማው እስራኤል በኢራን ላይ በከፈተችው ጦርነት እና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን የኒውክሌር ፋሲሊቲዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃቶችን ካደረገች በኋላ ነው።

የስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ታሚ ብሩስ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ኢራን የሰላምና የብልፅግና መንገድ መጠቀም እየቻለች ከኤጀንሲው ጋር ትብብሯን ለማቋረጥ መምረጧ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። አክለውም ኢራን ያለ ተጨማሪ መዘግየት ከኤጀንሲው ጋር ሙሉ በሙሉ መተባበር አለባት ሲሉ ተደምጠዋል።

አሜሪካ ምንም እንኳ ኢራን በዚህ መንገድ ለመጓዝ የምትመርጥ ከሆነ ሀገሪቱ የኒውክሌር ጦር መሳሪያን ለማበልፀግ ያላትን አቅም ወደ ኋላ የሚገታ ጥቃት ፈፅሜባታለው ብላ የምታምን ሲሆን ኤክስፐርቶች ደግሞ ጥቃቱ ኢራንን ወደ ኒውክሌር ጦር መሳሪያ መስራት ሊገፋፋት እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ።

ኢራን ከዚህ ቀደም የኒውክሌር ሃይል መርሃ ግብሯን የሚገድብ ስምምነት ለማድረግ ተስማምታ የነበረ ቢሆንም ዩናይትድ ስቴትስ ከስምምነቱ የወጣችው በትራምፕ የመጀመርያ የስልጣን ዘመን ወቅት ነው።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
ሱዌይስ ሞተርስ ቲክቶከር ሚስ ልዩን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ

የጀቱር ምርቶችን ጨምሮ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በሀገር ውስጥ በመገጣጠም ላይ የሚገኘው ሱዌይስ ሞተርስ ኩባንያ ወ/ሪት ልዩወርቅ መሃመድ (ሚስ ልዩን) የብራንድ የፊት ገጽ አድርጎ ሾሜል።

ሱዌይስ ሞተርስ ኩባንያ በአውቶሞቲቨ ኢንደስትሪ ውስጥ ቁልፍ ተሳታፊ በመሆን ባለፉት ዓመታት በነዳጅ እና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በሃገር ውስጥ በመገጣጠም በተመጣጣኝ ዋጋ ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ  የኩባንያው የሽያጭ ዘርፍ ስራ አስፈጻሚ አቶ መሃመድ አብዱልቃዲር ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ፡፡ 

ሱዌይስ ሞቶርስ ለሀገር ውስጥ ገበያ ከሚያቀርባቸው ተሽከርካሪ ውስጥ፣ JETOUR, SUZUKI, TATA, VICTORY እንዲሁም የሶስት እግር ተሽከርካሪ ምርቶችን የሚያቀርበው BAJAJ ይገኙበታል።

ለገበያው በተመጣጣኝ ዋጋ እና በበቂ ሁኔታ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የማከፋፈያ ማእከላትን ከፍቶ አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ይገኛል።

ይህንኑ ተደራሽነቱን ለማስፋት በማህበራዊ የትስስር ሚዲያዎች ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆነችውን ወ/ሪት ልዩወርቅ መሃመድን የማስታወቂያ እና የብራንድ የፊት ገጽ አድርጎ መምረጡ ተገልጿል ።

ሚስ ልዩ ወይም ልዪወርቅ መሃማድ በተለያዩ የማስታወቂያ ዘርፎች ላይ የተሳተፈች ስትሆን፣ በማህበራዊ ድረገፅ ላይ ማስታወቂየዎችን፣ በቴሌቭዝን አቅራቢነት፤ በፋሽን ዘርፍ ላይ ሞዴል በመሆን፣ እንዲሁም የግል ሀሳብዋን የኢቨንት ስራ ላይ ከዲጂታል ዶዝ ጋር በአጋርነት በመመስረት እና በማዘጋጀት፣ በኢትዮጵያ ተቀባይነት አግኝታለች።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ጆታ እና ወንደሙ አንድሬ ሲልቫ ነገ የቀብር ስነስርዓታቸዉ ይፈጸማል

የ28 አመቱ ዲዬጎ ጆታ እና የ26 አመቱ አንድሬ ሲልቫ የቀብር ስነ ስርአታቸው ቅዳሜ እለት እንደሚፈጸም ተሰምቷል። ጆታ የቀብር ስነስርዓቱ ፤ ሰርጉን በፈጸመበት በዚያው ስፍራ እንደሚሆን የአካባቢው ቄስ ጆሴ ማኑኤል ማሴዶ ተናግረዋል።

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
መስከረም ላይ ኢትዮጵያ ሁለት በዓል ታከብራለች

#GERD
#ዳጉ_ጆርናል
ሩሲያ ለአፍጋኒስታኑ የታሊባን መንግስት እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆነች

ሩሲያ የታሊባን አገዛዝ በይፋ እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች፤ የአፍጋኒስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሚር ካን ሙታቂ ውሳኔውን ደፋር  ሲሉ አሞካሽተዋል። በአፍጋኒስታን የሩሲያ አምባሳደር ዲሚትሪ ዚርኖቭን በትላንትናው እለት በካቡል ከሚኒስትሩ ጋር መክረዋል፣ አምባሳደር ዚርኖቭ ለአፍጋኒስታኑ ታሊባን መንግስታቸው እውቅና መስጠቱን በይፋ አሳውቀዋል። ሙታኪ “አዲስ የአዎንታዊ ግንኙነት፣ መከባበር እና ገንቢ መስተጋብር” መሆኑን ገልጸው ለውጡ ለሌሎች ሀገራት “አብነት” ይሆናል ብለዋል።

ታሊባን በነሀሴ 2021 ወደ ስልጣን ዳግም ከተመለሰ በኋላ በሰብአዊ መብት ላይ እየደረሰ ያለው ጥሰት እየጨመረ ቢመጣም አለም አቀፍ እውቅና እና ኢንቨስትመንትን አጥብቆ ይፈልጋል። ለአፍጋኒስታኑ የታሊባን መንግስት ይፋዊ እውቅና የመስጠቱ ተግባር በሀገራቱ መካከል ያለውን ውጤታማ የሁለትዮሽ ትብብር እንዲጎለብት ያደርጋል ብለን እናምናለን ሲሉ ሙታኪ አክለዋል። ሩሲያ በሃይል፣ በትራንስፖርት፣ በግብርና እና በመሰረተ ልማት ላይ "የንግድ እና ኢኮኖሚያዊ" ትብብርን እንደምታሳድግ እና ካቡልን የሽብርተኝነት እና የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎችን ስጋት ለመዋጋት መርዳቷን እንደምትቀጥል ተናግራለች።

ኤ.አ. በ 2021 በአፍጋኒስታን የሚገኘውን ኤምባሲያቸውን ካልዘጉ በጣም ጥቂት ሀገራት መካከል አንዷ ሩሲያ ስትሆን "ከካቡል ጋር ያለውን ውይይት ማስፋፋት" ከክልላዊ ደህንነት እና ኢኮኖሚያዊ እድገት አንፃር ወሳኝ መሆኑን ሞስኮ ገልጻለች ። ሀገሪቱ በተጨማሪም ዘይት፣ ጋዝ እና ስንዴ ለአፍጋኒስታን ለማቅረብ ተስማምታለች። ታሊባን ከሩሲያ የአሸባሪ ድርጅቶች ዝርዝር ውስጥ በዚህ አመት ሚያዝያ ወር ላይ የተፋቀ ሲሆን ከካቡል ጋር "ሙሉ አጋርነት" ለመመስረት መንገድ ለመክፈት በማሰብ በሚል መሆኑን የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው አመት ሀምሌ ወር ላይ ታሊባን ሽብርተኝነትን በመዋጋት "አጋር" ሲሉ ጠርተውታል፣ እ.ኤ.አ. በ2018 ተወካዮቹ ወደ ሞስኮ ለውይይት ተጉዘዋል። እ.ኤ.አ. በ1979 ሶቭየት ህብረት አፍጋኒስታንን ከወረረች በኋላ ለዘጠኝ አመታት ጦርነት ከፍታ 15 ሺ ወታደሮቿን ያጣች ሲህን በዚህም ሁለቱ ሀገራት ውስብስብ ታሪክ አላቸው። ሶቪየትች በመጨረሻም በየካቲት 1989 ከአፍጋኒስታን ለቀው ወጥተዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ማላዊ እና ሞዛምቢክ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ላይ ስምምነት ተፈራረሙ

ማላዊ እና ሞዛምቢክ የጋራ ወታደራዊ ልምምዶችን እና የጥበቃ ስራዎችን እንዲያደርጉ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ድንበር ተሻጋሪ ዕፅ እና ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመዋጋት ያለመ እርምጃው በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች “ግዙፍ እርምጃ” ሲሉ አወድሰዋል። የማላዊ የመከላከያ ሚኒስትር ሞኒካ ቺንግአናሙኖ እና የሞዛምቢክ አቻቸው ክሪስቶቫዎ ቹሜ በሞዛምቢክ ዋና ከተማ ማፑቶ በ 16 ኛው የሞዛምቢክ-ማላዊ የመከላከያ እና ደህንነት ቋሚ የጋራ ኮሚሽን በደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (ኤስ.ዲ.ሲ) ደቡብ አፍሪካ መከላከልን እና ወንጀሎችን ለመታገል የተቀናጀ እቅድ ሆኖ የጸደቀውን የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል።

በፊርማው ሥነ-ሥርዓት ላይ ሁለቱም ሀገራት ለድህነት እና ለኢኮኖሚያዊ እድገት እንቅፋቶች ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መጨመር ምክኒያት እንደሆነ ተናግረዋል። የማላዊ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን የሚከላከል የማላዊ ኔትወርክ ሊቀመንበር የሆኑት ሮድሪክ ሙሎኒያ ለአናዶሉ እንደተናገሩት በሀገሪቱ ያለውን መጥፎ ድርጊት ለመዋጋት ጥረት ቢደረግም ሁኔታው ​​​​አዳጋች ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል። ስለዚህ ይህ ስምምነት ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን በመዋጋት ረገድ ትልቅ እርምጃ ነው ነገር ግን ትግሉን ለማሸነፍ የተቀናጀ ጥረቶችን ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ይህንን ውጊያ ለማሸነፍ በእነዚህ ሁለት ሀገራት እና በቀጠናው ክልል ውስጥ ባሉ ሌሎች ሀገራት መካከል የቅርብ ትብብር ያስፈልጋል፤ ዘርፈ ብዙ አቀራረብን ማስገደድ አለብን ሲሉ ተደምጠዋል።እንደ አፍሪካ ሊጋል ኤድ ዘገባ ሁሉም የሳዲሲ አባል ሀገራት ህገ-ወጥ የሰዎች ማዘዋወር ለማገድ ህግን አውጥተዋል። ነገር ግን እነዚህ ጥረቶች ቢኖሩም በድህነት እና ውጤታማ ስትራቴጂዎች ትግበራ ውስንነት ምክንያት ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር አሁንም መቀጠሉን ድርጅቱ አስታውቋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ዜኒት ሴንት ፒተርስበርግ በኒኮ ዊሊያምስ ስም ለባርሴሎና ያበረከተዉ የገንዘብ ስጦታ እንዲመለስለት ጠየቀ

የሩሲያዉ ዜኒት ሴንት ፒተርስበርግ በባርሴሎና የቲክቶክ ገጽ ላይ ስጦታ (Gift) በኒኮ ዊሊያምስ ስም ስለማበርከቱ ዳጉ ጆርናል ስፖርት መረጃ አድርሶ ነበር።

የዜኒት ሴንት ፒተርስበርግ ይፋዊ የቲክቶክ ገጽ ባርሴሎና የሁዋን ጋርሲያን ፊርማ ይፋ ባደረገበት ልጥፍ ላይ "ከዜኒት ለኒኮ ዊሊያምስ" በማለት የጊፍት ስጦታ ልከዉ ነበር።

ታድያ በዛሬዉ እለት የባርሴሎና ደጋፊዎችን ጆሮ ጭዉ የሚያደርገዉ ዜና ከተሰማ በኋላ ዜኒት ገንዘቤን ማግኘት ችላለሁ ወይ ሲል ጠይቋል።

ኒኮ ለወራት ከባርሴሎና ጋር ስሙ ቢነሳም ፣ በደሞዝ ተስማምቷል ቢባልም ዛሬ ግን በተሰማ መሰረጃ በቢልባኦ ለ 10 አመታት ለመቆየት ከተስማማ በኋላ ነዉ ዜኒት ገንዘቤን መልሱ ያለዉ።

ባርሴሎና ከኒኮ ዊሊያምስ ጋር በግል ክፍያዎች ስምምነት ላይ ቢደርስም ቡድኑ ባለበት የፋይናንስ ችግር ፊርማዉን እንዳጣ ተገምቷል። ይህንንም ለማስተካከል ባርሴሎና ተጨዋች መሸጥ እንዳለበት ሲዘገብ ነበር።

ዜኒትም ገንዘቡን ማግኘት ይችል እንደሆነ ባርሴሎናን በኤክስ ገጹ ላይ ጠይቋል።

በበረከት ሞገስ

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባቱ እየከረረ በመምጣቱ አሜሪካ እና ኮሎምቢያ ዲፕሎማቶቻቸውን አስጠሩ

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኮሎምቢያ በኮሎምቢያ የግራ ክንፍ መሪ ላይ ተቃጥቷል የተባለውን ሴራ በመቃወም የየራሳቸውን ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በከፋው ግንኙነታቸው የተነሳ ወደ ሀገር ውስጥ አስጠርተዋል። ዋሽንግተን ዲሲ መጀመሪያ በኮሎምቢያ የሚገኙትን ሃላፊውን ጆን ማክናማራን ያስጠራች ሲሆን “ከኮሎምቢያ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የተሰጡ መሠረተ ቢስ እና ነቀፋዎችን መነሻ በማድረግ እርምጃ መውሰዷን” የውጭ ጉዳይ ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ታሚ ብሩስ ዝርዝር ጉዳዮችን ሳይጠቅሱ ተናግረዋል ።

ከማክናማራ ማስታወሻ በተጨማሪ ብሩስ ዩናይትድ ስቴትስ "በአሁኑ የሁለትዮሽ ግንኙነታችን ላይ ያለንን ጥልቅ ስጋት ግልጽ ለማድረግ ሌሎች እርምጃዎችን ትወስዳለች" ብለዋል ። በሰአታት ውስጥ የኮሎምቢያው ፕሬዝዳንት ጉስታቮ ፔትሮ በሰጡት የአፀፋ ምላሽ በዋሽንግተን ዲሲ ከፍተኛ ዲፕሎማታቸውን ወደ ሀገር ውስጥ ማስጠራታቸውን አስታውቀዋል። አምባሳደር ዳንኤል ጋርሺያ-ፔና "የሁለትዮሽ ውጥረቱን በተመለከተ ተገቢውን መረጃ ሊነግሩን መምጣት አለባቸው" በማለት ፔትሮ በኤክስ ላይ ጽፈዋል።

የዲፕሎማሲው ውጥረት የኮሎምቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለፈው ሐሙስ የሥራ መልቀቂያ በማስገባት ከፔትሮ መንግሥት የለቀቁ ከፍተኛ ባለሥልጣን ያደርጋቸዋል። "በቅርብ ቀናት ውስጥ እኔ የማልስማማባቸው ውሳኔዎች ተወስነዋል እናም ከግል ታማኝነት እና ተቋማዊ ክብር በመነሳት መደገፍ አልችልም" በማለት የፔትሮ የቀድሞ የሰራተኞች ዋና አዛዥ የነበሩት ላውራ ሳራቢያ በኤክስ ላይ ጽፈዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
የሳውዲ መከላከያ ሚኒስትር ከትራምፕ ጋር ከተገናኙ በኋላ ከኢራን ጦር አዛዥን ጋር በስልክ ተወያዩ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሳዑዲ መከላከያ ሚኒስትር ልዑል ካሊድ ቢን ሳልማን ጋር ሃሙስ እለት በዋይት ሀውስ በኢራን እና "በሌሎች ክልላዊ ጉዳዮች" ላይ መወያየታቸውን አክሲዮስ የዜና አውታር ዘግቧል።

ከስብሰባው በኋላ የሳውዲ አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን ታናሽ ወንድም ቢን ሳልማን የኢራን የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አብዶልራሂም ሙሳቪ ጋር በስልክ መነጋገራቸው ተዘግቧል።

የትራምፕ እና የቢን ሳልማን ውይይት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት የፊታችን ሰኞ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በዋይት ሀውስ ተቀብለው ለማነጋገር ጥቂት ቀናት ሲቀሩት የተካሄደ ነው።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
ፑቲን የትራምፕን የእርቅ ስምምነት ውድቅ በማድረግ በኪየቭ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ፈፀሙ

የዩክሬን ባለስልጣናት እንደገለፁት አርብ ጥዋት በኪዬቭ ከተማ ከሩሲያ ከባድ ጥቃቶች የተነሳ አየሩ በጭስ መሸፈኑን ገልፀዋል።የጨለማው ሰአታት በአየር መከላከያ ስርዓቶች ፣ በድሮኖች እና በትላልቅ ፍንዳታዎች ተደብድቧል። ዩክሬን እንዳስታወቀችው ሩሲያ 550 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና 11 ሚሳኤሎችን በመጠቀም የቦምብ ጥቃት መተኮሷን አስታውቃለች። ጥቃቱ የተካሄደው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የስልክ ውይይት ካደረጉ ከሰዓታት በኋላ ነው።

ትራምፕ ፑቲንን በዩክሬን ላይ ያለውን ጦርነት ለማስቆም ዝግጁ አለመሆናቸው በጣም እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል ። በሌላ በኩል የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ተከትሎ አንዲት ሴት በሩሲያ መገደሏን ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል።የሩስያ ደቡባዊ ሮስቶቭ ክልል ተጠባባቂ አስተዳዳሪ እንደተናገሩት ከዩክሬን ድንበር ብዙም በማይርቅ መንደር ላይ በተፈጸመ ጥቃት መሞቷን ተናግረዋል። የዩክሬን አየር ሃይል እንዳስታወቀው ራሺያ በአንድ ሌሊት ያካሄደችው የአየር ጥቃት ከፍተኛ ነው በማለት ክብረወሰን ሆኖ መመዝገቡን አስታውቋል።

ከ550 ሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት የፈፀሙ ሲሆን ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ከተመዘገበው 537 የበለጠ ነው። የአየር ኃይሉ የመልእክት መላላኪያ አፕሊኬሽኑ በቴሌግራም ላይ እንዳስታወቀው የአየር ወረራ ማንቂያዎች ከስምንት ሰአታት በላይ ተሰምቷል። የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ “ጨካኝ፣ እንቅልፍ አልባ ሌሊት” ሲሉ በመግለፅ ከጦርነቱ ዓመታይ ሁሉ በአሳዛኝ ሁኔታ ጉልህ ሆኖ የሚታየውን ጥቃት አውግዘዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
ቶማስ ፓርቴይ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ ተመሰረተበት

ቶማስ ፓርቴይ በአጠቃላይ በሁለት ሴቶች ላይ የ5 ጊዜ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እና በአንዲት ሴት ላይ የፆታዊ ትንኮሳ በማድረሱ ክስ መስርቷል።

የወንጀል ድርጊት ከ2021 እስከ 2022 ባለው ጊዜ ውስጥ ተፈፅሟል የተባለ ሲሆን ጉዳዩ በህግ እየታየ ይገኛል።

#ዳጉ_ጆርናል
2025/07/05 20:56:16
Back to Top
HTML Embed Code: