የየመን ሁቲዎች በእስራኤል አየር ማረፊያ ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈፀማቸውን ገለፁ
ሁቲዎች ቀደም ብሎ ወደ እስራኤል ከተተኮሰው ሚሳይል ጀርባ እጃቸው እንዳለበት አረጋግጠዋል፣ የእስራኤል ጦር በበኩሉ የተተኮሱትን ሚሳኤሎች ጠልፌ አምክኛለው ብሏል።
የሁቲ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ያህያ ሳሬ በቅርቡ በቴሌቭዥን ባስተላለፉት የተቀዳ መልዕክታቸው የየመን ቡድን ዞልፋሀር ባልስቲክ ሚሳኤል በቴል አቪቭ አቅራቢያ ወደ ሚገኘው የቤን ጉሪዮን አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ማስወንጨፉን ተናግረዋል።
ከ300 በሚበልጡ አከባቢዎች የአየር ወረራ ሳይረን እንዲሰማ በማድረግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጽዮናውያን ወደ መጠለያ ጣቢያ እንዲጣደፉ እና በአውሮፕላን ማረፊያው የአየር ትራፊክ እንዲቆም በማድረጋቸው “ዓላማውን በተሳካ ሁኔታ መቷል” ሲሉም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።
ሳሪ ሁቲዎች በእስራኤል ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት እንደሚቀጥሉ እና ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ያላቸውን በቀይ ባህር ላይ የሚጓጓዙ መርከቦች ላይም በጋዛ "እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እስካልቆመ ድረስ" እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።
የእስራኤል ጦር በበኩሉ ከየመን የተወነጨፈ ሚሳኤል መጥለፉን የተናገረ ሲሆን ሚሳኤሎቹ ግን በቴል አቪቭ እና በእስራኤል ሌሎች አካባቢዎች የአየር ወረራ ሳይረን እንዲሰማ ምክንያት ሆነዋል።
በሕዝብ ብዛት ያለውን የየመንን ክፍል የተቆጣጠሩት የሁቲ አማፅያን በጋዛ ከሚገኙ ፍልስጤማውያን ጋር የመተባበር ተግባር ነው ሲሉ በእስራኤል ላይ እየተኮሱ እና የመርከብ መንገዶችን እያጠቁ ነው። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ እስራኤል በየመን የወደብ ከተማ ሆዴይዳህ ላይ ጥቃት መፈፀሟ ይታወሳል።
በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል

👏67❤14👎8👍6😁2🕊1
በ2018 የትምህርት ዘመን ከ100 እስከ 260 በመቶ ጭማሪ የጠየቁ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን ተነገረ
የአዲስ አበባ ትምህርት ጥራት ባለስልጣኑ በ2018 የትምህርት ዘመን የአገልግሎት ክፍያ ጭማሪ ላይ ከተማሪ ወላጆች ጋር ባልተስማሙና በልዩነት ባጠናቀቁ ት/ቤቶች ላይ በአገልግሎት ክፍያ አሰራር ስርዓት ደንብ ቁጥር 194/2017 መሰረት ውሳኔ አስተላልፏል ።
ጉዳዩን አስመልክቶ በተደረገ ውይይት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ የሆኑት ዶክተር ዘላላም ሙላቱ እንደገለጹት እንደየ አካባቢውና እንደየ ማህበረሰቡ ሁኔታ በርካታ ት/ቤቶችና ወላጆች በጋራ በመወያየት የክፍያ ጭማሪውን አጽድቀው በጋራ በመግባባት ተለያይተዋል፡፡ ባልተስማሙ ት/ቤቶችና ወላጆች ላይ ደግሞ ባለስልጣኑ የውሳኔ አካል በመሆን በጋራ በመምከር ውሳኔውን አስቀምጧል፡፡
በትምህርት አገልግሎት ክፍያ አሰራር ስርዓት ደንብ መሰረት ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑ ት/ቤቶች ከወላጆች ጋር በመግባባት የተስማሙ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ባለመስማማታቸው አቤቱታቸውን ለባለስልጣኑ ማቀረባቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል። በዚህ መሰረት ባለስልጣኑ የወላጆችንም የመክፈል አቅም የትምህርት ተቋማቱንም ስራቸውን በአግባቡ የማስቀጠል አቅም ሚዛናዊ በማረድግ ውሳኔውን እንደሚያሳልፍ ገልጸዋል፡፡
ተቋማቱ ያቀረቡትን የጣራ ክፍያ፣በውይይቱ ወቅት ወላጅ ያቀረበውን ዋጋ፣እንዲሁም ባለስልጣኑ ያስተላለፈውን እያንዳንዱን የክፍያ ውሳኔ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ ውሳኔውንም ለት/ቤቶቹ በደብዳቤ እንደሚሠጥ ተገልጿል ፡፡
በተጨማሪም ምክንያታዊ የሆኑ ጭማሪዎች አስፈላጊ መሆናቸውን የገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በሌላ በኩል ከ100 እስከ 260 በመቶ ጭማሪ የጠየቁ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን መግለጹን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።
በኤደን ሽመልስ

👎16❤11👍4😱2
ለፊልም ጥበብ አፍቃሪያን ልዩ የአጭር ጊዜ ስልጠና ማዘጋጀቱን ልቀት ኮሌጅ አስታወቀ
👉ተ ወዳጅና ታዋቂ የፊልም ተዋንያንና ዳይሬክተሮች ስልጠናውን ይሰጣሉ
የፊልም ትምህርትን በዲግሪ ደረጃ ለማስተማር ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመጀመሪያና ብቸኛ የሆነው ልቀት ኮሌጅ ለ2017 ክረምት አጭርና እጅግ ውጤታማ የስልጠና መርሐ ግብር ማዘጋጀቱን ጠቁሟል ።
ስልጠናውን በአክቲንግ የስልጠና ዘርፍ ተዋናይ ግሩም ኤርሚያስ፣ በዳይሬክቲንግ ስልጠና ዳይሬክተር ሄኖክ አየለ፣ በሲኒማቶግራፊ ዘርፍ ሲኒማቶግራፈር ቢሊ መኮንን እንዲሁም ለስክሪን ፕሌይ ራይቲንግ ስልጠና የፊልም መምህሩ ዮሴፍ ሀይሉ ይሰጣሉ።
ስልጠናው በመጪው ቅዳሜ ሀምሌ 12 ቀን 2017 ዓ.ም መሰጠት የሚጀምር ሲሆን ቅዳሜና እሁድ በቀን መርሐ -ግብር ለተከታታይ ሳምንታት ይሰጣል።
ስልጠና መውሰድ የሚፈልጉ አራት ኪሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ጀርባ ኢክላስ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኮሌጁ አድራሻ በመምጣት ወይም
📱በ0984717144 እና በ0940089999 መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

❤14👍8
ከሰሜን ኮርያ የከዳች አንዲት ግለሰብ በኪም ጆንግ ኡን ላይ ክስ መሰረተች
ሰሜን ኮሪያ ከድታ የወጣች አንዲት ግለሰብ የሀገሪቱ መሪ ኪም ጆንግ ኡን እና ሌሎች አራት የፒዮንግያንግ ባለስልጣናት ላይ በእስር ላይ በነበረችበት ጊዜ ላደረሱባት ግፍ የፍትሐ ብሔር እና የወንጀል ክስ መስርታለች።ቾይ ሚን ክዩንግ ከሰሜን ኮሪያ ወደ ቻይና እኤአ በ1997 ተሰዳለች ነገር ግን በ2008 በግዳጅ ወደ ሀገሯ እንድትመለስ ሆኗል። ከተመለሰች በኋላ የፆታ ጥቃት እና እንግልት እንደደረሰባት ተናግራለች።
በመጪው አርብ በሚቀርበው ክስ አንድ የሰሜን ኮሪያ ተወላጅ ሀገሪቱን ከድቶ በገዥው አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ ሲወስድ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ሲል በደቡብ ኮሪያ መቀመጫውን ያደረገው እና ወይዘሮ ቾን የሚረዳ የመብት ተሟጋች ቡድን አስታውቋል። የደቡብ ኮሪያ ፍርድ ቤቶች ቀደም ባሉት ጊዜያት በደቡብ ኮሪያውያን ላይ በሰሜን ኮርያ አገዛዝ የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን በመቃወም ውሳኔ ሰጥተው ነበር። ነገርግን እንደዚህ አይነት የፍርድ ውሳኔዎች በአብዛኛው ተምሳሌታዊ ሲሆን በፒዮንግያንግ አገዛዝ ዘንድ ደግሞ ችላ ተብለዋል።
የመብት ተሟጋቹ የሰሜን ኮሪያ የሰብአዊ መብቶች ዳታ ቤዝ ማዕከል (NKDB) በተጨማሪም የወ/ሮ ቾይ ጉዳይን ወደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለመውሰድ እቅድ እንዳለው ይፋ አድርጓል። “ይህች ትንሽ እርምጃ ለነጻነት እና ለሰብአዊ ክብር መመለስ የማዕዘን ድንጋይ እንድትሆን ከልቤ እመኛለሁ፤ በዚህም ከአሁን በኋላ ንጹሃን ሰሜን ኮሪያውያን በዚህ አረመኔ አገዛዝ እንዳይሰቃዩ ይረዳል” ስትል ወይዘሮ ቾይ መናገሯን ማዕከሉ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። "ከሰሜን ኮሪያ አገዛዝ የተረፈች ሰለባ እንደመሆኔ፣ የኪም ስርወ መንግስት በሰው ልጆች ላይ ለሚፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂ ለማድረግ ጥልቅ እና አስቸኳይ ሀላፊነት እወስዳለሁ" በማለት አክላለች።
በስምኦን ደረጄ

❤24😁18🤔4🔥2
የ12 ዓመት ታናሽ እህቱ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ ቦላ ሃንጋጫ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኡሩቃ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ተከሳሽ የግል ተበዳይ የሆነችውን የ12 ዓመት ታዳጊ እህቱን በማታለል ወደ ጫካ በመውሰድ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈጸሙን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
የቁጫ ወረዳ ፖሊስ ጥቆማ ሲደርሰው ከወረዳው ሴቶች እና ህጻናት ልዩ ምርመራ እና ክስ ጉዳዮች ክትትል ዐቃቤ ህግ ጋር በጋራ በመሆን ምርመራ ካጣራ በኋላ የምርመራ መዝገቡን ለቁጫ ወረዳ ዐቃቤ ህግ ይልካል። ምርመራ መዝገቡ የደረሰው ዐቃቤ ህግም መዝገቡን መርምሮ ሰኔ 20 ቀን በወንጀል ህግ አንቀጽ 627(1) መሠረት ክስ መስርቶ ለቁጫ ወረዳ ፍ/ቤት ያቀርባል ።
ፍርድ ቤቱም በሰኔ 24 ቀን የዐቃቤ ህግ ክስ ካሰማ በኋላ ተከሳሹ የዕምነት ክህደት ቃሉን ተጠይቆ የወንጀል ድርጊቱን ሙሉ በሙሉ መፈጸሙን በዝርዝር ያመነ በመሆኑ ለፍርድ በተቀጠረበት ዕለት በሰጠው የዕምነት ቃል መሠረት ተከሳሹን ጥፋተኛ ነው ሲል ፍርድ ሰጥቷል፣
የጥፋተኝነት ፍርዱን ተከትሎ ፍ/ቤቱ ከግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየት ከተቀበለ በኋላ በቀን 01/11/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን በ 15 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በሳምራዊት ስዩም

🤬47💔14❤13🤔4
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
የአርሰናል ደጋፊዎች ክለባቸዉ ማዱኬን እንዳያስፈርም ፊርማ ማሰባብ ጀምረዋል።
ማዱኬ ከአርሰናል ጋር የ 5 አመት ዉል ለመፈረም የተስማማ ሲሆን በግል ክፍያዎችም ከክለቡ ጋር ተስማምቷል።
አርሰናልም ከቼልሲ ጋር በይፋ ድርድር ጀምሯል። ሆኖም የአርሰናል ደጋፊዎች ፊርማዉን እየተቃወሙ ነዉ።
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport

😁26❤10👍8
አሜሪካ የመንግስታቱ ድርጅት ባለሙያ ፍራንቼስካ አልባኔዝን በእስራኤል ትችት በመሰንዘሯ ማዕቀብ ጣለችባት
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤክስፐርት ፍራንቼስካ አልባኔዝ ላይ እስራኤል በጋዛ ላይ ባካሄደችው ጦርነት በፍልስጤማውያን ላይ ያደረሰችውን በደል በመተቸቷ ማዕቀብ ጥሏል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እንዳስታወቁት አልባኒዝ "በዩናይትድ ስቴትስ እና በእስራኤል ላይ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጦርነት ዘመቻ" አድርገዋል ሲሉ ተደምጠዋል።
በተያዘው የፍልስጤም ግዛት ላይ የተባበሩት መንግስታት ልዩ ተጠሪ ሆኖ የምታገለግለው አልባኒዝ የእስራኤልን የሰብአዊ መብት ረገጣ ለማስቆም እርምጃ እንዲወስድ በመጠየቅ ግንባር ቀደም ድምጽ ሆናለች። እስራኤል እና ደጋፊዎቿ አልባኔዝ ሲወቅሱ እና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስልጣኗ እንድትነሳ ለዓመታት ሲጠይቁ ቆይተዋል። አልባኒዝ ስራዋን ለመቀጠል ትኩረት እንደሰጠች እና የዩናይትድ ስቴትስን ማዕቀብ ውድቅ ማድረጓን አስታውቃለች። የተባበሩት መንግስታት ኤክስፐርቷ በጽሑፍ መልእክት ላይ "በማፊያ ስልት ላይ ምንም አስተያየት የለም" ብላለች። “አባል ሀገራት የዘር ማጥፋት ወንጀልን የማስቆም እና የመቅጣት ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል ስትል አክላለች።
በጋዛ በጦር ወንጀል ተከሰው በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (ICC) የሚፈለጉት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ወደ አሜሪካ በሚጓዙበት ጊዜ የአየር ክልላቸውን እንዲጠቀሙ የፈቀዱ የአውሮፓ መንግስታትን ኮንናለች። "የጣሊያን፣ የፈረንሳይ እና የግሪክ ዜጎች እያንዳንዱን የፖለቲካ እርምጃ ህጋዊ ስርዓቱን የሚጥስ፣ ሁሉንም የሚያዳክም እና አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን ማወቅ ይገባቸዋል ስትል አክላለች። ትራምፕ እስራኤል ላይ "በማነጣጠር" በተሳተፉ የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ICC ባለስልጣናት ላይ ቅጣት እንዲጣል በየካቲት ወር የስራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ መፈረማቸው ይታወሳል ።

👎60❤22👍3
ሀሰተኛ ባለ ሁለት መቶ ብር ወደ ባንክ ለማስገባት የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በዳውሮ ዞን የገሳ ጫሬ ከተማ አስተዳደር ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ሀሰተኛ ባለ ሁለት መቶ ሃያ ሺህ አራት መቶ ብር ወደ ባንክ ለማስገባት የሞከረው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል፡፡
ፖሊስ ከግለሰቡ ቃል እንዳረጋገጠው ተከሳሽ ወይፈን በሬ ሸጦ በግብይት ላይ እንደሰጡት የገለፀ ቢሆንም በህጉ መሠረት በእጁ የተገኘበት በአዘዋዋሪነት ወንጀል ይጠየቃል ሲል አስታውቋል፡፡
ፖሊስም የአርሶ አደሩ፣ሻጭና ሸማቾች የሚቀበሉትን ገንዘብ አጣርቶ መቀበል እንዳለባቸዉና ህብረተሰቡ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያገጥመው ለፀጥታ ኃይሉ በማሳወቅ የተለመደ ትብብሩን ማሳወቅ አለበት ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

❤30😁12👎10😭5👍2👏1🤬1
ትራምፕ በሱዳን ሰላም እንዲሰፍን ግፊት አደርጋለሁ አሉ
ትራምፕ በዋይት ሀውስ ከላይቤሪያ፣ ሴኔጋል፣ ጋቦን፣ ሞሪታኒያ እና ጊኒ ቢሳው መሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት "እንደ ሱዳን ባሉ አካባቢዎች ሰላምን እያመቻቸን ነው" ብለዋል። የፕሬዚዳንቱ አስተያየት የትራምፕ የአፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት ማሳድ ቡሎስ ባለፈው ሳምንት የሰጡትን መግለጫ ተከትሎ የተሰማ ነው። ቡሎስ በጁላይ 2 በአሻርክ ቲቪ ባሰራጨው ቃለ ምልልስ ዩናይትድ ስቴትስ የ"ኳርትትን" ተነሳሽነት ለማነቃቃት ከሳዑዲ አረቢያ፣ ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እና ከግብፅ የተውጣጡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን በዋሽንግተን በቅርቡ እንደሚያስተናግዱ ተናግረዋል።
ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣን ለሱዳን ትሪቡን እንደተናገሩት ከሆነም "ዩናይትድ ስቴትስ በሱዳን ያለውን ቀውስ ለመፍታት፣ ከተፋላሚ ወገኖች ጋር በመነጋገር እና ከዓለም አቀፍ አጋሮቻችን ጋር በማስተባበር ግጭቱ በዘላቂነት እንዲፈታ ለማድረግ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ጦርነቱ ከባድ ሰብዓዊ ቀውስ ፈጥሯል። የዩኤስ ባለስልጣን ዕርዳታ ፍሰቱን እንደቀጠለ አረጋግጠዋል፣ “ከ65,000 ሜትሪክ ቶን በላይ የአሜሪካ የጅምላ የስንዴ እህል እና የስንዴ ዱቄት በቅርቡ ወደ ፖርት ሱዳን ደርሰዋል” በማለት ለአንድ ወር ያህል 3.2 ሚሊዮን ሰዎችን ለመመገብ በቂ መሆኑን ገልፀዋል። ወደ ሰባት ጎረቤት ሀገራት ለተሰደዱ ከአራት ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎችም እርዳታ እየተደረገ መሆኑን ባለስልጣኑ ጨምረው ተናግረዋል።
ባለሥልጣኑ "የሰብአዊ እርዳታ ሰጪዎችን ደህንነት በማረጋገጥ እና ሲቪሎችን መጠበቅን ጨምሮ ሰብአዊ እርዳታን ያለመስተጓጎል እንዲገባ ማስቻል እንደሚያስፈልግ በድጋሚ እንገልፃለን" ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መልዕክተኛው ከአፍሪካ ህብረት ጎን ለጎን በኢትዮጵያ የተለያዩ ውይይቶችን ለማድረግ እቅድ እያጠናቀቀ መሆኑን አስታውቋል።

❤23😁18👎2👍1
ከ4.2 ሚሊየን ህዝብ በላይ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ኢንሹራንስ እንዲኖረው መደረጉ ተገለፀ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን የክልሉ ህብረተሰብ የጤና ኢንሹራንስ እንዲኖረው የተሰራው ስራ ውጤታማ እንደሆነ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ገልፀዋል። በ2017 በጀት ዓመት የህብረተሰቡን የጤና ኢንሹራንስ ለማረጋገጥ በተሰራው ጠንካራ ስራ ከክልሉ ህዝብ ውስጥ 80 በመቶ ወይም ከ4.2 ሚሊየን ህዝብ በላይ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ኢንሹራንስ እንዲኖረው ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
ከ4.2 ሚሊየን የጤና የኢንሹራንስ ተጠቃሚ የክልሉ ህዝብ ውስጥ 252ሺ 901 የጤና መድህን አባላት መክፈል የማይችሉ መሆናቸውን አስታውቀዋል። በክልሉ ለጤና ኢንሹራንስ አገልግሎት የሚውል ከ624 ሚሊየን ብር በላይ ከአባላት በመሰብሰብ ወደ ባንክ የገባ መሆኑን ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡ በበጀት አመቱ የክልሉ ህዝብ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ኢንሹራንስ እንዲኖረው ከማድረግ ጎን ለጎን አገልግሎት ሳይቆራረጥ አመቱን ሙሉ መስጠት የሚያስችል ስርዓት መዘርጋቱም አስታውሰዋል፡፡
ይህም ዞናል የፋይናንስ ቋት መመስረት ላይ በተሰራው ስራ በበጀት አመቱ ሶስት ዞኖች ማለትም ሀላባ ፣ የም እና ምስራቅ ጉራጌ ዞኖች ሙሉ ለሙሉ ስራ ያስጀመሩ ሲሆን ሌሎች ዞንም በጥሩ ደረጃ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ አመት ወደ ሙሉ ትግበራ ይገባልም ብለዋል፡፡ ይህ ስርዓት ከዚህ በፊት በክፍያ እና በፋይናንስ ችግር ይፈጠር የነበረውን ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እና የአገልግሎት መቆራረጥ በመቅረፍ አመቱን ሙሉ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችል ስርዓት መሆኑን ገልጸዋል።
በዞናል ቋት የተሻለ ከተፈፀሙ ዞኖች ውስጥ በሀላባ ዞን የፌደራልን ጨምሮ ከኦሮሚያ ፣ አማራ ፣ ሲዳማ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች እና ሌሎችም የተውጣጣ ቡድን የልምድ ልውውጥ ማድረጉ በበጀት ዓመቱ በክልሉ የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት ላይ ለአገር ልምድ የሚሆኑ ተግባራት የተፈጸመበት መሆኑን ማንሳታቸውን ብስራት ሬድዮ ከክልሉ ጤና ቢሮ ኮሙኒኬሽን ያገኘው መረጃ ያስረዳል።
በሰብል አበበ

❤13🤔1
ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት እሴት ከተጨመረባቸው የእንስሳት ምርቶችና ውጤቶች 120 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ አገኘች
ኢትዮጵያ በበጀት አመቱ የተለያይ የተቀነባበረ የእንስሳት ምርቶችን ለውጪ ገበያ ማቅረቧን የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዮት አስታውቋል።በኢንስቲትዮቱ የሶሺኦ ኢኮኖሚክስና እሴት ሰንሰለት አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ሳህሉ ሙሉ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በዉጪ ገበያ ከተላኩት ምርቶች መካከል የበግና የፍየል ስጋ ፣የግመል ስጋና ወተት፣ ማርና ሰምን ጨምሮ ሌሎችም ተጠቃሽ ናቸው።
በምርቶቹ ላይ እሴት በመጨመር በማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች እንዲቀነባበሩ ተደርገው 24 ሺህ 2 መቶ 65 ቶን ምርቶች ለገበያ እንዲቀርቡ ተደርጓል ያሉት ዶክተር ሳህሉ 112 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ነበር ብለዋል።ለሽያጭ ከቀረቡት ምርቶች መካከል 99 በመቶውን ድርሻ የስጋና እርድ ተረፈ ምርት መያዙን ገልፀው በምላሹ 120 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ተገኝቷል በማለት ዶክተር ሳህሉ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ይህ አፈፃፀም ከእቅድ በላይ ገቢ የተገኘበት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን የምርምር ስራን በማከናወን በዘርፋ ያሉትን ችግሮች መፍታት መቻሉና ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪዎች የተለያዩ ድጋፎች መደረጋቸው አስተዋፅኦ አድርገዋል።ኢትዮጵያ የስጋ ምርቶችን በዋናነት ወደ ገልፍ ሀገራት ለሽያጭ እንደምታቀርብ ተገልጿል።
በቅድስት ደጀኔ

❤21🤬4🤔2
በተያዘዉ ዓመት ከ38ሺ በላይ ስደተኞች በአነስተኛ ጀልባ እንግሊዝ መግባታቸዉ ተሰማ
የሀገር ውስጥ ቢሮ መረጃ እንደሚያመለክተው እ.ኤ.አ እስከ ማርች 2025 ድረስ 38,023 ሰዎች በትናንሽ ጀልባዎች ወደ እንግሊዝ የገቡ ሲሆን ይህም ካለፈው ዓመት 22 በመቶ ጨምሯል።በሰኔ ወር ውስጥ ይፋ የሆነዉ ይህ መረጃ እንዳመላከተዉ ከ2022 ከፍተኛ ከነበረበረት አመት በ17 በመቶ ያነሰ መሆኑን አክሎ ገልጿል።
በትናንሽ ጀልባዎች ላይ ከደረሱት ውስጥ ወደ ሶስት አምስተኛ የሚሆኑት ወይም 57 በመቶ የሚሆኑት ከአምስት ሀገራት የመጡ ናቸው። እነዚህም 16 በመቶ ከአፍጋኒስታን ፣ 12 በመቶ ሶርያውያን ፣12 በመቶ ኤርትራውያን ፣11 በመቶ ኢራናውያን እንዲሁም 9 በመቶ ሱዳናውያን ናቸዉ።እ.ኤ.አ. ከ2018 ዓመት ጀምሮ በ94 ትናንሽ ጀልባዎች 145 ሺ 834 ሰዎች ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ጥገኝነት ጠይቀዋል ሲል የሀገር ውስጥ ቢሮ ገልጿል።
ከእነዚህ ውስጥ 56,605 የጥገኝነት ደረጃ የተሰጣቸው ሲሆን 30,041 ያህሉ ውድቅ ተደርገዋል። 29,373 አሁንም ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ በቢቢሲ የተጠናቀረ መረጃ እንደሚያሳየው ከጁላይ 6 ጀምሮ በድምሩ 21,117 ሰዎች በትናንሽ ጀልባዎች ወደ ዩናይትድ ኪንግደም መግባታቸውን ያሳያል። ይህ ከ2024 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ56 በመቶ ጨምሯል።

❤27
ቱርክ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኤርዶጋን ተቃዋሚዎችን በቁጥጥር ስር አውላለች ተባለ
የቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ዋነኛ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከ500 በላይ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውን ሮይተርስ ባደረገው ሰፊ ምርመራ ደርሼበታለሁ ሲል ያስታወቀ ሲሆን በቅርብ ቀናት ውስጥ ደግሞ እስሩ በከፍተኛ ፍጥነት መጨመሩን ገልጿል። የቱርክ ፕሬዝደንት በበኩላቸው እስር የሚፈፀመው በምርመራ ነው በማለት የተበላሸውን እና የጥቅም ትስስር ያለውን መረብ የሚፈታ የጥፋት እጆች ወደ ሌሎች የቱርክ ክፍሎች እና ወደ ውጭ አገር የሚዘረጋው ምርሙራ የኦክቶፐስ አይነት ነው ብለዋል።
በኢስታንቡል የጀመረው ነገር ግን በመላ አገሪቱ የተስፋፋው ይህ ምርመራ ኢላማ ያደረገው በዋና ተቃዋሚው ሪፐብሊካን ፒፕልስ ፓርቲ ወይም CHP በሚተዳደሩት ማዘጋጃ ቤቶች ላይ ብቻ ነው፣ ይህ ተቃዋሚው ፒፕልስ ፓርቲ ወይም ሲኤችፒ የዘመናዊቷ ቱርክ ሴኩላሪዝም መስራች ሙስጠፋ ከማል አታቱርክ የሚመራ እንደነበር ይታወሳል። ፓርቲው ግን የሙስና ውንጀላውን ክስ በመካድ የቱርካውያን ዲሞክራሲያዊ አማራጭን ለማስወገድ እርቃናቸውን ለማስቀረት ያደረጉት ሙከራ ነው ሲል የአንካራ መንግስትን ተችቷል። ቱርክ በመካከለኛው ምሥራቅና በአውሮፓ ያላትን ተፅዕኖ እያሳደገች ባለችበት በዚህ ወቅት ርምጃው የኤርዶጋንን የሁለት አስርት ዓመታት የስልጣን ቆይታ አጠናክሮታል።
ለዚህም ነው ዲፕሎማቶች እና ተንታኞች እንደሚናገሩት በፀደይ ወቅት የጎዳና ላይ ህዝባዊ ተቃውሞዎች በቱርክ በተቀሰቀሱበት ወቅት እንኳን ከምዕራባውያን አጋሮች የዴሞክራሲ ስጋት ነው በማለት ብዙም ትችት ያልቀረበበት ሲሉ ይደመጣሉ። እንደ ህጋዊ ሰነዶች እና የመንግስት መግለጫ ሪፖርቶች መሰረት የኢስታንቡል ከተማ ከንቲባ እና የኤርዶጋን ዋና ተቀናቃኝ ኢክሬም ኢማሞግሉ ጨምሮ 14 የተመረጡ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ከንቲባዎች እና ከ 200 በላይ የፓርቲ አባላት ወይም የአካባቢ ባለስልጣናት ለእስር ተዳርገው ፍርድ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ ።

❤27👍9👎5😁1