የተቀመጠ ንብረት ዘርፈው በመውሰድ የሙስና ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
ብስራት ከዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ፍትህ መምሪያ ያገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ 1ኛ ተከሳሽ ሳላዲን አሰፋ፦ በተፈራ ሃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል በክሊኒካል ነርስ ባለሙያነት የሚሠራ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ ሀብታሙ ሞላ፣ 3ኛ ተከሳሽ አሰፋ ብርሃኑ፣ 4ኛ ተከሳሽ አማረ አዝመራው እና 5ኛ ተከሳሽ አሰሙ አድኖና ካልተያዙ 2 ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን የማይገባቸውን ጥቅም ለማግኘት ተንቀሳቅሰዋል።
በዚህም ንብረትነቱ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ጤና መምሪያ የሆነ 100 ካርቶን ዲዲት የተቀመጠበትን ኮንቲነር ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡00 አካባቢ ሰብረው በመግባትና በመኪና ጭነው በመውጣት ለመሰወር ቢሞክሩም ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም በጋዝጊብላ ወረዳ 01 ቀበሌ በፍተሻ በቁጥጥር ውለዋል።
ታድያ ምንም እንኳ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ቢውሉም ለዲዲቱ ዋጋ በማውጣት በቁጥጥር ሥር ያልዋለው ተጠርጣሪ ጌታነህ ቻሌ ለ1ኛና 3ኛ ተከሳሽ ለእያኝዳንዳቸው 400ሺ ብር፣ እጁ ላልተያዘ አንድ ተጠርጣሪ ደግሞ 100 ሺ ብር በአጠቃላይ 900 ሺህ ብር በየአካውንታቸው ገቢ በማድረግ በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል።
የሰቆጣ ከተማ ፖሊሲ ፅህፈት ቤትም ጉዳዩን አጣርቶ መዝገቡን ለዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ፍትህ መምሪያ የወንጀል የሥራ ሂደት እንዲላክ በማድረግ የፍትህ መምሪያው የወንጀል የሥራ ሂደትም መዝገቡን ከመረመረ በኋላ ተከሳሾች በመመሳጠር በፈፀሙት የሙስና ወንጀል ክስ በመመስረች ጉዳዩን ለዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል።
ፍርድ ቤቱም በጉዳይ ላይ ክርክር ሲደረግበት ከቆዬ በኋላ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሽ በ3 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራትና በ7ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ፣ 3ኛ ተከሳሽ በ3 ዓመት ከ7 ወር ጽኑ እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ፣ 5ኛ ተከሳሽ በ3 ዓመት ጽኑ እስራትና 5ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡና የተያዘው ኢግዚቭትም ወደ ሆስፒታሉ ገቢ እንዲሆን የዋግ ኽምራ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 3 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውሳኔ ማስተላለፉን ብስራት ሬድዮ ከብሔረሰብ አስተዳደሩ ፍትህ መምሪያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል

❤14😁1
ኢራን ለእስራኤል የጀብድ ድርጊት አሜሪካም ተጠያቂ እንደምትሆን ተናገረች
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቴህራን በተባበሩት መንግስታት ቻርተር መሰረት ለእስራኤል ጥቃቶች ምላሽ የመስጠት "ህጋዊ " መብት እንዳላት ተናግረዋል። ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ "በእኛ ተወዳጅ እናት አገራችን ኢራን ላይ የጽዮናውያን አገዛዝ ያደረሰው ጥቃት አደገኛ እና ሰፊ ውጤት መዘዞች የዚህ አገዛዝ እና የደጋፊዎቹ ኃላፊነት ይሆናሉ" ብሏል።
"የጽዮናውያን አገዛዝ በኢራን ላይ የወሰደው ኃይለኛ እርምጃ ያለ አሜሪካ ትብብር እና ፍቃድ ሊከናወን አይችልም። በዚህ መሰረት የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት የዚህ አገዛዝ ዋነኛ ደጋፊ እንደመሆኑ መጠን ለጽዮናዊ አገዛዝ ጀብዱ ለሚያስከትለው አደገኛ ውጤት እና መዘዝ ተጠያቂ ይሆናል" ሲል አክሏል።
የሪፐብሊካኑ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ማይክ ጆንሰን በዋሽንግተን እና ቴህራን መካከል የኒውክሌር ድርድር ቢደረግም ኢራንን በማጥቃቷ ለእስራኤል ያልተቋረጠ ድጋፍ አሳይተዋል። "እስራኤል ትክክል ናት እናም ራሷን የመከላከል መብት አላት!" ያሉት ጆንሰን የእስራኤልን ባንዲራ በማሳየት በማህበራዊ ሚዲያ ፅሁፋቸው ላይ አጋርተዋል።
የመብት ተሟጋች ቡድን አሜሪካ ከእስራኤል ጋር ያላትን ፍላጎት እንድታቆም ጠይቋል። መቀመጫውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው DAWN የተሰኘው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድን እስራኤል ኢራን ላይ ያደረሰችው ጥቃት "ህገ-ወጥ" ነው ብሏል። የ DAWN ተሟጋች ዳይሬክተር ሬድ ጃራር በሰጡት መግለጫ “ዩናይትድ ስቴትስ ከእስራኤል ግድየለሽ የጦርነት ዘመቻ ጥቅሟን ሙሉ በሙሉ ማላቀቅ እና በኢራን ላይ ለሚሰነዘረው ጥቃት ማንኛውንም ድጋፍ፣ ቁሳዊም ሆነ ፖለቲካዊ እምቢ ማለት አለባት ብሏል። "አሁን እስራኤል በሊባኖስ እና በጋዛ ላይ የፈፀመችውን አይነት ተንኮል የኢራን ባለስልጣናት መኖሪያ ነው ያላቸውን የኢራን ሰፈሮች በህገ-ወጥ መንገድ ስትደበድብ እያየን ነው።" ሲል አክሏል።
በስምኦን ደረጄ

❤29🤣11🔥6👍2👎2🥰1💯1💔1
"የማይቀረው የእስራኤልና ኢራን ግጭት"
ዛሬ ማለዳ ዓለም አዲስ ጥቃት የሰማችበት በርካቶች የደነገጡበት ቡዙኃን እጃቸውን በአፋቸውን የጫኑበት ጥቃት እስራኤል በኢራን ላይ ፈፀመች።
ከከፍተኛ የጦር አዛዦች እስከ የኒኩለር ሳይንቲስቶች ብሎም ንፁሐን ዜጎች ተገደሉ።
የዓለም ሀገራት መሪዎች አስተያየት ሰጡ፤ ኢራን ዛተች ሀማስ እኔም አለው አለ እስራኤልም አስፈላጊ ከሆነ ጥቃት መፈፀሟን እንደምትቀጥል ገለፀች።
በጥቂት ሰዓታት ብዙ ጉዳዮች ተከሰቱ እኛም (ጋዜጠኛ ስምኦን ደረጀና ሚሊዮን ሙሴ) አጠር መጠን ባለ ቆይታችን እንደሚከተለው ዳሰነዋል። ማስፈንጠርያውን በመንካት ተጋበዙልን።
https://youtu.be/i_3CSgNtWNM?si=xoJAepcbq2XeEI86

👍38❤7🕊2🤔1
በድሬዳዋ ባለፉት ዘጠኝ ወራት አራት ባለሀብቶች በሆቴልና ቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዘርፍ ግንባታ በማጠናቀቅ አገልግሎት መጀመራቸው ተነገረ
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት በበጀት አመቱ ዘጠኝ ወራት የኢንቨስትመንት አማራጮችን ምቹ በማድረግ ስድስት ባለሀብቶች በሆቴልና ቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲሰማሩ ታቅዶ አራቱ በቱሪዝም ኢንቨስትመንት ተሰማርተዉ የግንባታ እቃዎችን ከቀረጥ ነፃ ድጋፍ እንዲያገኙ መደረጉ ተገልጿል ።
በተደረገዉ ክትትልና ድጋፍ አራቱ ሆቴሎች ግንባታቸዉ ተጠናቆ አገልግሎት መጀመራቸዉን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወንደሰን አባይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ። እነዚህ አራት ሆቴሎች ሸረፍ ሆቴል ፣ኢስት ስታር ሆቴል ፣ አሚና ሆቴል እና ደበሶ በድሬ ሆቴል መሆናቸዉ ተገልጿል ።
2ዐዐ ደረጃቸውን የጠበቁ የመኝታ ክፍሎችን ወደ አገልግሎት ለማስገባት ታቅዶ ሲሰራ መቆየቱን የገለፁት ኃላፊዉ አገልግሎት መስጠት ከጀመሩ አራት ሆቴሎች 221 ደረጃቸውን የጠበቁ የመኝታ ክፍሎችን ወደ አገልግሎት ማስገባት መቻሉን ገልጸዋል ።
የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ጥራትና ደረጃ ለማሳደግ 81 የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ክትትልና ድጋፍ በማከናወን ቀልጣፋ አገልግሎት ለተገልጋይ እንዲሰጡ ማድረግ ተችሏል ፡፡ አዲስ ተከፍተው አገልግሎት መስጠት በጀመሩ ሆቴሎች ውስጥ በተለያዩ የሆቴል ሙያ ዘርፎች ለ487 ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል ተፈጥሯል።
በመባ ወርቅነህ

❤11👍7😁5
በእስራኤል አራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን
ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ይመልከቱ👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/i_3CSgNtWNM?si=xoJAepcbq2XeEI86
ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ይመልከቱ👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/i_3CSgNtWNM?si=xoJAepcbq2XeEI86
❤11👍7
ቻይና የእስራኤል ጥቃት እንዳሳሰባት በመግለፅ የሰላም ጥሪ አቀረበች
ቻይና እስራኤል ኢራን ላይ ለምትሰነዘረው ጥቃት ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት ለቀጠናው ሰላም እና መረጋጋት በሚጠቅም መንገድ እንዲሰሩ ጥሪዋን አስተላልፋለች ሲል የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ተናግሯል። ቻይና ኦፕሬሽኖቹ ሊያስከትሉ ስለሚችሉት አስከፊ መዘዞች በጥልቅ ተጨንቃለች እናም የሚመለከታቸው አካላት ተጨማሪ ውጥረቱን እንዳያባብሱ ትጠይቃለች ሲሉ ቃል አቀባይ ሊን ጂያን በመደበኛ ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ገልፀዋል ።
ሁኔታውን በማቀዝቀዝ ረገድ ቻይና ገንቢ ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል ።የሊባኖስ ፕሬዝዳንት በበኩላቸው የእስራኤል ጥቃቶች በመካከለኛው ምስራቅ መረጋጋት ላይ ያነጣጠሩ ናቸው ብለዋል። የሊባኖሱ ፕሬዝዳንት አውን እስራኤል በኢራን ላይ ያደረሰችው ጥቃት በኢራን ላይ ያነጣጠረ ብቻ ሳይሆን በመካከለኛው ምስራቅ እና በአጎራባች ሀገራት መረጋጋትን ለማስፈን እና የውጥረት መባባስ እንዳይፈጠር የሚደረጉ ሁሉም አለም አቀፍ ጥረቶች የሚጎዳ ነው ብለዋል ። እስራኤል ግቧን እንዳታሳካ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ውጤታማ እና ፈጣን እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል በመቶዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች በኢራን ኩም ከተማ በሚገኘው የጃምካራን መስጊድ በመሰብሰብ በእስራኤል ላይ “ከባድ የአፀፋ ምላሽ” እንዲሰጥ ጠይቀዋል። ተቃዋሚዎቹ የኢራን ባንዲራ በማውለብለብ እና ፀረ እስራኤል መፈክሮችን በማሰማት ከኢራን ዋና ከተማ በስተደቡብ 140 ኪሜ ርቀት ላይ ከሚገኙት የሀገሪቱ ቅድስተ ከተሞች በአንዱ ተሰብስበው ነበር ሲል የኢራን የዜና ወኪል ታስኒም በኤክስ ላይ የተለጠፈው ቪዲዮ ያሳያል። ዛሬ አርብ ማለዳ ላይ የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ ከፍተኛ የጦር አዛዦች እና የኒውክሌር ሳይንቲስቶች እንዲሁም ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ የበርካታ ሰዎች ህልፈት ተዘግቧል።

❤32😁8🤔1💔1
ሰበር: በቴህራን አቅራቢያ ፍንዳታዎች መሰማታቸው ተገለፀ
የኢራኑ ኑር የዜና ወኪል እንደዘገበው ከሆነ ከቴህራን በስተ ምዕራብ ባለው የአልቦርዝ ግዛት ፍንዳታዎች ከተሰሙ በኃላ ጭስ መታየቱ ዘግቧል።
ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ እንደረሰን እናቀርባለን።

😢18❤14😁3👎2🔥1👏1
በጋምቤላ ክልል ከመጠጥ በኃላ የሚደረግ ጥንቃቄ የጎደለው የግብረስጋ ግንኙነት የኤችአይቪ ስርጭት ከፍተኛ እንዲሆን ማድረጉ ተነገረ
በጋምቤላ ክልል የኤች አይቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት አሁንም ከፍተኛ ቢሆንም ምርመራ የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር አናሳ መሆኑን ክልሉ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
በ ጽ/ቤቱ የዘርፈ ብዙ ምላሽ የኤች አይ ቪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አቡላ ድንጉር ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት በሽታው በተለይም የነገ ሀገር ተረካቢ በሆኑት አፍላ ወጣቶችና ልጃገረዶች ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት ከፍተኛ ነው።
መጠጥን ተከትሎ የሚደረግ ጥንቃቄ የጎደለው የግብረስጋ ግንኙነት ያለ እድሜ ጋብቻ ዋና ዋና ከሚባሉት መካከል በምክንያትነት ይጠቀሳሉ ብለዋል።
ተመርምሮ ራስን ማወቅ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት እንደሚያግዝ የገለፁት አቶ አቡላ በክልሉ እየተደረገ ያለው የኤችአይቪ ምርመራ ግን አነስተኛ ነው ሲሉ አስረድተዋል።
እነዚህ ምክንያቶች ተዳምረው አፍላ ወጣቶችንና ልጃገረዶችን ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ እንዳደረጋቸው ገልፀዋል።
በክልሉ የኤች አይቪ ኤድስ ተጋላጭነትን ለመቀነስ የሚያስችሉ የግንዛቤ ስራዎች በትምህርት ቤትና ከትምህርት ቤት ውጪ ላሉ ወጣቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ዳይሬክተሩ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።
በተጨማሪም የኤች አይቪ ምርመራን እንዲያደርጉ እና ራሳቸውን እንዲያዉቁ የሚያስችሉ ስራዎች ይሰራሉ በማለት ተናግረዋል።
ቅድስት ደጀኔ

❤12😁5😭2
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
ሰበር: በቴህራን አቅራቢያ ፍንዳታዎች መሰማታቸው ተገለፀ የኢራኑ ኑር የዜና ወኪል እንደዘገበው ከሆነ ከቴህራን በስተ ምዕራብ ባለው የአልቦርዝ ግዛት ፍንዳታዎች ከተሰሙ በኃላ ጭስ መታየቱ ዘግቧል። ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ እንደረሰን እናቀርባለን። #ዳጉ_ጆርናል
በኢራኗ ታብሪዝ ከተማ ጥቃት ተፈፀመ
በሰሜን ምዕራብ ኢራን ውስጥ በታብሪዝ ከተማ ፍንዳታዎች መሰማታቸውን የሚገልጹ ዘገባዎች እየወጡ ያሉ ሲሆን የአካባቢው ሰዎች በማህበራዊ ትስስር መድረኮች ላይ የጋሩዋቸውና አልጀዚራ አረጋገጥኳቸው ያላቸው ተኔቀሳቃሽ ምስሎች ጥቃቱ ከተፈጸመበት ቦታ ጭስ ሲወጣ ያሳያሉ ተብሏል።
በተያያዘ መረጃ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቴህራን የአሜሪካን ጥቅም የሚወክለውን የስዊዘርላንድ አምባሳደር ሊያነጋግር መጠራቱን የሀገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
"በስብሰባው ወቅት የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ በዚህ የእስራኤል ጥቃት ዩናይትድ ስቴትስ የምትሰጠውን ድጋፍ በመቃወም የተሰማውን ጥልቅ ንዴት እና ጠንካራ ተቃውሞ አስተላልፏል" ሲል ኢአርኤን የተባለው ኦፊሴላዊ የዜና አገልግሎት ገልጿል።
በሚሊዮን ሙሴ

💔26❤11🔥7👏1
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (....)
🗣ኩንሃ አርሰናልን ፣ኒውካስልን እና ሌሎች የፕሪምየር ሊግ ክለቦችን ለምን ውድቅ እንዳረገ ሲጠየቅ...
"በእርግጥ እነሱ በደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ከፍ ብለው ነው ያጠናቀቁት ፣ ግን ዋንጫዎችን ማሸነፍ እመርጣለሁ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ሁል ጊዜ ዋንጫዎችን ያነሳል" ብሏል።
ለስፖርታዊ መረጃዎችን ይፋዊ የዳጉ ጆርናል ስፖርት ቻናል https://www.tg-me.com/Dagujournalsport ን ይቀላቀሉ
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት

😁67❤20💯6🔥3
የኢትዮጵያ እምባ ጠባቂ ተቋም የደመወዝና ጥቅማጥቅም አነስተኛ መሆን እና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ፍልሰት በበጀት ዓመቱ ያጋጠመው ችግር መሆኑን አስታወቀ
የኢትዮጵያ እምባ ጠባቂ ተቋም በ2017 በጀት ዓመት በተለያዩ ተቋማት እና ክልሎች ላይ ቅሬታ በቀረበባቸው የስራ ክፍሎች ላይ በትኩረት ሲሰራ እንደነበረ ተገልጿል ።የመንግስት አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ከወጡ መመሪያና ደንቦች እንዲሁም ከዜጎች መብት አንጻር ህግና አሰራርን ተከትለው እየተከናወኑ ስለመሆኑ ለመፈተሽ በተመረጡ 80 የክልልና የፌደራል ተቋማት ላይ ቁጥጥር መካሄዱ የተቋሙ የህዝብ ግንኙነት እና የኮሙኒኬሽን ክፍል ስራ አስፈጻሚ አቶ አንለይ ወርቄ ብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ቁጥጥር ባከናወነባቸው በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አገልግሎቶች በተለይ የልደት ምዝገባና የልደት ሰርተፍኬት አገልግሎቶች እስካሁን አለመጀመሩ ተመልክቷል። የውጭ ሃገር ስደተኞችን በሀገር አቀፍ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥርዓቶች ውስጥ ተሳታፊ ለማድረግና፣ የምዝገባ ድግግሞሽን በማስቀረት ግልጽ መረጃ ለመያዝ እንዲቻል የዲጂታል መታወቂያ ተግባራዊ አለመደረጉ ለህብረተሰቡ በሚቀርቡ የተሟላ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ ተመልክቷል ።
በሌላ በኩል በታዳጊ ክልሎች የቅድመ መደበኛና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት በአፍ መፍቻ ቋንቋ ለማስተማር በየትምህርት ዘርፉ የሰለጠኑ መምህራን በጣም አናሳ መሆናቸው ተነግሯል። በመሆኑም ቋንቋውን በመናገራቸው ብቻ ባልሰለጠኑበት የትምህርት መስክ እንዲያስተምሩ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል ። ይህም ጥራት ያለው የትምህርት ተደራሽነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ መኖሩ ተጠቁሟል።
በአጠቃላይ ተቋሙ በ2017 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ጊዜ ውስጥ አስተዳደራዊ በደሎችን የመከላከልና ተፈጽመው የተገኙትን ከማረም አንጻር ጥሩ የሚባል ስራ ተሰርቷል ተብሏል። ይሁን እና የተቋሙ አስፈጻሚ አካላት በተቋሙ የሚሰጡ የመፍትሄ ሀሳቦችን ተግባራዊ አለማድረግና ለስራ ተባባሪ አለመሆን፣ ከአቻ ተቋማት አንጻር የደመወዝና ጥቅማጥቅም አነስተኛ መሆን ጋር በተያዘ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ፍልሰት እና የበጀትና የግብዓት ዕጥረት ተቋሙን የገጠሙት ችግሮች መሆናቸውም አቶ አንለይ ወርቄ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በኤደን ሽመልስ

❤20😁6
በዓለም ላይ በቀን ከ80 ሚሊዮን በላይ የሳይበር ጥቃቶች ይሞከራሉ ተባለ
በእነዚህ ጥቃቶችም ሳቢያ በያዝነው የፈረንጆቹ አመት መጨረሻ አለም ከ10 ትሪሊየን ዶላር በላይ ኪሳራ እንደምታስተናግድ ጥናቶች ያሳያሉ ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አስታውቋል፡፡ በተለይም ደግሞ የፋይናንስ ዘርፉን ኢላማ ያደረጉ የሳይበር ጥቃቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ መምጣታቸው ተገልጿል።
3ኛው ዓለም አቀፍ የሳይበር ደህንነትና ዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።የኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት ማህበር እና የኢኖቬሺንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያዘጋጁት 3ኛው ዓለም አቀፍ የሳይበር ደህንነትና ዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ጉባኤም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
የኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት ማህበር ፕሬዚዳንት ብርሃኑ በየነ (ዶ/ር) በጉባኤው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ጉባኤው የመንግስትና የግል ባለድርሻ አካላት ልምድ የሚለዋወጡበት እና ትብብራቸውን የሚያጠናክሩበት ነው ማለታቸውን ብስራት ሰምቷል።በሳይበር ደህነነት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት እና ዲጅታል ትራንሰፎርሜሽንን ለማፋጠን የሀገራት ትብብር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፤ የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የሚችሉ ሀሳቦች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።በጉባዔው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ምሁራን ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በቅድስት ደጀኔ

❤11😁7
ሰበር: እስራኤል ከኢራን የተወነጨፉ ሚሳኤሎችን መመልከቷን አስታወቀች
የእስራኤል ጦር ከኢራን የተወነጨፉ ሚሳኤሎችን በራዳሩ ላይ ከተመለከተ በኋላ እስራኤላውያን በተከለሉ ቦታዎች መቆየት አለባቸው ሲል አስታውቋል።
"ከተከለለው ቦታ መውጣት የሚፈቀደው ግልጽ መመሪያዎችን ከተላለፉ በኋላ ነው" ሲል በወታደራዊው መግለጫ ይፋ አድርጓል።

🔥42❤14😱9😁7👏6⚡3🕊1
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
ሰበር: እስራኤል ከኢራን የተወነጨፉ ሚሳኤሎችን መመልከቷን አስታወቀች የእስራኤል ጦር ከኢራን የተወነጨፉ ሚሳኤሎችን በራዳሩ ላይ ከተመለከተ በኋላ እስራኤላውያን በተከለሉ ቦታዎች መቆየት አለባቸው ሲል አስታውቋል። "ከተከለለው ቦታ መውጣት የሚፈቀደው ግልጽ መመሪያዎችን ከተላለፉ በኋላ ነው" ሲል በወታደራዊው መግለጫ ይፋ አድርጓል። #ዳጉ_ጆርናል
#update
በማዕከላዊ ቴል አቪቭ ውስጥ የፍንዳታ ድምፅ ከተሰማ በኃላ ጭስ ታይቷል
ከቴል አቪቭ የተሰራጨ የቀጥታ ስርጭት እንዳሳየው ከሆነ ከቅጽበት በፊት ፍንዳታዎች የተሰሙ ሲሆን ቀጥሎም ጭስ ወደ አየር እየወጣ መታየቱን አልጀዚራ አስነብቧል።
ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን።

❤44👍15🔥9👏7