ሞቢሊቲኢ 50 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለደንበኞች አስረከበ
ሞቢሊቲኢ ከድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በመተባበር ለ50 ደንበኞች የኤሌክትሪክ መኪኖችን አስረክቧል
ሞቢሊቲኢ ከድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ገንዘብ ቆጥበው ሲጠባበቁ ለነበሩ 50 ደንበኞች የ5ኛ ዙር የቢዋይዲ መኪኖችን በዛሬው እለት አስረክቧል።
ሞቢሊቲኢ ከቢዋይዲ ሴጉል፣ ቢዋይዲ ኢ2፣ ቢዋይዲ ዩአን አፕ፣ ቢዋይዲ ዩአን ፕላስ እና ቢዋይዲ ሶንግ ፕላስ መኪኖችን በ50% ቅድመ ክፍያ እንዲሁም ቀሪውን ከድጋፍ ማይክሮ ፋይናንስ ጋር በመተባበር በ16.5% ወለድ ለደንበኞች በማቅረብ ላይ ይገኛል ሲሉ የሞቢሊቲኢ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ መንገሻ ተናግረዋል።
መጪውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ ደንበኞች ከነዳጅ መኪና በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ባለቤት እንዲሆኑ ሞቢሊቲኢ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለደንበኞች በማቅረብ ላይ ይገኛል ሲሉ አቶ ሲሳይ መንገሻ አክለው ተናግረዋል።
ሞቢሊቲኢ በ4 ዓመት የብድር ክፍያ መመለሻ ጊዜ ያቀረበውን ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ልዩ ቅናሽ በቦሌ ቡልቡላ ሪፌንቲ በሚገኘው ዋናው ሾውሩም እንዲሁም መስቀል ፋላወር እና ሃዋሳ ፒያሳ ሩት ገበያ በሚገኙት ቅርንጫፎች አመቻችቶ ተጨማሪ መኪኖችን ለማስረከብ ዝግጅቱን ጨርሷል።
ሞቢሊቲኢ ቦሌ ቡልቡላ ሪፌንቲ በሚገኘው ዋናው ሾውሩም በዛሬው እለት ለ50 ደንበኞች የቁልፍ የማስረከብ ስነስርዓት አከናውኗል።
በሰላማዊ ነጋሲ
#ዳጉ_ጆርናል

❤29🔥1
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ኢትዮጵያ ቡና የሸገር ደርቢን አሸነፈ
ኢትዮጵያ ቡና ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 0 ነዉ ያሸነፈዉ። ለቡና ግቦቹን ዲቫይን ዋቹኩዋ በ 28ኛዉ ደቂቃ እና አማኑኤል አድማሱ በ 66ኛዉ ደቂቃ አስቆጥረዋል።
ለስፖርታዊ መረጃዎችን ይፋዊ የዳጉ ጆርናል ስፖርት ቻናል https://www.tg-me.com/Dagujournalsport ን ይቀላቀሉ
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት

❤24🤬4👏3
ሰቨን ቢራ የ2025 ሞንዴ ሰሌክሽን ዓለም አቀፍ የጥራት ተሸላሚ ሆነ
የ2025 ሞንዴ ሰሌክሽን ዩናይትድ ቢቬሬጅ አክሲዮን ማህበር በሰቨን የቢራ ምርት ጥራት የወርቅ ተሸላሚ መሆኑን አስታውቋል። ተቋሙ ሽልማቱን በማስመልከት በሰጠው መግለጫ አለማቀፋዊ እውቅናን ያገኘንበት እንዲሁም የስራችንን ወጤት ያየንበት በመሆኑ ሽልማቱ ከሜዳሊያም በላይ ነው ሲል አስታውቋል። ሽልማቱ ዩናይትድ ቢቬሬጅ ለጥራት፣ ለደንበኞቹ ፍላጎት፣ እንዲሁም ታዓማኒነት እንደሚሰራ ምስክር መሆን የሚችል ሽልማት ነውም ተብሏል።
ኩባንያው " የተባበሩት ቢቬሬጅ አክስዮን ማህበር ለጥራት፣ ወጥነት ላለው ምርት እንዲሁም የደንበኞቹን እምነት ለመጠበቅ ዘወትር የሚተጋ በመሆኑ በሞንዴ ሰሌክሽን እውቅና ማግኘት መቻሉ ትልቅ ክብር ነው" ያለ ሲሆን "ይህ ሽልማት የመላው ቡድናችንን ትጋት እና ጥረት የሚያረጋግጥ ሲሆን ጥራትን ያስቀደመ የስኬት ማማ ላይ እንደሚቀመጥ ማሳያ ነው" ሲልም አክሏል።
ሞንዴ ሰሌክሽን የጥራት ሽልማት ብቻ አይደለም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው ማህተም ነው። ተጠቃሚዎች ከፍተኛውን ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን የሚያሟላ ምርት እንደመረጡ የሚያረጋግጥ የጥራት ምልክት ነው። ሞንዴ ሰሌክሽን ከሌሎች የሽልማት ዘርፎች ለየት ባለ መልኩ የራሱን መመሪያዎች በማዘጋጀት በተደራጀ መልኩ አለም ዓቀፍ በሆኑ እና የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው ገለልተኛ ዳኞች አሸናፊው የሚለይበት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።
የሞንዴ ሰሌክሽን ከሽልማትነት ባለፈ ከፍተኛ የጥራት መመዘኛዎች በማሟላት የተመረጡ ምርቶች ቡድን አንድ አካል መሆን መቻልም ነው። ይህም ተጠቃሚዎች በገለልተኛ አካል የተገመገመ እና በጥራቱ የላቀ ምርት በቀላሉ ለማግኘት ያስችላቸዋል ተብሏል። ይህ ስኬት ከተጠቃሚዎች እምነት ባሻገር ዩናይትድ ቢቬሬጅ አክሲዮን ማህበርም በዓለም አቀፍም ሆነ በሀገር ውስጥ ያለውን ገበያ ያጠናክራል በተጨማሪም ለአዳዲስ ስራዎች ፤ ተደራሽነቶች ፤ አጋርነቶች እንዲሁም ስኬቶች መንገድ ይከፍታል ተብሎለታል።
ሰቨን ቢራ ይኽን ሽልማት ማሸነፉ ዩናይትድ ቤቬሬጅ ለተዓማኒነቱ እና ለምርት ጥራቱ ተግቶ እንደሚሰራ ማረጋገጫ ነውም ተብሏል።
በሚሊዮን ሙሴ

❤17👍12👎6
“እኔ በሕይወት እያለሁ መምህራን መኪና ኖሯቸው ከማየት በላይ የሚያስደስተኝ ነገር የለም” ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ
ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የመምህራን ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
"እኔ በሕይወት እያለሁ መምህራን መኪና ኖሯቸው፣ መኪናቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤታቸው በር ላይ አቁመው ሲያስተምሩ ከማየት በላይ ለኔ ደስታ የለም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ውስጥ ውስጡን እየተሠሩ ያሉት ሥራዎች ሲሳኩ የመምህራን ጥያቄዎች ምላሽ ያገኛሉ ብለዋል።
የመምህራን ጥያቄ በደመወዝ ጭማሪ ብቻ የማይመለስ መሆኑን አንስተው፣ የደመወዝ ጭማሪው ላይ ብቻ ትኩረት ከተደረገ ያለችው ተበልታ ታልቃለች ብሏል።

🤣238👎38❤33😁12🤬6👍5
በእስራኤል አራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን
ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ይመልከቱ👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/i_3CSgNtWNM?si=xoJAepcbq2XeEI86

🔥15👍6❤4😁2
የቀነኒሳ በቀለ የመጀመሪያ ልጅ መጽሐፍ አሳተመች
የቀነኒሳ በቀለ የመጀመሪያ ልጅ መጽሐፍ አሳተመች። ኤልናታ ቀነኒሳ በቀለ ያሳተመችው የግጥም መጽሐፍ በውስጡ 17 ግጥሞች ያሉት ሲሆን ከመስከረም ጀምሮ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለሽያጭ ይቀርባል:: መጽሐፉ ትኩረቱን ሰላም ላይ ያደረገ እንደሆነ ለፋስት መረጃ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
መፅሐፉ በ350 ብር ቀርቧል።
Via ፋስት መረጃ

❤160😁34👏18👎4🔥3🤣2👍1
ኢራን በፈፀመችው የአፀፋ የሚሳኤል ጥቃት ቢያንስ አስር የእስራኤል ዜጎችን ገደለች
ኢራን በሀይፋ እና ቴል አቪቭ አቅራቢያ ባሉ የእስራኤል ኢላማዎች ላይ ሚሳኤሎችን በመተኮስ ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን የህክምና ባለሙያዎችና ሚዲያዎች ዘግበዋል። ጥቃቶቹ የተፈፀሙት የእስራኤል ሃይሎች በመላው ኢራን የሲቪል እና የኢነርጂ መሠረተ ልማቶችን በቦምብ ከመቱ በኋላ ቴህራን በሚገኘው ሻህራን የነዳጅ ተቋም ላይ የእሳት ቃጠሎ ሙድረሱን ተከትሎ ነው።
ኢራን በእስራኤል ላይ ባደረሰችው የሚሳኤል ጥቃት 10 ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናቱ አረጋግጠዋል። ከቴል አቪቭ በስተደቡብ በምትገኘው ባት ያም ከተማ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን ፖሊስ ገልጿል፤ ከነዚህም መካከል 2 ህጻናትን ጨምሮ። ሰባት ሰዎች የጠፉ ሲሆን የአደጋ ጊዜ አገልግሎቶች በፈራረሱ ህንፃዎች ላይ ፍለጋ እያደረጉ ይገኛል።በሰሜናዊ አረብ ከተማ ታምራ በተፈፀመ የኢራን የሚሳኤል ጥቃት አራት ሰዎች መሞታቸውን የአደጋ ጊዜ አገልግሎት እና የአካባቢው ሆስፒታል ገልጸዋል።
የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ ሀገሪቱ በማዕከላዊ እና በሰሜናዊ ክልሎቿ ኢራን ባደረሰችው ጥቃት ከምሽት ስንነቃ "በጣም አሳዛኝ እና አስቸጋሪ ጠዋት" አሳልፈናክ ሲሉ ኤክስ ለጥፈዋል። "ወንጀለኛው የኢራን ጥቃት" ገድሏል እና አቁስሏል ብለዋል። አይሁዶች እና አረቦች፣ የእስራኤል ዜጎች እና አዲስ ስደተኞች ፣ሕጻናት እና አረጋውያን ሴቶች እንዲሁም ወንዶች ጨምሮ ተጎድተዋል ሲሉ አክለዋል። "በቤተሰባቸው ላይ ከባድ ሀዘን የደረሰባቸውን ለደረሰው አሰቃቂ ጉዳት አዝኛለሁ፤ የተጎዱትን ማገገም እና የጠፉትን እንዲያገኙ እጸልያለሁ ፤አብረን እናዝናለን,ዴ አብረን እናሸንፋለን" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተደምጠዋል።
በስምኦን ደረጄ

4👏111❤33👎22🔥7😁6🕊3😭1
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የአንጋፋው ጋዜጠኛ የደረጄ ኃይሌ 60ኛ ዓመት የልደት በዓል ዛሬ በድምቀት ይከበራል ከፍተኛ የሆነ ተወዳጅነትን ያተረፈው ጋዜጠኛ ደረጄ ኃይሌ የሕይወቱን እና የሙያ ክህሎቱን ረጅም ጉዞ ለማስቃኘት ለማመስገን እንዲሁም 60ኛ ዓመት የልደት በዓሉን በአርትስ ቴሌቪዥን እና በወዳጆቹ አስተባባሪነት ዛሬ ታላቅ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ በርካታ የስነጥበብ አፍቃሪያን ቤተሰቦቹ ወዳጆቹ የአርትስ…
ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ የመኖሪያ ቤት ስጦታ ተበረከተለት
በትናንትናው እለት የ60ኛ ዓመት የልደት በዓሉን እያከበረ የሚገኘው አንጋፋው ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ ከጃምቦ ሪልስቴት የመኖሪያ ቤት ስጦታ ተበርክቶለታል።
በተጨማሪም ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ የጃምቦ ሪልስቴት የብራንድ አምባሳደር መሆኑ ይፋ ሆኗል።
የአንጋፋው ጋዜጠኛ ደረጀ ኃይሌ የሙያ ባልደረቦቹና ወዳጆቹ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የልደት በዓሉ ተከብሯል።
Via አርትስ ቴሌቪዥን

❤115👍17🤔1