Telegram Web Link
እረዳዳ የአረጋውያን በጎ አድራጎት ማህበር ለአረጋውያን እሮጣለው የድርሻዬን እወጣለው በሚል መሪቃል የገንዘብ ማሰባሰቢያ ሩጫ አዘጋጀ

እንረዳዳ የአረጋውያን በጎ አድራጎት ማህበር የአረጋውያንን መሰረታዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸውን ለመፍታት እንደ እድሜ ባለፀግነታቸውም የተከበሩና ጤናማ እንዲሆኑ በማለም 1990 ዓ.ም የተቋቋመ ድርጅት ነዉ።

ማሀበሩ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ጀምሮ ለ824 አረጋዊያን በተለያዩ መንገድ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል። ከእነርሱም በተጨማሪ 1558 የልጅ ልጆቻቸው በተዘዋዋሪ እርዳታ እያደረገ መሆኑ የእንረዳዳ የአረጋውያን በጎ አድራጎት ማህበር አምባሳደር የሆነው አርቲስ ይገረም ደጀኔ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ከምዕራባዉያን ሀገራት በልግስና ያገኘው የነበረው ገቢ ከጊዜ ወደ ግዜ እየቀነሰ በመምጣቱ ምክንያት አሁን ላይ እየሰጠ ያለው አገልግሎት ቀንሷል። በዚህም የአረጋውያን የልጅ ልጆች በተሻለ መልኩ ድጋፍ ለማድረግ ወደ ህዝቡ አድርሶ ማስተዋወቅና ገቢ መሰባሰብን ዓላማው ያደረገ መነሻና መድረሻው አድዋ መታሰቢያ ሙዚየም የሆነ የጎዳና ላይ ሩጫ ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል ።

በሩጫው ላይ ከ3ሺ እስከ 5 ሺ ሰው ይታደምበታል ተብሎ የሚጠበቀው የ 5ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በአትሌቶች መካከል የሚደረግ ውድድር ይከናወናል። የመሮጫ ቲሸርት ዋጋው ለአዋቂ 500 ብር ለታዳጊዎች 400 ብር ለሽያጭ መቅረቡን ብስራት ከአዘጋጆቹ ሰምቷል፡፡

በኤደን ሽመልስ
10😁2
አነስተኛ ዋጋ ፤ የተሻለ ጥራት 🔥
ሚኪያስ ጎማ ፣ ባትሪና ከመነዳሪ አከፋፋይ 

#ለቪትስ
#ለያሪስ
#ለዲዛየርና ስዊፍት
#ለኮሮላ
#3L & 5L እንዲሁም ለከባድ ተሽከርካሪዎች የሚሆኑ ጎማዎች እና ባትሪዎችን ይዘዙን ካሉበት እናደርሳለን

👉የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ጎማዎች (ትሪያንግል ፣ ስፖርትራክ ፣ ኮምፈርሰር ፣ አፖሎ ፣ ብሪጅስቶን እና ሌሎችም)

👉 የተገለገሉበት ጎማ ን ዋጋ ተምነን በአዲስ እንቀይርሎታለን

👉 በስልክ ቁጥር 📞...+251-913-701702 / +251-975293297 ይደውሉልን አልያም ተክለሀይማኖት ከሚገኘው ሱቃችን ይምጡ በደስታ እናስተናግድዎታለን
👍41
በእስራኤል አራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ጋር ይከታተሉ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/e4whZmVDFao?si=xKiZJdAhf3GiQA-g

#ዳጉ_ጆርናል
🔥11👍63👏2
ትራምፕ የኢራንን የምድር ውስጥ የኒውክሌር ጣቢያን ኢላማ ያደረገውን ​​የእስራኤል ጥቃት ለመቀላቀል እያሰቡ ነው

ትራምፕ በዋይት ሀውስ ሲችዌሽን ክፍል ውስጥ ከብሄራዊ ደህንነት ቡድናቸው ጋር በእስራኤል እና በኢራን ግጭት ፣ውጫዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። እስራኤል በፎርዶ የሚገኘውን ተቋምን ጨምሮ የኢራንን የኒውክሌር ቦታዎች ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ለመቀላቀል እያሰበ ነው ሲሉ ጉዳዩን የሚያውቁ አምስት ምንጮች ለሲቢኤስ ኒውስ ተናግረዋል። ርዕሰ ጉዳዩ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል። በትራምፕ የቅርብ አማካሪዎች መካከል ሙሉ ስምምነት የለም ሲሉ የሲቢኤስ ምንጮች አክለዋል።ትራምፕ ማክሰኞ እለት ከእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ማነጋገራቸው ተሰምቷል።

የተወያዩበትም ሆነ የተነገረው ጉዳይን በተመለከተ የታባለ ነገር ግን የለም፣ እዚያው የውይይቱ ጠረጴዛው ላይ ግን ምን እንዳለ መገመት እንችላለን ሲሉ ተንታኜች ተደምጠዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በሲችዌሽን ክፍል ውስጥ ለአንድ ሰዓት ከ20 ደቂቃ ያህል ካሳለፉ በኋላ ከካቢኔያቸው ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር መክረዋል። ከአንዳንድ ከፍተኛ ጄኔራሎች ጋር እየተገናኙ ነበር። ከጋራ ሹማምንቱ ሊቀመንበር ጋር ስለቀጣዩ ሂደት ተወያይተዋል። በአሁኑ ጊዜ ሁሉም የዲፕሎማሲ ወይም የስምምነት ንግግር እንደተቋረጠ ምልክቶች ይታያሉ። እናም የትረምፕ አስተዳደር ወደ አንድ ዓይነት ወታደራዊ እርምጃ እያመራ ያለ ይመስላል።

የኢራንን ሰማያት ስለመቆጣጠር ትራምፕ ሲናገሩ "እኛ" የሚለውን ቃል የተጠቀሙበት እነዚያን መልእክቶች፣ ትራምፕ "እኛ" ማለታቸው ጥምረት መኖሩን ያሳያል። የት እንዳለህ እናውቃለን ግን አንገድልህም በማለት ትራምፕ ለካሜኔ የተናገሩት ቃል በግጭቱ ውስጥ የአሜሪካን ተሳትፎ የሚያመላክት ሆኗል።ዩ ጎቭ የተሰኘ የጥናት ማዕከል በሰራው ዘገባ አብዛኛዎቹ አሜሪካውያን የአሜሪካ ጦር በእስራኤል እና በኢራን ግጭት ውስጥ መግባት የለበትም ብለው ያምናሉ ብሏል። 60 በመቶው አሜሪካውን የዋሽንግተንን የጣልቃ ገብነት እርምጃን ሲቃወሙ 16 በመቶው ብቻ ድጋፍ ይሰጣሉ።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
👎6629😁3👍1👏1
በወልቂጤ ከተማ የአራት ዓመት የእንጀራ ልጁን አስገድዶ የደፈረው አባት በእስራት ተቀጣ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ አበበ ምሳዬ የ28 አመት ወጣት ሲሆን ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ/ም ሰአቱ በዉል ባልታወቀ ምሽት ላይ በወልቂጤ ከተማ አዲስ ህይወት ቀበሌ ልዩ ቦታዉ ጃይካ ስፈር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የወንጀል ድርጊቱን ፈጽሟል፡፡

የ4 አመት ህፃን ከሆነችው የግል ተበዳይ የእንጀራ ልጁ ሚጣ ዉበቱ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት ፈጽሟል የሚል አቤቱታ ለከተማዉ ፖሊስ መቅረቡን የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ሀላፊው አቶ ኤሊያስ ሰብለጋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።የወልቂጤ ከተማ መርማሪ ፖሊስም የቀረበለትን ክስ መነሻ በማድረግ ወንጀሉ የተፈጸመበት ቦታ ድረስ በመሄድ የምስክሮችን ቃል በመቀበል ተጨማሪ ማጣራቶችንና አካላዊ ምልከታ አድርጓል። የግል ተበዳይ  የጤና ሁኔታ ምርመራ እንድታደርግ ከተመቻቸ በኋላም የህክምና ውጤት ማስረጃውን ምርመራ ካደረገችበት ሆስፒታል አስመጥቶ ከምርመራ መዝገቡ ጋር በማያያዝ ምርመራውን በማጠናቀቅ ወደ ዐቃቤ ህግ ይልካል።

መዝገቡ የደረሰው የወልቂጤ ከተማ የሴቶችና ህጻናት ልዩ ምርመራና ክስ ዋና ስራ ሂደት ዐቃቤ ህግም ከመዝገቡ ጋር ተያይዘው የቀረቡትን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ከተፈጸመው ወንጀልና ከህጉ ጋር በማገናዘብ ተከሳሽ በህፃን ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረ ሥጋ ድፍረት በደል ወንጀል እና በዘመዶች መካከል የሚፈፀም የግብረስጋ ግኑኙነት የፈጸመ በመሆኑ በተደራራቢ ወንጀሎች ሁለት ክስ በወልቂጤ ከተማ ፍርድ ቤት ተመስርቶበታል።

ፍርድ ቤቱም ተከሳሽ ጉዳዩን በዝርዝር እንዲያስረዳ ጠይቆ  ከግል ተበዳይ ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ያደረገ መሆኑን አምኖ በዝርዝር ለችሎት ገልጿል። ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ህግን አስተያየት ከተቀበለ በኋላ ተከሳሽ በተከሰሰበት የወንጀል ህግ ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ ነው በማለት የጥፋተኝነት ውሳኔ አሳልፎበታል። የወልቂጤ ከተማ ፍርድ ቤት ሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽን ያርማል ሌሎችንም ያስተምራል በማለት በ21 አመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን አቶ ኤሊያስ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።

በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል
💔5414😢8🤬6😱4🔥2🤔1
እስራኤል የሚሳኤል መከላከያ እና መጥለፊያ መሳሪያዋ እየተሟጠጠ እንደሚገኝ አንድ ሪፖርት አመላከተ

ዎል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው እስራኤል የመከላከያ ጠለፋ መሳሪያዎቿ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ እና ይህም ሀገሪቱ ከኢራን የረዥም ርቀት የባለስቲክ ሚሳኤሎችን የመምታት አቅም ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል ብለዋል። አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣን ለጋዜጣው እንደተናገሩት ዋሽንግተን ለወራት የአቅም ችግር እንዳለ ታውቃለች እናም የእስራኤልን መከላከያ በመሬት፣በባህር እና በአየር ላይ እያሳደገች ነው።

ዘገባው የእስራኤል ጦር በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ቢጠይቀው ፈቃደኛ አልሆነም ብሏል። በቀጠለው የአየር ላይ ውጊያ ረቡዕ ረፋድ ላይ የኢራን ሚሳኤሎች በማዕከላዊ እስራኤል አካባቢ የእሳት ቃጠሎ አስከትለዋል። የኢራን ፋርስ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው ከተደረጉት ኢላማዎች መካከል አንዱ በሰሜን እስራኤል የሚገኘው የሜሮን አየር ማረፊያ ነው ብሏል። ስፍራው ስለመመታቱ ግን ምንም ፍንጭ የለም።

በእስራኤል በጦርነት ጊዜ ወታደራዊ የመረጃ ሳንሱር አለ፣ እናም ሚስጥራዊነት ያላቸው ኢላማዎች ከተመቱ ሚዲያዎች ስለ ጉዳዩ እንዲዘግቡ አይፈቀድላቸውም። ሌላው ማክሰኞ ቀደም ብሎ የተመታው የጦር ስፍራ ሄርዝሊያ ነው። በዚያ አካባቢ አውቶቡሶች ተቃጥለዋል። የኢራን መገናኛ ብዙኃን ስፍራው ወታደራዊ ቦታ ነው እያሉ ይገኛሉ።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
89👎12😁12👏6👍4🕊3
በምግብ እጥረት ለተጎዱ ህፃናት የተላከ አልሚ ምግብ በመሸጥ ለራሱ ጥቅም ያዋለዉ የጤና ፅህፈት ቤት ኃላፊ በእስራት ተቀጣ

በምስራቅ ቦረና ዞን ዋጫሌ ወረዳ የዋጫሌ ጤና ፅህፈት ቤት ኃላፊ የሆነዉ ግለሰብ በምግብ እጥረት ለተጎዱ ህፃናት የተላከዉን አልሚ ምግብ በመሸጥ ለራሱ ጥቅም በማዋሉ በእስራት ተቀጣ ።

የምስራቅ ቦረና ዞን ፖሊስ ዋና መምሪያ የሙስናና የመንግስት ገቢዎች ላይ የሚፈፀም ወንጀሎች ምርመራ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ገልገሎ ዱባ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ተከሳሽ በሩ ሮባ በዋጫሌ ወረዳ ጤና ፅህፈት ቤት በማገልገል ላይ ሳለ 120 ካርቶን ከዓለም የምግብ ፕሮግራም የተላከ ፕላንፕሌት ከሚሰራበት ጤና ፅህፈት ቤት ጭኖ ለሸቀጣሸቀጥ ሱቆች ሲያከፋፍል በመገኘቱ በሙስና ወንጀል መከሰሱ ተገልጿል ።

ግለሰቡ ስልጣኑን በመጠቀም በፈፀመዉ ወንጀል አቃቤ ህግ ከፖሊስ ጋር በመሆን የምርመራ መዝገቡን በማጣራት የሙስናና የመንግስት ገቢዎች ላይ የሚፈፀም ወንጀል ለመከላከል የወጣዉን መመሪያ ቁጥር 881/2007 ንዑስ አንቀፅ 11 በመጥቀስ ክስ መስርቷል ።

የአቃቤ ህግን ክስ የተመለከተዉ የምስራቅ ቦረና ዞን ከፍተኛ ፍረድ ቤት ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት ተካሳሹ በ8 ዓመት ከ5 ወር እስራትና በ10 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ መወሰኑን ምክትል ኢንስፔክተር ገልገሎ ዱባ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል ።

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
😁2618👍8🤔4
ከሚጠብቁት ድርጅት በመስበር የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች ከነ አባሪዎቻቸው ተይዘው በእስራት ተቀጡ

ተከሳሾቹ ወንጀሉን የፈፀሙት የካቲት 16 ቀን 2017 ዓ/ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ቅጥር ግቢ ከሚገኘው ቶም ቪዲዮ ግራፊና ፎቶ ግራፊ ማሰልጠኛ ተቋም በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ ነው፡፡ ሁለቱ ተከሳሾች በፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው ቶም የቪዲዮ ግራፊና እና የፎቶ ግራፊ ማሰልጠኛ ውስጥ በጥበቃ ሰራተኝነት ተቀጥረው ይሰራሉ፡፡

ማስተዋል ገላና እና ሀብታሙ ታደሰ የተባሉ የማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ የጥበቃ ሠራተኞች መርክነህ ታንጋና ታደለ ማሩጫ ከተባሉ ግለሰቦች ጋር በመመሳጠር የማሰልጠኛ ተቋሙን ዕቃ ግምጃ ቤት ሰብረው በመግባት ጠቅላላ ግምታቸው 2.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ 29 የፎቶ ግራፍ ካሜራዎች፣ 3 ቪድዮ ካሜራዎች፣ 2 ስፖት ላይቶች፣ 2 ማንዋል ላይቶች፣  የካሜራ ባትሪዎች፣ 10 የባትሪ ቻርጀሮች፣ 2 ኤልኢዲ ላይቶች፣ 4 የገመድ ማይኮች እንዲሁም የቻርጀር ማራዘሚያ በመስረቅና በተሽከርካሪ በመጫን የተወሰነውን እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኝ የማስተዋል ገላና ፎቶ ቤት ውስጥ ያስቀምጣሉ።

የቀረውን ደግሞ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ወላይታ ሶዶ ከተማ በመውሰድ በሌሎች የስራ ቦታቸው የደበቁና እንዲሸጥ ያደረጉ ሲሆን ፖሊስ ባከናወነው ጠንካራ የምርመራና የክትትል ስራ ተጠርጣሪዎቹን ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወሳል።

ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ሶስተኛ ወንጀል ችሎት ማስተዋል ገላና ሀብታሙ ታደሰ በጥበቃ ሰራተኝነት ተቀጥረው የነበሩ እያንዳንዳቸው በ8 ዓመት ፅኑ እስራት ሲቀጡ በአባሪነት ተሳትፎ የነበራቸው መርክነህ ታንጋና ታደለ ማሩጫ እያንዳንዳቸው በ3 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል።

#ዳጉ_ጆርናል
15🔥8
በኢራን ላይ የደረሱት ጥቃቶች ከእስራኤል ጋር ሲነጻጸር በ5 እጥፍ ይበልጣል ተባለ

በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ መቀመጫውን ያደረገው የየመከላከያ አስተሳሰብ የ Critical Threats ፕሮጀክት እና የጦርነት ጥናት ተቋም (CTP-ISW) እንደዘገበው የእስራኤል ጦር በኢራን ውስጥ ባሉ ቦታዎች ላይ የአየር ጥቃቶችን ኢራን በእስራኤል ኢላማዎች ላይ ካደረሰችው ጋር ሲነጻጸር በአምስት እጥፍ ይበልጣል። የእስራኤል ጦር በሰኔ 13 ኢራን ላይ ጥቃት ከሰነዘሩበት ጊዜ ጀምሮ 197 ጊዜ የአየር ድብደባ ማድረጋቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

በአንጻሩ፣ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ፣ በእስራኤል ውስጥ የኢራን ባሊስቲክ ሚሳኤል ጥቃቶችን ወይም የመጥለፍን ተፅዕኖ 39 ጊዜ ያህል መሆኑን ሪፖርት አረጋግጧል።እስራኤል እና ኢራን ለቀናት በቀጠለው የሚሳኤል ጥቃት በቴህራን ላይ ድብደባ ደርሴል። በማዕከላዊ እስራኤል የእሳት ቃጠሎ አስከትሏል። የእስራኤላውያን የእሳት አደጋ ተከላካዮች እሳቱን በመቆጣጠር ላይ ሲሆኑ በርካታ መኪኖችን ያወደመ ይመስላል።

የእስራኤል ጦር አርብ ዕለት በዋና ከተማዋ ቴህራን እና በኢራን ገጠራማ አካባቢዎች ጥቃቱን ከጀመረ ወዲህ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኢራን ሲገደሉ በአንፃሩ በእስራኤል ቢያንስ 24 ሰዎች ተገድለዋል። መቀመጫውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በእስራኤል ጥቃት ቢያንስ 585 ሰዎች በመላው ኢራን ሲገደሉ 1,326 ቆስለዋል ብሏል። ቡድኑ ከሟቾቹ ውስጥ 239 ሲቪሎች እና 126 የጸጥታ አባላት መሆናቸውን ገልጿል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
👎6824🤣10👍4👏1🤔1😢1🕊1💔1
በጋሞ ዞን የሦስት ዓመት ህፃን ሰርቃ  በመኖሪያ ቤቷ አልጋ ስር እጁና እግሩን በማሰር አፉን አፍና የተገኘችው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ከንባ ወረዳ ካምባ ከተማ ጠፍቶ ሲፈለግ የነበረው ህፃን  በህይወት መገኘቱን የከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።ህፃን ናታን ቦጋለ ሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ከቤት ወጥቶ ከሠፈር ህፃናት ጋር ወደሚጫወትበት ቦታ ያቀናል፣ ከወጣበት ሰዓት ጀምሮ ከሠፈር ልጆቹ መሃል እንደተሰወረ ሲታወቅ ቤተሰቦቹና የአከባቢው ሕብረተሰብ ፍለጋ ያደርጋል፡፡

የሕጻኑን መጥፋት ያረጋገጡት ወላጅ ቤተሰቦች ለፖሊስ  ቀርበው ጉዳዩን ያመለክታሉ፡፡ ፖሊስም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማዉጣት ሕፃኑ የጠፋበትን ሙሉ አካባቢ ብርበራ በማካሄድ ተጠርጣሪ ያምቡቄ ኤዳ የተባለች ግለሰብ ከምትኖርበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ማግኘቱን አስታዉቋል፡፡

የሦስት ዓመቱ ታዳጊ ሰኔ 10 ከቀኑ 8:30 ተከሳሽ በምኖርበት መኖሪያ ቤት አልጋ ሥር እጁ፣እግሩ ታስሮ አፉ ታፍኖ ከታገተበት በህይወት መገኘቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በማገት ወንጀል የተከከሰሰችው ግለሰብ  በሕግ ቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተጣራባት መሆኑን የተገለፀ ይህን መሰል ወንጀል  በአከባቢው ያልተለመደና  አስነዋሪ ድርጊት በመሆኑ በሕፃናት ላይ ለሚፈፀም ወንጀል ፖሊስ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
27😱14🤔3👍1
5
በመካከለኛው ምስራቅ ከእስራኤል በመቀጠል ከፍተኛው የአይሁድ አማኞች በኢራን ይገኛሉ

በኢራን እና በእስራኤል መካከል እየተባባሰ የመጣውን ግጭት አስመልክቶ የኢራን አይሁድ ማህበረሰብ ሀገሪቱን ለዘመናት ቤታችን ብለው ይጠሯታል። በግምታዊ መረጃ መሰረት ከ17,000 እስከ 25,000 የሚደርሱ ኢራናውያን አይሁዶች በአብዛኛው እንደ ቴህራን፣ ኢስፋሃን፣ ሺራዝ፣ ሃመዳን እና ታብሪዝ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ይኖራሉ። ከእስራኤል ቀጥሎ ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአይሁድ እምነት ተከታዮች ይገኛል።

በኢራን ፓርላማ የሆነው መጅሊስ፣ ለአይሁድ ማህበረሰብ አንድ መቀመጫን በምክር ቤቱ ውስጥ ይፈቅዳል።በኢስፋሃን ከተማ ውስጥ ከታወቁት የአይሁድ ምኩራቦች አንዱ አል አቅሳ ከሚባለው መስጊድ አጠገብ ይገኛል። በቴህራን ከተማ ውስጥ ቢያንስ 50 ምኩራቦች ይገኛሉ ። የአይሁዶች ማህበረሰብ በቴህራን ውስጥ የሃይማኖት ልዩነት ሳይፈጥር ሁሉንም ታካሚዎች የሚያስተናግድ ሆስፒታል ያስተዳድራል። አይሁዳውያን ክምከኢራን ጋር ያላቸው ግንኙነት ከ2,700 ዓመታት በፊት የጀመረ ሲሆን በቴህራን የአብሪሻሚ ምኩራብ ከፍተኛ ራቢ የሆኑት ዩነስ ሃማሚ ላሌዛር ይናገራሉ።

አይሁዳዊቷ አስቴር እና አጎቷ መርዶክዮስ የተቀበሩት በምእራብ ሃመዳን ከተማ እንደሆነ ይታመናል። በአይሁድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምሮት መሠረት አስቴር ከፋርስ ንጉሥ ከዜርክስ ጋር ትዳር መስርታለች። በቅርብ ታሪክ ውስጥ፣ አገሪቱ ከስፔን ኢንኩዊዚሽን ለሸሹ አይሁዶች አስተማማኝ መሸሸጊያ ሰጥታለች። የጀርመኑ ናዚ መሪ አዶልፍ ሂትለር አውሮፓን በወረረበት ወቅት የፖላንድ አይሁዶች ኢራን ጥገኝነት ጠይቀዋል። ነገር ግን በሣፋቪድ እና በቀጃር ዘመን አይሁዶች በግዳጅ እምነታቸውን እንዲቀይሩ በመደረጉ፣ የ1979 አብዮት ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የኢራናውያን አይሁዶች ወደ አሜሪካ እና እስራኤል ተሰደዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
38👎14👍10🤔6😱3🙏2
2025/07/13 21:04:14
Back to Top
HTML Embed Code: