Telegram Web Link
Forwarded from ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal (#Me_Lion)
በእስራኤል አራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ጋር ይከታተሉ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/e4whZmVDFao?si=xKiZJdAhf3GiQA-g

#ዳጉ_ጆርናል
በጋምቤላ ክልል ባለፋት ዘጠኝ ወራት ከ1.9 ሚሊዮን በላይ ኮንዶም ተሰራጭቷል ተባለ

በጋምቤላ ክልል የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ በመሆኑ የነገ ሀገር ተረካቢ በሆኑት አፍላ ወጣቶችና ልጃገረዶች ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት ከፍተኛ ነው ሲል የክልሉ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት አስታውቋል።

የጽ/ቤቱ  ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ  በክልሉ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የበርካታ ወገኖች ህይወት በኤች አይ ቪ ኤድስ ምክንያት ማለፉን መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።አያይዘውም በክልሉ ያለዉ ስርጭት ባለፉት ዓመታት ከነበረበት የመቀነስ አዝማሚያ ቢያሳይም የሚፈለገውን ያህል ውጤት ማምጣት አለመቻሉን ተናግረዋል።

በጽ/ቤቱ የዘርፈ ብዙ ምላሽ የኤች አይ ቪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አቡላ ድንጉር በበኩላቸው ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ባለፋት ዘጠኝ ወራት ለ 1ነጥብ 9 ሚሊዮን ሰዎች የኮንዶም ስርጭት ተከናውኗል።የኮንዶም ስርጭቱም በነፃ መከናወኑን የገለፁት አቶ አቡላ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች መከፋፈሉን አብራርተዋል።

በዋነኛነት ለወሲብ ሰራተኞች፣ለረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች፣ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቃሽ የሆኑና ጨምሮ ለሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ማሰራጨት ተችሏል ሲል ጽ/ ቤቱ ጨምሮ ገልጿል፡፡

ቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
በናይጄሪያ ከደረሰው አስከፊ የጎርፍ አደጋ በኃላ እስካሁን ከ700 በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም

በናይጄሪያ ሰሜን ማእከላዊ ኒጀር ግዛት ከሶስት ሳምንታት በፊት ከባድ የጎርፍ አደጋ ካጋጠማት በኃላ ከ700 የሚበልጡ የሞክዋ ማህበረሰብ አባላት እስካሁን ድረስ ጠፍተዋል ሲል የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ እለት ዘግበዋል። የኒጀር ግዛት ገዥ ኡማሩ ባጎ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ግዛቱ በቅርቡ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 207 ሰዎች መሞታቸውን ዴይሊ ትረስት ዘግቧል።

በሜይ 29፣ በደቡብ ነጋዴዎች እና በሰሜናዊ የግብርና አምራቾች መካከል ያለው ቁልፍ የንግድ ትስስር በሆነው የሞክዋ አካባቢ አስተዳደር ለሶስት ቀናት ሳያቋርጥ ከጣለው ዝናብ በኋላ ከባድ የጎርፍ አደጋ አጋጥሟል። ፕሬዝደንት ቦላ ቲኒዩ የብሄራዊ የድንገተኛ አደጋ አስተዳደር ኤጀንሲ እና የጸጥታ ሃይሎች በተጎዱ ማህበረሰብ ውስጥ የፍለጋ እና የነፍድ አድን ስራዎችን እንዲያጠናክሩ አዘዋል። ገዥ ባጎ ደግሞ ከ3,000 በላይ አባወራዎች ተፈናቅለዋል ብለዋል።

ከ 700 በላይ ሰዎች አሁንም የጠፉ ሲሆን የት እንዳሉ ለማወቅ ገና አልቻልንም። የጎርፍ አደጋው ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፤ ሲሉ አክለዋል። 283 ቤቶችና 50 ሱቆችም ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ገልፀዋል። የግዛቱ ርዕሰ መስተዳድሩ አያይዘውም የጎርፍ አደጋውን መንስኤ ለማወቅ የክልሉ መንግስት ከሙያ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የግምገማ ውጤት እየጠበቀ ነው ብለዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በኢትዮጵያ የአንጀት ካንሰር በአስከፊ ሁኔታ እየተስፋፋ ነው ተባለ

👉 ዓይደር ሆስፒታል በወር በአማካይ እስከ 50 ለሚሆኑ ታካሚዎች የአንጀት ካንሰር ህክምና እየሰጠ ነዉ


በዓለም ዙሪያ ሆነ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ የመጣው የአንጀት ካንሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከጡት ካንሰር እና ከ ማህፀን በር ጫፍ ካንሰር በመቀጠል በሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ገዳይ በሽታ ነው። በዓይደር ኮምፐርሄንሲቭ ሲፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአንጀት ካንሰር ህክምና በአንድ ወር በአማካይ ከ30 እስከ 50 ለሚሆኑ ታካሚዎች ህክምና እንደሚሰጥ እና አብዛኛዎቹ ታካሚዎች ደግሞ ከ45 ዓመት በላይ የሆናቸው ሴቶች መሆናቸዓ በሆስፒታሉ የካንሰር ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ደስታ ሙሉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

የአንጀት ካንሰር መንስኤው የአመጋገብ ችግር እንደሆነ የገለፁት ስፔሻሊስቱ ይህም ማለት ጥሬ ስጋ መመገብ፣ ከፋብሪካ የወጡ ምግቦችን ማዘውተር፣ ሲጋራ ማጨስ እና የአልኮል መጠጦች አብዝቶ መጠጣት ለአንጀት ካንስር ዋና አጋላጭ ምክንያቶች መሆናቸውን እና በተጨማሪም በዘር የሚተላለፍ የካንሰር አይነት እንደሆነም ተናግረዋል። ከ50 አመት እድሜ ክልል በላይ የሚሆኑ ሰዎችም ለካንሰር ተጋላጭ እንደሆኑ ገልፀዋል። ይህ የካንሰር አይነት በዘር ሊተላለፍ ይችላል ያሉን ዶ/ር ደስታ እስከ 10 በመቶ የሚሆን የትልቁ አንጀት ካንሰር ከወላጅ ወደ ልጅ የሚተላለፍ ነው።

የአንጀት ካንሰር ምልክቶች ለማስረዳት የሚከብዱ አንድ አንድ ስሜቶች የሚስተዋሉ ሲሆን በፊንጢጣ የሚወጣ ደም እና ከባድ ድርቀት ምልክቶቹ እንደሆነም አንስተዋል፡፡ አያይዘውም ደረጃው ከፍ እያለ ሲመጣ ወደ ጉበት እና ሳንባ በመሄድ ዓይንን ቢጫ የማድረግ እና እግርን የማሳበጥ እንዲሁም ሳልን እንደሚያመጣም ገልፀዋል።በቶሎ ወደ ጤና ተቋም የሚመጡ ታማሚዎች በቀዶ ህክምና፣ የኬሞና የራድዮ ቴራፒ ህክምና ይሰጣቸዋል የሚሉት ስፔሻሊስቱ ነገር ግን ታማሚዎቹ በቶሎ ወደ ህክምና ተቋም ቢመጡም ካንሰሩ በፍጥነት ተሰራጭቶ የሚገኝበት ወቅት እንዳለም ዶክተር ደስታ ሙሉ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል
የእስራኤል ታንኮች የምግብ እርዳታ ለማግኘት በጋዛ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ በፈፀሙት ጥቃት 59 ሰዎች ተገደሉ

የእስራኤል ታንኮች በጋዛ ውስጥ ከጭነት መኪናዎች እርዳታ ለማግኘት ሲሞክሩ በተሰበሰበው ሕዝብ ላይ ተኩሰው ቢያንስ 59 ሰዎች መሞታቸውን የህክምና ባለሙያዎች ተናግረዋል። ተስፋ የቆረጡ ነዋሪዎች ለምግብ ፍለጋ ሲታገሉ ደም አፋሳሽ ክስተቶች ከተፈጠሩባቸው ሁኔታዎች መካከል አንዱ ነው።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋራ ቪዲዮ በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ በካን ዮኒስ ጎዳና ላይ በደርዘን የሚጠጉ አስከሬኖች እንደነበር ያሳያል። እ.ኤ.አ ከጥቅምት 2023 ጀምሮ በጋዛ በሃማስ ከሚመራው የፍልስጤም ታጣቂዎች ጋር ጦርነት የገጠመው የእስራኤል ጦር በአካባቢው መተኮሱን አምኖ ጉዳዩን እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል።

ሮይተርስ ያነጋገራቸው እማኞች እንደተናገሩት የእስራኤል ታንኮች መንገዱን ከሚጠቀሙ የእርዳታ መኪኖች ምግብ ለማግኘት በማሰብ በዋናው ምስራቃዊ መንገድ በካን ዮኒስ በኩል በተሰበሰቡ በሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ቢያንስ ሁለት የመድፍ ዛጎሎችን ተኩሰዋል። በናስር ሆስፒታል ከሮይተርስ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረገው የዓይን እማኝ አላአ “በድንገት ወደ ፊት እንድንሄድ ፈቀዱልን እና ሁሉም እንዲሰበሰብ አደረጉ፣ ከዚያም መተኮስ ጀመሩ” ሲል ተናግሯል፣ በናስር ሆስፒታል የቆሰሉ ተጎጂዎች መሬት ላይ እና ኮሪደሮች ላይ ወድቀው በቦታ እጦት ሲሰቃዩ ታይተዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በእስራኤል ኢራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ጋር ይከታተሉ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/e4whZmVDFao?si=xKiZJdAhf3GiQA-g

#ዳጉ_ጆርናል
ባለፉት 11 ወራት በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈፀሙ 24 ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

አብዛኛው የኢትዮጲያ ኢኮኖሚያዊ እና የማህበራዊ ልማት እንቅስቃሴዎች መሰረት የሚያደርጉት በኤሌክትሪክ ላይ በመሆኑ አስተማማኝ ኤሌክትሪክ ማቅረብ የህልዉናና ልማትነን የማፋጠን ጉዳይ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታዉቋል ።

ባለፋት ወራት በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማትና ኃይል ስርቆት ላይ 239 ወንጀሎች ለፖሊስ ክስ የተመሠረቱ ሲሆን በገንዘብ ሲተመን የ218 ሚሊዮን ብር ኪሳራ በተቋሙ ላይ መድረሱ ተነግሯል ።

ከእነዚህ ከቀረቡ 239 ወንጀሎች ዉስጥ ባለፋት 11 ወራት 24 ግለሰቦች ብቻ ጥፋተኝነታቸዉ ተረጋግጦ ከ4ወር እስከ 10 ዓመት እስራት እንዲቀጡ መወሰኑ ከደረሰዉ ጉዳት አንፃር ወንጀለኞችን ተከታትሎ ከመያዝ እና ለፍርድ ከማቅረብ አንፃር ሰፊ ክፍተት መኖሩን የሚያሳይ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የህግና ስነምግባር ስራ አስፈፃሚ አቶ አበበ ተስፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

የተሟላ የህግ ማዕቀፍ እና የአስፈፃሚ አካላት አደረጃጀት ቢኖርም እነዚህን ወንጀለኞች ተከታትሎ ተገቢዉን ምርመራ በማድረግ በህግ ከማስጠየቅ አንፃር ሰፊ ስራ እንደሚጠይቅ አቶ አበበ አክለዋል ። በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ የሚደርሱ ዉድመቶች ለደንበኞች የቅሬታ ምንጭ እየሆኑ መምጣታቸዉን የገለፁት ስራ አስፈፃሚዉ በተለይም ከፍተኛ የሀይል ማስተላለፊያ መስመሮች አከባቢ ጥቃት ሲደርስ ሰፊ ተደራሽ ህዝብን  ስለሚሸፍን የሚኖረዉ ተፅዕኖ ከፍተኛ ነዉ ብለዋል ።

ከሰሞኑ በአማራ ክልል ባህርዳር አከባቢ በሚገኙ ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ በደረሰ ዝርፊያ  በርካታ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደተቋረጠባቸዉ አቶ አበበ ጨምረዉ ለብስራት ተናግረዋል፡፡

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል
ሰሜን ኮሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን የሩስያ ኩርስክን ግዛት መልሶ ለመገንባት እንደምትልክ አስታወቀች

ሰሜን ኮሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን በሩሲያ በጦርነት የተመሰቃቀለውን የኩርስክ ግዛት መልሶ ለመገንባት እንደምትልክ የሞስኮ የጸጥታ ሃላፊ አስታውቀዋል።ከሰሜን ኮሪያው ኪም ጆንግ ኡን ጋር በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ የተነጋገሩት የሩስያ የፀጥታው ምክር ቤት ፀሃፊ ሰርጌ ሾይጉ ቡድኑን “ወንድማማች ረድኤት” ሲሉ ገልጸዋል በማለት የሩሲያ መንግስታዊ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ጎረቤት ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን እቅዱን በፍጥነት አውግዘዋል።ሴኡል በቡኩሏ ይህ እርምጃ የተባበሩት መንግስታት በሰሜን ኮሪያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ መጣስ ነው ስትል ተናግራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገውን ጦርነት እንድትዋጋ እንደረዱት በሪፖርቱ ወቅት በሁለቱ ሀገራት መካከል ጥልቅ የሆነ ወታደራዊ ትብብር ለወራት እንደነበር መረጃዎች ሲሽከረከሩ ቆይተዋል።

እሮብ እለት ላይ የሩስያ ታስ የዜና ወኪል ሾይጉን ጠቅሶ እንደዘገበው ሰሜን ኮሪያ የኩርስክ ክልልን መልሶ ለማቋቋም የሚረዳ "ግንበኞችን ፣ ሁለት ወታደራዊ ብርጌዶችን ወይም  5,000 ወታደሮች " እንዲሁም 1,000 ፈንጂ አምካኞችን እንደምትልክ በዘገባው ላይ ተገልጿል። "ይህ ከኮሪያ ህዝብ እና መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለአገራችን የተደረገ ወንድማዊ እርዳታ ነው" ሲሉ ሾይጉ መናገራቸውን የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ ያሳያል። የሰሜን ኮሪያ መንግስት መገናኛ ብዙሃንም ስብሰባው ኪም እና ሾይጉ ሌሎች "የረጅም ጊዜ እቅዶችን" ሲወያዩ እንደነበር አክሎ ገልጿል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
ብስኩት ልግዛልሽ በማለት አታሎ የስምንት ዓመት ታዳጊን አስገድዶ የመድፈር ጥቃት የፈጸመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በምስራቅ ቦረና ዞን ነገሌ ወረዳ አስተዳደር  በስምንት ዓመት ታዳጊ ላይ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት የፈጸመው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱ ተገልጿል ።

የምስራቅ ቦረና ዞን ፖሊስ ዋና መምሪያ የሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዘውድነሽ አበበ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ተከሳሽ ዮሴፍ ፈጠነ የታዳጊዋ ወላጆች ወደ ስራ መሄዳቸውን ጠብቆ ብስኩት ልግዛልሽ በማለት አታሎ  ወደ ራሱ መኖሪያ ቤት  በመውሰድ ጥቃቱን እንደፈጸመባት ተጠቁሟል።

ህጻኗ ደም እየፈሰሳት መንገድ ላይ  ወድቃ ያገኟት ነዋሪዋች  ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ  ወደ ህክምና  ቦታ ተወስዳ እርዳታ እንድታገኝ መደረጉ ተገልጿል ። ተጎጂዋ ህክምና ከተሰጣት በኋላ ለፖሊስ በሰጠችው መረጃ  መሰረት ጥቃቱን የፈጸመባት የ31 ዓመቱ ግለሰብ  በቁጥጥር  ስር መዋል ችሏል።

ፖሊስ አስፈላጊውን በምርመራ በሀኪም እና ከሰዎች በተገኛ መረጃ መሰረት በማጠናከር  መዝገቡን ለዓቃቢ ህግ ልኳል ። ዓቃቢ ህግ በወንጀል ህግ ቁጥር 6 /27 በህጻናት ላይ በሚፈጸም የህጻናት የግብረስጋ ድፍረት  በደል  በመጥቀስ ክስ መስርቷል።

ክሱን  ሲከታተል የቆየው የምስራቅ ቦረና ዞን  ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኔ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተለሳሽ የሱፍ ፈጠነ ዕድሜዋ ባልደረሰች ልጅ ላይ አታሎ የመድፈር ጥቃት በመፈጸም ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በአስራ አምስት ዓመት እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን  ዋና ኢንስፔክተር ዘውድነሽ አበበ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
ፑቲን የኢራኑን መሪ ካሜኔይን ለመግደል ስለሚቃጣ ማንኛውም ሙከራ የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ አደረጉ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እስራኤል ወይም አሜሪካ የኢራንን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒን ለመግደል ሙከራ ሊያደርጉ ይችላሉ በሚለው ግምት ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ከአለም አቀፍ ጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት የጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት የኢራን እና እስራኤል ግጭት ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ግፊት ማድረጋቸውን እንደቀጠሉ ተናግረዋል። በሴንት ፒተርስበርግ ከተካሄደው ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ፎረም ጎን ለጎን ሐሙስ ዕለት ስለ ካሜኒ ለተጠየቁት ጥያቄዎች ሲመልሱ "ከቻልኩ ይህ ለጥያቄዎ በጣም ትክክለኛው መልስ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፤ ስለዚህ ጉዳይ መወያየት እንኳን አልፈልግም ሲሉ ተደምጠዋል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ግጭቱ በኢራን የአገዛዝ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል ሲሉ ተናግረዋል። የእስራኤል ጥቃቶች ከፍተኛ የጦር መሪዎችን እና ከፍተኛ የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸውም ይታወቃል። መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የኢራን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እንደገለፀው ካለፈው አርብ ጀምሮ የእስራኤል ባደረገችው ጥቃት ቢያንስ 585 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን 239 ንፁሀን ዜጎች መሞታቸው ይታወሳል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዋሽንግተን ካሜኔ  ያሉበትን ቦታ ታውቃለች ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል። ምንም እንኳን አሜሪካ እስራኤል በኢራን ላይ የምታደርገውን ጥቃት ልትቀላቀል እንደምትችል ባይገልፁም ዩናይትድ ስቴትስ ለጊዜው እርምጃ እንደማትወስድ ተናግረው ነበር። ፑቲን የኢራን ህዝብ ከመንግስት ጀርባ አንድነቱን እንደቀጠለ ተናግረዋል። "ዛሬ በኢራን ውስጥ በሁሉም የውስጣዊ የፖለቲካ ሂደቶች ውስብስብነት እዚያ እየተከናወኑ እንደሆነ እና በሀገሪቱ የፖለቲካ አመራር ዙሪያ የህዝቡ ውህደት እንዳለ እናያለን" ብለዋል ።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በህገወጥ አደን ምክንያት በባቢሌ መጠለያ የሚገኙ የዝሆኖች ቁጥር ቀንሷል ተባለ

የሰው ሰራሽ ጫናዎችና የህገወጥ አደን ተግባራት በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ላይ አሉታዊ ተፅእኖን እያሳደሩ ይገኛሉ ሲል የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ በባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ  ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማካሄዱ ተገልጿል።የባለስልጣኑ  ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ በመድረኩ ላይ ባስተላለፋት መልዕክት የአየር ንብረት ለውጥ ፣የብዝሀ ህይወት ውድመት እና የአካባቢ ብክለት ዓለማችንን በከፍተኛ ሁኔታ እያስጨነቁ ያሉ ችግሮች ናቸው ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያን ጨምሮ አብዛኛዎቹ የጥበቃ ቦታዎች ወደ ከፋ ችግር እየገቡ ያሉት በአንድም በሌላም  ከእነዚህ ችግሮች ጋር  ተያያዥነት ባላቸው ምክንያቶች እንደሆነ አስረድተዋል።ከዚህ ችግር ለመውጣት ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል  የመፍትሄ አካል በመሆን  የተፈጥሮ ሀብትን በሀላፊነት ሊጠብቅ  ይገባል ሲሉ አሳስስበዋል።

በባለስልጣኑ የጥበቃ ቦታዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ አቶ ካሳዬ ዋሚ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ህገወጥ አደንን ተከትሎ በመጠለያው የሚገኙ ዝሆኖች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል።በዚህም የተነሳ ከዚህ ቀደም በመጠለያው ከ3መቶ እስከ ከ4 መቶ በላይ ዝሆኖች ይገኙ እንደነበር ገልፀው በአሁኑ ወቅት ላይ ግን ከ1መቶ 35 በላይ ዝሆኖች ብቻ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በመሆኑም የፓርኩን ህልውና ለመጠበቅ የጥበቃ ቦታውን ዳር ድንበር እንዴት መጠበቅ ይቻላል በሚለው ዙሪያ በውይይት መድረኩ የቀጣይ ጊዜ የመፍትሄ አቅጣጫ ተቀምጧል ሲሉ አቶ ካሳዬ ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
የመንግስት ስራተኛ የሆነው ግለሰብ 100 ሺህ ተቀጣ

በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በእግረኞች መንገድ ላይ በኮድ 4 ተሽከርካሪ ሲሄድ የተገኘ አንድ አሽከርካሪ 100,000 ብር ተቀጥቷል።

ይህ ግለሰብ ህብረተሰቡ የሰጠውን ጥቆማ ተከትሎ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን፣ ከፌደራል ፖሊስ ሲቲዝን ኢንጌጅመንት እና ከአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር ውሎ ነው ይህ ቅጣት የተላለፈበት።

ጉዳዩን ይበልጥ የሚያስገርመው ደግሞ ተሽከርካሪው የመንግስት ንብረት፣ በተለይም የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ-ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት የሚጠቀምበት መሆኑ ነው።

ይህ የሚያሳየው ህግን መጣስ የሚያስከትለው ቅጣት

* ለመንግስትም ሆነ ለግል፣
* ለግለሰብም ሆነ ለድርጅት

ምንም አይነት ልዩነት እንደማይደረግ ነው።

ምንጭ :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን

#ዳጉ_ጆርናል
ሕይወት ለማዳን ሕይወቱን ያለፈው የእሳት አደጋ ባለሙያ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ

በትላንት ሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ዕለት በአጋጠመ አደጋ የሰዉን ህይወት ለመታደግ ሲል መስዋዕት የሆነዉ የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ የቀብር ስነ-ስርዓት ተፈጸመ።

በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ የነበረዉ ዮናታን ገብሬ በትላንትናዉ እለት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በአጋጠመ አደጋ በአደጋ ዉስጥ የነበሩ ሰዎችን ለመታደግ ሲል መስዋዕት ሆኗል።

የቀብር ስነ-ስርዓቱም የኮሚሽኑ ከፍተኛና የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም የኮሚሽን መ/ቤቱ ሰራተኞችና ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት ዛሬ ሰኔ 12 ቀን 2017 ዓ.ም በቀጨኔ መድሀኒዓለም ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

#ዳጉ_ጆርናል
2025/06/29 09:15:16
Back to Top
HTML Embed Code: