Telegram Web Link
በእስራኤል ኢራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ጋር ይከታተሉ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/d45g1548L5Y?si=lQAUN_d-D8cTHNQZ

#ዳጉ_ጆርናል
6👍1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአልቤርቶ ቫርኔሮ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ


ከ1950ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ፈር ቀዳጅ በነበሩት አልቤርቶ ቫርኔሮ ህልፈት የተሰማኝን ሀዘን ለመግለጽ እፈልጋለሁ። ስራቸው የሀገራችንን የግንባታ ከባቢ እና ታሪካዊነት ያላቸው ምልክቶችን ላቅ ባለ ደረጃ የቀረፀ ነው።

ከታሪካዊ ስራዎቻቸው መካከል የአፍሪካ አዳራሽ (የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን)፣ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት፣ ሂልተን ሆቴል፣ ሚሊኒየም አዳራሽ፣ የጅማ አባጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ ማሻሻያ፣ የአብርሆት ቤተመጻሕፍት፣ የአንድነት ፓርክ እና የብሔራዊ ቤተመንግሥት እድሳት ሥራ ይገኙበታል።

የሥራ ውርሳቸው በነዚህ ብሔራዊ ምልክቶች እና በሚወክሉት የእድገት ትእምርት ሲታወስ ይኖራል። ለነፍሳቸው ረፍትን፣ በረፍታቸው ላዘኑ ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን።

#ዳጉ_ጆርናል
👎29👍1612🥰5😢5🕊1
ኤሌክትሪክ ተቋርጦ የሚቆይበትን ሰአት ቀድሞ ከነበረበት 365 ሰአት ወደ 152 ለማድረስ እየተሰራ ይገኛል ተባለ

የኤሌትሪክ ሀይል ተቋርጦ የሚቆይበትን ሰአት በ2012 ዓመት ከነበረው 365 ሰአት በ2017 ወደ 152 ለማድረስ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

በአገልግሎቱ የኮሚኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ አንዋር አብራር ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በሴክተሩ ከሚታዮ ዋነኛ ችግሮች መካከል የኤሌክትሪክ መቋረጥ ነው።በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱ  ለዜጎች የኤሌክትሪክ አገልግሎትን በአግባቡ ተደራሽ ለማድረግ ይህን ችግር ሙሉ ለሙሉ ለመቅረፍ እየሰራ ይገኛል።

ለሀይል መቋረጥ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ጥቅም እየዋሉ እንደሚገኙ የተገለፀ ሲሆን ሀይል ተቋርጦ የሚቆይበትን ሰአት ለመቀነስ ተቋሙ የአቅም ማሳደግና መልሶ ግንባታ ፕሮጀክቶችን በስፋት እያከናወነ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

በሀዋሳ፣በአዳማ፣በድሬደዋ፣በመቀሌ፣በደሴ፣ባህርዳር፣እና በጅማ ከተሞች የሀይል መቆጣጠሪያ ማእከል ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ተብሏል።በዚህም ሀይል ጠፍቶ እንዳይቆይ ፣የመስመሮችን ጤንነት ከአንድ ማእከል ለመከታተል ትልቅ ሚና እንዳለው ተገልጿል፡፡

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
😁4019🤔4👎3🤬2👍1🤝1
የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ሂዝቦላህ ከኢራን ጋር ጥምረት እንዳይፈጠር አስጠነቀቁ

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ የሊባኖሱን ሂዝቦላህ ቡድን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስጠንቅቀዋል፣ እስራኤልን በሚያስፈራሩ "አሸባሪዎች" ላይ ትዕግስትንችን ቀጭን ነው ሲሉ ዝተዋል። "የሂዝቦላህ ዋና ፀሃፊ ከቀደምቶቹ ትምህርት እየተማረ አይደለም እናም በኢራን አምባገነን ትእዛዝ መሰረት በእስራኤል ላይ እርምጃ እንደሚወስድ እየዛተ ነው" ሲሉ ካትዝ በኤክስ ላይ በለጠፈው ጽሁፍ አጋርተዋል።

የሂዝቦላህ የቀድሞ መሪ ሀሰን ናስራላህ ባለፈው አመት እስራኤል በሂዝቦላ ላይ ባካሄደችው ዘመቻ መገደላቸው ይታወሳል። "እስራኤላውያን በሚያስፈራሩ አሸባሪዎች ላይ ቴላቪቭ ትዕግስት እንዳጣች እንዲጠነቀቅ እና እንዲረዱት ለሊባኖሱ ሂዝቦላ ተግሳፅ አቀርባለሁ።" የሂዝቦላህ መሪ ናኢም ቃሴም ሃሙስ ዕለት እንዳሉት የሊባኖስ ቡድን በኢራን ላይ እየተወሰደ ያለውን "ጨካኝ የእስራኤል-አሜሪካዊያን ጥቃት" ላይ እርምጃ ቡድኑ እንደሚወስድ አስታውቀዋል።

በሌላ በኩል የሊባኖስ ተደማጭነት ያላቸው የፓርላማ አፈ-ጉባዔ ናቢህ በሪ፣ በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የሺዓ ፖለቲከኛ እና የሂዝቦላ የቅርብ አጋር ሲሆኑ ትናንት ምሽት ለሀገር ውስጥ ኤም ቲቪ ዜና ሲናገሩ ሊባኖስ በእስራኤል ግጭት ከኢራን ጋር እንደማትቀላቀል ያላቸውን ማረጋገጫ ገልፀዋል። “ሊባኖስ ወደ ጦርነት እንደማትገባ 200 በመቶ እርግጠኛ ነኝ” ሲሉ ቤሪ ለዜና ምንጩ ተናግረዋል፣ ምክንያቱም ይህን ለማድረግ ምንም ፍላጎት ስለሌላት እና ብዙ ዋጋ ስለሚከፍል ነው ብለዋል። አክለውም “ኢራን እኛን አትፈልግም። ድጋፍ የሚያስፈልገው ለእስራኤል ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
😁5826🕊4👏3🤬1
ካቦድ ማርኬቲንግ ሶሉሽን   የመኖሪያ ቤት እጥረት መቅረፍ ያስችላል የተባለለትን ለሶስት ቀን የሚቆይ ኤክስፖ አዘጋጀ

ካቦድ ማርኬቲንግ ሶሉሽን ላለፉት 20 ዓመታት  የሪል እስቴት ቢዝነሶቹን በማደራጀት፣ በሽያጭ ፣ ገዢዎችን ከሻጮች በማገናኘት ፣ለሽያጭ ባለሙያዎች ነጻ ስልጠናዎችን በመስጠት የስራ እድል በመፍጠር የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱ የካቦድ ማርኬቲንግ ሶሉሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ወ/ሮ ኤዶም ዳምጠው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ካቦድ ማርኬቲንግ ሶሉሽን እና እህት ኩባንያው የሆነው ዶክሳ ቢዝነስ ትሬዲንግ የሪል እስቴቶችን ኤክስፖ በዓይነቱ ለየት ባለ መልኩ  የሚዘጋጅ  እንደሚሆን እና   ቤት ለገዢው ሱቅ ለነጋዴው በሚል መሪ ቃል  መዘጋጀቱ ነግረውናል።

ካቦድ ማርኬቲንግ በኮሪደር  ልማት ላይ የተገነቡ  ሱቆችን ለነጋዴዎች ያቀርባል ተብሏል። ኤክስፖ ዓላማውን ያደረገው   ሪል እስቴቶች ትክክለኛ ስራቸው እንዲያሳዩ  ቤት ፈላጊዎች ደግሞ የሚፈልጉት መርጠው ቤተሰብ እንዲሆኑ በማሰብ ነው ።

በተጨማሪም  የረጅም ጊዜ አከፋፈል እና ጥራት ያላቸው ቤቶችን ለመምረጥ ትልቅ እድል ይከፍታል ተብሏል። የኤክስፖው አዘጋጅና አስተባባሪ አቶ አሜን ዳንኤል እንደተናገሩት ካቦድ ሪልእስቴት 2025  ለሶስት ቀናት ማለትም ከሰኔ27 እስከ 29  የሚቆይ ሲሆን ቴምር ሪልእስቴት፣ፕራይም ሪል እስቴት፣ ካቮድ ኮሜርሺያል፣ ፓልም ሪል እስቴት ፣ጌት አስ ሪል እስቴት ፣ኦቪድ ሪልእስቴት፣  ላይፍ ታይም ፕሮፐርቲስ ፣ ቤዝ ሪል እስቴት  ይገኙበታል ተብሏል ።

በኤክስፖ ላይ ከሚገኙት ሪል እስቴቶች ፓልም ሪል እስቴት 10 በመቶ ቅናሽ ካቮድ ኮሜርሻል ከ 1.2 እስከ 1.4 ሚሊዮን ብር ቅናሽ ፣ ቴምር ሪልእስቴት ደግሞ ሙሉ ክፍያ ለሚከፍል 25 በመቶ  ቅናሽ እንደሚያደርግ ሌሎችም  ለደንበኞች ያዋጣል ያሉትን ቅናሽ  እደሚያቀርቡ የካቦድ ማርኬቲንግ ሶሉሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ኤዶም ዳምጠው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

ይህ አይነት የሪል እስቴት ኤክስፖዋች የማማከር የማሰልጠን እንዲሁም በከተማው ውስጥ ያለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት መቅረፍ የሚቻልበት ነው ተብሏል።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
14😁9
እናት ባንክ በአካታች የባንክ አገልግሎት ዘርፍ ቀዳሚ ባንክ ሆና ተመረጠች

እናት ባንክ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር ባካሄዱት የአካታች የባንክ አገልግሎት የምዘና መስፈርት ከሀገሪቱ ባንኮች ቀዳሚ ሆና በመመረጥ እውቅና እንደተሰጣት ብስራት ሰምቷል።

እናት ባንክ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማጎልብት ሁሉን አቀፍ የሴቶች አካታች የባንክ አሰራርን አጠናክሮ  እንደሚቀጥል የገለፁት የባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዓለም ባንክ የሥርዓተ-ፆታ ፈጠራ ጋር በመተባበር በአካሄዱት የ2025 የባንኮች የስርዓተ ፆታ አካታችነት ምዘና መስፈርት መሰረት እናት ባንክ የተሻለ ስራ በመስራቱ ከ30 የኢትዮጵያ ባንኮች የመጀመሪያና ብቸኛ  ትራንስፎርሚሽናል ባንክ መባሉንም ተገልፆል፡፡

ከ55 በመቶ በላይ የባንኩ የቦርድ አባላት ሴቶች መሆናቸው እንዲሁም ከ22 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ስራ ፈጣሪ ሴቶች 1.4 ቢሊዮን ብር ካለዋስትና በማበደር የራሳቸውን ስራ እንዲጀምሩ ማስቻሏ ከተመረጠችባቸው ተግባራት ተጠቃሽ ናቸው ተብሏል።

እናት ባንክ ከምስረታዋ አንስቶ ሴቶች ወደ ተቋሟ ከፍተኛ አመራርነት ሚና እንዲመጡ በልዩ ሁኔታ እየሰራች መሆኑ የተነገረ ሲሆን ባንኳ ካላት ከ25 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች ውስጥ ከ15 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውም ተገልጿል።

በቀጣይ እናት ባንክ በመላ አገሪቱ  የቅርንጫፍና የዲጂታል  ባንኪንግ አገልግሎት  ተደራሽነቱን በማስፋት አዳዲስ አካታች የባንክ አሰራሮችን በመተግብር  በአካታች የባንክ አሰራር የተገኙ  ውጤቶችን ይበልጥ አጠናክሮ  እንደሚቀጥል ተነግሯል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
20👍4👎4😁3
የኢራን ፔዝሽኪያን እስራኤል ማጥቃት ከቀጠለች ኢራን የበለጠ ጠንካራ ምላሽ እንደምትሰጥ ተናገሩ

የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ግጭቱን ለማስቆም ብቸኛው መንገድ እስራኤል የምታደርገውን የአየር ጥቃት እንድታቆም ነው ብለዋል።በኢራን ሚዲያ በተላለፈዉ የፕሬዝዳንቱ መግለጫ "ሁልጊዜ ሰላም እና መረጋጋትን እንከተላለን" ብለዋል::"አሁን ባለው ሁኔታ ዘላቂ ሰላም የሚኖረው የጽዮናዊው ጠላት ጦርነቱን ካቆሙ እና የሽብር ቅስቀሳዎቹን ለማስቆም ጠንካራ ዋስትና ከሰጡ ብቻ ነው።"ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ፔዝሽኪያን "ይህን አለማድረግ ግን ከኢራን የበለጠ ኃይለኛ እና ጸጸት የሚያስከትክ ምላሽ እንደሚሰጥ" አስጠንቅቀዋል፡፡

በሌላ በኩል የኢራን የኒውክሌር ምርምር ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤትን ጨምሮ ከ60 በላይ የሚሆኑ የጦር አውሮፕላኖችን በቴህራን እና በሌሎች ቦታዎች በደርዘን የሚቆጠሩ ኢላማዎችን መምታታቸውን የእስራኤል ጦር አስታዉቋል።በደቡባዊ እስራኤል ቤርሳቤህ ከተማ የቴክኖሎጂ ፓርክን በመምታት የኢራን ሚሳኤል ቀደም ብሎ በተፈጸመ ጥቃት ህንጻዎች ላይ ጉዳት አድርሷል። የሞተ ሰው ባይኖርም ሰባት ሰዎች ግን በጉዳት ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።

በቴህራን ዩኒቨርሲቲ የአለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር ፎአድ ኢዛዲ ለአልጀዚራ በጄኔቫ ስለሚካሄደዉ ጉባኤ አስመልክቶ እንደተናገሩት የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ምንም አይነት ድርድር ለማድረግ እንዳልተዘጋጁ ግልፅ ነው የእስራኤል ጥቃት በመቀጠሉ የተነሳ ነዉ ብለዋል፡፡"ሲደራደሩ መስጠት እና መቀበል ነው" ነገር ግን በቴህራን እና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች ቦምቦች እየተጣሉ ኢራን በዚያ የመስጠት እና የመቀበል ዘይቤ ውስጥ መሳተፍ አትችልም ሲሉ ተደምጠዋል ።

አራግቺ በጄኔቫ "ከድርድር የተለየ ንግግር ያደርጋሉ" በማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአውሮፓ ባለስልጣናትን ከኢራን የፈለጉትን አይነት ስምምነት ማለትም የባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተው የሚባለዉ ነገር አይፈጠርም፤ ምክንያቱም ኢራን መከላከያ የሌላት መሆን ስለማትችል ነዉ ብለዋል፡፡"ኢራን የባሊስቲክ ሚሳኤሎች ባይኖሯት ኖሮ ዛሬ ቴህራን ውስጥ የእስራኤል እና የአሜሪካ ወታደሮች ታገኛላችሁ ብዬ አስባለሁ" ሲሉ አክለዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
70😁8👍1🤝1
2025/07/13 10:30:14
Back to Top
HTML Embed Code: