100 ሺህ ብር ተቀጣች
በብስክሌት መንገድ ላይ በመኪና የነዳች ግለሰብ የ100,000 ብር ቅጣት ተጣለባት!
አዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በለሚኩራ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 8፣ ሲኤምሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ በልማት ኮሪደር ውስጥ በተዘጋጀው የብስክሌት መንገድ ላይ መኪና ስታሽከረክር የተገኘች ግለሰብ ላይ የገንዘብ ቅጣት እንደጣለ አስታወቀ።
ግለሰቧ በሰላምና ጸጥታ አካላት እና በአዲስ አበባ ትራፊክ ፖሊስ ትብብር በቁጥጥር ስር ውሎ የተሽከርካሪዋ ባለቤት 100,000 ብር እንዲከፍል ተደርጓል። ባለስልጣኑ ግለሰቧ በቸልተኝነት የፈፀመችውን የትራፊክ ደንብ ጥሰት
የባለስልጣኑ ኦፊሰሮች ባደረጉት ክትትልና ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት እርምጃ መወሰዱን ገልጿል።
Via የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
#ዳጉ_ጆርናል

አሜሪካ ኢራን ላይ የአየር ጥቃት ሰነዘረች
አሜሪካ ፎርዶውን ጨምሮ ኢራን ውስጥ በሚገኙ 3 የኒውክሌር ተቋማት ላይ ጥቃት ማድረሷን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናግረዋል።
አሜሪካ በፎርዶ፣ ናታንዝ እና ኢስፋሃን በሚገኙ የኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ “በጣም የተሳኩ” ጥቃቶችን ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ገፃቸው “የቴህራን የኒውክሌር መርሃግብር ዘውድ” የሆነው ፎርዶው ጠፍቷል ሲሉ ጽፈዋል። ትራምፕ ኢራን ለመልሶ ማጥቃት ከተነሳች መዘዙ ከባድ መሆኑን አስጠንቅቀዋል። "አስታዉሱ ቀሪ ኢላማዎች አሉን" ሲሉ ኢራንን አስፈራርተዋል።
ኢራንም በፎርዶው የኒውክሌር ጣቢያ ጥቃት መድረሱን አረጋግጣለች። በጥቃቱ የዩኤስ ቢ-2 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች ተሳትፈዋል ተብሏል።
ሃማስ "በኢራን ላይ የአሜሪካ ወረራ አደገኛ ነው ብሏል። ግልጽ የሆነ የአለም አቀፍ ህግ መጣስ ነው" ሲልም አክሏል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የትራምፕን ዉሳኔ “ድፍረት የተሞላበት ውሳኔ” መሆኑን አወድሰው፣ እስራኤል እና አሜሪካ የፈጸሙት “በሙሉ ቅንጅት” ነው ብለዋል።
የዩኤስ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ማህበር የአሜሪካ ጥቃቶችን "ህገ-ወጥ" ሲል አውግዟል። ድርጊቱ ኢራንን እና ሌሎች ሀገራትን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የመፈለግ አደጋን ይጨምራልም ብሏል።
በአሁኑ ሰዓት በእየሩሳሌም እና ቴላቪቭ የፍንዳታ ድምፅ እየተሰማ እና የእስራኤል የቅድመ ማስጠንቀቂያ ድምጽ ለዜጎቿ እያሰማች መሆኑም ተዘግቧል።
ኡራን በተደጋጋሚ አሜሪካ ወደ ጦርነቱ እንዳትገባ ስታስጠነቅቅ የቆየች ቢሆንም አሜሪካ በይፋ ጦርነቱን ተቀላቅላለች። በቀጣይ የኢራን ምላሽ ይጠበቃል።
በበረከት ሞገስ
ይህ ዘገባ አዳዲስ መረጃዎች ተካተዉበታል👆🏼

ብሪታንያ አሜሪካ በኢራን ላይ በፈፀመችው ጥቃት ውስጥ አልተሳተፍኩም አለች
ዩናይትድ ኪንግደም በኢራን ላይ ጥቃት መፈጸሙን ታውቃለች ነገር ግን ጣልቃ እንድትገባ አልጠየቀችም ሲል የለንደን መንግስት አስታውቋል። ብሪታንያ አሜሪካ በኢራን ላይ ባደረገችው ጥቃት ውስጥ አልተሳተፈችም እንዲሁም የዲያጎ ጋርሲያ የጦር ሰፈር ጥቅም ላይ እንዲውል ጥያቄ አልቀረበላትም ነገር ግን ከጥቃቱ በፊት እንደተነገራት የንግድ ሚኒስትር ጆናታን ሬይኖልስ ተናግረዋል ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር ዛሬ ጠዋት ከአጋሮች ጋር ሲነጋገሩ ያሳልፋሉ ሲሉ ሬይኖልድስ ለስካይ ኒውስ ተናግረዋል። ቀደም ሲል ስታርመር በኢራን የኒውክሌር ቦታዎች ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ጥቃት አስመልክተው እንደተናገሩት ኢራን "በፍፁም የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንድታመርት አይፈቀድላትም" ሲሉ አሞካሽተዋል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ጦር በፎርዶ፣ ናታንዝ እና ኢስፋሃን በሚገኙ የኢራን የኒውክሌር መስሪያ ቤቶች ላይ “በጣም የተሳካ” ጥቃቶችን ማድረጋቸውን ተናግረዋል። እንዲሁም “አስታውስ፣ ብዙ ኢላማዎች ቀርተዋል” በማለት ከማንኛውም አጸፋ ምላሽ እንዳትሰጥ ኢራንን አስጠነቃቀዋል። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢራን "ሰላማዊ የኒውክሌር ክምችቶች" ላይ የሚሰነዘረው "አስፈሪ" የአሜሪካ ጥቃት "ዘላለማዊ ውጤት" እንደሚኖረው ተናግረዋል።
በስምኦን ደረጄ

የ70 ዓመት የእድሜ ባለፀጋው ከመቐለ ዩኒቨርስቲ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን አገኙ
መቀለ ዩኒቨርስቲ በትላንትናው እለት ለ31ኛ ጊዜ ተማሪዎቹን ባስመረቀበት ወቅት የ70 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ከተመራቂዎቹ መካከል አንዱ እንደነበሩ ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።
የእድሜ ባለጸጋው መምህር ታደስ ቢተውልኝ በ70 ዓመታቸው ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ በሶሽዮሎጂ በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆን መምህር ታደሰ ላለፉት 48 ዓመታት በአስተማሪነት ያገለገሉ መሆናቸውም ዳጉ ጆርናል ያገኘው መረጃ ያሳያል።
በሚሊዮን ሙሴ

Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ዜኒት ሴንት ፒተርስበርግ ለባርሴሎና የገንዘብ ስጦታ አበረከተ
የሩሲያዉ ዜኒት ሴንት ፒተርስበርግ በባርሴሎና የቲክቶክ ገጽ ላይ ስጦታ(Gift) በኒኮ ዊሊያምስ ስም አበርክቷል።
የዜኒት ሴንት ፒተርስበርግ ይፋዊ የቲክቶክ ገጽ ባርሴሎና የሁዋን ጋርሲያን ፊርማ ይፋ ባደረገበት ልጥፍ ላይ "ከዜኒት ለኒኮ ዊሊያምስ" በማለት የጊፍት ስጦታ ልከዋል።
ባርሴሎና ከኒኮ ዊሊያምስ ጋር በግል ክፍያዎች ስምምነት ላይ ቢደርስም ቡድኑ ባለበት የፋይናንስ ችግር ፊርማዉን በቀላሉ የሚያገኝ አይመስልም። ይህንንም ለማስተካከል ተጨዋች መሸጥ እንዳለበት ሲዘገብ ነበር።
ክለቡ ይህንን ያደረገዉ ባርሴሎና ተጨዋች ለማስፈረም ያለበትን የፋይናንስ ችግር ተንተርሶ ቀልድን ባዘለ መልኩ በመሳለቅ ነዉ። በተጨማሪም ዜኒት በኤክስ ገጹ ላይ "ማልኮምን ስለሰጣችሁን እናመሰግናለን" ብለዋል።
ማልኮም በ2018 ባርሴሎናን ከቦርዶ ቢቀላቀልም ከአንድ አመት በኋላ ክለቡን በመልቀቅ ወደ ዜኒት አቅንቶ ነበር። በክለቡ የ 4 አመታት ቆይታም የሊግ ዋንጫ ያሳካ ሲሆን በ 109 ጨዋታዎች 42 ግቦችንም አስቆጥሮላቸዋል። ባርሴሎና በወቅቱ ተጨዋቹን በ 40 ሚሊዮን ዩሮ ለዜኒት የሸጠዉ ሲሆን ዜኒት ደግሞ ለአልሂላል በ 60 ሚሊዮን ዩሮ ከ4 አመታት ቆይታ በኋላ ሸጦታል።
በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport

🌟 እውነተኛ ቅናሽ አስገራሚ እድል!
ቤት መግዛት ወይም ለንግድዎ ሱቅ ይፈልጋሉ ? 🏡
በዚህ የካቦድ የሪል ስቴት ኤክስፖ የሚፈልጉት ቦታ ከልዩ ቅናሽ ጋር ያግኙ ! 💼📊
🎯 ቦታ፡ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሙዚየም
📅 ቀን፡ ሰኔ 27-29
ቤት ለገዢው, ሱቅ ለነጋዴው! 🏠🛍️
ካቦድ የሪል ስቴት ኤክስፖ
ለመመዝገብ የሚከተለውን መተግበርያ ይጠቀሙ፦ https://www.kabodmarketingsolution.com/

አሜሪካ በኢራን ላይ የፈፀመችውን ጥቃት ሉዐላዊነትን መጣስ ነው ሲሉ የአረብ ሀገራት አወገዙ
በዋሽንግተን እና በቴህራን መካከል የኒውክሌር ድርድርን በማካሄድ ላይ የነበረችው ኦማን ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን የኒውክሌር ቦታዎች ላይ የምታደርገውን ጥቃት በጽኑ አውግዛለች። የባህረ ሰላጤው ሀገር ኦማን ሱልጣኔት “ዩናይትድ ስቴትስ የጀመረችውን ቀጥተኛ የአየር ጥቃት ያስከተለውን መባባስ ጥልቅ ስጋትን በመግለፅ ድርጊቱን አውግዛለች።
ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ጠንካራ የፀጥታ ግንኙነት ያላት እና የቅርብ ቀጣናዊ አጋር የሆነችው ሳዑዲ አረቢያ የኢራንን ሉዓላዊነት መጣሱን በማውገዝ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ "ፖለቲካዊ መፍትሄ ላይ ለመድረስ በእነዚህ እጅግ በጣም አሳሳቢ ሁኔታዎች ውስጥ ጥረቶችን አጠናክሮ እንዲቀጥል" ጠይቃለች ።የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሁን ያለው "አደገኛ ውጥረት በክልላዊ እና በአለም አቀፍ ደረጃ አስከፊ መዘዞች ያስከትላል" ሲል አስጠንቅቋል።
ግብፅ በነኩሏ "የቀጠናው አደጋ ወደ ተጨማሪ ትርምስ እና ውጥረት ውስጥ ሊገባ ይችላል" ስትል አስጠንቅቃለች። ፖለቲካዊ መፍትሄዎች እና ዲፕሎማሲያዊ ድርድር እንጂ ወታደራዊ መፍትሄ አይጠቅምም፤ ብቸኛው ከቀውሱ መውጫ መንገድ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ነው ብላለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሊባኖሱ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን እንዳሉት "በኢራን የኒውክሌር ፋሲሊቲዎች ላይ የተፈጸመው የቦምብ ጥቃት ከአንድ በላይ ክልል እንዲሁም በኢራን ውስጥ ያለውን ደህንነት እና መረጋጋትን አደጋ ላይ የሚጥል ውጥረቱ እንዲባባስ ስጋቱን ከፍ ያደርገዋል" ብለዋል።

አሜሪካ ኢራን ላይ የፈፀመችው ጥቃት ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነው ሲሉ ሩሲያ እና ስፔን አወገዙ
ሩሲያ በኢራን የኒውክሌር ቦታዎች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት የአለም አቀፍ ህግን መጣስ ነው ስትል ተደምጣለች። "የሉዓላዊ ሀገር ግዛት በሚሳኤል እና ለ
በቦምብ ማጥቃት ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔ፣ የሚቀርበው ክርክር ምንም ይሁን ምን፣ ዓለም አቀፍ ህግን፣ የተባበሩት መንግስታትን ቻርተር እና የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔዎችን በግልፅ ይጥሳል ሲል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫው ገልጿል።
"ጥቃት እንዲቆም እና ሁኔታውን ወደ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመመለስ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ጥረቶች እንዲጨምሩ እንጠይቃለን ሲል ሚኒስቴሩ አክሏል። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ነገ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ለመገናኘት ወደ ሞስኮ ለመጓዝ አቅደዋል። የስፔን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሴ ማኑኤል አልባረስ ቡዌኖ አሜሪካ በኢራን ላይ ባደረሰችው ጥቃት ምክንያት ውጥረቱ እየተባባሰ በመምጣቱ ሀገራቸው "በጣም አሳስቧታል" ብለዋል።
"በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እና መረጋጋት የሚያመጣው በወታደራዊ መፍትሄ ሳይሆን ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ነው ፤ ስለዚህ ሁሉም ሰው ወደ ድርድር ጠረጴዛው እንደሚመለስ ተስፋ እናደርጋለን" ሲሉ አልባረስ ተናግረዋል።

ነዳጅ የደብቁ ሁለት ማደያዎች ተቀጡ
የነዳጅ ዋጋ ይጨምራል በሚል ሀሳብ ነዳጅ በደብቁ ማደያዎች ላይ እርምጃ መወሰድ መጀመሩን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በአዲስ አበባ ከ5 ሚሊየን ሊትር በላይ ነዳጅ ቢኖርም፣ ነደጅ የለም በማለት አገልግሎት ያቆሙ ማደያዎች መኖራቸው መረጋገጡን አብራርተዋል።
በተደረገው ክትትልና ማጣራትም፣ በቂ ነዳጅ እያላቸው አገልግሎት ያቆሙ ሁለት ማደያዎች ከግብይት እንዲወጡና ስራ አስኪያጆቹ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
ባምቢስ ኖክ እና መርካቶ ሀበሻ እርምጃ የተወሰደባቸው ማደያዎች መሆናቸውን ያነሱት ሚኒስትሩ፣ በነዳጅ ላይ የሚጨመር ዋጋ አለመኖሩን አረጋግጠዋል።
መንግስት ከግንቦት ወር ጀምሮ ከነዳጅ ድጎማ መውጣቱን አስታውሰው፣ የነዳጅ ዋጋም በዓለም የነዳጅ ገበያ ብቻ ይወሰናል ብለዋል።
ከአሁን በኋላ በየወሩ የሚደረግ የዋጋ ጭማሪ እንደማይኖርም ሚንስተሩ ተናግረዋል።
Via AMN

የኢራን የኒውክሌር ምኞት ተደምስሷል ሲል ፔንታጎን አስታወቀ
የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ፔት ሄግሰት አሜሪካ ኢራን ውስጥ የሚገኙ የኒውክሌር ቦታዎችን በአንድ ጀምበር ከመታች በኋላ በፔንታጎን ህዝባዊ መግለጫ እየሰጡ ይገኛል። "የኢራን የኒውክሌር ምኞቶች ተደምስሰዋል" ያሉት ፔይ ሄግሰት የዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ "ኃይለኛ እና ግልጽ" ነበር ብለዋል።
ዳን ኬን የጋራ ወታደራዊ ኃይሎች ሊቀመንበር ሲሆኑ
በኢራን የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ በአንድ ጀንበር በተፈፀመው ጥቃት በተመለከተ ሲናገሩ በዋሽንግተን ውስጥ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ የዚህን እቅድ ያውቁ ነበር ብለዋል።ካይኔ “እቅድ አውጪዎች እና ቁልፍ መሪዎች” ብቻ ያውቁት ነበር ያሉት ጥቃቱ የ18 ሰአታት የፈጀው በረራ በኃላ ሰባት ቢ-2 ቦምብ አውሮፕላኖች ወደ ኢላማው ቦታ መግባታቸውን ተናግረዋል።
የአሜሪካ ሰርጓጅ ጦር መርከብ "ከሁለት ደርዘን በላይ" ቶማሃውክ የክሩዝ ሚሳኤሎችን በኢስፋሃን የኒውክሌር ቦታ ላይ "ቁልፍ ኢላማዎችን" ደብድበዋል። ጥቃቱን ስንፈፅም የኢራን የሚሳኤል መከላከያ ስርዓት አለመመልከቱን አክለዋል።

በአዲስ አበባ በአንድ ፔንሲዮን ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ ሁለት ሰዎች በጪስ ታፍነዉ ህይወታቸዉ አለፈ
በአደጋዉ የስድስት ሰዎችን ህይወት መታደግ መቻሉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
ትላንት ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 9:05 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 6 ሳሪስ በአንድ ፔንሲዮን በተነሳ የእሳት አደጋ ሁለት ሰዎች በጪስ ታፍነዉ ህይወታቸዉ ማለፉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል ።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደረጉት ርብርብ
በፔንሲዮን በክፍል ዉስጥ ተኝተዉ የነበሩ ስድስት ሰዎችን መታደግ የቻሉ ሲሆን የእሳት አደጋዉ ሳይስፋፋ በፍጥነት መቆጣጠር ችለዋል።
በጪስ ታፍነዉ በአንድ ክፍል ዉስጥ ህይወታቸን ያጡት የ30 ዓመት ወንድና የ25 ዓመት ሴት መሆናቸው የተነገረ ሲሆን በፔንሲዮኑ ክፍል ውስጥ በጭስ ታፍነው መሞታቸውን ለማወቅ ተችላል።
ፔኔሲዮኑ የዉስጥ ክፍሉ እሳትን መቋቋም ከማይቹሉና አደጋን አባባሽ ከሆኑ በችፑድ እና በጣዉላ የተከፋፈሉ መሆናቸዉ እሳቱ እንዲባባስና ጪስ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል ሲሉ አቶ ንጋቱ ጨምረው ተናግረዋል።
ፔንሲዮን የሆቴል አገልግሎት የሚሰጡ
ድርጅቶች ወይም ባለንብረቶች እንግዶች የሚያርፉባቸዉ ክፍሎች የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ያሟሉና የተጠበቁ በማድረግ የደንበኞቻቸዉ ደህንነት በመጠበቅ አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ማድረግ የሚገባቸዉ ሲሆን ኮሚሽኑ የአደጋ ደህንንነት መስፈርትን በማያሟሉ ሆቴልና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ አስፈላጊዉን እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል ።
በትግስት ላቀው

ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን እንዳትዘጋ ቻይና እንድታግባባት አሜሪካ ጠየቀች
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ኢራን ከዓለማችን እጅግ አስፈላጊ የመርከብ መንገዶች አንዱ የሆነውን የሆርሙዝ ሰርጥን ከመዝጋት እንድትከላከል ለቻይና ጥሪ አቅርበዋል ። ማርኮ ሩቢዮ ይህንን አስተያየት የሰጡት በኢራን መንግስት ስር የሚተዳደረው ፕሬስ ቲቪ የህዝብ እንደራሴዎች የባህር ዳርቻውን የመዝጋት እቅድ ማፅደቃቸውን ከዘገበ በኋላ ሲሆን የመጨረሻው ውሳኔ የጠቅላይ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ነው ሲል በዘገባው አክሏል።
በነዳጅ አቅርቦት ላይ የሚፈጠር ማንኛውም መስተጓጎል በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ መዘዝ ያስከትላል። ቻይና በተለይ የኢራንን ዘይት በመግዛት በዓለም ቀዳሚ ስትሆን ከቴህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላት። አሜሪካ በኢራን የኒውክሌር ቦታዎች ላይ የፈፀመችውን ጥቃት ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ ጨምሯል።በቤጂንግ የሚገኘው የቻይና መንግስት ስለዚህ ጉዳይ እንዲሰራ አበረታታለሁ ምክንያቱም በሆርሙዝ የባህር ዳርቻ በሚወጣው የነዳጅ ዘይት ላይ በእጅጉ ጥገኛ ናቸው ሲሉ ሩቢዮ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።
ኢራን የባህር ዳርቻውን ከዘጋች ኢኮኖሚያዊ ራስን ማጥፋት ይሆናል። ይህንን ለመቋቋም አማራጮችን ይዘን እንቀርባለን፤ ሌሎች ሀገራት ያንን መመልከት አለባቸው። ከኛ የባሰ የሌሎች ሀገራትን ኢኮኖሚ ይጎዳል ሲሉ ሩቢዮ አክለዋል። 20 በመቶ የሚሆነው የአለም ዘይት በሆርሙዝ ባህር ላይ ያልፋል፣ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ዋና ዋና ዘይት እና ጋዝ አምራቾች የውሃ መንገዱን ኃይል ለማጓጓዝ ይጠቀሙበታል።ቻይና በተለይ ከኢራን አብላጫውን የነዳጅ ዘይት ፍላጎቷን ትገዛለች። ከኢራን የምታስገባው ነዳጅ ባለፈው ወር በቀን 1.8 ሚሊዮን በርሜል እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ።

የፕላስቲክ ከረጢት ማምረት ላይ የወጣው አዋጅ ተግባራዊ ሲደረግ ከ800 በላይ ፋብሪካዎች ስጋት እንዳለባቸው ተገለፀ
የኢትዮጵያ የፕላስተቲክ እና ጎማ አምራች ማህበር የፕላስቲክ ከረጢት ወይም ፌስታል አንድ ግዜ ብቻ ተጠቅመን የምንጥለው ሳይሆን መልሰን ጥቅም ላይ የምናውለው ምርት ነው ሲሉ አስታወቀ
በቅርቡ ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኘ ከ2 እስከ 5 ሺህ ብር የሚያስቀጣው አዋጅ መፅደቁ ያስታወሰው ማህበር ያለውን ቅሬታውን አቅርቧል ።
የማህበሩ አባል እና የወቅታዊ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድ አዋጅ ዙሪያ ማህበሩ ያቋቋመው ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ በረከት ገ/ህይወት ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት የፌስታል ምርትን በመሰብሰብ መልሶ ጥቅም ላይ ውሎ አገልግሎት እንዲሰጥ እያደረገ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ደረጃው የጠበቀ ፌስታል እንዲመረት ግን መደረግ እንዳለበት አስታውቀዋል።
ከመላው ሀገሪቷ ተሰብስቦ በግዢ የሚረከቡት የፌስታል ደርቅ ቆሻሻን በኪሎ 30 ብር በመግዛት በመልሶ ምርት ፌስታል፣ የኤሌክትሪክ ኮንዲውት እና ለኮሪደር ልማት ላይ እየዋሉ የሚገኙትን ኤችዲ ፓይፕ እያመረቱ መሆኑን አስታውቀዋል።
ሆኖም በአዋጁ መሰርት አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ያመረተ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ለገበያ ያቀረበ ወይም የሸጠ፣ ለንግድ ዓላማ ያከማቸ ወይም ይዞ የተገኘ ከ50 ሺህ ብር በማያንስና ከ200 ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ እና ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ አዋጁ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ተፈጻሚ ይሆናል መባሉ ይታወሳል።
በመላው ሀገሪቱ መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውሉ ከ8መቶ በላይ የፕላስቲክ ማሽጊያ ፌስታል የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ያሉ ሲሆን ከ268 ሺ በላይ በስራው ላይ የተሰማሩ ዜጎች ይገኛሉ። አዋጁ ተግባራዊ ሲደረግ በዘርፉ የተሰማሩ ፋብሪካዎችን ሆን ሰራተኞችን ከመስኩ የሚያስወጣቸው እና ሲሳራ ላይ የሚጥላቸው መሆኑ ተነግሯል።
አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ አስፈፃሚ አካላት ፌስታል ከእንግዲህ ተከልክሏል በሚል ነጋዴዎች ላይ በፈጠሩት ጫና ምክንያት የምናመርተው ፌሰታል ወደ ገበያ ሊውጣ ባለመቻሉ አዋጁ ከአሁኑ ተፅኖ በማድረጉ በርካታ ፋብሪካዎች ስራ ፈተዋል ሲሉ አቶ በረከት ገ/ህይወት ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በሳምራዊት ስዩም