በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ከ8ሺህ ሊትር በላይ ናፍጣ ተያዘ
በወላይታ ዞን ዳሞት ሶሬ ወረዳ ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 8ሺ ሊትር በላይ በቁጥር በ34 የዉሃ መያዣ ታንከር የተከማቸ ናፍጣ በቁጥጥር ሥር ማድረጉን የወረዳው ፖሊሲ አስታውቋል::
አንድ ህገ ወጥና የተጨብረበረ የንግድ ደረሰኝ የያዘ የሰሌዳ ቁጥር ET-86230 ኮድ 3 የሆነ ሲኖትራክ የጭነት መኪና ከወላይታ ሶዶ ወደ ዳውሮ ዞን ሲሄድ ድንገተኛ ፍተሻ መደረጉ ተገልጿል።
በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ከንጋቱ 12:00 አከባቢ ሕጋዊ ያልሆነውን የናፍጣ ግዥ ሰነድ ሕጋዊ በማስመሰልና የተለያዩ የተጨብረበሩ ሰነዶችን በመያዝ ለማለፍ ሲሞክር ሊያዝ ችሏል።
በህገወጥ መንገድ ናፍጣ የተጫነበት ሲኖትራክ የጭነት ተሽከርካሪ በወረዳው በዶጌ ማሽዶ ቀበሌ ለፍተሻ በወጡት ፖሊስ አባላት ክትትል ቁጥጥር ሥር መዋሉንየደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል

እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ላይ የነበራቸውን የጦርነት አላማ ማሳካት አልቻሉም ተባለ
በቴህራን የመካከለኛው ምስራቅ ስትራቴጂክ ጥናት ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት አባስ አስላኒ እንዳሉት እስራኤል በጋዛ እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነቶችን ለማድረግ በምትወስንበት ጊዜ ጥሩ ታሪክ ስለሌላት ኢራን ወደ ተኩስ አቁም እየተቃረበች ያለችው በጥንቃቄ ነው።
"ለዚያም ነው ቴህራን ጠንቃቃ የምትሆነው እና ባለሥልጣናቱ በይፋ ለማረጋገጥ በፍጥነት ወደፊቱ አልወጡም ። በጊዜ ሂደት ምንም ጥሰት ከሌለ ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነትን የምታከብር ይመስለኛል" ሲሉ ለአልጀዚራ ተናግረዋል።አስላኒ ይህ በኢራን እና በእስራኤል እና በአጋሯ ዩናይትድ ስቴትስ መካከል የተደረገ ጦርነት መሆኑን ገልፀው ሁለቱ አጋሮች ግባቸውን የኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ማፍረስ እና በኢራን ውስጥ "የአገዛዝ ለውጥ" በማምጣት ያልተሳካ ጦርነት ነው ብለዋል ።
"በኢራን የኒውክሌር መሥሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን አይተናል፣ ነገር ግን የሀገሪቱ የኒውክሌር መርሃ ግብር በእነዚያ መገልገያዎች እና መሳሪያዎች ላይ ብቻ አይደለም፣ ኢራን የኒውክሌር ቁሳቁሶቿን ወደ አስተማማኝ ቦታ አዛውራለች፣ እውቀቷም ያልተነካ ነው "በማለት እስራኤል እንደመታችው የኢራን የሚሳኤል አቅምም አልጠፋም ሲሉ ተደምጠዋል። አስላኒ የኒውክሌር ድርድር በቀጠለበት ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል ኢራንን ስላጠቁ "ትርጉም ያለው" ከአሜሪካ ጋር የሚደረገው ድርድር በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊከናወን አይችልም ብለዋል።
ሁሉም ሀገራት በግጭቱ ድል እንደተጎናጸፉ እየተናገሩ ይገኛል፡፡ሁለቱም ወገኖች የተኩስ አቁምን የሚያከብሩበት ምክንያት አላቸው።እስራኤል ኦፕሬሽን Rising Lion ብላ የሰየመችውን የዘመቻውን ስኬት በተመለከተ ስትናገር የኢራንን ኒውክሌር እና ወታደራዊ አቅም በእጅጉ ጎድቷል፣ ከፍተኛ የጦር ባለስልጣናትን እና ሳይንቲስቶችን ገድሏል ትላለች።
ከዚህ በተጨማሪም በርካታ የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች ለማድረግ ፈቃደኛ ያልነበሩትን ጥቃት እንዲፈጽሙ ትራምፕን ማሳመን ችላለች።የተኩስ አቁም ስምምነቱ ለሁለት ዓመታት ያህል ከቆየ ጦርነት በኋላ በተዳከሙት እስራኤላውያን ላይ የሚደርሰውን ጫና ከፍተኛ ነዉ፡፡ ለኢራን፣ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተፈናቀሉበት የማያቋርጥ የቦምብ ጥቃት ውስጥ ለነበረው ህዝብ እፎይታ ነው። አሁን ላይ የወደሙትን አንዳንድ የመሠረተ ልማት አውታሮችን ጨምሮ፣ ከባድ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ የሚጥላት ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ማዕቀብ የተጣለባት በመሆኑ ረጅም መንገድ ይጠብቃታል፡፡
በስምኦን ደረጄ

የህዝብና የመንግስትን ጥቅም መሰረት አድርገው ከተፈፀሙ ወንጀሎች ከ53 ሚሊዮን ብር በላይ ተመላሽ ማደረጉን የጉራጌ ዞን ፍትህ መምርያ አስታወቀ
የጉራጌ ዞን ፍትህ መምርያ ሊጠናቀቅ የሳምንታት እድሜ በቀረው የ2017 በጀት ዓመት ላይ የህዝብና የመንግስትን ጥቅም በማስመልከት ከተፈፀሙ ወንጀሎች ከፍተኛ ሀብት በተሳካ ሁኔታ ተመላሽ ማድረጉን አስታዉቋል፡፡
የፍትህ መምርያው የህዝብና የመንግስትን ጥቅም መሰረት አድርገው በተፈፀሙ ወንጀሎች ከወረዳ እስከ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ባደረገው የፍታብሄር ክስ ክርክር 15 ሚሊየን 354 ሺ 497 ብር ገቢ ማድረግ የቻለ ሲሆን በድርድር ደግሞ 38 ሚሊየን 551 ሺህ 400 ብር በድምሩ 53 ሚሊየን 905 ሺህ 897 ብር ገቢ ለማድረግ መቻሉን የጉራጌ ዞን ፍትህ መምርያ ኃላፊ የሆኑት አቶ ኤልያስ ሰብለጋ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
ኃላፊው አክለው በሙስና ነክ ወንጀሎች፣ ከሙስና ጋር በማጣመር በቀረቡ የፍታብሄር ክሶች አፈፃፀምም፤ በክስ 950 ሺ 265 ብር ፣ በምርመራ ሂደት ደግሞ 13 ሚሊዮን 646 ሺ 31 ብር በድምሩ 14 ሚሊየን 596 ሺ 297 ብር ገቢ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በታክስና ኢኮኖሚ ነክ ወንጀሎች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዙ የነበሩ ከ6.9 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ንብረቶች ለመንግስት ገቢ ተደርገዋል ሲሉ የገለፁት አቶ ኤልያስ ውዝፍ የታክስ ዕዳ ከነበረባቸው ታክስ ከፋዮች ከገቢዎች መምሪያ ጋር በመቀናጀት በድርድር ከ8.1 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማድረግ መቻሉንም ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል።
በሰብል አበበ

የአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ
በአዲስ አበባ የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 89 በመቶ ወደ ቀጣይ ክፍል ማለፋቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ገለፀ።
የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላላሞ ሙላቱ ዛሬ ከሰዓት በሰጡት መግለጫ ዘንድሮ ከተፈተኑ 70 ሺህ 525 ተማሪዎች መካከል 62 ሺህ 639 ተማሪዎች ወደ 9ኛ ክፍል ተዛውረዋል ብለዋል።
እንደከተማ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ 20 ተማሪዎች 13ቱ ከአዳሪ ትምህርት ቤት ሲሆኑ 3ቱ ከልዩ ልዩ ትምህርት ቤቶች መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
ተፈተኝ ተማሪዎች በትምህርት ቢሮው የማህበራዊ ሚዲያ ውስጥ በሚገኘው ሊንክ ገብተው ውጤታቸውን መየት እንደሚችሉም በመግለጫው ተገልጿል።
የዘንድሮ የ8ኛ ክፍል ከፍተኛው ውጤት 97.3 ሆኖ ተመዝግቧል።

ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣሷ ከባድ ምላሽ ይጠብቃታል ስትል እስራኤል ዛተች
የእስራኤል መከላከያ ሚንስትር ኢዝራኤል ካትስ ባወጡት የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት "ኢራን የተኩስ አቁምን በመጣሷ በቴህራን እምብርት ላይ ባሉ የአገዛዙ ኢላማዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት በመሰንዘር በሀይል ምላሽ እንዲሰጥ" ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጥቃት የሚያቆመዉ እስራኤል ተመሳሳይ እርምጃ ከወሰደብ ብቻ እንደሆነ ቀደም ብሎ ተናግሯል።የእስራኤል ጦር ከኢራን የተወነጨፉ ሚሳኤሎችን ለይቻለሁ ሲል በዛሬዉ እለት አስታዉቋል፡፡የአየር መከላከያ ዘዴዎች ስጋቱን ለመጥለፍ እየሰሩ ሲሆን ሰዎች ወደ መጠለያ ገብተው እንዲቆዩ እየነገራቸው ይገኛል፡፡
የእስራኤል መከላከያ ሃይል (አይዲኤፍ) ዋና አዛዥ ወታደራዊው ኃይላችን ለኢራን ድርጊት "ከባድ ጥሰት" በማለት "የኃይል ምላሽ ይሰጣል" ብለዋል፡፡ኢያል ዛሚር እንደተናገሩት "በኢራን መንግስት የተካሄደውን የተኩስ አቁም ከፍተኛ ጥሰት ተከትሎ በኃይል ምላሽ እንሰጣለን" ሲሉ በኤክስ ገጻቸዉ ላይ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡
የኢራን መንግስት ሚዲያ ከተኩስ አቁም በኋላ በእስራኤል ላይ ሚሳኤል ተኮሰች የሚለውን ውንጀላ አስተባብሏል።የኢራን ታጣቂ ሃይሎች ለጠላት ጭካኔ አሳፋሪ እና አርአያነት ያለው ምላሽ መስጠቷን የገለጸችዉ ኢራን ትላንት ምሽት በኳታር በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ በደረሰው ጥቃት እና ጎህ ሲቀድ እስራኤል በሚሳኤል መመታቷን አስታዉቃለች፡፡የኢራን ከፍተኛ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ቴህራን በግዛቷ ላይ ለደረሰው ጥቃት ተመጣጣኝ እና በጊዜ ምላሽ ሰጥታለች ያለ ሲሆን "ጠላትን በግዳጅ እንዲጸጸት እና ሽንፈትን እንዲቀበል አድርጓል" ብሏል።

ከፍቼ አዲስአበባ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች በነዳጅ እጦት ምክንያት ስራ ለማቆም ተገደናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቀረቡ
ከፍቼ አዲስ አበባ የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች በነዳጅ እጦት ምክንያት አገልግሎት ሊያቆሙ በመገደዳቸው ተገልጋዮች ለእንግልት መዳረጋቸውን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በዚህም የትራንስፖርት ተጠቃሚው ማህበረሰብ ለእንግልት መዳረጉን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ተናግረዋል። አሽከርካሪዎች በበኩላቸው ትላንት ነዳጅ ለመቅዳት ቢሞክሩም ማደያ ላይ አልቋል የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸው በዚህም መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን ገልጸዋል። የተወሰኑ አሽከርካሪዎች ከህገወጥ የነዳጅ ቸርቻሪዎች ላይ አንድ ሊትር ናፍጣ በሁለት መቶ ብር ገዝተው ወደ ስራ መሰማራታቸው ብስራት ሰምቷል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ንግድ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ደረጀ ሰማ እንደገለጹት የነዳጅ እጥረቱ በዋነኛነት በሀምሌ ወር ይጨምራል በሚል ስጋት አንዳንድ ማደያዎች ከህግ ውጪ ነዳጅን ለተሽከርካሪዎች በጄሪካን በመሸጥ እንዲሁም ትስስር ላላቸው ነጋዴዎች በመሸጥ የነዳጅ እጥረቱ እንዲከሰት አድርገዋል ። ለዚህም በዋነኛነት፣ አንዳንድ የአስተዳደር ፣ የፀጥታ አካላት የንግዱ ማህበረሰብ እና የትላልቅ ማሽነሪ ተሽከርካሪ ባለቤቶች ከማደያዎች ጋር ያላቸው የጥቅም ትስስር ለነዳጅ እጥረቱ በር መክፈቱን ገልጸዋል።
በተጨማሪም በዞኑ ካሉት አስራ አንድ ማደያዎች መካከል በገብረ ጉራቻ፣ ሙከጡሪ ፣ጫንጮ አሌልቱ መናሃሪያዎች ላይ ቅጣት መጣሉን በመጥቀስ በተለይ የሙከጡሪ ማደያ ተደጋጋሚ የህግ ጥሰት በመፈፀሙ አስተማሪ ቅጣት እንደሚጠብቀው ነግረውናል።
በነዳጅ እጥረት ምክንያት በትራንስፖርት ዋጋ ላይ ጭማሪ ያደረጉ ህገወጥ አሽከርካሪዎች ላይ አስተማሪ ቅጣት በመስጠት ከማደያ ጣቢያ ያለውን ነዳጅ በተገቢው በማካፈል የትንራንስፖርቱን ፍሰት ማስተካከል መቻሉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።በሀገወጥ የነዳጅ ግብይት የተሰማሩ ስድስት ነጋዴዎችም ያጠራቀሙት ነዳጅ ውርስ ሆኖ ለተጠቃሚዎች እንደሚከፋፈል ተነግሯል።
በኤደን ሽመልስ

አዳማ ከተማ ከፕሪሚየር ሊጉ ወረደ
በ36ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር አዳማ ከተማ በሀዋሳ ከተማ ተሸንፎ ከፕሪሚየር ሊጉ ወርዷል፡፡
ዛሬ 9፡00 ላይ የተደረገው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
የሀዋሳ ከተማን ግቦች አቤኔዘር ዮሐንስ እና በረከት ሳሙኤል ሲያስቆጥሩ፥ አዳማ ከተማን ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ ቢኒያም አይተን ከመረብ አሳርፏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ በ39 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው አዳማ ከተማ፥ ስሑል ሽረ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ተከትሎ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ ተረጋግጧል፡፡
በሊጉ የመሰንበት እድሉን በራሱ ለመወሰን አንድ ነጥብ ብቻ የሚፈልገው ፋሲል ከነማ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ሲዳማ ቡናን ይገጥማል፡፡

የቱሉቦሎ - ኬላ አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ
የኦሮሚያ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችን የሚያገናኘው የቱሉቦሎ - ኬላ አስፋልት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታው ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
የመንገድ ፕሮጀክቱ 80 ኪሎሜትር የሸፈነ ሲኾን፥ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ነው የተገነባው። የመንገድ ግንባታውን የቻይናው ዓለም-አቀፍ የሥራ ተቋራጭ ሁናን ሁንዳ ሮድ ኤንድ ብሪጅ ኮርፖሬሽን አከናውኖታል።
ሀገር በቀሉ የተባበሩት የምህንድስና አማካሪዎች የግንባታውን ጥራት በመቆጣጠር እና በማማከር በኩል ተሳትፏል። ለፕሮጀክቱ የዋለው 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወጪ ሙሉ በሙሉ በፌደራል መንግስት ተሸፍኗል።
በመንገድ ፕሮጀክቱ ሦስት ድልድዮችን ጨምሮ አነስተኛ፣ ከፍተኛ ፍሳሽ ማስተላለፊያዎች፣ ቱቦዎች እና ከልቨርቶች ግንባታም ተካትቷል። መንገዱ በገጠር የመንገድ ትከሻን ጨምሮ 10 ሜትር፣ በወረዳ 20 ሜትር እንዲሁም በቀበሌ 15 ሜትር የጎን ስፋት አለው።
የመንገዱ መጠናቀቅ የአዲስ አበባ-ቡታጅራ -ሆሳዕና እና የአዲስ አበባ - ወልቂጤ - ጅማ መስመር ያሉትን አውራ መንገዶች ያገናኛል፡፡ ይህም ከዚህ ቀደም ይደረግ የነበረውን ዙሪያ ጥምጥም ጉዞ በማስቀረት የጉዞ ጊዜን ያሳጥራል።
የተቀላጠፈ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲኖር በማስቻል፣ የማኅበራዊ ተቋማት ተደራሽነትን በማስፋት እንዲሁም የገበያ ትስስሩን በማጠናከር የመንገዱ መገንባት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታል።
የቱሉቦሎ፣ ሀርቡጩሉሌ፣ ኮምበል፣ አጨበር፣ ቀሽት እና ኬላን ጨምሮ ሌሎች በርካታ አካባቢዎችን በቅርበት ያገናኛል።

አርኤስኤፍ ከግብፅ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማስተካከል የውይይት ጥሪ አቀረበ
የሱዳን ፓራሚሊተሪ ፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይል መሪ መሀመድ ሀምዳን ዳጋሎ ከግብፅ ጋር ያሉ አለመግባባቶችን በውይይት መፍታት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል። ዳጋሎ በሰፊው በዳርፉር ክልል ለወታደሮቹ ባደረገው ንግግር ከጎረቤት የግብፅ ሃይል ጋር ያለውን ውጥረት አስመልክቶ ተናግረዋል። ቀደም ሲል ግብፅን ለሱዳን ጦር ኃይሎች ወታደራዊ ዕርዳታ ታቀርባለች በሚል የሰላ ትችት ሰንዝረዉ እንደነበርም ይታወቃል።
"ግብፅንና ሌሎች ጎረቤቶቻችንን እናከብራለን እናም ማንኛውም ችግር በውይይት እና በውይይት ሊፈታ ይችላል" ሲሉ ሄሜቲ በንግግራቸዉ የተደመጡ ሲሆን አርኤስኤፍ በአቅራቢያ ካሉ አገሮች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማበላሸት በመሞከር ስማቸው ያልተጠቀሱ “ወንጀለኞችን” ከሰዋል።በሱዳን፣ በሊቢያ እና በግብፅ መካከል የሚገኘውን የኦዋይናት የድንበር ትሪያንግልን በቅርቡ የያዘው አርኤስኤፍ ቀጣናውን ከሽብርተኝነት፣ በኮንትሮባንድ እና በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ለመከላከል እንሰራለንም ሲሉ ዳጋሎ ተናግረዋል።
አክለውም "ፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይሎች ከጎረቤት ሀገር ጋር ምንም ችግር የለባቸውም" ብለዋል።የአርኤስኤፍ እና የሱዳን ጦር ኃይላቸውን ለማዋሃድ ባወጡት እቅድ ምክንያት የገዢነት አጋርነታቸው ከፈራረሰ በኋላ ከሁለት አመት በላይ ሲዋጉ ቆይተዋል። ግጭቱም ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ ፈጥሮ ሚሊዮኖችን አፈናቅሏል።ዳጋሎ በንግግራቸው በዳርፉር የእርዳታ አቅርቦትን ለማመቻቸት ቃል የገቡ ሲሆን ከሚያዝያ 15 ቀን 2023 ጀምሮ ለወታደሮቻቸው ዕዳ መልሰው እንደሚከፍሉም ተናግረዋል።
በሠራዊቱ ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት በማደስ እና የተቀሩትን ሃይሎች እንደሚያሸንፉ ቃል የገቡት ጀነራሉ ከጦር ኃይሉ ጋር ለተባበሩ ሌሎች የታጠቁ አንጃ መሪዎችም የእርቅ ጥሩ አቅርበዋል። የሱዳን ነፃ አውጪ ንቅናቄ እና የፍትህ እና የእኩልነት ንቅናቄ መሪዎችን በመጥቀስ "ከሚኒ (አርኮ ሚናዊ) እና ከጅብሪል (ኢብራሂም) ጋር ምንም ችግር የለንም ዛሬ ወደ እኛ ቢመጡ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለን እንቀበላቸው አለን ሲሉም ተደምጠዋል።
በሚሊዮን ሙሴ

በመቱ ከተማ ወድቆ ያገኙትን ከ173 ሺህ ብር በላይ ለፖሊስ ያስረከቡ ጓደኛማቾች ምስጋና ተቸራቸው
በኢሊባቡር ዞን መቱ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ሁለት ጎረቤታም ሴቶች ወደ ገበያ ሲያመሩ መሬት ላይ የወደቀ ጥቁር ፌስታል አይተው ገንዘብ መሆኑን ሲገነዘቡ ለፖሊስ ማስረከባቸውን የመቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል ።
የመቱ ከተማ ፖሊስ ዋና መምርያ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር አሸብር ጌታሁን ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ወይዘሮ የሺህ ሀረግ ይርጉ እና ወይዘሮ አገርቱ ዴቢሳ የተባሉ የመቱ ከተማ አባ አሳያ ቀበሌ ማርያም ሰፈር ነዋሪ ናቸው።
ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም የሰኞ ገበያ ዕቃ ለመግዛት በመውበት ይህ አጋጣሚ ተከስቷል። ጎረቤታሞቹ የግል ጥቅም እና ፍላጎት ሳያሸንፋቸው በቀጥታ በጥቁር ፌስታል የተጠቀለለውን 173 ሺህ ብር ከሀምሳ ሳንቲም ለመቱ ከተማ ፖሊስ አስረክበዋል።
ሁለቱ ሴቶች በታማኝነት ብሩን እንዳስረከቡ የብሩ ባለቤት አቶ ሰሚር ሙሰማ የተባሉና በመቱ ከተማ አባ አሳያ ቀበሌ ማርያም ሰፈር ነዋሪ የዳቦ መጋገርያ ቤት ባለቤት ከሰዓታት ቆይታ በኋላ በመምጣት ሁለቱ ሴቶች መሬት ላይ ወድቆ ያገኙት ብር የራሰቸው መሆኑን ያመለክታሉ።
ፖሊስም ሁለቱ ሴቶች ያገኙት ብር የአቶ ሰሚር ስለመሆኑ ባደረገው ማጣራት ዱቄት ገዝተው ለመመልስ ወደ ሱቅ መደብር መጓዛቸውን ከዚያም ከቤት ይዘውት የወጡትን ብር ሲያፈላልጉ መገኘቱን በመስማታቸው ወዲያው ወደ ፖሊስ ፅ/ቤት መቅረባቸውን ባቀረቡት ማስረጃ ማረጋገጡን ገልፀዋል።
ብሩ ምንም ሳይጎድል እንዲያገኙ ላደረጉላቸው ሁለት ሴቶች ትልቅ ምስጋና አቅርበው ለዚህ ታማኝነት ተግባር ወሮታ ከፋይነኝ ሲሉ መግለጻቸውን ረዳት ኢንስፔክተር አሽብር ጌታሁን ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል።

የድሬዳዋ ምድር ባቡር ግቢን የቱሪስት መዳረሻ ስፍራ ለማድረግ እየተሰራ ነዉ ተባለ
የድሬዳዋ የምድር ባቡር ተርሚናል እድሳት ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን በተመደበለት በጀት ጥገና ተደርጎለት ከሁለት ወራት በፊት መጠናቀቁን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት አስታዉቋል ።
ቅርሱ እድሳት የተከናወነለት ታሪካዊ ይዘቱን ሳይለቅ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ዉድመት ደርሶባቸዉ ለነበሩ መስኮቶችም ተመሳሳይ ቁሳቁሶችን በመጠቀም ወደነበረበት የመመለስ ስራ መከናወኑም ተገልጿል ።
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት የቅርስ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አብረሃም ያረጋል ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት የድሬዳዋ ምድር ባቡር ምድረ ግቢን የቱሪስት መዳረሻ ስፍራ ለማድረግ በኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን በተመደበ በጀት በአማካሪ ድርጅት የሰነድ ዝግጅት ለማካሄድ በጨረታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ሂደቱ በቅርቡ ተጠናቆ የሰነድ ዝግጅት ይከናወናል ።
በምድር ባቡር ግቢ ውስጥ የሚገኝ የባቡር ፉርጎን ጥቅም ላይ በማዋል የከተማዋን ባህል የሚገልፁ እና ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ እንደ ፈጣን ምግብ ያሉ አገልግሎቶችን ለማቅረብ ፕሮጀክት በመቅረፅ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር የዲዛይን ስራ እንደሚከናወን ተገልጿል ። ይህም የኮሪደር ልማቱን ባማከለ መልኩ የሚከናወን መሆኑን የገለፁት አስተባባሪዉ ይህንን የባቡር ፉርጎ በመጠቀም የሚሰጠዉን አገልግሎት በድሬዳዋ ከተማ ለገሀር አደባባይ አከባቢ ለመገንባት መታቀዱን አክለዋል ።
በመባ ወርቅነህ

እስራኤል በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት ቢያንስ 43 ፍልስጤማውያንን ተገደሉ
በጋዛ በተስፋፋው ረሃብ ውስጥ ቢያንስ 43 አጥብቀው የምግብ እርዳታ የሚሹ ፍልስጤማውያን በማእከላዊ የጋዋ ግዛት አካባቢ በተፈጸመ ጥቃት ተገድለዋል ሲል የአልጀዚራ የእውነታ ማረጋገጫ ክፍል ሳናድ ዘግቧል።
እንደ ዘገባው ከሆነ ተጎጂዎቹ የተገደሉት ከዋዲ ጋዛ በስተደቡብ በሚገኘው የሳላህ አል-ዲን ጎዳና ላይ ምግብ በመጠባበቅ ላይ በነበሩበት ወቅት ነው።
በሳናድ የተገኘ የምስል ቅጅ የተጎጂዎች አስከሬን በጋዛ ናስር ሜዲካል ኮምፕሌክስ እና በአል-አውዳ ሆስፒታል ተከማችቶ ያሳያል። በእስራኤል እና በአሜሪካ የሚደገፈው የጋዛ የሰብዓዊ ፋውንዴሽን እ.ኤ.አ ግንቦት 27 ቀን እርዳታ ማከፋፈሉን ከጀመረ ወዲህ እስራኤል የእርዳታ ማዕከላት አቅራቢያ ፍልስጤማውያን ላይ ባደረሰችው ጥቃት ከ400 በላይ ሰዎችን ሲገደሉ 1,000 የሚያህሉ ቆስለዋልም ተብሏል።