Telegram Web Link
ነዳጅ ደብቀዉ የተገኙ ሁለት  ማደያዎች  የንግድ ፈቃዳቸዉ ተሰርዞ ከገበያ እንዲወጡ ተደረገ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀድያ ዞን ሾኔ ከተማ እና በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ 234 ሺህ 572 ሊትር ነዳጅ  ደብቀዉ የተገኙ ሁለት ማደያዎች  ንግድ ፈቃዳቸዉ ተሰርዞ ከገበያ እንዲወጡ  መደረጉን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታውቋል፡

በሾኔ ከተማ የሚገኝ እና ግሎባል በሚል ስያሜ የሚጠራ ነዳጅ  ማደያ 94 ሺህ 572  ሊትር ነዳጅ ደብቆ የተገኘ ሲሆን በዱራሜ ከተማ የሚገኘው ኖክ ማደያ ደግሞ 140ሺህ ሊትር ነዳጅ ደብቆ መገኘቱን የገለፀዉ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሁለቱም ማድያዎች  የንግድ ፈቃድ ተሰርዞ  ከገበያ እንዲወጡ ማድረጉን አስታዉቋል።

በተጨማሪም   በፌደራል አዋጅ  ቁጥር1363/2017 መሰረት ነዳጅ በሚደብቁ ህገ-ወጥ የነዳጅ  ማደያዎች ላይ  ህጋዊ  እርምጃ  መወሰድ መጀመሩን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ም/ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ  ተናግረዋል።

በክልሉ በቂ የሆነ የነዳጅ አቅርቦት መኖሩን የገለፀዉ ቢሮዉ  የነዳጅ ዋጋ በመጨመር  ያልተገባ ትርፍ ለማግኘት ነዳጅ  በሚደብቁ  ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ  እርምጃ መዉሰዱን  አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን  ገልጿል።ህብረተሰቡ መሰል ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት   በ9348 ነጻ የስልክ መስመር  በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል፡፡

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
በእስር ላይ የሚገኙት የቻድ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸው ተሰማ

የቻድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ሱሰስ ማሳራ መታሰራቸውን በመቃወም የረሃብ አድማ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። የቻድ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ ለስ ትራንስፎርማተርስ መሪ እና የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት ማሳራ በግንቦት 14 በሎጎን ኦክሳይደንታል ግዛት ውስጥ በተፈጠረው የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት በዋና ከተማዋ ኒጃሜና በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ፅሁፎች ላይ ጥላቻን እና ሁከትን በማነሳሳት፣ ከታጠቁ ወንበዴዎች ጋር በመተባበር እና በግድያ ወንጀል ተባባሪ በመሆን በርካታ ክሶች ተመስርቶባቸዋል። ከማክሰኞ ጀምሮ ከሁላችሁም ጋር በመተባበር እና የማይገባን ኢፍትሃዊ ድርጊት በመቃወም የርሃብ አድማ እጀምራለሁ ሲሉ ማስራ ለፓርቲያቸው ደጋፊዎቻቸው በጻፉት ደብዳቤ ላይ ተናግረዋ።

ከ40 ቀናት በፊት ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ደጋፊዎቼ ሁሉ የታሰርኩበትን ምክንያት ለማወቅ እየጣሩ እንደሆነም ተናግረዋል። እ.ኤ.አ በሜይ 2024 በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተወዳድረው የነበረ ሲሆን በወቅቱ የሽግግር ፕሬዚደንት የነበሩት ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ ምርጫውን አሸንፈዋል። ባለፈው ወር ሂዩማን ራይትስ ዎች ማስራ “በትክክለኛ ወንጀል ካልተከሰሱ” ባስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
🌟 እውነተኛ ቅናሽ አስገራሚ እድል!

ቤት መግዛት ወይም ለንግድዎ ሱቅ  ይፈልጋሉ ? 🏡
በዚህ የካቦድ የሪል ስቴት ኤክስፖ የሚፈልጉት ቦታ ከልዩ ቅናሽ ጋር ያግኙ ! 💼📊

🎯 ቦታ፡ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሙዚየም
📅 ቀን፡ ሰኔ 27-29

ቤት ለገዢው, ሱቅ ለነጋዴው! 🏠🛍️
ካቦድ የሪል ስቴት ኤክስፖ

ለመመዝገብ የሚከተለውን መተግበርያ ይጠቀሙ፦ 
https://www.kabodmarketingsolution.com/
ባለፋት ዘጠኝ ወራት የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ከ 6ሺህ 6 መቶ በማይበልጡ ቱሪስቶች መጎብኘቱ ተነገረ

ባለፋት ዘጠኝ ወራት 96 ሺህ የሚደርሱ ቱሪስቶች የኢትዮጵያን ዋና ዋና ፓርኮች እና የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎችን ጎብኝተዋል ሲል የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።በባለስልጣኑ የዱር እንስሳት አጠቃቀም ዴስክ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ወርቁ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በዘጠኝ ወሩ ይህን ያህል ቱሪስቶች የጥበቃ ቦታዎችን ቢጎበኙም  በፀጥታ ችግር ምክንያት የቱሪስት ፍሰቱ መቀዛቀዙን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ካሏት ዋና ዋና የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች መካከል አንዱ የሆነው የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ አንፃራዊ ሰላም የታየበት ቦታ በመሆኑ ከሌሎች ፓርኮች በቀዳሚነት ተጎብኝቷል ያሉት አቶ ዳንኤል  የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ደግሞ የሁለተኛ ደረጃን መያዝ ችሏል ብለዋል።ፓርኩ በዩኔስኮበዓለም ቅርስነት ከተመዘገበ ወዲህ የቱሪስቶችን ቀልብ በመሳብ ረገድ ጥሩ መሻሻሎች እየታዮ እንደሚገኙ ገልፀው ባለፋት ዘጠኝ ወራት 7ሺህ የሚጠጉ ቱሪስቶች እንደጎበኙት አስረድተዋል።

የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ከሀገር ውስጥ ይልቅ በውጪ ሀገር ቱሪስቶች ይበልጥ መጎብኘቱን የገለፁት አቶ ዳንኤል በእግር መጓዝንና ተራራን መውጣት የፈለጉ ስፍራውን ለጉብኝት ተመራጭ ያደርጉታል። በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በኢትዮጰያ ሁለተኛው በዓለም ደግሞ 11ኛው ታላቅ የተፈጥሮ ቅርስ ሆኖ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣የሳይንስና፣የባህል ድርጅት(ዮኔስኮ)  መመዝገቡ ይታወሳል።በ 1962 ዓ.ም የተቋቋመው ፓርኩ የቆዳ ሥፋቱ 2 ሺህ 150 ካሬ ኪሎ ሜትር ቦታ ይሸፍናል፡፡

በውስጡም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ትልቁ ተራራ ቱሉ ዲምቱ የሚገኝ ሲሆን  የተለያዩ ብርቅዬ የእፅዋት እና የዱር እንሥሣት ዝርያዎች እንደሚገኙ ይነገራል።


ቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
የሱዳን ታጣቂ ቡድን ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በካቢኔ ቦታዎች አለመስማመቱን ተከትሎ ግጭት መፈጠሩ ተነገረ

በ2020 የሰላም ስምምነት ላይ በተቀመጠው መሰረት የሱዳን የሚኒስትርነት ቦታውን እንደሚቀጥል በመግለፁ ምክንያት በሱዳን ውስጥ ከፍተኛ አቅም አለው ተብሎ የሚታመን ታጣቂ ቡድን ከአዲሱ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር አለመግባባት ውስጥ ገብቷል። ውዝግቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ካማል ኢድሪስ ሰኔ 19 ላይ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ያካተተ የገለልተኛ ቴክኖክራቶች ካቢኔ ለማቋቋም ማቀዳቸውን ካስታወቁ በኋላ አዲስ መንግሥት ለመመስረት የሚገጥስማቸውን ፈተና አጉልቶ ያሳያል።

ከጠቅላይ ሚኒስቴሩ ጋር ግጭት ውስጥ የገባው ቡዱን የጁባ የሰላም ስምምነት ቁልፍ ፈራሚ የሆነው የፍትህ እና የእኩልነት ንቅናቄ (ጄኤም) ሲሆን አዲሱን ውሳኔ አልቀበልም በማለት ሀላፊነት እንደማይለቅ አስታውቋል። የጄኤም ቃል አቀባይ መሀመድ ዘካሪያ ፋራጃላህ በሰጡት መግለጫ "ለጁባ የሰላም ስምምነት፣ መርሆዎች እና መብቶች ሙሉ በሙሉ ቁርጠኝነት እንዳላቸው በማረጋገጥ በእሳቸው ስር የተፈቀዱትን የስራ አስፈፃሚ ቦታዎች ይዘው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

እ.ኤ.አ. በ 2020 የተደረሰው ስምምነት ፣ የታጠቁ ቡዱኖች 25 በመቶ የመንግስት የስራ ቦታዎች ተሰጥቷቸዋል፣ እነዚህም ስድስት የካቢኔ መቀመጫዎች ፣ ሶስት የሉዓላዊ ምክር ቤት መቀመጫዎች እና ዋና የክልል ገዥ ቦታዎች ያካትታሉ።  ፋራጃላህ ስምምነቱ እነዚህ ቦታዎች እስከ ሀገሪቱ የሽግግር ጊዜ ማብቂያ ድረስ መያዛቸውን ያረጋግጣል ስለዚህ አንለቅም ብለዋል።

የጄኤም ቃል አቀባይ ምንም እንኳ አሁን አለመግባባቶች ቢኖሩም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ምክክር አሁንም እንደቀጠለ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
በጋምቤላ ክልል የክረምት ወቅትን ተከትሎ የኃይል መቆራረጥ እንዳይኖር ያረጁ የኤሌክትሪክ መስመሮችን የመወጠር ስራ እየተሰራ ይገኛል ተባለ

በጋምቤላ ክልል ከኤሌክትሪክ ሀይል ተደራሽነት ጋር በተገናኘ የመልሶ ግንባታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል።የጋምቤላ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ አማረ ገብረመድህን ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት  በጋምቤላ ከተማ የኃይል አቅርቦትን አስተማማኝና ተደራሽ ለማድረግ  አዲስ የኃይል መስመር ዝርጋታ ለማከናወን ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም የነበረው የኃይል መስመር ዝርጋታ በእንጨት ምሰሶ የተከናወነ በመሆኑ በእርጅና ምክንያት እየወደቀ የኃይል መቆራረጥ የሚያስከትል መሆኑ ተነግሯል።አሁን ላይ ለችግሩ መፍትሄ ለማምጣት አዲስ የኃይል መስመር ዝርጋታ ለማካሄድ እየተሰራ ነው ያሉት አቶ አማረ  ያረጁ ምሰሶዎችንና መስመሮችን የመቀየሩ ስራ በክልሉ ይስተዋል የነበረውን የኃይል አቅርቦት መቆራረጥ ችግርን በመፍታት የተሻለ አገልግሎት እንዲኖር ለማስቻል እንደሚረዳ ተናግረዋል።

በተለይም ደግሞ የክረምት ወቅትን አስመልክቶ አሁን ላይ የረገቡ የኤሌክትሪክ መስመሮችን የመወጠር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አቶ አማረ ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።የኃይል መሠረተ ልማት አገልግሎትን ተደራሽነት ለማረጋገጥ የመስመርና የትራንስፎርመር ችግርን ለመቆጣጠር የሚያስችል ቡድን መዋቀሩ ተመላክቷል።

ቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
ዩናይትድ ኪንግደም የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መያዝ የሚችሉ ተዋጊ ጄቶችን ልትገዛ ነው

የብሪታኒያ መንግስት ትልቅ የተባለውን እና የኒውክሌር መከላከያ ማስፋፊያ አድርጎ የገለፀውን ታክቲካል የኒውክሌር ጦር መሳሪያ መተኮስ የሚችሉ ደርዘን ኤፍ-35 ኤ ተዋጊ ጄቶች እንደሚገዛ አስታውቋል። የሎክሂድ ማርቲን ጀቶች ግዢ የብሪታንያ አየር ሀይል ከቀዝቃዛው ጦርነት ማክተሚያ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዲይዝ ያስችለዋል ሲል ዳውንኒንግ ስትሪት አስታውቋል።

"በጣም እርግጠኛ ባልሆነበት ወቅት ሰላምን እንደ ቀላል ነገር መውሰድ አንችልም ለዚህም ነው መንግስቴ በብሄራዊ ደህንነታችን ላይ ኢንቨስት እያደረገ ያለው" ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር በሰጡት
መግለጫ ተናግረዋል።ብሪታንያ የመከላከያ ወጪን በመጨመር ወታደራዊ ኃይሏን እያሳደገች ነው፣ የባህር ሰርጓጅ መርከቦችን ጨምሮ፣ ከሩሲያ እየጨመረ ያለው ጠላትነት እየተጋፈጠች ትገኛለች። ዩናይትድ ስቴትስ የአውሮፓ ደኅንነት ተሟጋች ከነበረችበት ከባሕላዊ ሚናዋ በማፈግፈጓ ብሪታኒያ ክፍተቱን ለመሙላት እየጣረች ነው።

የብሪታኒያ መንግስት የጄቶች ግዢ ባለሁለት አቅም ያላቸውን አውሮፕላኖች ለኔቶ በማዋጣት ግጭት በሚፈጠርበት ጊዜ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንዲይዝ እንደሚያስችላት ተነግሯል።የኔቶ ዋና ፀሃፊ ማርክ ሩት “ይህ አሁንም ሌላ ጠንካራ የብሪታንያ ለኔቶ የሚደረግ አስተዋፅዖ ነው” ብለዋል። የብሪታንያ የኒውክሌየር መከላከያ በአሁኑ ጊዜ በትሪደንት ሰርጓጅ ላይ፣ የተመሰረተ ስርዓት ላይ ብቻ ያረፈ ሲሆን ይህም ባለፈው አመት በተደረገ ሙከራ የተሳሳተ ሙከራ ሆኗል። ይህም በ 2016 አንድ ኮርስ ከተቋረጠ በኋላ ሁለተኛው ተከታታይ የሙከራ ውድቀት ነው።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በእስራኤል ኢራን ውጥረት ዙሪያ ትንታኔውን ከጋዜጠኛ ሚሊዮን ሙሴ እና ስምኦን ደረጄ ይመልከቱ

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/puuEkWZf1gM?si=rq0vNfJCKFRDxr6t

#ዳጉ_ጆርናል
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በቻይና ጉዋንግ ዶንግ 4.5 በሬክተር ስኬል የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ባጋጠመበት ወቅት አንድ ታዳጊ ያደረገዉ ነገር መነጋገሪያ ሆኗል

በቻይና ጉዋንግ ዶንግ 4.5 በሬክተር ስኬል የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ አጋጥሟል።

በቤት ዉስጥ ከነበረ ካሜራ የተቀረጸ ምስዕል እንዳሳየዉ አንድ የቤተሰብ አባል የሆኑ ሰዎች የመሬት መንቀጥቀጡ ባጋጠመበት ወቅት ራት በመመገብ ላይ ነበሩ።

በዚህ መካከል የተሰማቸዉን የመሬት ንዝረት ለመሸሽ መለዉ ቤተሰብ ሲሯሯጥ አንድ ታዳጊ ልጃቸው ግን በጠረቤዛዉ ላይ እየተመገበ የነበረዉን ምግብ ትቶ ለመሮጥ ልቡ ፈራ ተባ ሲል ታይቷል።

ታዳጊዉ መላዉ ቤተሰብ ከቤት ለመዉጣት ሲሯሯጥ ከጀመረዉ ሩጫ እየተመለሰ "አንድ ለመንገድ" በሚመስል መልኩ ጠብሰቅ እያደረገ ሲጎርስ ታይቷል።

ሳቅን የፈጠረዉ የተዳጊዉ ድርጊት የብዙ ሰዎችን አስተያየት አስተናግዷል። "ከሞት ሆዱ በለጠበት" ያሉም ነበሩ። ሌሎችም "ታዳጊዉ በረሃብ ዉስጥ ሆኖ መሞት አልፈለገም ነበር" ሲሉ ቀልደዋል። አንዳንዶችም "የመጨረሻዉ ራት" ሲሉ ሃሳባቸውን ጥፈዋል።

ከተሰጡ አስተያየቶች ዉስጥ "በረሃብ ከመሞት በመሬት መንቀጥቀጥ መሞትን መርጧል" ያሉም አልጠፉም። "ምግቡ እንዴት ቢጣፍጥ ነዉ" ብለዉ ጥያቄ ያነሱም አሉ።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
በኬንያ ሰለፈኞች ከፖሊስ ጋር በመጋጨታቸው ቢያንስ ስምንት ሰዎች ሲገደሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቆሰሉ

በኬንያ የፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግስትን በመቃወም በተቀሰቀሰ ህዝባዊ ተቃውሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ጎዳና በመውጣት በተፈጠረው ቀውስ ቢያንስ ስምንት ሰዎች ሲገደሉ 400 ቆስለዋል። እ.ኤ.አ. በ 2024 በሀገሪቱ ከተቀሰቀሰው ፀረ-መንግስት የሰልፍ ማዕበል ከአንድ አመት በኋላ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ እና በሌሎች ከተሞች ፖሊስ ከተቃዋሚዎች ጋር ተጋጭቷል። አብዛኞቹ ሰልፈኞቹ “ሩቶ ስልጣን መልቀቅ አለባቸው” በማለት አገዛዙን በሰላማዊ መንገድ እንደሚቃወሙ ምልክት አድርገው ቅርንጫፎቹን እያውለበለቡ ታይተዋል።

መንግስት የተቃውሞ ሰልፎቹን በቀጥታ የቴሌቪዥንና የሬድዮ ስርጭት እንዳይተላለፍ ቢከለክልም አዋጁ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሽሯል። ሩቶ ተቃዋሚዎች ሰላምና መረጋጋት እንዳያደፈርሱ አሳስበዋል።"የተቃውሞ ሰልፎች የኬንያን ሰላም ማፍረስ መሆን የለባቸውም። ነገሮች ሲበላሹ የምንሄድበት ሌላ ሀገር የለንም፤ የሀገራችንን ሰላም መጠበቅ የኛ ኃላፊነት ነው" ብለዋል።

ፖሊሶች ዋና ዋና መንገዶችን በተለይም ወደ ፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግስት እና ፓርላማ የሚወስዱትን መንገዶች ዘግተዋል። ባለሥልጣናቱ እሮብ እለት በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የሟቾችን አኃዝ እስካሁን አልገለፁም፤ ነገር ግን የኬንያ የሕክምና ማህበር፣ የኬንያ የህግ ሶሳይቲ እና የፖሊስ ማሻሻያ የስራ ቡድን በጋራ ባወጡት መግለጫ ቢያንስ ስምንት ተቃዋሚዎች መገደላቸውን አስታውቀዋል።

ከተጎዱት 400 ሰዎች መካከል 83ቱ "ልዩ ህክምና" የሚያስፈልጋቸው ሲሆን ስምንቱ ደግሞ በጥይት ቆስለዋል። ጉዳት ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል ሶስት የፖሊስ አባላት እንዳሉም መግለጫው አክሎ ገልጿል። የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው አምነስቲ ኬንያ የሟቾችን ቁጥር 16 አድርሶታል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
ህንድ ከ41 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን የጠፈር ተመራማሪ ወደ ህዋ ላከች

ህንዳውያን ጠፈርተኞችን ጨምሮ ከብዙ ሀገር ሰራተኞች ጋር የጀመረውን የአክሲዮም-4 (አክስ-4) ተልእኮ በተሳካ ሁኔታ የጀመረበትን በዓል ሲያከብሩ ቆይተዋል። ተልዕኮውን በመምራት ላይ ያለው የቡድን ካፒቴን ሹብሃንሹ ሹክላ ወደ ጠፈር የተጓዘ ሁለተኛው ህንዳዊ ሆኗል። ከ26 ሰአታት በላይ ባለው ጉዞ ውስጥ መንኮራኩሯ በአለም አቀፍ የጠፈር ጣቢያ (አይኤስኤስ) ስትደርስ የቡድን ካፒቴን ሹክላ የናሳን ምህዋር ላብራቶሪ ሲጎበኝ የመጀመሪያው ህንዳዊ ይሆናል።

ይህ የጠፈርተኛው ጉዞ የተደረገው ኮስሞናዊት ራኬሽ ሻርማ በ1984 በሩሲያ ሶዩዝ ተሳፍሮ ወደ ጠፈር በመብረር የመጀመሪያው ህንዳዊ ከሆነ ከ41 ዓመታት በኋላ ነው።በቀድሞው የናሳ የጠፈር ተመራማሪ ፔጊ ዊትሰን ጉዞ ተመርቷል። ፔጊ ዊትሰን የአይኤስኤስ ሁለት ጊዜ አዛዥ የነበረ ሲሆን የጠፈር አርበኛ በመሆን ከ675 ቀናት በላይ በህዋ ላይ አሳልፏል። 10 የጠፈር ጉዞዎችን አድርጓል።

አክስ-4 ከናሳ ኬኔዲ የጠፈር ማእከል በፍሎሪዳ እሮብ እለት ተነስቷል። በአክስ-4 ተሳፍሮ ወደ አይኤስኤስ የተደረገው ጉዞ በሂዩስተን በሚገኝ የግል ኩባንያ አክሲዮም ስፔስ የሚመራ የንግድ በረራ ነው። በናሳ የህንድ የጠፈር ኤጀንሲ ኢስሮ እና የአውሮፓ ጠፈር ኤጀንሲ (ኢሳ) መካከል ትብብር አለ። የጠፈር ተመራማሪዎቹ እሮብ እለት ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ሳምንታትን በለይቶ ማቆያ ክፍል ውስጥ አሳልፈዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በሰሜን አሜሪካ በሙቀት ማዕበል የተነሳ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ሆስፒታል ገቡ

የበጋው የመጀመሪያው ከፍተኛ የሙቀት ማዕበል በምስራቃዊ ሰሜን አሜሪካ መከሰቱን ተከትሎ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ከሙቀት ጋር በተያያዙ በሽታዎች ሆስፒታል ገብተዋል። የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት የከተማዋ ከንቲባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ባወጁበት ወቅት ከ150 በላይ ሰዎች ሰኞ እለት በፓተርሰን ኒው ጀርሲ ከቤት ውጭ በነበረ የትምህርት ቤት የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ታመዋል።

በዋሽንግተን ዲሲ በደቡብ ኮሪያ ባንድ 'ስትሬይ ኪድስ' የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ስድስት ሰዎች የሆስፒታል ህክምና ያስፈለጋቸው መሆኑን ሲቢኤስ ዘግቧል። የሙቀት ማስጠንቀቂያዎች ከዩናይትድ ስቴትስ ሚድዌስት እስከ ኢስት ኮስት እንዲሁም በካናዳ ኦንታሪዮ፣ ኩቤክ እና ኖቫ ስኮሺያ ክፍሎች የተሰጠ ሲሆን በሳምንቱ ውስጥ ከ160 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ይጎዳል ተብሎ ይጠበቃል።

በስተደቡብ በአሜሪካ ምስራቃዊ የባህር ጠረፍ፣ በሰሜን ካሮላይና ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ከሙቀት ጋር የተያያዙ ጉዳቶች ህክምና ፈልገው መጥተዋል። በማዕከላዊ ሰሜን ካሮላይና ውስጥ ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 41 ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን የሀገር ውስጥ የዜና አውታሮች ዘግበዋል። የፓተርሰን ከንቲባ አንድሬ ሳዬግ በሙቀት ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ በአካባቢው የሚደረጉ የመዝናኛ እንቅስቃሴዎችን በመሰረዝ የማቀዝቀዣ ማዕከላትን ከፍተዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
አውስትራሊያዊቷ ጋዜጠኛ በጋዛ ዙሪያ ባጋራችው ዘገባ ከስራ መሰናበቷ ፍትሃዊ አይደለም በሚል የመሰረተችውን ክስ አሸነፈች

አውስትራሊያዊቷ ጋዜጠኛ አንቶኔት ላቶፍ በኤቢሲ ቴሌቪዥን ላይ ያቀረበችውን በህገወጥ መንገድ ከስራ ተቀንሻለው የሚለውን ክስ በመርታቷ 45,511 የአሜሪካን ዶላር  ማሸነፏን የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል። የፌዴራል ፍርድ ቤት እንዳስታወቀው ቴሌቪዥን ጣቢያው ፍትሃዊ የስራ ህግን ተቃውማለች በሚል ምክንያት “የእስራኤልን ወታደራዊ ዘመቻ በመቃወም የፖለቲካ አስተያየት ሰንዝራለች ” በሚል ስራዋን በማቋረጥ እንዳሰናበታት ኤቢሲ ኒውስ ዘግቧል።

የሊባኖስ-አውስትራሊያዊት ጥምር ዜግነት ያላት ጋዜጠኛ ላትቱፍ በኤቢሲ ተቀጥራ የምትሰራ ሲሆን  በሂዩማን ራይትስ ዎች የጋዛ ጦርነትን አስመልክቶ በኢንስታግራም የለጠፈውን ዘገባ በኢንስታግራም ገጿ ካጋራች በኋላ ከስራዋ ተባራለች። ይህም ድርጊቷ ኤቢሲ የአርትኦት ፖሊሲውን መጣስ ነው ብሏል። አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በጋዛ የሚገኙ የእስራኤል ባለስልጣናት ረሃብን የጦር መሳሪያ አድርገው እንዴት እንደሚጠቀሙበት የሚገልጽ ጥናት አሳትሞ ነበር።

ላትቱፍ በፖለቲካ አመለካከቷ፣ በዘሯ እና በእስራኤል ደጋፊ ቡድኖች ሎቢ አድራጊነት ከስራ እንደተባረረች በመግለጽ በተሳሳተ መንገድ ከስራ እንደተባረረች ክስ አቅርባለች። እ.ኤ.አ ከጥቅምት 2023 ጀምሮ የእስራኤል ጦር በጋዛ ላይ በከፈተው ጥቃት ከ56 ሺ በላይ ፍልስጤማውያንን ሲገደሉ አብዛኛዎቹ ሴቶች እና ህጻናት ናቸው። ባለፈው ህዳር የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትራቸው ዮአቭ ጋላንት በጋዛ በፈጸሙት የጦር ወንጀሎች እና በሰብአዊነት ላይ ወንጀሎች የእስር ማዘዣ አውጥቷል። እስራኤልም በአካባቢው ባደረገችው ጦርነት በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት የዘር ማጥፋት ወንጀል ክስ ቀርቦባታል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
ሱሉልታ መውጫ ፍተሻ ጋር በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰው ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ከባድ ተሽከርካሪ በሌላ ተሽከርካሪ ላይ ወድቆ መሆኑን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።

የተጎጅዎችን አስከሬን ለማውጣት የአደጋ ግዜ ሰሬተኞች ርብርብ እያደረጉ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

ዝርዝር መረጃ እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።


በትግስት ላቀው
#ዳጉ_ጆርናል
2025/07/04 01:37:33
Back to Top
HTML Embed Code: