Telegram Web Link
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
የአሜሪካ ፖሊስ በክለቦች የአለም ዋንጫ ዉድድር ጥበቃ ለሚጠቀማቸዉ ዉሾች ጫማ መጠቀም ጀመረ

የአሜሪካ ፖሊስ በስራዎቹ ለሚያግዙትን የሰለጠኑ ዉሾች ጫማ መጠቀም ጀመሯል። የአሜሪካ ፖሊስ በክለቦች የለም ዋንጫ የጸጥታ ስራዉ ነዉ ዉሾቹን የሚጠቀመዉ።

ፖሊስ ለዉሾቹ ጫማ መጠቀም የጀመረዉ በሀገሪቱ በአሁኑ ሰዓት ካለዉ ከፍተኛ ሙቀት የተነሳ መሆኑ ተዘግቧል። በክለቦች የአለም ዋንጫ ተጨዋቾች ያለዉን ሙቀት መቋቋም ሲያቅታቸዉ ተመልክተናል።

ለአብነት ከትናንትና በስቲያ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ ከኡልሳን ጋር ባደረገዉ ጨዋታ የአየር ንብረቱ ወይም ሙቀቱ ከ 42 ሴንቲግሬድ በላይ ነበር።

በተቀያሪ ወንበር ላይ የሚቀመጡ ተጨዋቾችም ሙቀቱን መቋቋም አቅቷቸዉ በመልበሻ ክፍል ጨዋታዉን በቴሌቪዥን ሲከታተሉ በተደጋጋሚ ተመልክተናል።

የአሜሪካ የአሁኑ የአየር ንብረት ሁኔታ በቀጣይ አመት ሀገሪቱ ከካናዳ እና ሜክሲኮ ጋር በጋራ በምታዘጋጀው የሀገራት የአለም ዋንጫ ዉድድር ላይ ጥላ እንዳያጠላ ተሰግቷል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
በአረብ ሀገራት የሚገኙት አብዛኛዎቹ አቦሸማኔዎች በህገወጥ መልኩ ከኢትዮጵያ የተወሰዱ ናቸው ተባለ

በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ሀብት ላይ ከተደቀኑ በርካታ ችግሮች መካከል ህገወጥ የእንስሳት ዝውውር አንዱ መሆኑን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።በባለስልጣኑ የዱር እንስሳት ህገወጥ ዝውውር ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዳንኤል ጳውሎስ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ለተለያዩ አላማዎች ሲባል በኢትዮጵያ የሚገኙ የዱር እንስሳት ከነህይወታቸው በህገወጥ መንገድ ይዘዋወራሉ።

በዚህ መልኩ ከሀገር የሚወጡ እንስሳቶች በርካታ ቢሆኑም  በቀዳሚነት አቦሸማኔ ይጠቀሳል ። አቦሸማኔ በተለይም በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል በሱማሌ ክልል መኖሪያውን በማድረጉ የአካባቢው ማህበረሰቦች ባካበቱት ተፈጥሮአዊ ዘዴ የአቦሸማኔ ቡችላዎችን በመያዝ ሶማሌላንድ አካባቢ ለሽያጭ እንደሚያቀርቡ ተጠቁሟል።

በዚህ መልኩ ይህ እንስሳ ወደ መካከለኛው የአረብ ሀገራት ጭምር ላሉ ባለሀብቶች የሚሸጥበት ሁኔታ መኖሩን የገለፁት አቶ ዳንኤል ግለሰቦቹ የራሳቸው የሆነ መካነ አራዊት ስላላቸው እንስሳቱን የመግዛት ፍላጎታቸው ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል።ወደ መካከለኛው ምስራቅ የአረብ ሀገራት የሚገኙት አቦ ሸማኔዎችም ከአፍሪካ ቀንድ በተለይም ከኢትዮጵያ የተወሰዱ ስለመሆናቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ ሲሉ ባለሙያው ጨምረው ለጣቢያችን ተናግረዋል።

አቦሸማኔን ጨምሮ ሌሎች እንስሳትን ከህገወጥ ዝውውር ለመታደግና ኢትዮጵያ ከእንስሳት ሀብቷ ተጠቃሚ እንድትሆን አሁን ላይ በአነፍናፊ ውሾች የታገዘ የቁጥጥር ስራ እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል።

ቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
በኢራን የስለላ ድርጅት ውስጥ ይሰራል ተብሎ የተጠረጠረ ወጣት በእስራኤል በቁጥጥር ስር ዋለ

በሰሜን እስራኤል ከሚገኘው ከዴር አል አሳድ የመጣው የ22 ዓመት ተማሪ ኢራንን ወክሎ ተልእኮዎችን በማከናወን ክስ ሊመሰረትበት እንደሚችል ፖሊስ እና የሀገሪቱን የሺን ቤት የደህንነት አገልግሎትን ጠቅሶ ሃሬትዝ ዘግቧል።

ባሻር ሀሰን ቃሲም ሙሳ በደቡብ እስራኤል በቤር ሼቫ በማዕከላዊ ግዛት ላይ የመንገድ የተለያዩ ተቀጣጣይ ነገሮችን ካስቀመጠ እና ሰው ለመጉዳት ከሞከረ በኋላ ለኢራን የስለላ ስራ በመስራት ተጠርጥሮ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉን የእስራኤሉ ጋዜጣ ዘግቧል። ነግር ግን ሺን ቤት የሙሳን ኢላማ ማንነት ግልፅ አለመሆኑን ሃሬትዝ አክሏል።

በሌላ መረጃ የእስራኤልጦር በዮርዳኖስ ሸለቆ አካባቢ የጦር ልምምዱን ከሀሙስ ከጠዋት ጀምሮ እስከ ከሰአት በኋላ እንደሚደረግ ገልጿል። በልምምድ ወቅት በአካባቢው ከፍተኛ የወታደራዊ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንደሚኖርም አክሏል። ልምምዱ እስራኤል በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አደራዳሪነት ከኢራን ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ከጀመረች ከቀናት በኋላ ነው።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
በህገ- ወጥ መልኩ ከ2 ሺህ በላይ ፕላምፕሌት ይዞ የተገኘ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በሰቆጣ ከተማ በህገ- ወጥ መልኩ ፕላምፕሌት ከመጋዝን ውስጥ ይዞ የተገኘ ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት አስታወቀ።

የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤልያስ አስፋ  ነዋሪነቱ በሰቆጣ ከተማ 01 ቀበሌ ሲሆን ተከሳሽ አቶ ወንድሙ ቢክሰኝ በ2012 ዓ.ም የወጣው የኢፌድሪ ምግብና መድኃኒት አሥተዳደር አዋጅ ቁጥር 1112/2012 አንቀጽ 67/4/ የተደነገገውን በመተላለፍ በምግብ እጥረት ለተጎዱ ህጻናት የመጣን 2ሺህ 1መቶ 83 ፕላምፕሌት ሚያዚያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡ 00 ሰዓት አካባቢ መጋዝን ውስጥ ይዞ  መገኘቱን ተከትሎ ክስ ተመስርቷል።

የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት የወንጀል ጉዳዮች ሥራ ሂደትም ከፖሊስ ተጣርቶ የቀረበለትን የምርመራ መዝገብ  በመያዝ በተከሳሽ  አቶ ወንድሙ ላይ ክስ መስርቶ  የሰቆጣ ወረዳ ፍርድ ቤት የፍርድ ብያኔ እንዲሰጠበት ጉዳዩን ሲከታተለው መቆየቱን አቶ ኤልያስ  ገልጸዋል።ፍትህ ጽ/ቤቱ በተከሳሽ አቶ ወንድሙ ላይ ያቀረበውን ክስ የሰቆጣ ወረዳ ሲያከራክር ቆይቶ ሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን ጥፋተኛ በማለት 2 ዓመት እስራትና 5ሺህ ብር እንዲቀጣና በኢግዚቪት የተያዘው 2ሺህ 1መቶ 83 ፕላፕሌትም ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ተወስኗል ሲሉ አቶ ኤልያስ ተናግረዋል።

የፍትህ ጽ/ቤት የተቋቋመው የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው ያሉት አቶኤልያስ ወንጀል ፈጽሞ ከህግ መሰወር የማይቻል መሆኑንም አስረድተዋል። በጤና ባለሙያዎች ከታዘዘለት ግለሰብ ውጭ ፕላምፕሌት ይዞ  የተገኘም ሆነ ሌሎች ወንጀሎችን የተፈጸሙ ማንኛውም ሰው በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን አውቆ ወንጀል ከመፈጸም ሊቆጠብ ይገባል ሲሉ ኃላፊው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል
ወደ ሰሜን ኮርያ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሩዝ እና ዶላር ሊልኩ የነበሩ አሜሪካውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ

የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት 1,300 የሚገመቱ የፕላስቲክ ጠርሙሶችን በሩዝ፣በዶላር እና በመፅሀፍ ቅዱስ በመሙላት ወደ ሰሜን ኮሪያ በባህር ሊልኩ ሲሞክሩ የነበሩ ስድስት የአሜሪካ ዜጎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የዜና ዘገባዎች አመልክተዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች የተያዙት አርብ ማለዳ ላይ ጠርሙሶቹን ከሰሜን ኮሪያ ጋር በተከለከለው የፊት ለፊት ድንበር አካባቢ አቅራቢያ ከሚገኘው ከጓንግዋ ደሴት ወደ ባህር ለመልቀቅ ሲሞክሩ ከተያዙ በኋላ ነው ሲል የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣን ዮንሃፕ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ስድስቱ ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት አካባቢውን የሚጠብቅ የባህር ዳርቻ ወታደራዊ ክፍል ለፖሊስ ካሳወቀ በኋላ ነው። ደቡብ ኮሪያ ከሰሜናዊ ድንበር አቋርጠው የሚመጠ የፕላስቲክ ጠርሙሶች ወይም የሚበር ፊኛዎች ላይ የሚላኩ ቁሳቁሶች በኮሪያ ልሳነ ምድር ላይ ውጥረት ፈጥረዋል። ዮንሃፕ እንዳለው ፀረ ፒዮንግያንግ ፕሮፓጋንዳ ወደ ሰሜን እንዳይጀምር የሚከለክል አስተዳደራዊ ትእዛዝ ለአካባቢው ተግባራዊ ሆኗል ።

እ.ኤ.አ. በ 2023 ፣ የደቡብ ኮሪያ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት የ 2020 በራሪ ወረቀቶችን እና ሌሎች እቃዎችን ወደ ሰሜን ኮሪያ መላክን ወንጀል የሚያደርግ ህግን የሻረ ሲሆን የመናገር ነፃነትን ከመጠን በላይ ይገድባል ብሏል ። ነገር ግን በጁን መጀመሪያ ላይ ስልጣን ከያዙ ወዲህ የፕሬዚዳንት ሊ ጄ-ሚንግ አዲሱ የሊበራል መንግስት ከሰሜን ኮሪያ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት ለማስቀረት እና የግንባር ቀደምት የደቡብ ኮሪያ ነዋሪዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ እንዲህ ያሉ የሲቪል ዘመቻዎችን ከሌሎች ከደህንነት ጋር በተያያዙ ህጎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ እየሞከሩ ይገኛል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እስራኤል በዌስት ባንክ 'የግዳጅ ማፈናቀል' እየፈፀመች ነው አለ

የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) በዌስት ባንክ ውስጥ በሚገኘው ማሳፈር ያታ አካባቢ በ3 የፍልስጤም ማህበረሰቦች የሚኖሩባቸው ሁሉም ህንፃዎች እንደሚወድሙ የእስራኤል ጦር ማሳሰቢያ አውጥቷል። ቢያንስ 1,200 ሰዎች፣ ከ500 በላይ ህጻናትን ጨምሮ፣ አሁን ወታደሮቹ ያቀዱትን የማፍረስ ተግባር ከፈጸሙ “በግዳጅ የመፈናቀል” ስጋት ላይ ናቸው ሲል ኦቻ ገልጿል።

በዌስት ባንክ ውስጥ ለፍልስጤማውያን የከፋ ሁኔታ በተመለከተ የቅርብ ጊዜ የኩነት ዘገባ እንዳመናከተው፣ ኦቻ ከሰኔ 13 እስከ 23 ባለው ጊዜ ውስጥ የእስራኤል ወታደሮች 240 የፍልስጤም ቤቶችን እንደ ወታደራዊ መጠለያ እና የምርመራ ማዕከላት ለመጠቀም ለጊዜው “እንደያዙ” ዘግቧል። የቤቶቹ ባለቤቶች በግዳጅ ተፈናቅለዋል ወይም ታስረዋል ሲልም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በወታደራዊው የቤት ወረራ ወቅት ገልጿል።

በዌስት ባንክ ቱልካሬም እና ኑር ሻምስ የስደተኞች መጠለያ ካምፖች 100 የሚጠጉ ግንባታዎች በተለይም ቤቶች በዚህ ወር በእስራኤል ወታደሮች ፈርሰዋል። በምስራቅ እየሩሳሌም ውስጥ ደግሞ 320 የሚጠጉ ነዋሪዎች በሶስት የፍልስጤም ማህበረሰቦች ውስጥ እንደገና የመፈናቀል እና የማፍረስ ዛቻዎች ተደቅኖባቸዋል ሲል ኦቻ አስታውቋል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
ኢትዮጵያ  ከፍተኛ ኃይል ከሚያመነጩ አስር የአፍሪካ ሀገራት ተርታ በሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ተባለ

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ኃይል እያመነጩ ካሉ አስር የአፍሪካ ሀገራት መካከል በሰባተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

በአገልግሎቱ ፕሮሰስ እና ኳሊቲ ማኔጅመንት ስራ አስፈፃሚ አቶ እሱባለው ጤናው ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በዘርፋ ከምርጥ አስር የአፍሪካ ሀገራት ተርታ ተመድባ ባታውቅም ከህዳሴ ግድብ ወዲህ ግን ኃይልን ከማመንጨት አንፃር የ7ኛ ደረጃን ይዛለች።

ከአፍሪካ ሀገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ ለዜጎቿ በፈረቃ ኤሌክትሪክን የምታዳርስ መሆኗን አንስተው እንደ ግብፅ፣ሞሮኮና አልጀሪያ ያሉ ሀገራት ደግሞ የተሻለ እና የተረጋጋ ኤሌክትሪክን ለዜጎቻቸው ከሚያዳርሱት መካከል ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።

ምንም እንኳን ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ከምርጥ አስር የአፍሪካ ሀገራት ተርታ ብትመደብም ካላት ሰፊ የህዝብ ቁጥር አንፃር እንዲሁም ወደ ኢንዱስትሪው ዘርፍ ለመሸጋገር ከምታደርገው ጥረት አኳያ የኤሌክትሪክ ዘርፋን ማሳደግ ይጠበቅባታል ሲሉ ስራ አስፈፃሚው  ጨምረው ተናግረዋል።በተለይም ደግሞ በቀጣይ ያላት የህዝብ ቁጥር እየጨመረ በሚመጣ ወቅት ኃይል የማመንጨት አቅሟን ይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባት ተጠቁሟል።

ቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (Beⓒk)
ሰር ዴቪድ ቤካም ከ 23 አመት በፊት ለደረሰበት ጉዳት የቀዶ ህክምና አደረገ

ሰር ዴቪድ ቤካም ከ 23 አመት በፊት እንግሊዝ ከደቡብ አፍሪካ ባደረጉት ጨዋታ ለደረሰበት ጉዳት ከአመታት በኋላ የቀዶ ህክምና አድርጓል። ቤካም በእጁ ላይ በደረሰዉ በወቅቱ በጨዋታው ተቀይሮ ለመዉጣት የተገደደ የነበረ ቢሆንም ህክምናዉን ግን ከ 23 አመታት በኋላ ነዉ ያደረገዉ።

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
ዩናይትድ ስቴትስ ከጥቃቱ ምንም አላተረፈችም ሲሉ የኢራን ከፍተኛ መሪ ተናገሩ

የኢራን ጠቅላይ መሪ ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ማክሰኞ ዕለት ከተደረሰ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረጉት ንግግር አሜሪካ በቴህራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ በከፈቷቸው ጥቃቶች “ምንም ስኬት አላስገኘችም” ሲሉ አጥብቀው ተናግረዋል ። ጥቃቱ የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር ለማደናቀፍ ምንም አይነት ፋይዳ አላስገኘም ያሉት አያቶላህ አሊ ካሜኒ፣ በኳታር የሚገኘው የአሜሪካ የአየር ጦር ሰፈር ላይ የወሰድነው አጸፋም “ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት” ገልጸዋል። ኢራንን ይህንን ትበል እንጂ ጥቃቱ የኢራንን የኒውክሌር ምኞቷን በእጅጉ ጎድቷል ስትል ዋሽንግተን መናገሯ ይታወሳል።

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ፔት ሄግሥት በዩናይትድ ስቴትስ እና በእስራኤል የተሰበሰቡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ኦፕሬሽኑ "የኒውክሌር መርሃ ግብሩን በእጅጉ በመጎዳቱ ለአመታት ወደኋላ ኢራንን እንድትመለስ አድርጓል" ብለዋል።ከዚህ ቀደም የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ውስጥ በሦስት ቁልፍ የኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን የገለፁ ሲሆን ጉዳቱ ከተጠበቀው ያነሰ ሊሆን እንደሚችል ስማቸው ያልተጠቀሰ የአሜሪካ ባለስልጣናት ተጠቅሶ የተሰራውን ዘገባ በቁጣ የሀሰት ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሃሙስ ማለዳ ላይ በፔንታጎን ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከከፍተኛ ጄኔራል ዳን ኬይን ጋር ንግግር ሲያደርጉ ሄግዝ እንደተናገሩት ተልእኮው “የኢራንን የማበልጸጊያ ተቋሞች ከስራ ውጪ ያደረጉ ታሪካዊ ስኬት” ነው ብለዋል። ካሜኔይ ትራምፕ የኒውክሌር ጣቢያ ጥቃቶች ያስከተለውን ተጽእኖ በተመለከተ የተናገሩት “የተጋነኑ” መሆናቸውን በመግለጽ “ምንም ነገር ማከናወን አልቻሉም እና አላማቸውን ማሳካት አልቻሉም” ብለዋል። በኳታር የሚገኘው የአሜሪካ የአየር ጦር ሰፈር ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በመጥቀስ ካሜኒ “ይህ ክስተት ወደፊትም ሊደገም የሚችል ነው፣ እናም ማንኛውም ጥቃት ቢደርስ ለጠላት እና ለአጥቂው የሚያስከፍለው ዋጋ በጣም ከፍተኛ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም” ብለዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
በደቡብ ጎንደር ዞን ተቋርጦ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ እንዳልተፈታ ተገለፀ

በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ መካነ ኢየሱስ ከሰሞኑን የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ በመቆየቱ ህብረተሰቡ ለከፍተኛ እንግልት  ተጋልጦ እንደነበር  የመካነ-ኢየሱስ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ተጠሪ ጽ/ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።በዞኑ የኮሚኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ እሱባለው መስፍን ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በአካባቢው ተቋርጦ የነበረው የትራንስፓርት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ አልተፈታም።

በሁሉም አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ የትራንስፖርት ሊቋረጥ የቻለው በፀጥታ ችግር እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን  ይህም አሽከርካሪዎች ለከፍተኛ ድብደባ  ፣ግድያ እና እንደተጋለጡ ተነግሯል። ባለሀብቶች በንብረታቸው ማዘዝና በገንዘባቸው መጠቀም፤ ነጋዴዎች ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ ሸቀጣ ሸቀጥ ማቅረብ አለመቻላቸውም ተጠቅሷል።

በተጨማሪም የትራንስፖርት አገልግሎቱ በመቋረጡ የተነሳ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና ለማደናቀፍ ጥረት መደረጉን አቶ እሱባለው ገልፀው አሁን ላይ ተማሪዎች ፈተናው ወደ ሚሰጥበት ማዕከል መሄድ የሚችሉበት ሁኔታ መፈጠሩን ለጣቢያችን አስረድተዋል።እንደዚሁም የከተማው አስተዳደርና የወረዳው አመራሮች ከባለሀብቶችና አሽከርካሪዎች ጋር  ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
ኢራን በስለላ ወንጀል የተጠረጠሩ ተጨማሪ ሰዎች ማሰሯን አስታወቀች

የኢራን ሆርሙዝ ግዛት ባለስልጣናት ከእስራኤል ጋር ለ12 ቀናት በዘለቀው ጦርነት በስለላ ወንጀል ተሳትፎ የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፖሊስ ቃል አቀባይን ጠቅሶ የእስልምና ተማሪዎች የዜና አገልግሎት (ኢስና) ዘግቧል። ተጠርጣሪዎቹ በሆርሞዝጋን የስለላ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር የዋሉት በሀገሪቱ ውስጥ ሊነጣጠሩ ስለሚችሉ የጥቃት ለመምከር ከውጪ አካላት ጋር በመገናኘት ነው ሲል የፖሊስ ቃል አቀባይን ጠቅሶ ኢኤስኤንኤ ዘግቧል።

ወንድ እና ሴት ተጠርጣሪዎቹ መዋቢያዎችን በማስመጣት እና የሳተላይት ስልኮችን ለመጠገን በሚል ስም ተግባራቸውን ደብቀው እንደነበር የገለፀው ዘገባው፥ ለሥራቸውም “ከፍተኛ ገንዘብ” እንደተከፈላቸው ገልጿል። “መደበቂያ ቦታቸው” ላይ በተደረገ ፍተሻም የቴሌኮሙኒኬሽን መሳሪያዎች፣ እንዲሁም ጂፒኤስ እና ሳተላይት ስልኮች መገኘቱን ኢስና ዘግቧል።

የኢራን ባለስልጣናት በመላ ሀገሪቱ ሰፊ የጸጥታ ሃይሎችን በማሰማራት ከ700 በላይ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል በሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ላይ ስጋት ፈጥሯል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
የእስራኤል መከላከያ አዛዥ ነፍሰ ገዳዮች አያቶላህ ካሚኔይን ለመግደል ሲፈልጓቸው ነበር አሉ

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትዝ ለእስራኤል ህዝብ በቀጥታ ስርጭት ባስተላለፉት መልእክት ቢቻል ኖሮ ወታደሮቹ የኢራንን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ካሚኒን ከቴህራን ጋር ለ12 ቀናት በዘለቀው ግጭት ውስጥ ይገድሉ እንደነበር ገልፀዋል።

ከእስራኤል ቻናል 13 ጋር ባደረጉት የተለየ ቃለ ምልልስ፣ ካትዝ የእስራኤል ኦፕሬተሮች ካሜኔን “ብዙ ፈልገዋል” ነገር ግን ጥቃት ለመፈጸም “የአሰራር እድል” ማግኘት አልቻሉም ብለዋል። የኢራን ባለስልጣናት ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ደካማ የተኩስ አቁም ስምምነት ቢደረግም እስራኤል ካሚኔይን ለመግደል እየፈለገች ሊሆን እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

በተጨማሪም ካትዝ ለቻናል 13 እንደተናገሩት "ኢራን የኒውክሌር መስሪያ ቤቶችን ዳግም የምታስጀምርበት ሁኔታ አይታይም" በዩናይትድ ስቴትስ እና በእስራኤል ሃይሎች ጥቃት ሳብያ ቴህራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የመገንባት አቅሟ "በአጠቃላይ ወድሟል" ብለዋል። ሆኖም ካሜኒ ከተኩስ አቁም ስምምነቱ በኋላ ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግራቸው የዩናይትድ ስቴትስ ጥቃቶች ለኢራን የኒውክሌር ፋሲሊቲዎች ምንም አይነት ፋይዳ አላሳዩም ብለዋል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል
Forwarded from ዳጉ ጆርናል-ስፖርት (....)
ፒኤስጂ ሊዮንን ወደ ሁለተኛ ዲቪዚዮን እንዳይወርድ ለማዳን እየረዳ ነዉ ተባለ

ፒኤስጂ ሊዮንን ወደ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ከመውረድ ለማዳን እየረዳው ስለመሆኑ ተሰምቷል።

ክለቡ ብራድሌይ ባርኮላን በ 45+5 ሚሊዮን ዩሮ የፈረመውን የዝውውር ሂሳብ ቀደም ብሎ ከፍሏል።

ይህ እርምጃ ሊዮን የፋይናንስ አቋማቸውን እንዲያሻሽሉ አስችሎታል ተብሏል። ሊዮን ከሰሞኑ ባጋጠመዉ የፋይናንስ ቀዉስ ከፈረንሳይ ሊግ እንዲወርድ ተወስኖ ነበር።

የክለቡ ደጋፊዎችም በክለቡ ባለቤት አሜሪካዊዉ ባለሃብት ጆን ቴክስተር ላይ ተደጋጋሚ ተቃዉሞ ሲያሰሙ ነበር። ባለሃብቱ ከወራት በፊት ክለቡ እስከመዉረድ አይደርስም እንታደገዋለን ብለዉ የነበረ ቢሆንም ቃላቸዉን ሳይጠብቁ መቅረታቸዉ የሊዮንን ደጋፊዎች አስከፍቷል።

ክለቡ ይግባኝ አቅርቧል የተባለ ሲሆን ወደ ሊግ 1 እንደሚመለስ ተስፋ አድርጓል።

በስምኦን ደረጄ

#ዳጉ_ጆርናል_ስፖርት
@Dagujournalsport
2025/06/27 21:15:48
Back to Top
HTML Embed Code: