Telegram Web Link
Audio
💠"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::"💠 /ማቴ ፫:፫/


"" የፍቅር ሐዋርያ ""
(ዮሐ. ፳፩:፳)

"" ❇️(ገድለ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ)❇️ ""

(ጥር 4 - 2014)

በመምህርዲ/ዮርዳኖስ አበበ

❇️ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)❇️

" 🔶ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::🔸
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://www.tg-me.com/zikirekdusn
Audio
ጸሐፊ ፡ዲ.ን ዶ.ር ቴዎድሮስ በለጠ
አንባቢ ፡ ሐና
ሰላም እንዴት ናችሁ!
ቸር አላችሁ🙏
መርሐ ግብራችን ላይ ያላችሁን አስተያየት ላኩልን!
ይጨመር፣ይቀነስ፣ይቀየር የምትሉት ካለ
@Zeboanerges
ይላኩልን🙏🙏🙏
Watch "ጥምቀት በ ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ" on YouTube
https://youtu.be/mggqb-huerA
የተመረጠች ድንግል እና ሰማዕት ቅድስት #ምኅራኤል ከተወዳጅ ወንድሟ #አባሖር ጋር

"" ሃብቷ : በረከቷ በዕለተ ዕረፍቷ ይድረሰን !! ""
ጥር14
❇️ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)❇️

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል:: አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://www.tg-me.com/zikirekdusn
ጥር 17፦

ዛሬ ደጉ ሐዋርያ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ የተጠራበት ዓመታዊ በዓሉ ነው።
Audio
🎧 ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ🎧

🎤 #በሐና ማርያም🎤

@zeneser

ጥር 17፦

ዛሬ ደጉ ሐዋርያ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ የተጠራበት ዓመታዊ በዓሉ ነው።
"ምንትኑ ያፈርሐኒ፣
ወትግርምተ መኑ ያደነግጸኒ፣
እንዘ ሰማዕት ጊዮርጊስ ሀሎከኒ፣"
6 ስንክሳር የካቲት.pdf
42.2 MB
📕ስንክሳር ዘወርኀ የካቲት📕
ለዳዊት ማን ነገረው?

መዝሙረ ዳዊት የመጨረሻው እንዲህ ሚል የሚገርም ንግግር አለ።

እንዲህ ይላል " መኑ ነገሮ ለእግዚእየ "

ለጌታየ ማን ነገረው? ማለት ነው።

የጌታስ የጌታ ነው ሁሉን የሚያውቅ ነውና

ነጋሪ አይፈልግም

አበው ምን ይላሉ ለዳዊት ማን ነገረው

ይህንን ሁሉ የልባችንን ልመና ለዳዊት

ማን ነገረው ደስ ሲለን

“በልቤ ደስታን ጨመርህ፤ ከስንዴ ፍሬና ከወይን ከዘይትም ይልቅ በዛ።”
— መዝሙር 4፥7

እያልን::

ስንፈራ:

መዝሙር 27
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?

² ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥ ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ በቀረቡ ጊዜ፥ እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ።

³ ሠራዊትም ቢሰፍርብኝ ልቤ አይፈራም፤ ሰልፍም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለሁ።

እያልን እንድንዘምር ለደስታችን

ለሐዘናችንም የልባችንን ለዳዊት ማን

ነገረው?

ስንበድል
“በፍጹም ልቤ ወደ ፊትህ ተማለልሁ፤ እንደ ቃልህ ማረኝ።”
— መዝሙር 119፥58

እያልን እንድንዘምር ለዳዊት ማን ነገረው?

ለቅዱስ ለልበ አምላክ ዳዊት ማን ነገረው?

መዝሙር 51
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።
² ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ፤
³ እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።

እያልን ስለበደላችን እንድንጸልይ ማን ነገረው?

ለቅዱስ ዳዊት ማን ነገረው?

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እንዴት ናችሁ ወዳጆቼ🙏
እንኳን ለታላቁ ዐቢይ ጾም አደረሳችሁ!
ሀላችንንም መፈረም ያለብን 'petition' ነው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞችን የሚደርሰውን ግፍ
ለማስቆም ይህችን ቀላል ነገር እናድርጋት!

"እኔም ሞዐ ተዋሕዶ ነኝ"

https://moaorthodox.com/home/
++ ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ++

ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ፊት በዚያች ምሽት በጭንቀት ቆመዋል፡፡ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሠጠኛል ብሎ ነግሯቸዋል፡፡ ስለዚህ ተጨንቀዋል፡፡ ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? እያሉ ዐሥሩ ደቀ መዛሙርት ተራ በተራ ጠየቁት፡፡

የቀሩት ሊሸጠው ተስማምቶ የመጣው ይሁዳና ወንጌላዊው ዮሐንስ ናቸው፡፡ ይሁዳ እኔ እሆንን ማለቱ ልቡ እያወቀ ስለነበር ከዐሥሩ ጋር አብረን አንቆጥረውም፡፡ ዮሐንስ ደግሞ ለጌታ ካለው የፍቅር ጥልቀት የተነሣ እኔ እሸጠው ይሆን? የሚል ሥጋት ስላልነበረበት ‘’ጌታ ሆይ አሳልፎ የሚሠጥህ ማነው?’’ አለ እንጂ እኔ እሆንን አላለም፡፡ የሐዋርያቱ የጭንቀት ጥያቄ በማግሥቱ መልስ አግኝቷል፡፡ ሆኖም ይህንን ትሕትና የተሞላ ጥያቄያቸውን ለእኛ ሳይበጅ አይቀርም፡፡

በዙሪያችን ለተደረጉ ፣ ለሚደረጉ ክፉ ነገሮች ሁሉ ምክንያቱ ምንድር ነው? ጥፋቱ የማን ነው? መነሻው ምንድርን ነው? ብንባል ሁላችንም ጣት የምንቀስርበት ሰው አናጣም፡፡
አዳም ዕጸ በለስን ለመብላቱ ‘’ም ክን ያቴ ሔዋን ናት ‘’ አለ
ሔዋን ‘’ዕባብ አሳተኝ ‘ አለች
ዕባብም ጠያቂ ቢያገኝ ሰይጣን ማለቱ አይቀርም ነበር፡፡
አንዳቸውም ‘’ጌታ ሆይ እኔ እሆንን?’’ ማለት አልቻሉም፡፡ እንደ ዳዊት ‘’እኔ መተላለፌን አውቃለሁ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊትህ ነው’’ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ለሚሆኑ ነገሮች ሁሉ የምንከስሰው ሰው አናጣም:: መፍትሔው ግን ራስን ማየት ነው:: "እስመ አዕይንቲሁ ለጠቢብ ዲበ ርእሱ" (የጠቢብ ዓይኖቹ በራሱ ላይ ናቸው) እንዲል

ቅዱሳን በምንም ነገር ራሳቸውን ይወቅሱ ነበር:: በገድላቸው ብዛት በሚጸልዩበት ሥፍራ ዶፍ ዝናብ እየወረደ ሳለ እርሳቸውን እንዳይነካቸው በቆሙበት ሥፍራ እንዳይዘንም ያደረገላቸው ዳግማዊው ኤልያስ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያሉትን እናስታውስ:: በቆሙበት ሥፍራ ዝናም እንዳልዘነመ ሲያዩ "ይህችን መሬት በኃጢአቴ ዝናም አስከለከልኳት" ነበር ያሉት:: ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ማለት ይህም አይደል?

የሙሴ ወንድም አሮን በእስራኤል ግፊት ጣኦት ሠራ፡፡ ከወርቅ አቅልጦ ጥጃ አምላክ አድርጎ ሠራላቸው፡፡ ከሠራ በኋላም መሥዋዕት ለጣኦቱ አቀረበ፡፡
ሙሴ መጥቶ ሲቆጣ ሲያይ ግን አሮን ፈራና በሕዝቡ አሳበበ የራሱን ድርሻ በተመለከተ ግን እንዲህ አለ
‘ወርቅ ሰጡኝ በእሳት ላይ ጣልሁት ይህ ጥጃ ወጣ’ {ዘጸ 32፡24}
ራሱ ከእጃቸው ተቀብሎ በመቅረጫ ቀርጾ የሠራውን ጣኦት ‘ስጥለው ጥጃ ሆነ’ አለ፡፡ ራሱ ሕዝቡን ‘ስድ ለቅቋቸው’ የነበረ በመሆኑ ‘’ጌታ ሆይ እኔ እሆንን?’’ ብሎ ራሱን ሊከስስ ይጠበቅበት ነበር፡፡

በትምህርት ቤት ሕይወታችን የማይረሱ ቀናት ግሬድ የሚለጠፉባቸው ቀናት ናቸው፡፡ ከብዙ የመታወቂያ ቁጥር መካከል ውጤቱን ያየ ተማሪ በዚያ የትምህርት ዓይነት A እንዳገኘ ሲያውቅ ለጓደኞቹ ‘’A አገኘሁ እኮ’’ ይላል፡፡ በተቃራኒው ‘F’ ያገኘ ከሆነ ‘’F ሠጠኝ’’ ይላል እንጂ ‘F አገኘሁ’ አይልም፡፡ A ከሆነ ያገኘው ተማሪው ነው ፤ F ከሆነ ግን በድክመቴ አገኘሁ ከማለት ይልቅ ጥፋቱ የመምህሩ ይሆናል፡፡ ነገሩን አልኩ እንጂ ሀገር ሰላም ብሎ የቆመ በር ጋር ስንጋጭም ‘በሩ መታኝ’ እንጂ መታሁት አንልም፡፡
እናም በሕይወታችን ለሆኑትና ለሚሆኑት ነገሮች ‘ጌታ ሆይ እኔ እሆንን? ማለት ትልቅ ጸሎት ነው፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 20 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ
"አማን ተንስአ ክርስቶስ መድኃኒነ ፡
ክርስቶስ መድኃኒታችን በእውነት ተነስቷል!"
እንኳን አደረሳችሁ🙏
የምትበላውን ስጧት
ማርቆስ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴² ብላቴናይቱም የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረችና ወዲያው ቆማ ተመላለሰች። ወዲያውም ታላቅ መገረም ተገረሙ።
⁴³ ይህንም ማንም እንዳያውቅ አጥብቆ አዞአቸው፦ የምትበላውን ስጡአት አላቸው።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት ያስነሳትን ብላቴና "የምትበላውን ስጧት"
አላቸው! ሌሎች በመነሳቷ ደስታ ውስጥ ሆነው ያላስተዋሉትን ረሐቧን አውቆ የሚያስፈልጋትን ነገራቸው!
ጌታ ሆይ እኛም የምንበላው ያስፈልገናል ...ሰዎች እንዲሰጡን አንፈልግም አንተ ሁሉን ታውቅ አይደል ድጋሚ የማያስርብ የምንበላው ምግብ ያስፈልገናል።
ሌሎች እንደተራብነው የማያውቁት እኛም ያላስተዋነው ጉድለታችንን አንተው ሙላልን ርቦናል የምንበላው ስጠን።
የምንበላው ፍቅር ፣የምንበላው መተሳሰብ፣ የምንበላው ቸርነት የለንም ርቦናል የምንበላውን ከማያልቀው መሶብ በሰፊው መዳፍህ ዘግነህ ስጠን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
                                          25/09/14
                                 @zeboanerges/hana
"ጌታ ሆይ ክርስቲያን አድርገኝ
ክርስቲያን ሆኜ ልኑር
ክርስቲያን ሆኜ ልሙት
ዳግም ልትፈርድ ስትመጣ ክርስቲያን ሆኜ ልገኝ::"

ቅዱስ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
እርሱ ምኞቴ ነው!
ስዕል የመሳል ፍላጎቴ አላስቀምጥ ቢለኝ የገዛሁትን የስዕል መሳያ ይዤ ወደ ቤቴ እየገባሁ አንድ ወዳጄ እንዲህ አለኝ፦
"የያዝሽው ምንድን ነው?"
መለስኩለት"ስዕል መሳያ"
"ክርስቶስን ልትስይ ነው?"አለኝ በለበስኩት ነጠላ መንፈሳዊነቴን አግዝፎ የሚያይ ሰው ስለነበር መሰለኝ ይሄ ሐሳብ የመጣለት እኔም ፈጠን አልኩና"እርሱ ብቻ ነው የሚሳል?" አልኩት
"እርሱን ብቻ ነው የምታውቂ" አለኝ ይሔ ንግግሩ ልቤ ላይ ቀረ
እንዴት አትሉኝም?
ቃለ ምልልሴን ገትቼ መንገዴን ቀጠልኩ በልቤ እንዲህ እያልኩ፦
ወዳጄ አሁን ያልከው ምኞቴ ነው!
እርሱን ብቻ ባውቅ ሌላ ባላውቅ ደስ ይለኝ ነበር።
ሲፈልጉት ቸል የማይል፣ሁሌም አብሮ የሚኖር ወዳጅ፣ምሽግ፣አምባ፣መጠጊያ እርሱን ብቻ ባውቅ ምኞቴ ነው።
ክፉ ቀን ደግ ቀን አይል የዘላለም ወዳጅ፣ የልብ ደስታ እርሱ ብቻ ነውና እርሱን ብቻ ባውቅ ምኞቴ ነው።
ቅዱሳን ያወቁት አውቀው ደስ የተሰኙበት፣ዓለም ላይ የቃረሙትን ምናምንቴ እውቀት ያስናቃቸው እርሱ አይደል?
ወዳጄ ተሳስቶ ነው እርሱን ብቻ ነው ምታውቂ ያለኝ።
እርሱን ብቻ ማወቅ ግን ለእኔ ምኞቴ ነው!
አንድ ጥያቄ አለኝ ለእናንተ!
እግራችን ድጁ ይሔዳል ግን ክርስቶስ ያውቀዋል?
እጃችን እመቱን ይነካል ግን ክርስቶስ ያውቀዋል?
ዐይናሽን ጉልላቱን ይመለከተዋል ግን ክርስቶስን ያውቀዋል?
ልባችንስ?
መልሱን በልባችሁ❤️
ወስብሐት ለእግዘአብሔር🙏
@zeboanerges
23.01.15
2024/05/19 04:36:01
Back to Top
HTML Embed Code: