Telegram Web Link
ባለስልጣኑ በ90 ቀናት በሚከናወነው የንቅናቄ ስራዎች ዕቅድ ላይ ውይይት አደረገ፡፡
(ሰኔ 10 ቀን 2017ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የከተማውን የ90 ቀን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የእቅድ በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ዳዊት ለቀጣይ 90 ቀናት የሚከናወነው እቅድ ዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በዕቅድ ውይይቱ ላይ የባለስልጣኑ ጠቅላላ ካውንስል አባላት የተገኙ ሲሆን
ዕቅዱ የበጎ አድራጎት እና ኢንሼቲቭ ሥራዎች ማጎልበት፣የአቅመ ደካማ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ቤት ማደስ፣ የበጎ አድራጎት ተግባራትን ማከናወን፣ የአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ላይ እምርታ ማምጣት፣የአረንጎዴ አሻራ ሽፋን ማሳደግ፣የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ስራ ማሳደግ እና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዩች ላይ ትኩረት በማድረግ እንደሚተገበር በዕቅዱ ተመላክቷል፡፡
በውይይቱ የተገኙት የስራ ኃላፊዎች እንደገለፁት ከዚህ ቀደም ባለት ተግባራት ላይ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመው በዘንድሮ ዓመትም በልዩ ሁኔታ በትኩረት መሰራት እና ድጋፍ እና ክትትል በማጠናከር ንዑስ እና አብይ ኮሚቴ በማዋቀር እቅዱ በአግባቡ እንዲተገበር መረባረብ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡
በዕለቱ በቀረበው እቅድ ላይ ሠፊ ውይይት አድርገዋል፡፡

#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.tg-me.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
የባለስልጣኑ የአስተዳደር ዘርፍ የፕሮሰስ ካውንስል የአራተኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ፡፡
(ሰኔ 10 ቀን 2017ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የአስተዳደር ዘርፍ የፕሮሰስ ካውንስል የአራተኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ገምግመዋል፡፡በዚህም የስራ ክፍሎቹ የዓመቱን የማጠናቀቂያ ተግባራት እንዲሁም ያጋጠሟቸውን ችግሮች አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡
አቶ ብርሃኑ ተሾመ የባለስልጣኑ አማካሪ እንደገለጹት የስራ ክፍሎቹን በዚህ ልክ ክንውናቸውን መገምገም መቻል ያሉትን ክፍተቶች በማወቅ በቀሪ ጊዜያት ስራዎችን ለማጠናቀቅና ለቀጣይ በጀት ዓመት እቅዶችን ለማስተካከል ይጠቅማል ብለዋል፡፡
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.tg-me.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
በ2017ዓ.ም የትምህርት ዘመን እውቅና ፈቃድ እድሳት ከተሰራላቸው ተቋማት መካከል ከስታንደርድ በታች ከሆኑ የግል ት/ቤት ባለቤቶች ጋር ውይይት ተደረገ፡፡
(ሰኔ 10 ቀን 2017ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2017ዓ.ም የትምህርት ዘመን እውቅና ፈቃድ እድሳት ከተሰራላቸው ተቋማት መካከል ከስታንደርድ በታች ከሆኑ የግል ት/ቤት ባለቤቶች/ ተወካዮች ጋር ውይይት ተደረገ፡፡
አቶ ያሬድ ካሳ የበላስልጣኑ የእውቅና ፍቃድ እድሳት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡ ሲሆን የውይይቱን አላማ ሲጠቅሱ በ2017ዓ.ም የትምህርት ዘመን እውቅና ፈቃድ እድሳት ከተሰራላቸው ተቋማት መካከል ከስታንደርድ በታች የሆኑ 66 ከቅድመ አንደኛ እስከ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ የሚገኙ የትምህርት ተቋማት ሲሆኑ አነስተኛ ግብአት ማሟላት የሚጠበቅባቸው ተቋማት በማስጠንቀቂያ እንዲቀጥሉ፣ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን እንዲቀበሉ እና እስከ ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም ድረስ ግብአቶችን በማሟላት ወደ ስታንዳርዱ እንዲገቡ እና ለስታንዳርዱ ዝግጁ በመሆን እንዲመዘኑ ብቁ ሆነው ሲገኙም እንዲቀጥሉ ለማሳሰብ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና የጥራት ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት የትምህርት ስራ የተናጠል ሥራ አለመሆኑን ጠቅሰው በእውቀት በክህሎትና አመለካከት የታነጸ ትውልድ ሃገርን የሚያሻግር ነው፤በመሆኑም ብቃት ያለው ትውልድ ለማፍራት ስታንዳርዱን ያሟላ ተቋም መሆን የግድ እንደሆነ የጠቀሱ ሲሆን፤
ተቋማት ለ2018ዓ.ም የትምህርት ዘመን በማስጠንቀቂያ እንዲቀጥሉ ሲደረግ የትውልዱን፣የማህበረሰቡን፣የትምህርት ተቋማቱንም ጭምር ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የትምህርት ተቋማቱን ከመዝጋት በማስጠንቀቂያ እንድትቀጥሉ ተደርጓል፤ሆኖም በቀጣይ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጎደሉትን ግብአቶች በማሟላት ወደ ስታንዳርዱ ካልመጡ ተቋማቱ እንደሚዘጉ ገልጸው ያልተለወጡና ወደ ስታንዳርዱ ያልመጡ ተቋማትን ለማህበረሰቡ ባለሰልጣኑ እንደሚያሳውቅ አስገንዝበዋል፡፡

አቶ አለልኝ ወንዴ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና የምዘና ዘርፍ ሃላፊ በኩላቸው እንደገለጹት መድረኩ መዘጋጀቱ እርስ በእርስ በመመካከር እና በመገምገም ነባራዊ ሁኔታዎችን በማየት እድሉ እንዲሰጣቸው ሲወሰን ለትምህርት ጥራት ትኩረት በመስጠት ስታንዳርዱን የማስጠበቅ ስራ ሰርተው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ እድሉን በመጠቀም አቅማችሁን በማሰባሰብ ዝግጅት እንድታደርጉና አንድታስተካክሉ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡በመሆኑም ይህ የተሰጠው እድል ማህበረሰቡን እንዲጠቅም በማሰብ የተወሰነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት የትምህርት ቤት ባለቤቶችና ተወካዮች እንደተናገሩት እድሉ መሰጠቱ ጥሩ መሆኑን ገልጸው በተሰጠው ጊዜ ስታንዳርዱን ለማሟላት ጠንክረው እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.tg-me.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
በ90 ቀናት ለሚከናወነው የንቅናቄ ስራዎች እቅድ ላይ የባለስልጣኑ አመራሮችና የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ተወያዩ፡፡
(ሰኔ 10 ቀን 2017ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የእቅድ በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ነብዩ ዳዊት ለቀጣይ 90ቀናት የሚከናወነው እቅድ ዝርዝር አቅርበዋል፡፡
ዕቅዱ በ90ቀናት ውስጥ የሚተገበሩ የተለያዩ ግቦችን የያዘ እና ተግባራቱ የሚተገበሩበት ጊዜ እና ዝርዝር አፈጻጸሞችን የያዘ ሲሆን የ90 ቀናቱ ግቦች የተሳኩ እንዲሆን አብይ ኮሚቴ እና ንዑስ ኮሚቴዎች ተዋቅረዋል፡፡
በእቅዱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሚተገበሩትን ግቦች ካስኬድ በማድረግ እንዲሰሩ እና ለተግባራቱ የሚያስፈልጉትን ሀብቶች እንዲያሰባስቡ የሚያመላክት ነው፡፡
በውይይቱ የተገኙት የስራ ኃላፊዎች እንደገለፁት ተግባራቱ የሚከናወኑት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆኑ በተለይ የሀብት ማሰባሰብ የሚያስፈልጋቸው ግቦች ከወዲሁ ከትምህርት ተቋማት ጋር በመወያየት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
እንዲሁም እቅዱን በተቀመጠው ጊዜ እና ጥራት ተጠያቂነት በሠፈነበት አሠራርን በመፍጠር በቁርጠኝነት በትብብር መንፈስ ከተሠራ እቅዱ መሳካት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ላይ በቀረበው እቅድ ላይ ሃሳብ እና አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡

#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.tg-me.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
2025/07/13 20:27:14
Back to Top
HTML Embed Code: