Telegram Web Link
የህዝባችንን ጥያቄዎች የምንመልሰዉ የሚታዩ፣ የሚጨበጡ እና ዘላቂ መፍትሄዎች ላይ በማተኮር ነዉ።

ዛሬ ጠዋት ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የኢንዱስትሪ ክላስተር ጎብኝተናል። 93 ሄክተር መሬት በመመደብ በ7 ቢሊዮን ብር ወጪ ግንባታው እየተከናወነ ያለዉ ይህ የኢንዱስትሪ መንደር የመጀመሪዉ ምዕራፍ ከ120 በላይ ሼዶች ያሉት ሲሆን ለብረታብረት ሥራ፣ ለእንጨት ውጤቶች፤ ለጨርቃ ጨርቅ ፣ ለፕላስቲክ እና ለኬሚካል ማምረቻነት፣ የምርት ማሳያ እና መሸጫ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ናቸዉ።

ይህ ግዙፍ የኢንዱስትሪ መንደር ግንባታ፤ የመስሪያ ቦታ ችግርን ከማቃለል ባሻገር የማኑፋክቸሪንግ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመፍታት፣ ሰፊ የስራ ዕድልን ለመፍጠር የኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥ ረገድ ሚናው የጎላ ነው። የግንባታው ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ምርቶች የሚሆኑ ሼዶችን የያዘ ነው።

ይህ የኢንዱስትሪ መንደር ከዚህ ቀደም ከነበሩት ሼዶች በተለየ ሁኔታ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግብአቶችን እንዲጠቀም ተደርጎ እየተገነባ ነዉ።
በተጨማሪም ከቦሌ ኤርፖርት በጥቂት ደቂቃ መድረስ የሚያስችል አዲሱ የአቃቂ ቦሌ ካርጎ መንገድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ምርት ማጓጓዝን ታሳቢ ያደረገ እና ስትራቴጂክ ስፍራ ላይ የሚገኝ ፕሮጀክት ነው።

አዲስ አበባን የኢትዮዽያ ብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን !

ፈጣሪ ኢትዮጵያውያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
2025/06/28 18:15:34
Back to Top
HTML Embed Code: