Telegram Web Link
በትምህርት አገልግሎት የዋጋ ጭማሪ ክፍያ ላይ ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር ውይይት አደረጉ፡፡፡
(ሰኔ 15 ቀን 2017ዓ.ም) ከወላጆች ጋር ውይይት ካደረጉ ት/ቤቶች መካከል በዛሬው ዕለት በጉለሌ ክ/ከተማ በአሚጎንያ ት/ቤት በመገኘት ውይይቱን የተከታተልን ሲሆን ት/ቤቱ የክፍያ ጭማሪ ያደረገበትን ፕሮፖዛል እና የክፍያ መጠኑን ለወላጆች በዝርዝር ያቀረበ ሲሆን ወላጆችም ሀሳባቸውን በሰፊው አንስተው ተወያይተዋል፡፡

በዚህም ት/ቤቱ በቀጣይ ሶስት አመታት ጭማሪ የሚያደርግበትን ምክንያት ሲያስረዳ ለግብዓት ማሟያ፣የትምህርት ጥራት ስታንዳርዱን ለማጠበቅ፣ስቴሽሪ እቃዎችን ለማሟላት፣አስተዳደራዊ ወጪዎችን ለመሸፈን፣የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን ለመጠቀም እንዲሁም በዋናነት መምህራን ተረጋግተው ማስተማር እንዲችሉ የደመወዝ ጭማሪ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ወላጆች በቀረበው የመነሻ ሃሳብና በምክንያቱ ዙሪያ እንደተናገሩት ከሆነ ጭማሪው የወላጁንም አቅም ግምት ውሰጥ በማስገባት እንዲሆን ት/ቤቱም ቀጣይነት እንዲኖረው በሚያስችል መልኩ እንዲሆን ሃሳብ የሰጡ ሲሆን ከት/ቤቱ እና ከወላጅ በተነሱት ሃሳቦች ሰፊ ውይይትና ክርክር በማድረግ ድምጽ እንዲሰጥ ከተደረገ በኋላ መግባባት ላይ በመድረስ ውይይታቸውን ፈጽመዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ያገኘናቸው አቶ ፍቅሩ ገቢሳ በትምርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የጉለሌ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ እንደገለጹት የትምህርት አገልግሎት ክፍያ አሠራር ሥርዓት ደንብ ቁጥር 194/2017 በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ መጽደቁ ት/ቤቶች የዋጋ ጭማሪ ሲያደርጉ ደንቡን ተከትለው ጭማሪ እንዲያደርጉ እንዲሁም የዋጋ ጭማሪው በደረጃ በመሆኑ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሚያግዝ ይሆናል ብለዋል፡፡
አቶ ያሬድ ካሳ የባለስልጣኑ የእውቅና ፍቃድ እድሳት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላችው እንደተናገሩት ለትምህርት ጥራት ግብዓት አንዱ መነሻ ነው ግብአቱን ተጠቅሞ ወደ ሂደት በመቀየር ውጤትን በማምጣት የተሻለ ጥራት ያለው ትምህርት እንዲኖር ያስችላል፤ በመሆኑም ወላጆችና ት/ቤቱ በመስማማት የሚያደርጉት የዋጋ ጭማሪ ት/ቤቱ በአግባቡ በስራ ላይ ማዋሉን ባለስልጣኑ ክትትል እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በተገኘንበት አሚጎንያ ት/ቤት የባለስልጣኑ እና የቅ/ጽ/ቤት አመራሮች፣መድረኩን በታዛቢነት የሚከታተሉ ተወካዮች እንዲሁም የወተመህ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን በቀጣይ ሳምንትም ውይይቱ ባልተካሄደባቸው በሌሎች ት/ቤቶች ላይ ውይይት እንደሚከናወን ታውቋል፡፡

#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.tg-me.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
ባለስልጣኑ የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የማነቃቂያና የእውቀት ሽግግር መርሃ-ግብር አካሄደ፡፡
(ሰኔ 16 ቀን 2017ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አመራሮችና አጠቃላይ ሰራተኞች በተገኙበት የወርቃማ ሰኞ ማለዳ የማነቃቂያ የእውቀት ሽግግር መርሃ-ግብር ተከናወነ፡፡

በዛሬው የወርቃማ ሰኞ ማለዳ መርሃ-ግብር ላይ አቶ ነብዩ ዳዊት የባለስልጣኑ የእቅድና በጀት ዝግጅትና ክትትል ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የ90 ቀናት የንቅናቄ ተግባራትን እቅድ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡በዚህም የበጎ አድራጎት የኢኒሼቲቭ፣የአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር፣የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ማጠቃለያ ግምገማ፣የአረንጓዴ አሻራ ሽፋን ማሳደግ፣ት/ት ለትውልድ ንቅናቄ፣ የፋይዳ ምዝገባ እና ኢትዮ ኮደርስ፣ተግባራትን በህዝብ ግንኙነት አግባብ ሽፋን መስጠት በሚሉ ሰባት ግቦች ያሉትና የአፈጻጸም አቅጣጫ እንዲሁም ስራውን የሚያከናውኑ ኮሚቴዎች የተዋቀሩበትን ዝርዝር የያዘ እቅድ ያቀረቡ ሲሆን ውይይትም ተደርጎበታል፡፡

አቶ ኢዘዲን ሙስባህ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ በመርሃ- ግብሩ ላይ እንደገለጹት በቀረበው በ90 ቀናት እቅድ የክረምት ዘላቂ ስራችንን አጠናክረን የአሰራር ግልጽነትን በመፍጠር፣ስራን ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ በማከናወንና የእቅዱ አካል ሆነን ከለውጥ ጋር በመጓዝ ለአፈጻጸማችን ውጤታማነት መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
https://web.facebook.com/photo/?fbid=1268190525316633&set=a.479956377473389 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በFM 97.1 የሚደረገውን ወቅታዊ የቀጥታ ስርጭት እንድትከታተሉ ጋብዘናችኋል፡፡
የባለስልጣኑ ስትራቴጂክ ካውንስል እና የዘጠኙ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች በ2018 ዓ.ም የበጀት እቅድ ላይ ውይይት አደረጉ፡፡
(ሰኔ 17 ቀን 2017 ዓ.ም) በትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ስትራቴጂክ ካውንስል አባላትና የዘጠኙ ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች በ2018 ዓ.ም የበጀት እቅድ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
በዚህም በ2018 የስራ ዘመን የሚኖረውን በጀት የጋራ በማድረግና ለታለመለት አላማ አሰራሩን ጠብቆ ኖርምን መሰረት በማድረግ በቁጠባ መጠቀም አስፈላጊ መሆኑም በመተማመን ውሳኔ አሳልፈዋል፡፡
ከዚህም ሌላ በመድረኩ በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ የሚያደርጉ የትምህርት ተቋማት ከወላጆች ጋር ባለፈው ቅዳሜና እሁድ ያደረጉትን ውይይት አስመልክቶ የቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ሂደቱን አስመልክቶ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በዚህም ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ ቅዳሜና እሁድ ውይይት የሚያደርጉ የትምህርት ተቋማትና ወላጆች የባለስልጣኑ ታዛቢ ተወካዮች በሁሉም ተቋማት ላይ በመገኘት ግልጽነትን በመፍጠር ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸው ተገልጿል፡፡

#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.tg-me.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
2025/06/28 12:50:12
Back to Top
HTML Embed Code: