Telegram Web Link
እንኳን ለ35ኛው የአፍሪካ ሕፃናት ቀን በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
የነገ ሃገር ተረካቢ ሕፃናት እናንተ የመጪው ዘመን ተስፋዎች ሁሉም ሥራችን የናንተን የነገ ህይወት መንገድ ለማቅናት የሚደረግ ነው፣የነገ እድገታችሁ እዳ የሌለበት ነፃ ለትውልድ የምትተርፉ እንዲሆን ከእቅድ እስከ እለት እለት ትግበራችን ለእናንተ እንሰራለን፡፡ለዚህ ነው የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ያስፈለገን ፡፡

የቀዳማይ ልጅነት ሣምንት እና በአፍሪካ ለ35ኛ እንደ ሃገር ለ34ኛው ጊዜ"የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ለማነጽ ሕፃናት ተኮር ተግባራትን እናከናውን!" በሚል መሪ ቃል ሲከበር ዛሬ አብሬያችሁ ደስታችሁን ስካፈል አሁንም ቀጣይ ስራዎች እንዳሉብን አደራችንን ሳንዘነጋ ነው፡፡

መንግስት እና ማህበረሰቡ እናንተ ሕፃናት ለሃገር ያላችሁ ተስፋ እውን እንዲሆን ከማኅፀን ጀምሮ በሚደረግ እንክብካቤ ፣በአልሚ ምግብ ፣በጨዋታ መማር፣ በትምህርት ቤት ምገባ ፣በቤተሰባዊ ትስስር መልካም እድገት እንዲኖራችሁ ፣ሁለንተናዊ መብቶቻችሁ እንዲከበሩ፣ በአገራዊ ግንባታ ፣ልማቶችና እድገቶች ውስጥ የእናንተ ሕፃናት ተሳትፎ እንዲረጋገጥ፣የሕፃናት ፓርላማ እንዲጠናከርና ዴሞክራሲያዊ አሠራር ልምምድ እንዲኖራችሁ እና ለሃገር ተስፋ ያለው ትውልድ እንድትሆኑ መስራታችንን እንቀጥላለን፡፡
የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ እንደሚባለው ዛሬ የነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ እንድትሆኑ አድርገን እናሳድጋችኋለን፤አገር ተረካቢ ትውልድም ሆናችሁ ትሰራላችሁ፡፡
ከተማችሁ ሀገራችሁ ትወዳችኋለች፡፡ሁሌም ምርጥ ምርጡን ለናንተ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
2025/07/13 20:24:25
Back to Top
HTML Embed Code: