የህዝባችንን ጥያቄዎች የምንመልሰዉ የሚታዩ፣ የሚጨበጡ እና ዘላቂ መፍትሄዎች ላይ በማተኮር ነዉ።

ዛሬ ጠዋት ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የኢንዱስትሪ ክላስተር ጎብኝተናል። 93 ሄክተር መሬት በመመደብ በ7 ቢሊዮን ብር ወጪ ግንባታው እየተከናወነ ያለዉ ይህ የኢንዱስትሪ መንደር የመጀመሪዉ ምዕራፍ ከ120 በላይ ሼዶች ያሉት ሲሆን ለብረታብረት ሥራ፣ ለእንጨት ውጤቶች፤ ለጨርቃ ጨርቅ ፣ ለፕላስቲክ እና ለኬሚካል ማምረቻነት፣ የምርት ማሳያ እና መሸጫ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ናቸዉ።

ይህ ግዙፍ የኢንዱስትሪ መንደር ግንባታ፤ የመስሪያ ቦታ ችግርን ከማቃለል ባሻገር የማኑፋክቸሪንግ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመፍታት፣ ሰፊ የስራ ዕድልን ለመፍጠር የኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥ ረገድ ሚናው የጎላ ነው። የግንባታው ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ምርቶች የሚሆኑ ሼዶችን የያዘ ነው።

ይህ የኢንዱስትሪ መንደር ከዚህ ቀደም ከነበሩት ሼዶች በተለየ ሁኔታ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን እና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግብአቶችን እንዲጠቀም ተደርጎ እየተገነባ ነዉ።
በተጨማሪም ከቦሌ ኤርፖርት በጥቂት ደቂቃ መድረስ የሚያስችል አዲሱ የአቃቂ ቦሌ ካርጎ መንገድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ምርት ማጓጓዝን ታሳቢ ያደረገ እና ስትራቴጂክ ስፍራ ላይ የሚገኝ ፕሮጀክት ነው።

አዲስ አበባን የኢትዮዽያ ብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋታለን !

ፈጣሪ ኢትዮጵያውያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ቅ/ጽ/ቤቱ የአገልግሎት አሰጣጥ የተገልጋይ እርካታ ዳሰሳ ውጤት፣ የ2017 በጀት ዓመት የ12 ወራት እቅድና የቅንጅዊ ስራዎች አፈፃጸም ግምገማ ለተገልጋዮችና ለባለድርሻ አካላት አቀረበ፡፡
(ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የየካ ቅ/ጽ/ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ፣ የተገልጋይ እርካታ ዳሰሳ ውጤት ፣ የ2017 በጀት ዓመት የ12 ወራት እቅድና የቅንጅዊ ስራዎች አፈፃጸም ግምገማ ለተገልጋዮችና ለባለድርሻ አካላት አቀረበ፡፡
አቶ ዘመነ አብዩ የቅ/ጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ በመርሃ-ግብሩ ላይ እንደገለጹት የተሻለ ውጤት የምናስመዘግበው ህጉን ተከትለን ህጋዊነታችንን እያከበርን ስንሰራ ነው ህጋዊነት ዋስትና አለው ስለዚህ ህግ በማክበር የጋራ የትስስር ስራዎችን የበለጠ አጠናክርን የትምህርት ጥራትን አብረን የጋራ ሀላፊነቶቻችንን በመወጣት የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ እንፍጠር ብለዋል፡፡
ወ/ሮ ሰላማዊት አለማየሁ የቅ/ጽ/ቤቱ የፋይናንስ ባለሙያ ሰነዱን ያቀረቡ ሲሆን የ2017 ዓ.ም የ2ኛ በጀት ዓመት የውጪ ተገልጋዮች እርካታ ዳሰሳ ጥናት ሰነድ፣የ2017 በጀት ዓመት የ12 ወራት ቁልፍ የግብ አፈጻጸሞች (KPI) መልካም አስተዳደር ማስፈን፣ጸረ-ሌብነትና ብልሹ አሰራር፣ቅንጅታዊ ስራዎች አፈጻጸም፣ያጋጠሙ ችግሮችና የተፈቱበት መንገድ የመፍትሄ እርምጃ ለተገልጋይና ለባለድርሻ አካላት በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት በማድረግ ሃሳብና አስተያየት ተሠጥቶበታል፡፡
በ2018 የትምህርት ዘመን ማስተማር የማይችሉ ተቋማትን ስለማሳወቅ
(ሰኔ 18 ቀን 2017 ዓ.ም)
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2018 የትምህርት ዘመን ማስተማር የማይችሉና እውቅናቸው የተሰረዘባቸውን የትምህርት ተቋማት ሲያሳውቅ በ2016 ማጠቃለያ ላይ በተደረገው የእድሳት ፍቃድ ምዘና ለ2017 የትምህርት ዘመን ካሳዩት ዝቅተኛ ውጤት መሻሻል እንዲያደርጉ እስከ 2017 ታህሳስ ድረስ ዝግጅት እንዲያደርጉ የጊዜ ገደብ ተሰጥቷቸው በ2017 የትምህርት ዘመን ላይ በማስጠንቀቂያ እንዲያስተምሩ ጊዜ ቢሰጣቸውም በታህሳስ 2017 በተደረገ የእድሳት ፍቃድ ምዘና ውጤታቸው መሻሻል ባለማሳየቱና ዝቅተኛና ከደረጃ በታች መሆኑ የተረጋገጠና የጸደቀ ስለሆነ ለ2018 የት/ት ዘመን ማስተማር የማይችሉ መሆኑን እያሳወቅን የትምህርት ማህበረሰቡ እና ወላጅ ይህን በማወቅ የቅድመ ዝግጅት ተግባርን እንድታከናውኑ እናሳሰባለን፡፡
#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.tg-me.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
ባለስልጣኑ 2017 በጀት ዓመት የጥሬ ገንዘብና የንብረት ቆጠራን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
(ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የኦዲት ዳይሬክቶሬት የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የጥሬ ገንዘብ እና የንብረት ቆጠራን በተመለከተ የማዕከል እና ለዘጠኙ ቅ/ጽ/ቤቶች ለቆጠራ ኮሚቴ እና አስቆጣሪዎች እንዲሁም ለስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክተሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
አቶ ሰለሞን አለማየሁ የባለስልጣኑ አማካሪ እንደገለጹት ዘርፉ ሙያዊ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው እንደመሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው አስፈላጊ እና ወቅታዊ መሆኑን ገልጸው ስራን በአግባቡ ለማከናወን እንዴት ይሰራል? በምን አግባብ ይሰራል? ከባለፉት አመታት የተለዩ ጉዳዮች ምንድን ናቸው? የሚሉትን ነገሮች በስልጠና ማስደገፍ አስፈላጊ ነው ያሉ ሲሆን በዚህም መሰረት ተግባራቶቻችንን ወጥ በሆነ መልኩ ማከናወን ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ወ/ሮ አለም ታደገ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የዘመናዊ የውስጥ ኦዲት ማህበራዊ ቡድን ዘርፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን አጠቃላይ የቆጠራ ስራ በሚመለከት ከኦዲተር ምን ይጠበቃል፣የቆጠራ ቡድኑ አባላት የስራ ተግባር፣በስቶክ ቆጠራ ወቅት የመ/ቤቱ ሀላፊነት፣የጥሬ ገንዘብ ቆጠራ አስፈላጊነት እና መሰል ተግባራት እንዲሁም አጠቃላይ የበጀት ዓመቱን የቆጠራ አጠቃላይ ሂደት በዝርዝር አስረድተዋል፡፡
ወ/ሮ ትግስት ጌታነህ የባለስልጣኑ የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደገለፁት ለስራው ወጥነት እና ቀልጣፋነት እንዲሁም አጠቃላይ ሙያዊ ግንዛቤ ለማሻሻል መድረኩ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

#ፌስቡክ;https://www.facebook.com/AA-Educational-Training-Quality-Occ-Competency-Assurance-Authority-100864428091362/?__tn__=-UC*F
#ድረ_ገጽ; educoc.gov.et
#ቴሌግራም https://www.tg-me.com/AAEQOCAA
#ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@educationtraning2?_t=ZM-8u2f6smztvr&_r=1
#ነጻ_የጥቆማ_የስልክ_መስመር_9302
2025/06/27 10:34:05
Back to Top
HTML Embed Code: