Telegram Web Link
አይኑን ሰ'ቶ ሄደ
በልቡ ብርሃን፣ከሰማይ ሊገባ:
አይኑን ሰ'ቶ ሄደ፣ሆደ ቡቡው ባባ።
ከሞቱስ እንዲህ ነው፣በደንብ ተዘጋጅቶ፡
እስከ ሒወት ፍፃሜ፣በጎ ስራ ሰርቶ።

እርግጥ፦
የኪራይ ቤታችን፣ይህች ከንቱ አለም፡
በብልጭልጭ አስራ፣መኖር ብታጓጓም፡
የሰማዩን ሒወት፣ፈፅሞ አንዘንጋ፡
ለምድሩ ስንሮጥ፣ከላይ እንዳይዘጋ።

እናም፦

ነገ መኖራችን፣ከዛሬ ተሻግረን፡
ዋስትና የለንም፣ሸክላ ሒወት ይዘን፡
የበደልነው ካለ፣ዛሬውኑ ይቅርታ፡
ሸፍጥ ቂም አሻጥር፣በጊዜ ይገታ፡
ለወደድናቸውም፣ፍቅራችን እንግለጥ፡
ዛሬ ነገ ስንል፣ሒወት እንዳታመልጥ፡
በየ'ለት ኑሯችን፣ሞታችን እናስብ፡
ከክፉ ነገሮች እንድንሰበሰብ፡፡

ድንቅ የጥበብ ሰው አ'ተናል።ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን እመኛለው።

(አድናቆት ክፍሌ የብርቱካን)
https://youtu.be/e-IepEfpmu8
በድንግልና፣ከቅድስት ማርያም፡
ተወልዶ ጌታ፣ወለደን ዳግም።
ከመላእክት ጋር፣በአንድ ማህበር፡
አብረን እንድንል፣ስብሀት ለእግዚአብሔር ፡
ዕድሉን ሰጠን፣ሰው ሆኖ ጌታ፡
ምን ይሆን መልሱ?፣ለዚህ ውለታ።

ከዘመን አስቀድሞ የነበረ፣ተወልዶ በጎል፡
እርቅ ፈፀመ፣በእግዚአብሔር እና በሰው መሀከል።
ድቅድቁም ጠፋ፣ሞላ ብርሃን፡
ልጅ ሆኖ ኢየሱስ፣ስለኛ መዳን።🙏

እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በሠላም አደረሳችሁ።🙏

@Adnakotkifle
ለኔ ያለህ ፍቅር፣ምን ያህል ነው ብለሽ፣
ችዬ ላልመልሰው፣አጠይቂኝ 'ባክሽ።
"በግምት ንገረኝ፣እባክህ" ካልሽ ግን፡
እወድሻለሁኝ፣በሚወዱኝ ሴቶች፣በቁጥራቸው መጠን።😄

ታድለሽ።😜
https://youtu.be/adubY9oUb2I
ለፍርድ ትቅረብልኝ።

ይህች በምስሉ ላይ የምትመለከቷት በእምነት ትባላላች፤እህቴ ናት።ዛሬ መታመሜን ምክንያት በማድረግ፤ዜሮ አምፖል የምታክል መቀመጫዬ ላይ ፖል የሚያክል መርፌ ወጋችኝ።😔አስቡት ኮትኩቼ ያሳደኳት እህቴ፣በእኔ ታላቅ ወንድሟ መቀመጫ ላይ መርፌ ስታነሳ😢
በእርግጥ መርፌው ይሁን፣አልያም እሷ እዚህ ደርሳ ማየቴ አስደስቶኝ ባለውቅም አሁን በጎ ነኝ።በጎ ብሆንም ግን ከተጠያቂነት አትድኚም።😳

https://youtu.be/adubY9oUb2I
ዩቲዩብ ገና የከፈተኩ ሰሞን፤አንድ ቪዲዮ ለቅና 'mother' ጋ ደውዬ ለቅቂያለው እዩ።😂 አንድ ሁለት 'view' ለቀም፤በዛ ላሉ ጓደኞቼ ቪዲዮን ሼር አድርጊ ጥቂት ቪዮች ሸመት፤በየሰከንዱ ስንት view ደረሰ ብዬ ለማየት ስገባ 5 በጣም ከበዛ ሰባት።😂ከዛ ማሰብ ጀምራለው "ለእናቴ ልኪያለው ስለዚህ ከሷ ቢሮ ቢያንስ 3 view አለኝ፣የራሴ አንድ አለ።ስለዚህ ከጓደኞቼ መሀል ያላደረገ አለ ማለት።ቆይ ላግኘው ብቻ "እላለው።
ደ'ሞ ቆየት እልና "6ወር ስለ ዩቲዩብ አጥንቶ ከገባ ሰው ይሄ አይጠበቅም፤በዛ ላይ አሁን ትልቅ ቦታ የደረሱ የሀገር ውስጥም የሀገር ውጪም ዩቲዩበሮች መነሻቸው ላይ የነበረውን አስቂኝ ወጣውረዶች አይተሃል ፤"ስለዚህ ብሮ ዳይ ወደ ስራ" ብዬ እራሴን አነቃዋለው።
"ህዝቡ ትምህርት ውይም ስድብ የለሌለው መዝናኛ አይፈልግም፤ከቻልክ እንደውም ዜና ብትጨምርበት በአንዴ ነበር ቻናልህ የሚተኮሰው የሚሉ ሀሳቦች መነቃቃቴን ሊገዳደሩ ቢሞክሩም፤እኔ ብሶት የወለደኝ የ'Adnakot Tube' ባለቤት ግን ጥቂት ሰብስክራይበሮቼን እና እፍ ቢሏት የምጠፋ አምስት ቪዩዌን ይዤ ቀጠልኩ።😄

ይሄው አሁን በቀን ቢያንስ 10 ሰው ፈልጎ ሁለት ሰው ጋብዤው ይገባል።ከታች እንደምትመለከቱት 785 ሰአት የታየ 9.8 ከ view ያገኘ፣343 subscriber ያሰገኘ፣አሁንም እየታየ ያለ ቪዲዮ ማሞረት ጀምሪያለው።"ብርቅ ነው እንዴ እንዳትሉ"😄"ትምህርታዊ ቪዲዮ ለቆ ብዙ view ማግኘት ብርቅ ነው።👌ይልቅ እናንተም በሊንኩ በመግባት የድርሻችሁን እውቀት ተቋደሱ።ቪዲዮ ለሚያገዛቸውም ወዳጆቻችሁ share አድርጉ።👌

በመጨረሻም ቻናሌን የከፈትኩት ሰሞን ቪዲዮ ላይ comment ሲፃፍ ዩቲዩብ ቪዲዮውን እንደሚያሰራጨው ስለማውቅ አዲስ ቪዲዮ ስለቅ በእህቴ አካውንት ገባና"በርታ ወንድማቸን"ብዬ እንደምፅፍ ብነገራችሁ ስለምትስቁብኝ ለሌላ ቀን ላቆየው።😂

ይህን ሁሉ ሀተታ የምነግራችሁ እኮ ላነቃቃችሁ ወይም ልጎርር አይደለም"ቶንሲሌን ስላመመኝ ዛሬ ቪዲዮ መስራት ስለማልችል ቢያንስ ቻናሌን ላልተቀላቀላችሁ እንድትቀላቀሉ በማስታውስ ቻናሌን በምንም ሁኔታ ውስጥ አብሪያት እንዳለው ለማስታወስ ነው።😄
ፍሬን(ኢትዮ ቴሌኮም) ከሳፋሪ ሲምካርድ ስትገዛ ሳያት ኢንተርኔት ቶሎ እንደማይለቀቅ ገባኝ።😜7 አይነት ቪፒኤን እንዳስጫነችም ሰምቻለው።ያው በህልሜ ስለነበር ማን እንደነገረኝ ባላስታውስም።😄
ዋናው ጉዳይ Adnakot Tube ሞኒታይዝ ሆኗል።ኢንተርኔት ሲለቀቅ ላበስራችሁ ባስብም፤በቅርብ የሚለቀቅ ስላልመሰለኝ ላላችሁት ላሳውቃችሁ ብዬ ነው።
እስኪ ገባ በሉና በvpn ሀገር እየቀያየራችሁ አንዴ አሜሪካ፣ፈረንሳይ፣ኢራቅ...እየሆናችሁ ባለኝ 0.000001 ዳላር😜 ላይ .000002 ጨምሩበት።
ዩቱቡ ላይም ከየት ሀገር እንዳያችሁኝ ኮመንት ፃፉልኝ።

ሼር
https://youtu.be/AqU0gs7sU3Y
ባያነሳ ጋሻ፣ሚኒሊክ ተነስቶ፣
'Leonardo' ነበርኩ፣አድናቆት ተረስቶ፡፡
ባትዘምት ጣይቱ፣ተነስታ በወኔ፡
እምነት ባህል አልባ፣ከነቱ ነበርኩ እኔ፡፡
ጂጂ ድምፅ ታጥቃ፣ባተነሳ 'ማይክ'፡
ማን ያስረዳኝ ነበር?፣አደዋን በዚህ ልክ፡፡
ቴዲስ ባይጋራ፣ማይኩን ከጂጂ፡
ጥቁሩን ሰው ለአለም፣ማን ነበር? አስረጂ፡፡?
ጥንት እናት አባቶች፣ባይሰጡኝ ነፃ ሀገር፡
በ'ኢታሊክ' ነበር፣ግጥሜ ሚደረደር፡፡😄

(አድናቆት ክፍሌ የብርቱካን)

@Adnakotkifle
በሰማያዊው ቤት፣ለሚገኘው ዋጋ፡
ምድራዊው በር፣መስኮት በአንድነት ተዘጋ።🙏

ትልቅ አክብሮት።🙏
@Adnakotkifle
ወንጀለኛ?

ምን ሰረቼ ሲል ደነገጥኩ፡
የማረባ ነኝ ሲል አፈርኩ።
ከደካማዎች ጋር እየዋለ፡
ለነሱ ደስታ እየታገለ፡
ደካማ ሰው ነኝ፣ተኝቼ 'ምውል፡
አታጨብጭቡ ለኔ ክብር ሲል፡
ደነገጥኩ፡
እራሴን ታዘብኩ።

ለተቸገረ ሰው፣በአመት አንድ ጊዜ እጄ ቢዘረጋ፡
አይኖቼ ሚዋትተቱ፣ካሜራ ፍለጋ፡
ይህንን ሰው ሳየው፣ተዋጥኩኝ በሀፍረት፡
ለታይታ መስጠቴን፣ዞሬ ስመለከት።
ደነገጥኩ፡
እራሴን ታዘብኩ።

አረጋውያንን ሰብስቦ፡
አሳክሞ፣አጣጥቦ፡፡
ሐይማኖት ዘር ሳይል፣በአንድ እያኖረ፡
ሕይወቱን በፍቃድ፣ለሌሎች የቸረ፡
ወንጀለኛ ነኝ ሲል፣ሀጥያተኛ ነኝ ሲል፡
ብዙ መልዕክት አለው፣ልብ ያለው ልብ ይበል።

በዘር ተከፋፍለን ጥላቻ፣ምንዘራ፡
ሌላን ለማንቋሸሽ፣ሌት ተቀን ምንሰራ።
ግፍን የምንፈፅም፣ሕይወት የምንቀማ፡
ወንጀለኛ ነኝ ሲል፣ይህን ሰው ስንሰማ፡
ግድ ይለም ለአንድ አፍታ፣ቆም ብለን እናስብ፡
ወንጀላችን አውቀን፣ከክፉ ተግባራት እንድንሰበሰብ።🙏

ቢንያም በለጠ(የክብር ዶ/ር) 🙏🙏🙏🙏

(አድናቆት ክፍሌ የብርቱካን)
@Adnakotkifle
የገጣሚዎችን ቀን በማስመልከት ከምወዳችሁ እና ከማደንቃችው ውስጥ ከብዙ በጥቂቱ፦
1.በረከት በላይነህ(አመዶ)
2.ጌትነት እንየው
3.ኤፍሬም ስዩም
4.አልያስ ሽታሁን
5.አስታወሰኝ ረጋሳ
6.ምልዕቲ ኪሮስ
7.በላይ በቀለ ወያ
8.ህሊና ደሳለኝ
9.በዕውቀቱ ስዩም
10.ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን

ማሳሰቢያ
ከላይ የሰፈሩት ስሞች በቅደም ተከል እንዳልሆኑ ልብ እንድትሉልኝ  እያሳስብኩ፤ሁሉም ገጣሚዎችም ከአያቴ መስታወት ወደሬ ቀጥሎ እንደሚመጡ እንድታውቁልኝ እፈልጋለው።እርግጥ አያቴ አትፅፍም፤በቃሏ ግን ቃላት ላይ መጫወት ትችላለች።👌

አያቴ እንኳን አደረሰሽ።😄🙏
@Adnakotkifle‌‌
ሴጣንን ፈልጌው፣ለአንድ ሁለት ጥያቄ፡
አብሬው ለመሆን፣ጠየኩት አጥብቄ፤

እሱም፦
በጥርጣሬ አይን፣በፍርሀት እያየኝ፡
አርባ ክንድ እርቆ፣እንዲህ ተናገረኝ፤

"ሰው የምናሳስት፣እኛ ነበርን ድሮ፡
አሁን ሰው በልጦናል፣ዘመን ተቀይሮ፡
ጭካኔም አልፎናል፣በእጥፍ የሰው ልጅ፡
ሽንፈታችን አውቀን፣ቆየን ከሰጠን እጅ፤

ስለዚህ ወዳንተ፣አልመጣም በጭራሽ፣
ክፋትን ተምሬ፣እንዳልበለሻሽ።"

አድናቆት ክፍሌ የብርቱካን

@Adnakotkifle
2024/05/15 20:11:01
Back to Top
HTML Embed Code: